ኢትዮጵያና አዘርባጃን፣ ከዲፕሎማሲ ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያና አዘርባጃን ጠንካራ ዲፕሎማሲዊ ግንኙት እየገነቡ መጥተዋል፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙት እነዚህ ሁለት ሀገራት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት፣ የመከላከያ እና የቴክኖሎጂ ትብብሮችን ወደ ጠንካራና አዲስ ምዕራፍ ለማሳደግ እየሰሩ ናቸው።
ሀገራቱ የሶቪየት ኅብረት መፍረስን ተከትሎ አዘርባጃን ሪፐብሊክ ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች በኋላ ግንኙነታቸውን ቀስ በቀስ እያጠናከሩ መጥተዋል።
ኢትዮጵያና አዘርባጃን ለበርካታ ዓመታት በዘለቀው ግንኙነታቸው የየሀገራቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጉብኝቶችን አድርገዋል፡፡
ሕዳር 2017 ዓ.ም አዘርባጃን ባስተናገደችው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ29) ለመሳተፍ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ወደ ባኩ ተጉዘው ነበር፡፡
በቆታቸውም የአዘርባጃንን የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ 3ኛው የኢትዮ-አዘርባጃን የፖለቲካ ምክክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን÷ መድረኩ የሁለቱን ሀገራት የፖለቲካ ትስስር ወደ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚያመላክት ነበር፡፡
በመቀጠልም የካቲት 2018 ዓ.ም ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባኩ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ከፍ አድርጓል።
በዚህ ሳምንት ደግሞ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ የፓርላማ አፈ ጉባዔ ሳሂባ ጋፋሮቫ ኢትዮጵያን እየጎበኙ የሚገኙ ሲሆን÷ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ከፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች ጋር መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያና አዘርባጃን በታሪክና በጂኦግራፊያዊ አቀማመጣቸው ቢለያዩም በርካታ የጋራ ባህሪያት አሏቸው።
ሁለቱም ጂኦፖለቲካዊ ፉክክር ባሉባቸው ቀጣናዎች ይገኛሉ፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ፤ አዘርባጃን ደግሞ በደቡብ ካውካሰስ ክልል፡፡ በየቀጣናቸው ሁለቱም ሀገራት ለሰላምና ደህንነት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ፖለቲካም ሁለቱ ሀገራት ከምሥራቅና ከምዕራቡ ዓለማት ጋር ሚዛኑን የጠበቀ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ይከተላሉ፡፡
ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን መሠረተ ልማትን፣ ዲጂታል ሽግግርን፣ ኢንዱስትሪን እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለልማትና ዕድገታቸው ትኩረት ሰጥተው እየሰሩባቸው ያሉ ዘርፎች ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዘርባጃንን በጎበኙበት ወቅት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊየቭ የሀገራቱን ግንኙነት አስመልክተው ሲገልጹ፣ "አጋርነታችን በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮችን ያካተተ ነው" ነበር ያሉት።
ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በወታደራዊ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች ዘርፎች ግንኙነታቸው እያደገ መምጣቱን መሪዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊየቭ ብልፅግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉን አስመልክቶ በላኩት የደስታ መልዕክት፣ "በአዘርባጃን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት በአዎንታዊ አቅጣጫ እያደገ መሆኑ የሚያስደስት ነው" በማለት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአዲስ መልክ እየተጠናከረ መምጣቱን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በአቪዬሽን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ረገድ የተከናወኑ የጋራ የኢኮኖሚዊ ትብብሮች፣ የሁለቱን ሀገራት አጋርነት እያደገ መምጣት ያመለከተ ነው ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት አንደኛቸው ከሌላኛው በበርካታ ዘርፎች ልምዶችን እየተለዋወጡ ሲሆን÷ ለአብነትም ኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአዘርባጃኑ አሳን ክድመት (ASAN Khidmet) የመንግሥት ዲጂታል አገልግሎት ልምድ የተወሰደ የዲጂታል አሰራር ሥርዓት ነው።
አዘርባጃን በበኩሏ በኢትዮጵያ በኩል ወደ አፍሪካ ገበያ ለመግባት ጥሩ መደላድል ታገኛለች። በዚህ መልኩ ሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅምን በማስፋት በዓለም ኢኮኖሚና ጂኦፖለቲካ አወቃቀር ውስጥ ይበልጥ የሚጎለብት አጋርነት ሊገነቡ ይችላሉ።
ሁለቱ ሀገራት የሚጋሯቸው የልማት ርዕይ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ፣ የዲጂታል ሽግግር፣ የኢኮኖሚ ብዝሃነት እና ቀጣናዊ ትብብሮች ግንኙነታቸውን ከፍ ወዳለ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሳድግ ነው።
በቴዎድሮስ ሳህለ

5 days ago