1 day ago
የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀላቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው::
ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ አወግዛለሁ::
በአርሲ በተደጋጋሚ ንፁሀኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተበራከተ በየጊዜው ለቅሶ እና ዋይታ ብቻ እየተሰማ ያለ መፍትሄ መቀጠሉ እጅግ ያሳምማል::
ንፁሃን ዜጎች እያለቁ ያለው ከውጪ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን ወንድም ወንድሙ ላይ እየሰነዘረው ባለው አሳዛኝ ከጭካኔ ጥቃት ነው::
በሀገሩ ምድር በድህነት ህይወቱን እየመራ ለሚገኝ ንፁህ ህዝብ ከግራ እና በቀኝ ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎች በማያውቁት አጀንዳ ለሞት፣ ለእልቂት፣ ለስደት መዳረጉ ልብ ሰባሪ ነው::
ይህ የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::
በአርሲ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለው::
ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ አላህ እንዲረዳቸው እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው::
አላህ ሀገራችንን እና ወገኖቻችንን ይጠብቅልን::
ሰላም መግባባቱንና መተዛዘኑን በመላው ሀገራችን ሀያሉ ጌታችን አላህ(ሱ.ወ) ያስፍንልን
ኡስታዝ አቡበከር
Seledadotio

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀላቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው:: ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ አወግዛለሁ

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ አላህ እንዲረዳቸው እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው
አላህ ሀገራችንን እና ወገኖቻችንን ይጠብቅልን::
ሰላም መግባባቱን እና መተዛዘኑን በመላው ሀገራችን ሀያሉ ጌታችን አላህ(ሱ.ወ) ያስፍንልን
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

♦️የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው ዓመታዊው የግማሽ ማራትን ውድድር እሁድ ይካሄዳል
♦️የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ በዴንማርክ ኮፐንሃገን አለም አቀፍ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ
እ.ኤ.አ አቆጣጠር ሴፔቴምበር 20 ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የአለም አትሌቲክስ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌቶች በወንድም በሴቶችም የሚመረጡበት የአዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።
ጅማሬውንና ፍፃሜውን መስቀል አደባባይ የሚያደርገውና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያከናውነው 19ኛው የ21 ኪ.ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር በርካታ አትሌቶች በወንድም በሴትም የሚሳተፉበት ሲሆን በውድድሩ የተሻሉ ሆነው የሚያጠናቅቁ አትሌትች በሁለቱም ፃታ ሀገራቸውን ወክለው ሴፕቴምበር 20 በዴንማርክ ኮፐንሃገን የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ የሚያሳትፋቸውን ትኬት ይቆርጣሉ።
የአለም የግማሽ ማራቶን(የጎዳና ውድድርን)በሁለቱም ፆታ ሪከርዱን የያዙት ኢትዮጵያዊያን አቴሌቶች ሲሆኑ በወንዶች አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ 57:30፣በሴቶች ደግሞ ለተሠንበት ግደይ 1:02:52 በሆነ ሠዓት በመግባትና በማሸነፍ የሪከርዱ ባለቤቶች ሆነዋል።
የአለም ግማሽ ማራቶን በዴንማርክ ኮፐንሃገን ሲካሄድ ከግማሽ ማራቶኑ በተጨማሪ የ5ኪ.ሜ እና የ1 ማይልስ ወይም የ1,609ኪ.ሜ ውድድርም እንደሚካሄድ ከተያዘው ፕሮግራም ለመረዳት ተችሏል።
ለሴፕቴምበር 20 የዴንማርክ ኮፐንሃገን የአለም አቀፍ ግማሽ ማራቶን የሚያሳልፈውን ትኬት የሚያስገኘው የአዲስ አበባው ግማሽ ማራቶን ውድድርን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፊታችን ዓርብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሠጥ ቀይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

11 days ago
መላው የአፍሪካ ወንድም እህቶቻችን እንኳን ለአፍሪካ ቀን አደረሳችሁ ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***********
HAPPY AFRICA DAY TO ALL OUR AFRICAN BROTHERS AND SISTERS!
63 years ago, our forefathers gathered right here in Addis Ababa and dared to dream of a free, united Africa, and that dream still burns bright.
Today, as the proud home of the African Union, Ethiopia stands shoulder to shoulder with every African nation in that same spirit of unity.The work is far from over. Let us move from words to action, from promises to progress.
Africa's greatest resource has always been her people, and together, WE RISE!
Ethiopian Broadcasting Corporation #africaday #africa #ethiopia

አብረን ከርመን አብረን ሳንሆን ቀረን!
ፋናን እንደተቀላቀልኩ አንድ ሳምንት የተሻገረኝ አይመስለኝም። በወቅቱ 7ኛ ፎቅ ላይ ከነበረው የጋዜጠኞች መሥሪያ (Workstation) እና መሰባሰቢያ ቦታ ተቀምጦ የነበረ አንድ ባለ ጆሮ-ገብ ድምፅ ከወትሮ በተለየ ስሜት ውስጥ ሆኖ ወደ ተቀመጠበት እንድጠጋው በእጁ አመለከተኝ። እዚያ ተቋም ስንገናኝ ለሁለተኛ ጊዜ ቢሆንም፣ ሰላምታውና አቀባበሉ ለከረመ ወዳጅ ይመስል ነበር።
የግራ እጁን ሁለት ጣቶች አገጩ ላይ ጭኖ፣ በቀኝ እጁ ከደረቱ ትይዩ ካስቀመጠው ወፍራም የግል ኮምፒውተር (PC) “መለስተኛ ሳጥን ብንለው😂” ውስጥ ፋይል መበርበር ጀመረ። “ይሄ ልጅ ከተዋወቅን ገና ሁለተኛ ሰላምታ ስሰጠው ነው፤ ምን ይዞብኝ ይሆን?” ብዬ ሳስብ፣ ከመቅጽበት የሆነ ፎቶ አወጣና፣ “ይሄ ልጅ አንተ ነህ አይደል?” አለኝ።
ፎቶውን ሳይ እራሴን ለመካድ ዳዳኝ። ለካስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለን፣ እነሱ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርታዊ ጉዞ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በመጡ ጊዜ፣ የJOCOSA ፕሬዝዳንት ስለነበርኩ አቀባበልና ግብዣ (የውሃ😂) አድርጌላቸው ነበር። በዚያ ጊዜ ያስቀረነውን ፎቶ ነው መዞ ያሳየኝ። እኔ ግን በፍጹም አላስታወስኩትም ነበር። የተማሪነት ጊዜው አዳነ ከጋዜጠኛው አዳነ ጋር የተራራቁ ናቸው።
ከአዴ ጋር የጓደኝነት ውላችን ከዚያች ቀን የጀመረ ይመስለኛል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ደስ የሚል ቤተሰባዊ ጓደኝነት ፈጥረን ኖረናል። በእኔ ወሳኝ ደስታና ሐዘን ውስጥ እሱ አለ፤ እኔም በተመሳሳይ።
እኔ ባለቤቴን ሳጭ፣ ሽምግልና ከሄዱት ውስጥ አዴ አንዱ ነው። ሳገባም ሚዜዬ ነበር። በተቃራኒው፣ እሱ “እጮኛውን ታገቢኛለሽ?” ሲል ከተገኙት ጥቂት ወዳጆቹ መካከል እኔ ነበርኩ። ሽምግልና ከሄዱት ታላላቅ ሰዎች መካከልም ተገኝቻለሁ።ይሄን ጋብቻ በህግ ለማፅናት ቀበሌ ተገኝተው የጋብቻ ውል(80) ሲፈራረሙም አንዱ እማኝ ነበርኩ።
ይህን ሂደት በታላቅ ሥርዓት ለመቋጨትና ለሰርጉ ሲሰናዳም፣ ሚዜው ሆኜ ከአጠገቡ ለመቆም እኔ ብቻ ሳልሆን፣ ውድ ባለቤቴም የእሱ ባለቤት ሚዜ ሆና የማይረሳውን ቀን በጋራ ለማሳለፍ አቅደን፣ ልብስ ተለክተን፣ መኪና ተከራይተን ዝግጁ ብንሆንም፣ ሰርጉ ሳምንት ሲቀረው በሥራ ምክንያት ከአገር መውጣት ግዴታ ሆነብኝ።
ከዓመታት በፊት ማግባቱን ሲወስንና ሲያሳውቀኝ፣ ቀን ቆጥረን የጋብቻ እቅድ አውጥተን፣ እንደ ወንድም ቀኑን በጋራ ናፍቀን እንደከረምን ሰዎች፣ በዚህ ውብ ቀን አጠገቡ አለመቆም የሚፈጥረው ስሜት ከባድ ቢሆንም፣ መልካም ምኞትን ከማስፈር ውጪ ሌላ አማራጭ የለም።
አዴ እና B2 መልካም ጋብቻ እንዲሆንላችሁ ከውዷ ባለቤቴ ጋር እንመኝላችኋለን።
Haikemikael_Debisa

Sponsored by
Surafel
14 days ago
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሰብዓዊ ክብር እና ሕይወት በተመለከተ የተላለፈ ሐዋርያዊ ጥሪ
“ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና”. (ማቴ 5:7)
ለፖለቲካ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ሚዲያዎች እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች
እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት በመላው አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታች እንዳሳሰበን ለመግለጽ እንፈልጋለን። በአገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች አገራቸውን ለቀው የሚወጡት ለአገራቸው ፍቅር በማጣት ሳይሆን፣ የተሻለ የሥራ ዕድል እና የኑሮ ሁኔታ በመፈለግ ነው። ተነሳሽነታቸው እጅግ ሊከበር የሚገባው እና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፤ ይህም ህይወታቸውን ለማሻሻል፣ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እና በመጨረሻም ለአገራቸው እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ስደተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ሰብዓዊ ክብር ከማግኘት ይልቅ በመዋቅራዊ ብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በገለልተኝነት እና በከባድ ተጋላጭነት ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። ሁኔታቸው ምንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ቅዱስ የሆነው ሰብአዊ ክብራቸው ግን በድንበር፣ በሕጋዊ ሁኔታ ወይም በኢኮኖሚ ስርዓት ችላ ሊባል ወይም ሊጠፋ አይችልም።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፤ “በኢኮኖሚ የበለጸጉ መንግስታት፣ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ጸጥታንና ለመተዳድሪያ የሚሆን ገቢ በማጣታቸው ወደ አገራቸው ሲገቡ ተቀብለው የተቻላቸውን እርዳታ መስጠት አለባቸው” (CCC 2241)። ይህ ትምህርት ስደተኞች እንደ ውጭ ወይም እንደሸክም መታየት እንደሌለባቸው ይልቁንም እንደ ወንድምና እህት ሰብዓዊ ክብራቸው ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባ ያስተምረናል።
ይሁን እንጂ፣ ብዙ ስደተኞች በስደት ጉዟቸው ወቅት ከባድ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፤ በእጅጉም ይሰቃያሉ። እኛም ከዚህ በታች የተገለጹትን ቁልፍ የስደት መዳረሻዎች እና ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን ተያያዥ ችግሮች ተመልክተናል።
1) አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፡-
• ሳውዲ አረቢያ፡- በሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚኖሩ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አሉ። የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በሰማነው መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በተፈረደው የሞት ፍርድ ያለንን ስጋት፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ለዜጎቻችን ሁሉ ርህራሄ እና ምሕረት እንዲያደርጉ ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እንዲጠብቁ እንጠይቃለን።
• የመን፡- በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ የመን ለመግባት ወይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመጓዝ በቀይ ባህር፣ በጅቡቲ ወይም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል ያልፋሉ። የመን ብዙውን ጊዜ ወደ ሌሎች የባህረ ሰላጤ አገሮች እንደ መጓጓዣ መንገድ ትጠቀማለች፤ ሆኖም ግን፣ ብዙ ስደተኞች በመንገድ ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ይደርስባቸዋል፣ ዓመፅ፣ በደል እና ኢ-ሰብአዊ ተግባራት ይደርስባቸዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በጉዞው አደገኛ ባህሪ እና በሚገጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ።
• ሊባኖስ፡- በሊባኖስ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአገሪቱ ውስጥ ባለው ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ትውልድ አገራቸው በሰላም ለመመለስና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ።
• የባህረ ሰላጤ አገሮች፡- በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሌሪካ በእስራኤል እና በኢራን መሃከል በተፈጠረው ጦርነት እና ግጭት ምክንያት በጭንቅ ውስጥ ይገኛሉ።
2) የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሌላ መዳረሻ ናት። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ለሕይወታቸውና ለንብረታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ወደአስቡበት ሳይደርሱ በጉዞ ላይ እያሉ እስራት ይገጥማቸዋል፣ ሌሎቹ ደግሞ ወደ መድረሻቸው የሚደርሱ ሰዎች በፍርሃትና ውስጥ በምኖር ላይ ናቸው። በሚደርሱን ዘገባዎች መሰረት በደቡብ አፍሪካውያን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የተነሳ በዓመፅ፣ እና በግድያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ክቡር ሕይወታቸው እየጠፋ ነው።
3) የሱዳን - ሊቢያ - የአውሮፓ መንገድ፡ ይህ መንገድ ለረጅም ጊዜ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በብዛት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ እና ህልፈተ ህይወት አስከትሏል። ብዙዎች አስቸጋሪ እና አደገኛ የሆነውን የበረሃ መንገድ በኢሰብአዊ ሁኔታዎች ሲያቋርጡ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ይህንን ጉዞ የበለጠ አደገኛ አድርጎታል። ሊቢያ የሚደርሱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እስር፣ ዝርፊያ፣ የጉልበት ብዝበዛ እና ከባድ በደል ይደርስባቸዋል። አንዳንዶቹ በክርስትና እምነታቸው ምክንያት ስደት ደርሶባቸዋል እና ህይወታቸውን አጥተዋል። በአደገኛ ጀልባዎች የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ሲሰምጡ፤ ብዙዎቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ያጣሉ፣ ጥቂቶች ብቻ ወደ ላምፔዱዛ ዳርቻ መድረስ ችለዋል። ላምፔዱዛ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ወቅት በባህር ላይ ለሞቱት ሰዎች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለስደተኞች ያላትን አንድነት፣ ርህራሄ እና ለስደተኞች ድምጽ የመሆን ተልዕኮ ለማስቀጠል ደሴቲቱን በቅርቡ እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
ይህ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስቃይ ከቁጥርም በላይ ውድ እና የተከበረ ህይወት ያላቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በእንባ፣ በመስዋዕትነት እና በተስፋ የሸኟቸው ልጆች ናቸው። ብዙ ጊዜ ግን እነዚህ ስደተኞች በብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በደል፣ በመገለል እና ለጥቃት በመጋለጥ አላስፈላጊ ስርዓቶች ውስጥ ይወድቃሉ። ብዙዎች ለማሰብ አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎችን ውስጥ በህይወት ለመቆየት ይታገላሉ።
በክርስቲያያዊ የበጎ አድራጎት እና በዓለም አቀፍ የወንድማማችነት መንፈስ፣ ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ማናቸውም የታቀዱ ግድያዎች እንዲቆሙ እና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምሕረትን እንዲያደርጉ ልመና እናቀርባለን። ምህረት ፍትህን አያዳክምም። ምህረት ፍትህን ከፍ በማድረግ ተስፋ ለቆረጡ ተስፋን ይሰጣል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን የሚያባብሱትን ጥልቅ ምክንያቶች ከመሰረቱ ለማስወገድ ይተባበር ዘንድ ዕድል የሚሰጥ ሊሆን ይገባል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ የከባቢ አየር ሁኔታ መቃወስ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በዓለም ዙሪያ አደገኛ የፍልሰት መንገዶችን እንዲከተሉ እንደሚያስገድዳቸው አስተውለናል። እነዚህን ዋና ዋና ምክንያቶች ችላ የሚል ዓለም የፍልሰት ቀውስን መፍታት አይችልም። በእርግጥም፣ የሰብዓዊነታችን እና የሥልጣኔ መለኪያ በዙሪያችን ያሉ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በምናሳሳየው እንክብካቤ ላይ የተመሠረተ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት፣ ውይይት፣ ምሕረትና ጥበብ ተስፋ መቁረጥንና ሞትን እንዲያሸንፉ አጥብቀን መጸለያችንን እንቀጥላለን። እነዚህን ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ሁሉንም ውሳኔ ሰጪዎች ለሁሉ ቻይ በሆነው የእግዚአብሔርን አምላክ ምህረት እና እገዛ ያገኙ ዘንድ እንጸልያለን።
የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ
አዲስ አበባ
10/09/2018

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) —የቀድሞው የኩባ መሪ ራውል ካስትሮ እና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በፍሎሪዳ በሚገኝ የአሜሪካ የህግ አስከባሪ ክስ እንደተመሰረተባቸው ዛሬ ረቡዕ ይፋ የተደረጉ የፍርድ ቤት ሰነዶች አመለከቱ።
በ94 ዓመቱ ራውል ካስትሮ ላይ የቀረበው ይህ አዲስ የፌደራል ወንጀል ክስ፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኩባ መንግስት ላይ እያካሄደ ያለውን የጫና ዘመቻ ከፍ ወዳለ እና ወደተባባሰ ደረጃ ያሸጋገረው መሆኑ ተገልጿል።
ተከሳሹ ራውል ካስትሮ የሟቹ የኩባ አብዮት መሪ ፊደል ካስትሮ ወንድም ሲሆኑ፣ አሁንም ድረስ በሀገሪቱ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ተጽዕኖ እና ስልጣን ካላቸው ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

16 days ago
''ማንቺስተር ያሸነፈ ቀን !''
ትናንት አርሰናል አሸነፈ! በህይወቱ ሙሉ ሲመኘው የነበረውን ይህን ድል ቆሞ ማየት የነበረበት አንድ ሰዉ ነበር።
ብዙ ጊዜ ማንቺስተር አሸንፎ ደጋፊዎቹ መሬት አልበቃቸው ብሎ ሳይ እንደሁሌውም ትዝያለኝ ያ ራሱን 'የአርሰናል ቁልፍ ሰው' አድርጎ ይቆጥር የነበረው ታናሽ ወንድሜ ነው
በፍቃዱ ብርሃኑ ይባላል… እማዬ “ፍቃዴ” ትለው ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ እሱን የሚያውቁት ሁሉ “ፍቄ” ብለው ነበር የሚጠሩት፡፡ በህጻን አዛውንቱ ተወዳጅ የነበረ ወንድሜ .... ዛሬ በህይወት የለም።
ፍቄ ሁሌም ማታ የጠንቋይ መጣፍ የመሰለ ደቃቅ ጽሁፍ የታጨቀበትን ሊብሮ ጋዜጣ ይዞ ወደቤት ይመጣል። ገና ጎረምሳ ነው፡፡ ረጅም ...1 ሜትር ከ87 ሳ.ሜ ቁመቱን በአሮጌው ሶፋ ላይ ዧ አድርጎ እንሩን አንፈራጦ ይቀመጥና …. ፊቱን ጋዜጣው ውስጥ ቀብሮ …ኮስተር ፈታ እያለ ‘የነቡናን እና የነአርሴን' ወግ ይጨመጭማል።
“… ምንድነው ግን የምታነበው?” ትለዋለች እማዬ፡፡ ”ስፖርት ነው እማ.. ብዙም አታውቂውም” ይላታል።
”ኡኡቴ! አዋቂ ነኝ ብለህ ሞተሃል..ደሞ ለቅሪላ ወሬ!” ትላለች።
” ጭንቅላትህን በኳስ ዕወቀት ከምትሞላ ትምህርትህ ላይ አትበረታም ነበር? …ደደብ!! …ነገ አርሰናል መጥቶ ይፈተንልህ መሰለህ? ..” ብዬ ልጮህበት እፈልጋለሁ።
ግን ብዙ ጊዜ ይህንን ብዬው ጉሮሮዬን አመመኝ እንጂ ያመጣሁት ለውጥ የለም።
እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን በምትሄድባቸው ቀናት ወደእግዜር ከምትወስደው የራሷ ጥያቄዎች በተጨማሪ ፍቄ የሚያዛት ተጨማሪ ፀሎት አለ። ጨዋታ ያለ ቀን ወይ ቡና… ወይ አርሰናል እንዲያሸንፍ እንድትጸልይለት ይነግራታል፡፡
የሆነ ጊዜ የቡና ረከቦቷን የምትሸፍንበትን ጨርቅ አነስቶ ጥሎ በምትኩ ሁለት የቡና አርማ ያለበትን ባንዲራ አሰርቶ አመጣና አንዱን “የቡና ስኒ በቡና አርማ ነው መሸፈን ያለበት” ብሎ ሰጣት፡፡ አንዱን ደግሞ የቤታችን ግድግዳ ላይ በሚስማር መትቶ ሰቀለው፡፡ ቤት ስገባና የሆነውን ሳይ ተናደድኩና ገንጥዬ ጣልኩበት፡፡ የረከቦቱን ግን እማዬ ከለከለችኝ፡፡ "ይሁን፣በገዛ ሲኒዬ ምን አገባህ" ብላ ፡፡ እነዚያ ጨርቆች ዛሬም ድረስ ቤታችን አሉ፡፡
እማዬን “ እሙ!” ነበር የሚላት፡፡ የሚተኛው ከሷ ጋር ነው፡፡ የመጨረሻ ልጅ ስለሆነ ነው መሰለኝ እንደነፍሷ ትወደዋለች፡፡ ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን ለመሄድ ስትነሳ የተሸፈነበትን ብርድልብስ ገለጥ ያደርግና “እሙ! ዛሬ የኔ ቡድን ይጫወታል።እንዲያሸንፍ ጸልዪልኝ ...ካሸነፍን ስለት ታስገቢልኛለሽ! ” ይላታል፡፡
“አይ እዳዬ!..... ደሞ ዛሬ አቡነ ተክለሃይማኖት እንዴት ያረጉኝ ይሆን” ትላለች ። እማዬ ስትምልም ስትለምንም በአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡
አንድ ቀን 'የምር ስለሱ ኳስ ጨዋታ ትጸልያለሽ?' ብዬ ጠየቅኳት፡፡ “እንዴ አዎና!...ተክልዬ !! የዚህን ልጅ ልብ የበሉት ባለኳሶች እንዲያሸንፉ እርዱልኝ…..ጉድ እንዳይሰሩኝ ኋላ! እላቸዋለሁ” አለችና አሳቀችኝ።
ምን ታድርግ? የርሱ ክለብ የተሸነፈ’ለታ ቤታችን የሚፈጠረውን ነገር ስለማውቅ አልፈረድኩባትም፡፡
ጨዋታ ያለ ቀን ገና በጠዋቱ አጠገቤ ቆም ይልና…”መላ’ዬ …ጨዋታው 3 ከ 45 ይጀምራል። ከዚያ በፊት ሃይላይት አለ። ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ ያልቃል። እንደጨረስኩ ወዲያው እመጣለሁ።” ይላል።
ማስፈቀዱ ነው፡፡ ዝም እላለሁ።ቆሞ ያየኛል።ዝም እላለሁ። አይሄድም፡፡ እኔ ጥዬው እሄዳለሁ።
አንዳንዴ የሆነ ልቡን ስልብ አድርጎ ራሱን የሚያስተው ነገር አለ፡፡ ሲጨነቅ ወይም ሲበሳጭ እንዲያ ይሆናል፡፡
አርሰናል የተሸነፈ’ለት ታዲያ ብዙ ጊዜ ያ ህመም ይነሳበታል፡፡ ቤት እንደገባ በዚያ ቁመቱ ሶፋ ላይ ዧ ብሎ ይወድቃል፡፡ ጸጥ ነው የሚለው፡፡ አንዳንዴ ሞተ ብለን የምንጮህበት ቀን አለ።ውሃም ጸበልም ደፋፍተንበት ነፍስ ከዘራ በኋላ “ደህና ነኝ እኮ” ሲል ደግሞ የኔ ንዴት በተራው አናቴ ላይ ይወጣል።
“አንተ በማይረባ ኳስ እየመጣህ ትዘረጋለህና እኛ መጨነቅ አለብን?” ብዬ እጮህበታለሁ፡፡ መልስ አይሰጠኝም፡፡ሌላ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡
የሆኑ ከሌላ ሰፈር የሚመጡ የጊዮርጊስ ይሁኑ የማንቺስተር ደጋፊዎች እሱን ሁሌም እንደተቃረኑት ነበር። ኳስ የሚያዩት አብረው መሰለኝ ፡፡
ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ...ብዙ ጊዜ እኩለ ሌሊት ከእንቅልፌ የሚያባንነኝ በራችን አቅራቢያ የምሰማው የብዙ ልጆች ዘፈን የሚመስል ጫጫታ ነበር። እኛ ቤት በር ላይ አርሰናልን የሚሳደብ ዘፈን ከሰማሁ በቃ ነገር አለ ማለት ነው !።
ፍቄን ለማብሸቅ የሚዘፈን ዘፈን መሆኑን አውቃለሁ።
ልጆቹ የሚሉት ነገር አይገባኝም። ግን ሁለቱ ቡድኖች ከማንም ጋር ይጫወቱ ብቻ አርሰናል ከተሸነፈ ወይም ማንቺስተር ካሸነፈ እሱን ለማብሸቅ እኩለ ሌሊት በራችን ላይ ይመጡና ይጨፍራሉ።
አንድ ቀን ከነሱ ጋር ሲደባደብ ፖሊሶች ደረሱና ብዙዎቹን ያዟቸው፡፡ እሱንም ይዘውት መኪና ላይ ከጫኑት በኋላ የኔ ወንድም መሆኑን ሲነግራቸው ደውለው ጠርተውኝ ፊቴ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ለቀቁት፡፡ ለእማዬ ብዬ እንጂ እስር ቤትን ትንሽ ቢቀምሳት ቅር አይለኝም ነበር፡፡
እሱ የሚደግፈው ቡድን ያሸነፈ’ለት ደግሞ ታሪክ ይገለበጣል፡፡እማዬ ይህንን ስትሰማ ወደሰማይ እያንጋጠጠች “ዛሬስ ተክለሃይማኖት ገላገሉኝ !” ትላለች።
የዚያን ቀን ታዲያ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አይወስደውም። ብቻውን ይስቃል። አልጋው ራስጌ ፎቷቸውን የሰቀለውን ማንነታቸውን የማላውቃቸውን ተጨዋቾች በተኛበት አንጋጦ ያያቸዋል፡፡ ጸጥ ባለው ሌሊት ድንገት ይነሳና “ይሄ የተረገመ ልጅ! ሰራላቸው እኮ!” ብሎ በሳቅ ፍርስ ይላል።
አንዳንዴ ዝም ብዬ ሳየው ጤነኛ ሁሉ አይመስለኝም ነበር ።እማዬ ግን “ተወው ልጅ አይደል? ብቻ አይመመው እንጂ ሲለፈልፍ ቢያድር እኔ ምን ቸገረኝ…ሲያድግ ይተወዋል” ትላለች፡፡
ፍቄ ገና በ21 ዓመቱ አንድ እሁድ ቀን ድንገት ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ሆስፒታል በገባ በሶስተኛ ቀኑ …እኛንም የሚወዳቸውን ቡናና አርሰናልንም ሳይሰናበት በዚያው ሄደ።
የቀብሩ ዕለት የነበረው ህዝብ ብዛት እስካሁን ሳስበውም ይገርመኛል። በዚያ እድሜው ትምህርቱን ትቶ በሚሰራው ስራ የሚያገኘውን ደመወዝ ሁሉ የሰፈር አቅመደካሞችን ፣ ልጅ ያላቸው የኔ ቢጤዎችን ወዘተ በቋሚነት ይረዳበት እንደነበር ያወቅኩት የለቅሶው ሰሞን ሰዎች ስለርሱ ሲያወሩ በሰማኋቸው ታሪኮች ነው፡፡
በስሙ ትልቅ የእግር ኳስ ግጥሚያ ተዘጋጅቶለትም ነበር፡፡ የዋንጫው ቀን አሸናፊውን ቡድን ስሸልም ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር ፡፡
አሁንም ታዲያ ኳስ በሚታይባቸው ቤቶች በኩል ሳልፍ የደጋፊዎችን ጩኸት ስሰማ ፊቴ ላይ ድቅን የሚልብኝ አሱ ነው ። ምን ያደርጋል ያንን ምድር የማይበቃው የሚመስል ዋልያ …ያች ቀዝቃዛ ቀን እንደዋዛ ይዛው ሄደች....የርሱ መጉደል በቤታችን ይዞት የመጣው ከባድ ሃዘን እናቴን ህመምተኛ አድርጓት ኖሯል፡፡ ባሰብኩት ቁጥር የሚናፍቀኝ ከፊቱ የማይጠፋው ፈገግታ ነው፡፡
ፍቄ ወንድሜ ! ….ነፍስህ በሰላም ትረፍ !!
የሚናፍቅህ ወንድምህ
መላኩ ብርሃኑ

17 days ago
ዛሬ ቀን 25/8/18 ሰሞ ለዋይ አንበሉ የተባለች የቤት ሠራተኛ ከአያት ዛን5 ከመኖሪያ ቤትውስጥ በርካታ ወርቅ ዘርፋ ተሰውራለች ያለችበትን የጠቆመ ወረታውንእንከፍላለን የተያዦም ስም ወንድምነው አበሩ ይባላል በዚህ ስልክ የጠቁሙን 0911690370/ ወይነም 0911221998
Sponsored by
Surafel
17 days ago
መጋቢ ዐቢይ ታደለ “መልክአ-ስብዕና” የተሰኘ መጽሐፋቸውን አስመረቁ።
የኤክሌሺያ ዓለምአቀፍ የወንጌል አማኞች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር እና የኪያ ሾው መርሐግብር አዘጋጅ፣ የመጋቢ ዐቢይ ታደለ (ኪያ) “መልክአ-ስብዕና” መጽሐፍ፣ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም በቤዛ ዓለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ለምረቃ በቅቷል።
በምረቃው ሥነ ሥርዓትም የመጽሐፉ ደራሲ መጋቢ ዐቢይ ታደለ፣ የመጋቢ ዐቢይ ታደለ ባለቤት ወ/ሮ ማክዳ ጌታቸው፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የመጋቢ ወዳጆች ተገኝተዋል።
በወንድም የኔነህ መድረክ አጋፋሪነት ቅደም ተከተል የተሰጣቸው የመርሐግብሩ አካላት ጸሎት፣ “የእንኳን ደስ አለህ” መልእክት፣ ዝማሬ፣ የመጽሐፍ ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን በመጋቢ ዐቢይ ታደለ አወያይነት “መሆን ለተጽዕኖ” የተሰኘ የፓናል ዲስከሽን ተካሂዶ፣ የመጋቢ ዐቢይ ታደለን አገልግሎት የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ፊልም ለተመልካቾች ቀርቧል።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው፣ “መልክአ-ስብዕና” የተሰኘው መጽሐፍ፣ በኢትዮጵያ የአመራር እና የስብዕና ግንባታ ታሪክ ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፣ መሪነትን በውስጣዊ ማንነት እና በታማኝነት መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችሉ አሥራ አንድ መሠረታዊ፣ ምሥጢር አዘል ምዕራፎችን አካትቷል።
በምረቃው የመጽሐፍ ዳሰሳ መርሐግብር እንደተገለጸው መጽሐፉ ለዘመናችን መሪዎች እና አገልጋዮች፣ የመሪነት ስጦታ ላላቸው ወጣቶች እንዲሁም ለተተኪው ትውልድ፣ በቤተክርስቲያን እና ከቤተክርስቲያን ውጪ ላሉ ሁሉ፣ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት የጊዜው መልእክት ነው።
ለአሥራ አንድ ዓመታት በኪያ ሾው መርሐግብር በክርስቲያን ሚዲያ ላይ ተጽዕኖ የፈጠሩት እና ከዚህ ቀደም “አካላዊ አስተሳሰብ” የተሰኘ መጽሐፍ ወደ አንባቢ ያደረሱት መጋቢ ዐቢይ ታደለ፣ ከ“መልክአ-ስብዕና” የመጽሐፍ ምረቃ በኋላ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ሁለት መጽሐፍትን ወደ አንባቢ እንደሚያደርሱ ገልጸዋል።

የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ለቅሶ በአባቱ ትውልድ ሃገር ጋሞ ዞን በባህላዊ ስነ-ስርዓት ተከናወነ!
የአርቲስት ነፃነት አባት ወርቅነህ ዕምሩ የተወለዱት በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ አፋ ጉታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
ሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ በልጅነታቸው ወደ አዲስ አበባ ለሽመና ስራ የሄዱ ሲሆን በደርግ ዘመነ መንግስት ሃገራቸውን በውትድርና ሲያገለግሉ እንደነበሩም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።
ከውትድርና መልስ በአዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት ሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ዘርፍ ለዓመታት ማገልገላቸውንም የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል።
ሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያገለገሉ ሳሉ ባደረባቸው ሕመም በአዲስ አበባ ፖሊስ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው የቀብር ስነስርዓታቸው በቀጨኔ መድኃኔዓለም መፈፀሙንም ገልፀውልናል።
የሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ ስርዓተ ቀብር አዲስ አበባ ከተፈፀመ በኋላ የለቅሶ ስነ-ስርዓት በትውልድ አካባቢያቸው በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ቀበሌ ወዳጅ፣ ዘመዶቻቸው በተገኙበት መከናወኑን ሰምተናል።
ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ባጋጠመው ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ ስርዓተ ቀብሩ በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መፈፀሙ ይታወቃል።
ይህንንም ተከትሎ በክፍለሀገር የሚገኙ የአርቲስቱ አባት ቤተ ዘመዶች የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህን ለቅሶ ዕርማችንን እናውጣ በማለት በጠየቁት ጥያቄ መሠረት የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የለቅሶ ስነ-ስርዓት በአባቱ ትውልድ ሃገር በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ የነፃነት ወርቅነህ ወንድም ወንደሰን እና እህቱ መሰረት በተገኙበት በባህላዊ ስነስርዓት ተከናውኗል።
የአርቲስት ነፃነት አባት ሻምበል ወርቅነህ እምሩ ከሃገር ቤት ከወጡ ከ60 ዓመት በላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ልጆቻቸውን ጋሞ ዞን ከሚገኙ ቤተ ዘመዶቻቸው ጋር ሳያስተዋውቁ መቅረታቸውንም ጠቅሰዋል።
በጋሞ ባሕል በየትኛውም አካባቢ ሰው ይሙት ለቅሶ በአባት ሃገር ሳይለቀስ አይቀርም ያሉት ምንጮቻችን ለቅሶውን በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ቀበሌ ለማስለቀስ በተደረገው ጥረት በዛሬው ዕለት በባሕላዊ ስነስርዓት የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ወንድም ወንደሰን እና እህቱ መሰረት በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።

የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የለቅሶ ስነ-ስርዓት በጋሞ ዞን ተከናወነ
#fastmereja I በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የለቅሶ ስነ-ስርዓት፣ “በየትኛውም አካባቢ ሰው ይሙት ለቅሶ በአባት ሀገር ሳይለቀስ አይቀርም” የሚለውን የጋሞን ባህል ተከትሎ በአባቱ የትውልድ ስፍራ በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ቀበሌ ዛሬ በባህላዊ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቀብሩ መፈጸሙን ተከትሎ፣ በክፍለሀገር የሚገኙ የቤተሰብ አባላት "ዕርማችንን እናውጣ" በማለት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የአርቲስቱ ወንድም ወንደሰን እና እህቱ መሰረት በተገኙበት የለቅሶ ስነ-ስርዓቱ በድምቀት ተፈጽሟል።
የአርቲስት ነፃነት አባት ሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ ከ60 ዓመታት በፊት በልጅነታቸው ለሽመና ስራ ከሀገር ቤት ወጥተው ወደ አዲስ አበባ ካቀኑ በኋላ በውትድርና፣ በፖሊስነት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ዘርፍ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። ሻምበል ወርቅነህ ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በአዲስ አበባ በቀጨኔ መድኃኔዓለም መፈጸሙ ይታወቃል። አባት ሻምበል ወርቅነህ ከሀገር ቤት ከወጡ ረጅም ዓመታት በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጋሞ ዞን ከሚገኙ ቤተ ዘመዶቻቸው ጋር ሳያስተዋውቁ የቆዩ ቢሆንም፣ አሁን የተከናወነው ባህላዊ የለቅሶ ስነ-ስርዓት የአርቲስቱ ወንድምና እህት በስፍራው በመገኘት ከቀሪው ቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙና የቤተሰብ ትስስሩ እንዲቀጥል ትልቅ አጋጣሚ ፈጥሯል ሲል ዱቡሻ ሚዲያ ዘግቧል።

18 days ago
ከቤተ-መንግሥት ወደ ስብከት መድረክ
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሽግግር እንቆቅልሽ
የአንድ አገር መሪ ከስልጣን ሲወርድ የሚመርጠው መንገድ የራሱን የነበረውን ማንነት የወደፊት እጣ ፈንታውን እና የህዝቡን የታሪክ ትውስታ ይወሰናል። በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ በማስገባት የመጀመሪያው መሪ በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ያ ውሳኔ በወቅቱ ለነበረው ህዝባዊ አመፅና ውጥረት የተወሰነ መተንፈሻ የሰጠ በጎ እርምጃ ተደርጎ ቢወሰድም ከስልጣን በኋላ የመረጡት የሕይወት መስመር ግን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄና ትዝብትን እያስከተለ ይገኛል።
በተለይም በቅርብ ጊዜያት በመድረኮች ላይ እንደ ወንጌል ሰባኪና የሃይማኖት መምህር ሆነው መታየታቸው ፖለቲካው በፈጠረው ቁስል ላይ የወንጌል ፈውስ ወይስ የታሪክ ሽሽት? የሚል ጠንከር ያለ ክርክር አስነስቷል።
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩባቸው ዓመታት (ከ2005 እስከ 2010 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የዜጎች መፈናቀልና የብዙ ወጣቶች ህይወት የጠፋባቸው ከባድ ዓመታት ነበሩ። ምንም እንኳን ውሳኔዎች በጋራና በፓርቲ (ኢህአዴግ) መዋቅር ይሰጡ የነበረ ቢሆንም እርሳቸው የአገሪቱ የመጨረሻው የሥልጣን ማማና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው መጠን በዚያ ዘመን ለደረሰው መከራና የደም መፋሰስ ቀጥተኛ የታሪክና የሞራል ተጠያቂነት አለባቸው።
ህዝብ በበደልና በደምና በደመ ነፍስ የታለፉ ቁስሎችን በቀላሉ አይረሳም። በጥይት የተመቱ ወጣቶች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች፣ የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ትውስታ ዛሬም ትኩስ ነው። ስለሆነም ያንን ሁሉ መከራ ያስተናገደ ህዝብ በወቅቱ የነበረው መሪ በአንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ በመድረክ ላይ ሲሰብክ ሲያይ መገረሙ መጠራጠሩና መቆጣቱ ሰብአዊና አመክንዮአዊ ምላሽ ነው።
በክርስትና እምነት (በተለይም አቶ ኃይለማርያም በሚከተሉት የሃዋርያት እምነት መሠረት) ማንኛውም ሰው በማንኛውም ጊዜ ንስሐ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የመመለስና የማገልገል መብት አለው። ይሁን እንጂ የወንጌል መሠረታዊ አስተምህሮ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ብቻ ሳይሆን ከበደሉት ሰውና ማህበረሰብ ጋር መታረቅንም ይጨምራል።
"እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ ከዚያም መጥተህ መባህን አቅርብ።" (ማቴዎስ 5:23-24)
የአቶ ኃይለማርያም ወደ ወንጌል አገልግሎት መግባት ትልቅ ጥያቄ የሚነሳበት እዚህ ጋ ነው። በመሪነታቸው ዘመን ለተፈጠሩት ስህተቶች፣ ለጠፋው ሕይወትና ለፈሰሰው ደም የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ፣ በግልጽና በስም ጠርተው ይቅርታ ጠይቀዋል ወይ? ጥፋቱን አምኖ ንስሐ መግባት፣ የተበደሉትን መካስና ይቅርታ መለመን የወንጌል ስብከት መነሻ እንጂ መድረሻ ሊሆን አይገባም ነበር?
እነዚህ ጥያቄዎች ሳይመለሱ በቀጥታ ወደ መድረክ ወጥቶ መስበክ ለብዙዎች ታሪኬ ተረስቶልኛል ከሚል ግምት ወይም የህዝብን ቁስል ካለማክበር የመነጨ ሊያስመስለው ይችላል።
በሌላ በኩል የአቶ ኃይለማርያምን ወገን የሚከላከሉ ሰዎች እርሳቸውም ቢሆኑ የራሳቸው የህሊና ጉዞ እንዳላቸው ይከራከራሉ። ስልጣን በገዛ ፈቃድ መልቀቅ ራሱ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ የመጸጸትና ለውጥ የመሻት መግለጫ እንደነበር የሃይማኖት አገልግሎታቸውም የዚሁ የውስጥ ለውጥና ሰላምን የመፈለግ ጉዞ አካል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
በተጨማሪምከፖለቲካው ዓለም ሙሉ በሙሉ ርቀው በግል ሕይወታቸውና እምነታቸው ላይ ማተኮራቸው መብታቸው እንደሆነ ይነገራል።
ነገር ግን ግለሰቡ ተራ ዜጋ ሳይሆኑ የአገር መሪ ነበሩ።
የአገር መሪ የህዝብ ሃብት ነው ታሪኩም፣ ውሳኔውም፣ ከስልጣን በኋላ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ሁሉ በህዝብ መነጽር መቃኘቱ አይቀሬ ነው።
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የወንጌል ሰባኪነት ጉዞ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አሁንም የተደበላለቀ ስሜት ይፈጥራል። በአንድ በኩል የሰው ልጅ መለወጥና ወደ እምነቱ መመለስ የሚደገፍ ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ያለ ይፋዊ ይቅርታና የፖለቲካ ተጠያቂነት ወደ መንፈሳዊ መድረክ መሻገር የህዝብን ቁስል የሚነካ ሆኖ ተገኝቷል።
እውነተኛ የወንጌል አገልግሎት የሚጀምረው ከእውነትና ከፍትህ ነው። አቶ ኃይለማርያም ካለፈው ታሪካቸው ጋር በግልጽ ተጋፍጠው ለደረሰው ጥፋት የድርሻቸውን ሃላፊነት ወስደው ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታን እስካላወረዱ ድረስ ስብከታቸው ምንም ያህል ጥራዝ ቢኖረው በብዙሃኑ ዘንድ ካለፈው ታሪክ የመሸሻ ጥላ ተደርጎ መታሰቡ አይቀሬ ነው።
ታሪክ አይረሳም የህዝብ እምባም ዝም ብሎ አይታለፍም።
Via Henock Megerssa

22 days ago
የጥቁር ሕዝቦች ድምፅ በተመድ አዳራሽ - ኢትዮጵያ ለነፃነት የከፈለችው ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላቸው ትሥሥር እንደ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብቻ የሚታይ ሳይሆን፣ በታሪክ አውድማ ላይ በፅናት እና በሉዓላዊነት የተገመደ የክብር ሰንሰለት ነው።
ከሰማንያ ዓመታት በፊት ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍርስራሽ ላይ ቆማ አዲስ ተስፋን ስትፈልግ፣ ኢትዮጵያ ከ51ዱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ሆና የቻርተሩን ሰነድ ስትፈርም ተራ ተሳታፊ አልነበረችም።
ይልቁንም፣ የዲፕሎማቶቻችን ድምፅ የኃያላንን የበላይነት ለመሞገት እና የደካማ ሀገራትን መብት ለማስጠበቅ የሚተጋ የፍትሕ ጩኸት ነበር።
በወቅቱ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር ለነበሩት ወንድም የአፍሪካ እና የእስያ ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ተሟጋች ሆና መቅረቧ፣ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” የሚለውን ብሂል ወደ ጎን በመተው ለሰው ልጅ ሁሉ ነፃነት መቆሟን ያሳየ ታላቅ የሞራል ልዕልና ነበር።
ይህ የታሪክ አሻራ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈ ይገኛል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ የሰላም ዘቦችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማሠማራት፣ በዓለም ሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ ያላትን የማይናወጥ ሚና በተግባር አሳይታለች።
የሀገራችን ሠራዊት በሄደበት ሥፍራ ሁሉ የሚታወቅበት የጥንካሬ፣ የዲሲፕሊን እና የሕዝባዊነት ገጽታ፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ከሚያዋጡ ሀገራት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርጓታል። ይህ መሥዋዕትነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻችን እና ለመላው ዓለም ሰላም መቆማችንን የሚያረጋግጥ የቆራጥነት ማሳያ ነው።
በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚከናወኑት እነዚህ ተልዕኮዎች፣ የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገውታል።
ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸው እና የድርጅቱን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እዚህ በታሪካዊቷ ከተማችን እንዲከበር መወሰኑ፣ እንዲሁ የተገኘ ድንገተኛ ክስተት አይደለም። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ያበረከተችው ታሪካዊ አስተዋፅኦ እና ለዓለም ሰላም የከፈለችው መሥዋዕትነት የተሰጠው ታላቅ እውቅና ነው።
“መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል” እንዲሉ፣ የሀገራችን የዲፕሎማሲ ጥንካሬ እና የሠራዊታችን አኩሪ ገጽታ ለስምንት ዐሥርተ ዓመታት ተጠብቆ ቆይቶ ዛሬም በዓለም መድረክ ድምፃችን ጎልቶ እንዲሰማ አድርጎታል።
ይህም የአፍሪካን ዳግም መነሣት የሚያበስር ምልክት እና ለጋራ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን የጥንካሬ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ እና ተመድ በዘላቂ ልማት ግቦች ዙሪያ ያላቸው ትብብርም ሌላው የትሥሥሩ ገጽታ ነው። ድህነትን ለማጥፋት፣ ፕላኔቷን ለመጠበቅ እና ለሁሉም ሰው ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት፣ ሀገራችን ከድርጅቱ ጋር ያላትን ስትራቴጂክ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል።
ወደፊትም ቢሆን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ደጀን እና የልማት ተምሳሌት ሆና በመቀጠል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፍትሐዊ ሥርዓት እንዲሰፍን እና የጋራ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የነበራትን የሞራል መሪነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጥርጥር የለውም።
የታሪካችን ጥንካሬ እና የሠራዊታችን ፅናት ዛሬም ለዓለም ሰላም ዋስትና፣ ለትውልድም ኩራት ሆኖ ይቀጥላል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #diplomacy #un #un80

25 days ago
ተወዳጇ የጥበብ ፈርጧን እናሳክማት
ድምጻዊት ማዲቱ ወዳይ ( እሽክም) በስራ ምክንያት ከኮምቦልቻ ወደ መኖሪያ ቤቷ ወልድያ እየተጓዘች እንዳለ በ26/08/2018 ዓ.ም አመሻሽ ወልድያ ለመግባት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩ እየተጓዘችበት የነበረው መኪና ሞላ-ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከመድረሳችን በፊት የተሰበረ ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደርሶባት ለከፍተኛ ህክምና አዲስ አበባ መሄዷም ይታወቃል።
በአሁኑ ሰአት ድምጻዊት ማዲቱ ወዳይ ለከፍተኛ ህክምና ሜክሲኮ ከአፍሪካ ህብረት ፊትለፊት በሚገኘው ድሪም የአጥንት የአደጋዎችና የአከርካሪ ህክምና ማዕከል ትገኛለች።
የተደረገላት የራጅ፣ ሲቲስካንና ኤም አር አይ ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ግራ እጇ 3 ቦታ ላይ የአጥንት ስብራት ያለው ሲሆን ጀርባዋ (አከርካሪዋ) ከነርቭ ጋ በተያያዘ ጉዳት ደርሶባታል ፡፡
በተጨማሪም ሳምባዋም ላይ ችግር በመኖሩ ሁሉንም ችግሮች ለመፍታት ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት በባለሞያዎች ተነግሯቸዋል።
በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አድናቂዎቿ በምን እናግዛት የሚለውን ጥያቄ ፈጥነን ለማሳወቅ ለህክምናው የሚያስፈለገው ጠቅላላ ብር እስኪታወቅ ድረስ እየጠበቅን ስለነበር እገዛው ዘግይቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናዋ ተጀምሮ እስክታገግም ድረስ እስከ ብር 2,000,000 ( ሁለት ሚሊየን ብር) እንደሚያስፈልግ ታውቋል ።
በመሆኑም በመላው አለም ያላችሁ ወዳጆቿ፣ አድናቂዎቿና የጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ ገቢው አሁን ላይ ከጎኗ ሆኖ እያስታመማት በሚገኘው ባለቤቷ_ወርቅነህ_አበበ_ተሰማ ንግድ ባንክ አካውንት እንደሚሰበሰብ እና ሁሉም ሰው በይፋ እንዲያግዛት ወደ እናንተ መጥተናል፡፡
በሞያችሁም ሆነ በገንዘባችሁ ልታግዟት ያሰባችሁ የጥበብ ባለሞያዎች፣ በመላው አለም የምትገኙ ቲክቶከሮች ትልልቅ የሚድያ ገጽ ያላችሁ ወንድም እህቶች በመላው አለም የምትገኙ ወዳጆቿ አድናቂዎቿ በፍጥነት እንድትታከም በቻላችሁት ሁሉ እናግዛት ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ወርቅነህ አበበ ተሰማ (ባለቤቷ)
ንግድ ባንክ 1000088015097
ስልክ +251911095021
+251918252448

26 days ago
u201cu12a8u121bu121bu1230u12eb u12a5u1235u12a8 u1236u134bu2026u1240u122du12a8u1203 u12e8u1265u1228u1275 u12c8u1295u12f5u121du201d | u12cdu120e | u134bu1293 u1356u12f5u12abu1235u1275 | Fana Podcast","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[],"color_ranges":[]},"id":"UzpfSTEwMDA2OTY3MjY0MTY1OTpWSzoxNDc5MTQ5Njk3MjM2MjQz
“ከማማሰያ እስከ ሶፋ…ቀርከሃ የብረት ወንድም” | ውሎ | ፋና ፖድካስት | Fana Podcast
26 days ago
እንኳን ለልደታ ማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም።
በህግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።" ይላል ታላቁ ሊቅ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም፡፡
አባቷ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙር 86÷1-7 ግንቦት አንድ ቀን በሊባኖስ ተራራ የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ላይ ናቸው፡፡” በማለት አስቀድሞ ትንቢት ተናግሮላታል፡፡ “የተቀደሱ ተራሮች” ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ምስጢር ሲያመለክት ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ትንቢቱንና የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ “እመቤታችን በአባቷ ከንጉሡ ከዳዊት፤ በእናቷም ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው” ብላ ታስተምራለች፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡” በማለት በምዕራፍ 11÷1 ይናገራል፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ልደት ከሰው ሁሉ ልደት ይልቅ የከበረ ለአምላክ ሰው መሆን፣ ለተስፋው ቃል መፈጸም መንገድ የጠረገ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም አበባ የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት የተናገረው ከአበይት ነቢያት አንዱ ኢሳይያስ “ከዕሴይ ስር ትወጣለች” ያላት አበባን የምታስገኝ በትር፣ አምላክ ሰው የሆነባት፣ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመባት፣ በግንቦት አንድ ቀን የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የእመቤታችን ወላጆች ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷ ቅዱስ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በጊዜው ካህናቱ የመካኖችን መብዓ አይቀበሉም ነበርና፣ ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘን እንዲያርቅላቸው በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽመው ይማልዱ ነበር፡፡
የለመኑትን የማይነሳ አምላክም የልባቸውን መሻት ተመለከተ፡፡ ክቡር አባታችን ቅዱስ ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቆሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው በመውረድ የመልአኩን ብስራት ለቅድስት ሐና ነገራት። እርሷም ቃሉ እውነት እንደሆነ አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች፤ ሴትም ወንድም ብትወልድ በዘመናቸው ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ልታደርግ ስዕለት ተሳለች፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና የመጽነሷ ነገር ሲሰማም ቤተ ዘመዶቿ መጥተው ጎበኗት፡፡ አንድ አይኗ የማያይ ዘመድ ነበረቻት፣ “ሐና እግዚአብሔር ያደረገልሽ ይህ ድንቅ ነገር ምንድነው?” ብላ ማሕጸኗን በዳሰሰችበት እጇ አይኗን ብትነካው በርቶላታል፡፡
ይህን አብነት አድርገው ሕሙማን እየመጡ ይፈወሱ ነበር፡፡ አይሁድም ለምቀኝነት አያርፉምና የእነዚህ ወገን ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ቀጥቅጠው ገዙን አሁን ደግሞ ከዚህች የሚወለድ ሊገዛን ነውን? በድንጋይ ወግረን እንግደላት ብለው ተነሱ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ኢያቄምን ወደ ሊባኖስ ተራራ ይዘሀት ሽሽ ብሎት በዚያ ሳሉ ግንቦት 1 ቀን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዳለች፡፡ በድንጋጤና በጥድፊያ ሲወጣ ከያዘው ስንዴ በስተቀር የሚያቀርብላት ምግብ አልነበረውምና ንፍሮ ቀቅሎ፣ ቂጣ ጋግሮ አቅርቦላታል፡፡
በልደታ ቀን ንፍሮና ቂጣ የምንበላው ይህን አብነት አድርገን ነው፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ትተው፣ ከምግብ ርቀው ለነፍሳቸው ሲገዙ እርሷን ተስፋ አድርገው ነውና ጸሎታቸውን ፈጥና ታሳርጋለች፡፡ ምልጃዋ ሕይወትን በሚያሰጥ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም ገዳማውያኑን እንደግፍ በዓታቸውንም እናጽና፡፡ ከበረከትቷ እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

27 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሰው ልጅ ህይወት፣ ያውም የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ኃላፊነት በተሰጠው የፀጥታ አካል እጅ ሲቀጠፍ ከማየት በላይ ልብ የሚሰብር ክስተት የለም። በአዲስ አበባ ከተማ የተፈፀመውን አንጀትን የሚበላ የአንድ ዜጋ ግድያ ተከትሎ፣ የከተማው ፖሊስ ተቋም ድርጊቱን በፅኑ ሲያወግዝ፤ "ዲሽታጊና" በሚለው ተወዳጅ ስራው የሚታወቀው ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሲ ደግሞ ጥላቻን እና ፍርሃትን የሚያወግዝ ጥልቅ የልብ ጩኸቱን አሰምቷል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አካባቢ ነው። በዕለቱ ከቀኑ 10፡40 ላይ፣ ረዳት ሳጅን ማቴዎስ ተመቸው የተባለ የፖሊስ አባል አቶ ተገኝ ባልቻ የተባሉትን ግለሰብ በክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተኩሶ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል። ፖሊስ ግድያውን የፈፀመውን አባል ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ጀምሯል።
ከዚህ ዘግናኝ ድርጊት ጀርባ ያለውን መንስኤ ፖሊስ ሲያብራራ፣ በሟች እና በፖሊስ አባሉ መካከል ከዚህ ቀደም የተፈጠረ ቂም እንደነበር ጠቁሟል። ከዚህ በፊት በተፈጠረ ጠብ አቶ ተገኝ በፖሊስ አባሉ ላይ ጉዳት አድርሰው ታስረው በዋስ ወጥተው ነበር። ይሁንና በዕለቱ ሟች በሌላ ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው ወደ ጣቢያ ሲመጡ፣ ከመኪና ወርደው ወደ ውስጥ አንገባም በማለታቸው በተፈጠረ ግብግብ ይህ አሳዛኝ ግድያ ሊፈፀም ችሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህንን ድርጊት "ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት" ሲል በፅኑ አውግዞታል። ምንም እንኳን ግለሰቡ ከፖሊስ አባላት ጋር ግርግር መፍጠራቸው ተገቢ ባይሆንም፣ የፖሊስ አባሉ የወሰደው የጭካኔ እርምጃ የፖሊስን ዓላማ የሚፃረር እና ተቋሙን የማይወክል መሆኑን አስረግጦ በመግለፅ፤ ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የሰዎችን ህይወት በከንቱ መጥፋት በቅርበት የሚታዘበው ተወዳጁ ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሲ (ዲሽታጊና)፣ ሀዘኑን ከመግለፅ ባለፈ ልብን ሰርስሮ የሚገባ የማንቂያ መልዕክት አስተላልፏል። በአሁኑ ወቅት ሰዎችን እርስበርስ እያባላ ያለውን የፍርሃት እና የጥርጣሬ ግድግዳ እንድናፈርስ ጥሪውን አቅርቧል።
"ጎረቤትህ ጠላትህ አይደለም፤ እሱም እንደ አንተ በኑሮ ውድነት የሚቃጠል፣ የሰላም ጥማት ያለው ወንድምህ ነው" በማለት የፃፈው ታሪኩ፣ ችግራችን የዘር ሳይሆን እርስ በእርሳችን እንድንፈራራ የሚያደርገን የፍርሀት ግድግዳ መሆኑን አስምሮበታል። አክሎም "እኛ ስንተማመን ጭቆና በራሱ ይፈርሳል፤ እጅ ለእጅ እንያያዝ፤ ያኔ ፍርሀት ቦታ አይኖረውም" ሲል ጽፏል።
የፖሊስ ጥብቅ የምርመራ ቃል እና የድምፃዊው የመተማመን ጥሪ በአንድ ላይ ሲታዩ፣ እንደ ማህበረሰብ ከጥላቻ እና ከበቀል አዙሪት ወጥተን "የነገውን የመተማመን ቤት አብረን እንገንባ" የሚለውን ጥልቅ መልዕክት የሚያስተጋቡ ናቸው። የሰው ልጅ ህይወት ክቡር ነው፤ ፍትህ ለሟች ቤተሰቦች እንዲሰጥና መሰል አሳዛኝ ድርጊቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

29 days ago
ኢትዮጵያ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም እያስተዋወቀች ነው - የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች
****************
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል።
ጉባኤውም ከነገ ሚያዚያ 29 እስከ 30/2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው።
የ471 ሚሊዮን ተከታይ ባለቤት የሆኑ የ30 ሀገራት የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እየከተሙ ይገኛል።
በአጠቃላይ 321 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ሲሆን፤150 ሚሊዮን ተከታይ ያሏቸው 120 ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን የማህበራዊ ሚዲያ የይዘት ፈጣሪዎች ይቀላቀሏቸዋል።
አዲስ አበባ የገቡ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አፍሪካ የሚነገሩ ብዝኅ እውነቶችና ፀጋዎች ሳሏት ዓለም በተሳሳተ ትርክት እንደሚረዳት ገልጸዋል።
ቦትስዋናዊው ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ ዊሊያምላስት ኬአርኤም፤ በአስደናቂ ውበትና ዕድገት እየተጎናጸፈች የምትገኘው የአፍሪካዊያን መናገሻዋ አዲስ አበባ ሁለተኛ ቤቴ ናት ብሏል።
የአፍሪካን እውነተኛ ታሪክ ለዓለም ለመግለጥ በሚፈጥራቸው ይዘቶችም ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካን እውነት ለዓለም በመግለጥ አስደናቂ ሥራ እየሰራች ነው ያለው ዊሊያምላስት፤ ይዘት ፈጣሪዎችም የራሳችን ታሪክ በትክክል በማስተዋወቅ የተዛባ ትርክትን ማረም አለብን ብሏል።
ማህበራዊ ሚዲያ ታሪክን በራስ ድምፅ ከመናገር አንጻር ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥቷል።
ዑጋንዳዊቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አኳንጃ ኢስተር፤ የአፍሪካን የተሳሳተና የተዛባ ትርክት ለመቀየር የአህጉሪቷ ልጆች የሌላ ዓለም ነጋሪ እንደማያሻቸው ገልፃለች።
በጉባኤው ለመታደም አዲስ አበባ ከተማ በመገኘቷም ከአህጉሪቷ ወንድምና እህቶቿ ጋር ጠንካራ የትስስር ዕድል የምትፈጥርበት መሆኑን ተናግራለች።
አፍሪካዊያን ታሪካችንን በራሳችን እጆች ካልጻፍን ሌላው ወገን በተሳሳተ መንገድ ይከትብብናል ያለችው ደግሞ ሌላኛዋ ዑጋንዳዊት የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኒያኮ አካንጃ ናት።
የአፍሪካን አዎንታዊ ምስል ለዓለም ለማሳየትም የአህጉሪቱ ይዘት ፈጣሪዎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝባለች።
ጉባኤውም አፍሪካዊ ወንድምና አህትማማችነትን በማጠናከር እውነተኛ የአፍሪካ ትርክት ማስተጋባት የሚያስችል ወሳኝ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግራለች።
በተመሳሳይ የጉባኤው ተሳታፊ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዑጋንዳዊው ኦንጅዮ ጆሾዋ፤ ጉባኤው የእርስ በእርስ ትውውቅን በመፍጠር ለጋራ ዓላማ መስራት የሚያስችል ነው ብሏል።

30 days ago
የትውልዱ ታሪካዊ ጥሪ
**********
(የዕለቱ መልዕክት)
“ቢተባበሩ ግንድ ይነቅሉ፣ ቢነጣጠሉ ቅጠል ይበጥሱ” እንዲሉ ዛሬ ይህንን አባባል ወደ ተግባር የምንቀይርበት ታሪካዊ ጊዜ ላይ እንገኛለን።
የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የፀጥታ፣ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የሕክምና እና የትምህርት ዐርበኞች ተባብረው ካልቆሙ የሀገር ሕልውና ፈተና ውስጥ ይወድቃል።
በተለይ ይህ ትውልድ የሚጠበቅበት ዐርበኝነት የታሪክ ሸክሙን የሚመጥን ሊሆን ይገባል። የቀደሙት እናት እና አባት ዐርበኞቻችን እግራቸውን ለሾኽ፣ ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ከፋሺስት ወራሪ ጋር የተጋደሉት ለሀገር እና ለወገን ብለው ነበር።
ክብርን በውርደት፣ ነፃነትን በባርነት ላለመቀየር ሲሉ የሞት ሞታቸውን ተፋለሙ። "እናትህን በሞት ወንድምህን በጦር" እንደሚባለው ሁሉ፣ እነርሱ ለነጻነታችን ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን ገብረዋል።
"ዐርበኝነት በጦር ሜዳ መሞት ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚበጅ ሥራን ሠርቶ ማለፍም ጭምር ነው። ዐርበኝነት የሞት ብቻ ሳይሆን የሕይወትም፣ የልማትም መንገድ ነው። በአሁኑ ወቅት የዐርበኝነት ትርጓሜ ከጥይት ድምፅ ባለፈ በብዕር ጫፍ፣ በቴክኖሎጂ ምጥቀት እና በላብ ጠብታ ውስጥ ይገኛል።
የጥንት ዐርበኝነት በዱር በገደሉ እንደነበረው ሁሉ የዘመኑ ዐርበኝነት ደግሞ በዕውቀት፣ በሥነ-ምግባር እና በሥራ ትጋት የሚገለጽ ነው።
በሀገራችን የተጀመረውን ሀገራዊ ምክክር እና ጠቅላላ ምርጫ ማሳከት የዘመናችን ትልቁ ዐርበኝነት ነው።
"የቤት ሥራውን የጨረሰ እንግዳ አይፈራም" እንዲሉ፣ የውስጥ አንድነታችንን በማጠናከር እና የዴሞክራሲ ተቋሞቻችንን በመገንባት የውጭ ተጽዕኖን መቋቋም ይቻላል። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር የሚከፈል፣ ከራስ ወዳድነት አረንቋ የነጻ ታላቅ መሥዋዕትነት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉትም ዓላማው ሀገርን እና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ እንጂ ለግል ዝና ወይም ለቡድን ክብር የሚሰለፉበት አውድ አይደለም።
ትውልዱ ካለፈው ታሪክ ሀገር ተረክቧል፤ ለሚቀጥለው ትውልድ ደግሞ የተሻለች እና የበለጸገች ሀገር የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። "ልጅ ለወላጁ፣ ሀገር ለልጇ" እንዲሉ፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ ዛሬ የምንከፍለው መሥዋዕትነት የነገው ማንነታችን ማኅተም ነው።
የዘመኑ ዐርበኝነት በየተሰማራንበት መስክ የምናሳየው ታማኝነት፣ ለሕዝብ የምንሰጠው ቅን አገልግሎት እና የሌብነትን እና የጥፋትን መንገድ "አይሆንም" ብለን የምንቆምበት ጽናት ነው።
የዲጂታሉ ዓለም የሐሰት ወሬ እና የከፋፋይነት ዘመቻ ሌላኛው የውጊያ ግንባር ነው። በዚህ ግንባር እውነትን አንግቦ መቆም፣ የታሪክ አደራን መጠበቅ እና የሀገርን ገጽታ መገንባት ከዘመኑ ዐርበኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
ዐርበኝነት ለጥቂቶች የተተወ የቤት ሥራ አይደለም። "አንድ ሰው ካልመከረ፣ ጭድ በዝቶ ካልመገረ" እንደሚባለው፣ ሁላችንም በጋራ ካልቆምን የግል ነጻነታችንም ቢሆን ትርጉም አይኖረውም።
የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚረጋገጠው በየቢሮው፣ በየእርሻው፣ በየላቦራቶሪው እና በየጥበቃ ግንባሩ ራሳቸውን ለሀገር ክብር የሚገብሩ ዐርበኞች ሲበዙ ነው። ይህ ትውልድ የቀደምቶችን ታሪክ እያነበበ ብቻ መኖር የለበትም፤ የራሱም አዲስ ታሪክ መጻፍ ይኖርበታል።
"ካለፈው ተምሮ ለወደፊቱ መኖር" ብልህነት ነው። ስለዚህም፣ ከባንዳነት እና ከከፋፋይነት መንፈስ ወጥተን፣ ለብልጽግና እና ለነጻነት የምንሰለፍበት የዘመኑ ዐርበኝነት ጥሪ ዛሬም በደጃችን ላይ ይገኛል።
ይህንን ጥሪ ተቀብሎ ሀገርን ወደ ብልጽግና ማማ ማውጣት የታሪክም የትውልድም ግዴታ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #patriotism #patriotsday #unity

1 month ago
የሦስት አስርተ ዓመታት የፍቅር እና የጽናት ጉዞ የአንጋፋዎቹ ተወዛዋዦች ዳምጠው ወርቁ እና ጌጤ በሰይፉ አስደናቂ የትዳር ምስጢር
#ethiopia | በትዳር መፍረስ ዜናዎች በበዙበት በዚህ ዘመን ለሰላሳ ዓመታት በፍቅር እና በአንድነት የዘለቁት አንጋፋዎቹ የሀገር ፍቅር ቴአትር ተወዛዋዦች ዳምጠው ወርቁ እና ጌጤ በሰይፉ ሾው ላይ ቀርበው ያካፈሉት ተሞክሮ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ነው። ይህ ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የትዳር ሕይወታቸው ስኬት ቁልፉ መቻቻል እና ትዕግስት መሆኑን ጥንዶቹ ገልጸዋል።
ትዳር እንደ አንድ ትልቅ ተቋም በሂደት የሚገነባ መሆኑን የገለጹት እነዚህ ጥንዶች ከባልና ሚስትነት ባለፈ ወደ ጥልቅ ጓደኝነት እና እንደ እህትና ወንድም ወደ መተሳሰብ ደረጃ መሸጋገር መቻሉ ለፍቅራቸው መጽናት ትልቁ ምስጢር እንደሆነ አስረድተዋል።
ለአስራ ስምንት ዓመታት በአሜሪካ ቢኖሩም ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን እና ባህላቸውን ጠብቀው የቆዩት ጥንዶቹ ዛሬም ድረስ በማንኛውም የደስታ ስፍራ አብረው በመጨፈር ይታወቃሉ።
ዳምጠው ወርቁ እንደገለጸው እንደ ጉራጊኛ፣ ወላይትኛ እና ትግርኛ ያሉ የሀገራችን ባህላዊ ውዝዋዜዎች ከየትኛውም የሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት በላይ ለጤና ተመራጭ እና ለረጅም ዕድሜ ጠቃሚ ናቸው።
ባለቤቱ ጌጤ በበኩሏ ስጋን ከመመገብ በመቆጠብ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል ውበቷን እና ወጣትነቷን መጠበቅ እንደቻለች ተናግራለች።
በስደት ዓለም የሚገጥሙትን የሥራ ጫናዎች በጽናት በማለፍ እና ልጃቸውን በመልካም ስነምግባር በማሳደግ ውጤታማ መሆን የቻሉት ጥንዶቹ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለወገናቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
በተለይም ባለቤታቸው ለሥራ ጉዳይ ለስምንት ወራት በራቁበት ወቅት ጌጤ በብቸኝነት ያሳለፈችው የእርግዝና ጊዜ ለትዳራቸው ጥንካሬ ትልቅ ትምህርት እንደሆነ አስታውሰዋል።
በመጨረሻም ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት ያላቸውን መልካም ምኞት በመግለጽ ለፍቅር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ መክረዋል።
#ethiopianart #marriageadvice #loveandresilience #ethiopianculture #relationshipgoals #inspiration #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ከሜዳው በስተጀርባ ያለው ፍቅር
የቀድሞው ከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ስፖርተኞች መታሰቢያ ውድድር
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በ1970 እና 1975 ዓ.ም መካከል በከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ በጋራ ያሳለፉ አብሮ አደጎች፣ በሕይወት የሌሉ የቡድን መሪዎችንና ተጫዋቾችን ለመዘከር የታለመ ልዩ መርሐ ግብር አካሄደዋል።
ይህ መርሐ ግብር ያለፈውን ትዝታ ከማደስ ባለፈ፣ ለወደፊት ትልቅ የበጎ አድራጎት አሻራ ጥሏል።
የታሰቡ ባለውለታዎች
አመራሮችና አሰልጣኞች
አቶ ጌታቸው ወርቄ (የቡድን መሪ) እና አስር አለቃ በቀለ እሽቴ (ወጌሻ)።
ተጫዋቾች
ደጀን ሀጎስ፣ እስጢፋኖስ ሀብቴ፣ ልዕል ገብረህይወት፣ ግርማ መገርሳ፣ ወንድሙ አንጌቻ፣ ሰለሞን አባተ፣ አበበ ዘውዴ እና ሰመረ ደበሳይ።
እነዚህ ታታሪ ስፖርተኞች በቤተሰቦቻቸውና በቀድሞ ጓደኞቻቸው (አስማማው ጥጋቡ ክብረትን ጨምሮ) አማካኝነት በክብር ታስበዋል።
የቀበሌ 09 ነዋሪዎች ኅብረት
ይህ መርሐ ግብር በዋናነት አሁን በሕይወት ያሉ ወንድምና እህቶችን በጋራ ለመርዳት የሚቋቋመው ኀብረት መሠረት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም ለቄራ 09 የጤና ስፖርት ቡድን የ20 ማልያና የኳስ ስጦታ በመስጠት ለአዲሱ ትውልድ አርአያነታቸውን አሳይተዋል።
የጨዋታው ውጤት
በነባር ተጫዋቾችና በጤና ቡድኑ መካከል በተደረገው ጨዋታ፣ መደበኛው ሰዓት 3 ለ 3 በሆነ ውጤት ተጠናቆ በመለያ ምት የቀድሞው ከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ቡድን አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል።
እግር ኳስ ድልና ሽንፈት ብቻ አይደለም፤ እንዲህ ያለ የጠበቀ ጓደኝነትና የሰፈር ፍቅር መገለጫም ነው። የቀድሞ አብሮ አደጎች ተሰባስበው ታሪካቸውን ሲያድሱና ያለፉትን ሲያስቡ ማየት ትልቅ የሞራል ጥንካሬ ይሰጣል። ይህ ኅብረት ለሌሎች ሰፈሮችም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።
ክብርና መታሰቢያ ለታታሪ ስፖርተኞቻችን!
#getu #kebele09legacy #addisababafootball #veteranplayers #ethiopiansporthistory #communityunity #sportforgood #ቀበሌ09 #መታሰቢያ #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ለቀድሞ የስፖርት ባልደረቦች መታሰቢያ የሚሆን የእግር ኳስ ውድድር ተካሄደ
በ1970 እና 1975 ዓ.ም መካከል በከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ በጋራ ያሳለፉ አብሮ አደጎች፣ አሁን በሕይወት የሌሉ የቡድን መሪዎችንና ተጫዋቾችን ለመዘከር የታለመ ልዩ መርሐ ግብር አካሄዱ።
ክብርና መታሰቢያ ለታታሪ የስፖርት ቤተሰቦች
ይህ የውድድርና የመታሰቢያ መርሐ ግብር በዋናነት የተዘጋጀው የሚከተሉትን ባለውለታዎች በክብር ለማሰብ ነው ከቡድኑ አመራሮችና አሰልጣኞች
አቶ ጌታቸው ወርቄ (የቡድን መሪ)፣ አስር አለቃ በቀለ እሽቴ (የቡድኑ ወጌሻ) ከቡድኑ ተጫዋቾች ደጀን ሀጎስ፣እስጢፋኖስ ሀብቴ፣ልዕል ገብረህይወት ፣ግርማ መገርሳ፣ ወንድሙ አንጌቻ፣ ሰለሞን አባተ፣ አበበ ዘውዴ እና ሰመረ ደበሳይ ሲሆን በዕለቱም አስማማው ጥጋቡ ክብረት እና ሌሎች የቀድሞ የቡድን አባላት በመገኘት እነዚህን ስፖርተኞች በቤተሰቦቻቸው ተወክለው እንዲታሰቡ አድርገዋል።
አዘጋጆቹ እንደገለጹት ይህ መርሐ ግብር ያለፈውን ከማሰብ ባለፈ የወደፊት ትልቅ ዓላማ አለው። ይህም አሁን በሕይወት ያሉ ወንድምና እህቶችን በጋራ ለማገዝ ታስቦ እየተቋቋመ የሚገኘው "የቀበሌ 09 ነዋሪዎች ህብረት" መሠረት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ለስፖርቱ መነቃቃትና ለአዲሱ ትውልድ ማበረታቻ እንዲሆን ከከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ነባር ቡድን ለቄራ 09 የጤና ስፖርት ቡድን የ20 ቁምጣና ማልያ እንዲሁም የኳስ ስጦታ ተበርክቷል።
በመጨረሻም በነባር ተጫዋቾችና በጤና ቡድኑ መካከል በተደረገው ጨዋታ፣ መደበኛው ሰዓት 3 ለ 3 በሆነ ውጤት ተጠናቆ በመለያ ምት የቀድሞው ከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ቡድን አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል።

2 months ago
#የልህቀትና #የትሕትና ##ተምሳሌት# #ዶክተር #ዋቆ #ገዳ !
#ethiopia | በዓል ማለት ለብዙዎቻችን ከቤተሰብ ጋር መሰብሰብ ፣ በሞቀው ማዕድ ዙሪያ መሳቅና መጫወት ማለት ነው ።
እንዲያውም አንድ የቢሮ ሰራተኛ እንኳን ቀኑን ከቤቱ ውጪ ለማሳለፍ በማይፈቅድበት ፣ ትልቁ የፋሲካ ዕለት ነገር ግን ለየት ያሉ መሪዎች "ቤተሰብ" የሚለውን ትርጓሜ ከገዛ ቤታቸው አጥር አሻግረው ያዩታል ።
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አንድ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ተፅፏል ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዴንት ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ የፋሲካን ዕለት ከገዛ ቤተሰባቸው ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ፣ "ቤተሰቦቼ ናቸው" የሚሏቸውን ተማሪዎቻቸውን በማሰብ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው በዓሉን አብረው አሳልፈዋል ።
ይህ ተግባር እንዲሁ በቀላሉ የመገኘት ጉዳይ ፤ ሳይሆን የእውነተኛ የመሪነት መገለጫ ፣ አመራር ከቢሮ ወንበር በላይ መሆኑን ያሳየ ፤ የአባትነት ፍቅር ፣ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ባሉበት ወቅት ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ያደረገ ፤ የትሕትና ልክ ፣ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ሆኖ ራስን ዝቅ አድርጎ ከተማሪዎች ጋር መሳተፍ ለሌሎች አመራሮችም ትልቅ ትምህርት ነው ።
ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ ተማሪዎችን እንደ ወንድም ፣ እንደ እህትና እንደ ልጅ ተመልክቶ በበዓል ዕለት አብሮ በመሆን የመጀመሪያው ከፍተኛ አመራርና ፕሬዚዴንት በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ፅፈዋል ።
ለዚህ ድንቅ መሪና ፕሬዚዴንት ፣ ለዚህ ትሁት አገልጋይና ለዚህ የለውጥ ሰው ያለንን ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እንገልጻለን ‼️
ኢትዮጵያ እንደ ዶክተር ዋቆ ያሉ ፣ የሕዝባቸውን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ መሪዎች ያስፈልጓታል ።
ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ! 👏🙌
ጌታቸው ባይባ ሚዛን አማን !
#mizantepiuniversity #leadership #inspiration #drwakogeda #ethiopia #serviceaboveself

ግዮን መጽሔት በቅዳሜ ዕትሟ !!!
አቶ ክቡር ገና ታዋቂ የምጣኔ ሃብት ምሁር ናቸው ለዛሬ ስለ ባንኮቻችን ምን ይሉናል።
ትልልቅ ባንኮችን ቅዱስ፤
ትንንሽ ባንኮችን እርኩስ ያደረጋቸው ማነው?
በግዮን እንግዳ አምዳችን -የሪል ስቴቶች ችግራቸዉና መፍትሄዉ ምንድነዉ በሚለዉ ዙሪያ ሰፊ ቃለ-ምልልስ አድርገናል ተከታተሉት።
‹‹ሀገር ጥለው የጠፉና ድርጅቶቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱ አሉ››
‹‹[ሪልስቴቶች] ስማቸውን ማጽዳት አለባቸው›› አቶ አለማየሁ ከተማ
(የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት)
ነገረ ትንሣኤ - ከምሥጢሩ እስከ ማኅበራዊ ፋይዳው ታብራራለች
‹‹በዓለም ዙሪያ በርካታ ኮሚኒስቶች ነበሩ፣ ማናቸውም አገራቸውን ለመበተን አልቃጡም››
የምርጫ 1997 ዓ.ም አጣሪ ኮምሽነር የነበሩት ዳኛና ፕሬዝዳንት ፍሬሕይወት ሳሙኤል ጋር የነበረንን ቆይታ ተጋብዘዋል።
‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ
በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)
ዝክረ ጥላሁን ገሠሠ
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ(ለንደን)
በኢኮኖሚ አምዳችን -እየወደቀው ያለው የግማሽ ክፍለ ዘመን ኃያልነት! ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
በጆሀንስበርግ በ16 ጥይት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ወንድምነህ አየለ
የምርጫ ካርድ፡ የአገር ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ - (YCDF) ከአውሮፓ የምርጫ ድጋፍ ማዕከል (ECES) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
በዓለም አቀፍ አምዳችን ስለ ኢራን ጦር ያሰናዳነዉንና በመጽሔታችን የተዘጋጁትን የተለያዩ መጣጥፎችን እንድታነቡ ተጋብዛችኋል ። መልካም ንባብ !!!

ክርስቲያን ቲዩብ 12ኛ ዓመቱን አከበረ
*ያሠራውንም ስቱድዮ አስመረቀ
(ከዕዝራ እጅጉ)
ከ550ሺህ በላይ ተከታዮችን ያፈራውና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ያገለገለው ክርስቲያን ቲዩብ ታላላቅ አገልጋዮች በተገኙበት 12ኛ አመቱን አክብሯል።
የሚኒስትሪው መስራች ወንድም ክብረአብ ማናዬም አገልግሎቱ ለዚህ ደረጃ በመብቃቱ እግዚአብሔርን አመስግኗል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ መጋቢ ዶ/ር ጌትነት ለማ፤ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪ መጋቢ ታምራት አበጋዝ
እና ሌሎች አገልጋዮች በታደሙበት የክርስቲያን ቲዩብ በይፋ ወደ ሚኒስትሪ አገልግሎት ማደጉ ተነግሯል።
ክርስቲያን ቲዩብ ሚኒስትሪ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የተመዘገበ እና ህጋዊ ሰውነት ያለው የሚዲያ ሚኒስትሪ ሲሆን የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል በሚዲያ በማስተላለፍ እና ለቤተክርስቲያን በተለያየ ዘመናት ድምፅ በመሆን ከ12 አመታት በላይ ያገለገለ ሚድያ ነው።
የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጌትነትም ሚድያው ለ12 አመታት በፅናት ወንጌላውያንን ማገልገሉን ዕውቅና ሰጥተው ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።መጋቢ ታምራትም በተመሳሳይ መልኩ የሚድያ ሥራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ በመሆኑ የክርስቲያን ቲዩብ ባልደረቦችም ይህን አደራ እንደሚወጡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ተቋማችንም በሚችለው መልኩ ለማገዝ ጥረት ያደርጋል በማለት ሚኒስትሪው እዚህ በመድረሱ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልፀዋል።
ክርስቲያን ቲዩብ በማህበራዊ ድረገጾች መረጃ ከማስተላለፉ አስቀድሞ 'ማራናታ' መፅሄትን በማሳተም ያሰራጭ እንደነበር በዕለቱ ተነግሯል።
ክርስቲያን ቲዩብ በጊዜው ብቸኛ ሊባል የሚችል የወንጌል አማኞች የፌስቡክ ገፅ በመሆንም አገልግሎት ሰጥቷል።በጊዜው መንፈሳዊ መልዕክቶችን ቶሎ ቶሎ በማድረስ ኃላፊነቱን የተወጣው ይህ ሚድያ አሁን ትልቅ ቦታ የደረሱ አገልጋዮችን ገና ሲጀምሩ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ያበረታታ መሆኑም ተነግሯል።
የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያንን መጋቢ ዮናታን አክሊሉ ገና አገልግሎት ሲጀምር የክርስቲያን ቲዩብ መስራች ወንድም ክብረአብ ማናዬ ቃለ መጠይቅ በማድረግ አገልግሎቱን እንደደገፈው ገልፆ ለዚህም ምስጋናዬን አቀርብለታለሁ በማለት የወንድም ክብረአብን አገልግሎት እግዚአብሔር እንዲባርከው መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ወንድም ክብረአብ ማናዬ ለተወዳጅ ሚድያ ሲናገር ".... አስራ ሁለተኛ አመታችን ላይ ጌታ ረድቶን አገልግሎታችንን ወደ ሚኒስትሪ አሳድገናል። ለወንጌል መስፋፋት፣ ለክርስቶስ አካል መታነፅ፣ ለሰዎች መዳንምክንያት የሚሆኑ ሥራዎችን ለመስራት እየተዘጋጀን እንገኛለን። ለዚህም እንዲረዳን ዘመናዊ ስቱዲዮ እንዲሁም ድህረገፅ አሰርተን አስመርቀናል። ይህ ድረ ገፅ በዲጂታል አለም የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል ለማሠራጨት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል።
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን አሁናዊ ሁኔታ የምንረዳበት ትልቅ መድረክ በመሆኑ ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል"ብሏል።
https://christiantubeminis...
እስከዛሬ ክርስቲያን ቲዩብ ላይ የቤተክርስቲያን ትምህርቶች ፣ የቤተክርስቲያን ተከላዎች፣ ሚሽነሪነት ፣ የአብያተክርስቲያናት እና የአገልጋዮች ታሪኮች በስፋት የቀረቡ ሲሆን ይህም ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወንድም ክብረአብ ያስረዳል።
በዕለቱ ንግግር ካደረጉ አገልጋዮች ውስጥ ሐዋርያ ዘላለም ጌታቸው፣ መጋቢ ሔኖክ መንግሥቱ፣ መጋቢ ፍፁም ንጉሤ ሁሉም በአንድ ድምፅ ክርስቲያን ቲዩብ በዲጂታል አለሙ ለወንጌል መከታ በመሆን በትጋት ማገልገሉን የተናገሩ ሲሆን ወደፊትም ከሚኒስትሪው ጎን በመሆን በገንዘብ፣ በማቴሪያል እና በምክር እንደግፋለን ብለዋል። ይህን ቃላቸውንም እዚያው መድረኩ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ከ100,000 ጀምሮ በመስጠት ለሚኒስትሪው ማደግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የክርስቲያን ቲዩብ መሥራች ወንድም ክብረአብ በመርሀግብሩ ላይ ለታደሙት እና ድጋፋቸውን ላሳዩት በሙሉ ምስጋናውን ገልፆ ሚኒስትሪው ወደፊት ትልልቅ ሥራዎችን እንደሚሠራም ተናግሯል።
ከዩኒቲ ዩንቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ወንድም ክብረአብ ማናዬ የጋዜጠኝነት እና የሚድያ ፍቅር ከልጅነቱ ጀምሮ እንዳደረበት ይናገራል።
"...መንፈሳዊ ፅሁፎችን እፅፍ ነበር። እናም ከአንድ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ባሮክ የሚል መፅሔት የተወሰነ ቅፅ ብቻ የታተመ አዘጋጀሁ። ከዛም ራሴ ማራናታ የተሰኘች ለአመታት የታተመች መንፈሳዊ መፅሄት ማዘጋጀት ጀመርኩ።ከልጅነቴ ጀምሮ መፅሀፍቶችን ማንበብ በተለይ የ ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ እና የአዳም ረታ በጣም አድናቂ ነበርኩኝ። ሌሎችን ልብ ወለዶችን በጣም አብዝቼ አነብ ነበር። ከዛም በጊዜው የነበሩ መፅሄቶችን አንድም ሳያልፈኝ አነብ ነበር። በሂደትም ወደ ሚድያ ሥራ ውስጥ በመግባት ክርስቲያን ቲዩብን መመስረት ቻልኩ" ሲል ወንድም ክብረኣብ ለተወዳጅ ሚድያ በሰጠው ቃል ተናግሯል።

የሀምበሪቾ 777 ደረጃ የተራራ ላይ ውድድር! 🏃♂️💨
ሀምበሪቾ 777 ተራራ ብቻ አይደለም፤ የታታሪነታችንና የጥንካሬያችን አርማ ነው!" በሚል መሪ ቃል፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የሚገኘው ድንቁ የሀምበሪቾ ተራራ፣ ታላቅና ታሪካዊ የተራራ ላይ የደረጃ ውድድር ሊያስተናግድ ቀጠሮ ተይዟል።
ይህ ውድድር የሰው ልጅ ጽናትና የተፈጥሮ ውበት የሚገናኙበት፣ የከምባታ ህዝብ ኩራት ለዓለም የሚታይበት ልዩ መድረክ ነው!
ፈታኙ የ777 ደረጃዎች ጉዞ፦
ተወዳዳሪዎች ከተራራው ግርጌ ካለው ለምለሙ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ ተነስተው፣ የ 777ቱን አስደናቂ ደረጃዎች በመርገጥ የተራራውን አናት ቀድመው ለመርገጥ ብቃታቸውን ይፈትናሉ። ይህ በአፍሪካ ደረጃ ለየት ያለ የከፍታ ሩጫ (Vertical Race) ተሞክሮን ይሰጣል።
ዳጎስ ያለና አበረታች ሽልማት፦
ለጽናታቸው አሸናፊዎች (ለወንድም ለሴትም) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ማራኪ የገንዘብ ሽልማት፣ የክብር ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል።
የኪነ-ጥበብና የባህል ድግስ፦
በተራራው አናት ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የባህል ቡድኖች፣ የከምባታ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ አልባሳትና የጥበብ ስራዎች ለታዳሚው በድምቀት ይቀርባሉ።
የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ስህበት፦
ውድድሩ ሀምበሪቾን በዓለም አቀፍ የስፖርት ቱሪዝም ካርታ ላይ ለማስፈርና አካባቢውን ለኢንቨስትመንት ምቹ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ሰንቋል።
👕 የውድድሩ ቲሸርቶችና ምዝገባ፦
ልዩ ዲዛይን ያላቸው ቲሸርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተዘጋጅተዋል። ቲሸርቶቹን በመግዛት የውድድሩ ተሳታፊ መሆን ይቻላል።
ቲሸርቶቹን ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የዞኑ ከተሞች በሚገኙ መሸጫ ጣቢያዎች ያገኛሉ!
የዕለቱ መርሃ-ግብር መረጃ፦
ቀን፦ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
መነሻ ቦታ፦ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ (ከተራራው ግርጌ)
መድረሻ ቦታ፦ የሀምበሪቾ ተራራ አናት (777ኛው ደረጃ)
አድራሻ፦ ዱራሜ ከተማ፣ ከምባታ ዞን
ኑ!
የታሪክ አካል ይሁኑ! Betty Event Organizer (ቤቲ ፕሮሞሺን) ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ይህንን ዝግጅት በላቀ ጥራት አሰናድተው ይጠብቁዎታል።
📞 ለበለጠ መረጃ፣
ለምዝገባና ለቲሸርት ትዕዛዝ በዚህ ስልክ ይደውሉ፦ 0902917695
ሀምበሪቾ 777 -
ወደ የከፍታ የምንወጣበት፣ ኩራታችንን ለዓለም የምናሳይበት!
#hambericho777 #hamberichostairsrace #777stepchallenge #mounthambericho #durame #kambata #centralethiopia #visitethiopia #mountainrace #bettyevents #athleticsethiopia #ethiopia #ሀምበሪቾ777 #ደረጃሩጫ #ከምባታ #ዱራሜ #ቱሪዝም #ጌጡተመስገን #getutemesgen #getu

የሟች ህፃን ናኦድ አጎት የሞት ቅጣት ተላልፈበት
#ethiopia | ላልተገባ ጥቅም ሲባል ህፃን ናኦድ ተኽላይን በአስቃቂ ጭካኔ የገደሉ አራት ወንጀለኞች ከሞት እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።
ከአራቱ ወንጀለኞች አንዱ በሌለበት የ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲከታተለው የቆየው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ አግኝቷል።
ሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ ሀምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ዙሪያ ነበር አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት።
ግድያው የተፈጸመው ታግቶ ለማስለቀቂያ 2 ሚሊዮን ብር ከተጠየቀበት በኋላ ነው።
የሟች እናት ወ/ሮ ዮርዳኖስ ጋይም " በልጄ ግድያ ቁጥር አንድ ተጠርጣሪ የሆነው የቅርብ ቤተሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ቢሆንም እስከ አሁን የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የለም " በማለት የፍትህ መዘግየቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው መግለፃቸውን አስነብበን ነበር።
" የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል " ሲሉ ነበር የሟች እናት የገለጹት።
ጭካኔ የተሞላበት የግድያ አፈፃፀሙ ከአንድ ዓመት በላይ ሲከታተል የቆየው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በሦስት ወንጀለኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚሁ መሰረት ፦
- የሟች ህፃን ናኦድ እናት #ወንድም በሆነው አንደኛ ተከሳሽ ክብሮም ገ/ማርያም የሞት ቅጣት፤
- ከሰተ ደበብና ፀጋይ የተባሉ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው የ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤
- ወንጀሉን ፈፅሞ የተሰወረው አራተኛ ተከሳሽ ዓንዶም ገ/ሊባኖስ በሌለበት የ25 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #rip #deathpenalty #court #tigray #mekelle

#የቀብር ስነስርአት በደቡብ አፍሪካ በ16ጥይት በአሰቃቂ የተገደለው ወንዴ ዜብራ (ወንድም አገኝ አየለ😭😭😭😭😭😭
#ለሚዲያ ዲያ ተቋማት በሙሉ
#የባልደረባችንና የሙያ አጋራችን የጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ አጎት(የአክስት ልጅ) የሆነዉና ወንድማችን አብሮ አደጋችን ታታሪዉ ዲያስፖራ #ወንድሜነህ አየለ በባለፈው ሳምንት መጋቢት 17/2018 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ ባልታወቁ ገዳዮች በ16 ጥይት ህይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ አልፏል
ታታሪዉ እና የጥረትተምሳሌቱ ኢትዮጵያዊ ወጣት አቶ ወንድሜነህ አየለ የቀብር ስነስርዓት ነገ ረቡዕ በአዲስአበባ ላፍቶ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
ስለሆነም ነገ ረቡዕ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በደብረ ትጉኃን ቅዱስ ሚካኤል ላፍቶ ስርዓተ ቀብሩ ስለሚፈፀም የሚዲያ ተቋማቶች በመገኘትና በመዘገብ ፍትህ ርትህ እንድናገኝ ድምፅ እንድትሆኑን እንጠይቃለን። ቤተሰብቹ😭😭😭😭😭😭😭😭😭
🎯መቼ
ረቡዕ መጋቢት 23/2018 ዓ.ም.ከቀኑ 9:00 ሰዓት
🎯የት
በላፍቶ ትጉኃን ቅዱስ ሚካኤል(ላፍቶ ሚካኤል በቤተክርስቲያን
*መኖሪያ ቤት ሳሪስ ቀይ አፈር ከአብዮት ፋና ት/ቤት ወረድ ብሎ
ወደላፍቶ መሸጋገሪያ ድልድይ አጠገብ