የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የለቅሶ ስነ-ስርዓት በጋሞ ዞን ተከናወነ
#fastmereja I በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የለቅሶ ስነ-ስርዓት፣ “በየትኛውም አካባቢ ሰው ይሙት ለቅሶ በአባት ሀገር ሳይለቀስ አይቀርም” የሚለውን የጋሞን ባህል ተከትሎ በአባቱ የትውልድ ስፍራ በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ቀበሌ ዛሬ በባህላዊ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቀብሩ መፈጸሙን ተከትሎ፣ በክፍለሀገር የሚገኙ የቤተሰብ አባላት "ዕርማችንን እናውጣ" በማለት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የአርቲስቱ ወንድም ወንደሰን እና እህቱ መሰረት በተገኙበት የለቅሶ ስነ-ስርዓቱ በድምቀት ተፈጽሟል።
የአርቲስት ነፃነት አባት ሻምበል ወርቅነህ ዕምሩ ከ60 ዓመታት በፊት በልጅነታቸው ለሽመና ስራ ከሀገር ቤት ወጥተው ወደ አዲስ አበባ ካቀኑ በኋላ በውትድርና፣ በፖሊስነት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ዘርፍ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። ሻምበል ወርቅነህ ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በአዲስ አበባ በቀጨኔ መድኃኔዓለም መፈጸሙ ይታወቃል። አባት ሻምበል ወርቅነህ ከሀገር ቤት ከወጡ ረጅም ዓመታት በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጋሞ ዞን ከሚገኙ ቤተ ዘመዶቻቸው ጋር ሳያስተዋውቁ የቆዩ ቢሆንም፣ አሁን የተከናወነው ባህላዊ የለቅሶ ስነ-ስርዓት የአርቲስቱ ወንድምና እህት በስፍራው በመገኘት ከቀሪው ቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙና የቤተሰብ ትስስሩ እንዲቀጥል ትልቅ አጋጣሚ ፈጥሯል ሲል ዱቡሻ ሚዲያ ዘግቧል።

17 days ago