3 days ago
የሴዶ እና የጆኒ ታላቅ የMMA ፍልሚያ ነሐሴ 21 ይካሄዳል!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የማርሻል አርትስ እና የቦክስ ስፖርት ታሪክ ያልተነካውን እምቅ አቅም ለዓለም ለማሳየትና ስፖርቱን ለወጣቶች የቋሚ ገቢ ምንጭ ለማድረግ ያለመው ''አድዋ ፋይት ናይት 2" (ETFC 002) ታላቅ የውድድር ምሽት ነሀሴ 21 እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት ተገለፀ።
ነሀሴ 21 በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ በስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው እና በጉጉት የሚጠበቀው ዋና ፍልሚያ (Main Event) በጆኒ (Johnny) እና በሴዶ (Sedo) መካከል የሚደረገው ድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ግጥሚያ እንደሆነ ተገልጿል።
ዛሬ በተሰጠው የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተወዳዳሪዎች በፊት ለፊት ፍጥጫ (Face-to face) የተገናኙ ሲሆን እርስ በእርስ ያቀረቧቸው የተፎካካሪነት እና የስነ-ልቦና የበላይነት የመውሰጃ አስተያየቶች በስፍራው የነበረውን ስሜት ያጋገሉት ሲሆን፣ ሁለቱም ስፖርተኞች ለነሐሴ 21ዱ ታላቅ ፍልሚያ ያላቸውን ከፍተኛ ዝግጁነትና የማሸነፍ በራስ መተማመን አሳይተዋል።
የውድድሩ አዘጋጅና የስዊት ቦክስ መስራች እና ስራ አ አቶ ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው፣ ETFC 002 የቀደመው ETFC 001 ከተካሄደበት ፍጥነትና ሁኔታ በተሻለ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
አዘጋጆቹ ለፕሮግራሙ መዘገየት ይቅርታ በመጠየቅ፣በተወዳዳሪዎቹ የስነ-ምግባር ጥንካሬ ላይ ሙሉ እምነት እንዳላቸውና ስፖርተኞቹ ሀገራቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ማስጠራት የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በምሽቱ 11 የተመረጡ ፍልሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ 4 የቦክስ (Boxing) 4 የኤምኤምኤ (MMA) 3 የሙአይ ታይ (Muay Thai) ፍልሚያዎች ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ልዩ ቦታ የተሰጠው ሲሆን፣ አትሌት አብስላት እና ዛራ በተወዳዳሪነት የሚሳተፉ ሲሆን በቀጣዩ «አድዋ ፋይት ናይት 003» ውድድር ላይ ደግሞ የሴት ተወዳዳሪዎች ቁጥር እንዲጨምርና ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ በቀደሙት ዝግጅቶች የነበረውን የመቀመጫ መደራረብ ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የተሰራ ሲሆን በዚህም ተመልካቾች ትኬት በሚቆርጡበት ወቅት ቀጥታ የመቀመጫ ቦታቸውን (Seat) መርጠው እንዲይዙ እንደሚደረግም ነዉ የተገለፀዉ።
አዘጋጆቹ እንዳብራሩት፣ በቅርቡ በሚካሄዱት ETFC-003 እና ETFC-004 የውድድር መድረኮች ላይ የሀገር ውስጥ ስፖርተኞች ከውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎች ጋር እንዲጋጠሙ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደ ኡሲክ (Usyk) ያሉ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ቦክስ ውድድሮችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማዘጋጀት ለተያዘው ታላቅ ዕቅድ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
ይህ ዝግጅት በአድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች አስተዋጽኦ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስፖርት አፍቃሪያን የነሐሴ 21ዱን የሴዶ እና ጆኒ ፍልሚያ በከፍተኛ ጉጉት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
📷 ከበደ መክብብ

2 months ago
አዲስ አበባ ፡ የኤምኤምኤ እና የቦክስ ስፖርት ውድድር ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የንክኪ ስፖርት ሁነቶች ሁሉ እጅግ ግዙፍ የሆነው የኢትዮ ፋይት ናይት የውድድር መድረክ ይፋ ሆኗል::
ዝግጅቱ የአዲስ አበባ ኪክ ቦክስ ፌዴሬሽን፣ የአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን ነሀሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (Aug 29/2026) በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል::
በዚህ ልዩ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ላይ በድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ሀገራችንን ወክለው ደግሞ ቢኒያም ሽብሬ፣ ክብሮም ንጉሴ እና አገረሰላም አርባን ጨምሮ በርካታ ስፖርተኞች ወደ መድረኩ ይወርዳሉ::
በጠቅላላው ከ6 እስከ 8 የሚደርሱ ብርቱ ፍልሚያዎች የሚስተናገዱ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ የተመረጡት በውድድር ታሪካቸው፣ በዓለም አቀፍ ልምዳቸው፣ በአካል ብቃት ጥንካሬያቸው እና ማራኪ ትዕይንት ማሳየት በሚችሉበት ብቃታቸው ላይ ተመስርቶ ነው::
አትሌቶቹ በፌዴሬሽኑ ህግ መሰረት አስፈላጊውን የህክምና ምርመራ፣ የክብደት ልኬትና የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ያጠናቀቁ ሲሆን ዝርዝር የክብደት መጠናቸውና ዜግነታቸው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል::
ይህንን ታሪካዊ ፍልሚያ ለመታደም ከ8,000 እስከ 10,000 የሚደርሱ የስፖርት አፍቃሪዎች በአዳራሹ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::
አዘጋጆቹ የአፍሪካንና የሀገራችንን ስፖርታዊ አቅም ለዓለም የሚያስተዋውቅ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ፍጹም ሙያዊ ብቃት የተላበሰ ዝግጅት ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል::
የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ የንክኪ ስፖርቶችን ከማሳደግ ባለፈ ለሀገር ውስጥ አትሌቶች ሙያዊ መድረክ መፍጠር፣ ወጣቶችን ማነሳሳት፣ ስፖርታዊ ቱሪዝምን በአዲስ አበባና በኢትዮጵያ ማስፋፋት እንዲሁም ሀገራችንን የዓለም አቀፍ ውድድሮች ማዕከል ማድረግ ነው::
ዝግጅቱ የሚስተናገድበት አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር (AICC) ዘመናዊ የዲጂታል ምስልና የድምፅ መገልገያ መሳሪያዎች የተሟሉለት በመሆኑ ለታዳሚው ምቹ መዝናኛን ለመፍጠር ተመራጭ አድርጎታል::
ገራሚ ኢቨንትስ የዝግጅቱን አጠቃላይ የፕሮዳክሽን ስራ በማስተናገድ ከባለቤቶቹ ጋር በጋራ የሚሰራ ሲሆን ለአትሌቶች ስልጠና፣ ለደህንነት፣ ለቦታ ዝግጅትና ለሎጂስቲክስ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈሷል::
ይህንን ውድድር በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ ተከታታይነት ባለው መልኩ ለማዘጋጀት የታቀደ በመሆኑ፣ የዝግጅቱን ጥራት ይበልጥ ለማሳደግ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት በስፖንሰርሺፕ፣ በሚዲያ ሽፋን፣ በዲጂታል ግብይትና በቪአይፒ ተሳትፎ ላይ አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል::
የመግቢያ ትኬት ዋጋንና የስርጭት ሽፋንን በተመለከተ ከሚዲያ አጋሮች ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን የቴሌቪዥንና የዲጂታል ቀጥታ ስርጭት መረጃዎች በቅርቡ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል::
#mma #boxing #ethiofightnight #sportstourism #aicc #ethiopianathletes #geramievents #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
በ3.5 ሚሊዮን ብር ሸልማት የታጀበው ''የመድን Grand Fight Night" ሊካሄድ ነዉ!
#fastmereja : በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት የውጊያ ስፖርቶችን በአንድ መድረክ ላይ የሚያገናኘው "የመድን Grand Fight Night I" የተሰኘው ዘመናዊ የውድድር መድረክ የፋታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም እንደሚካሄድ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ይህ ታሪካዊ ዝግጅት የሚክስድ ማርሻል አርትስ (MMA)፣ ሟይታይ (Muay Thai) እና ቦክሲንግን (Boxing) በአንድ ላይበማጣመር በሀገሪቱ የስፖርት ኢንዱስትሪ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተስፋ ተጥሎበታል።
ዝግጅቱን ስዌት ቦክስ ጂም፣ ሸጋ ኤቨንትስ እና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የዝግጅቱ ዋነኛ ስፖንሰር (Title Sponsor) በመሆን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የዝግጅቱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያ በማራቶን ያላትን ዝና በውጊያ ስፖርቶችም እንድታገኝ ማስቻል ሲሆን ዝግጅቱ በዘርፉ ያሉ ወጣቶች ያላቸውን ያልተነካ እምቅ አቅም ለዓለም በማሳየት፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ የውድድር መዳረሻ የማድረግ ራዕይ እንዳለዉም ነዉ የተገለፀዉ።
ከዚህም ባሻገር ውድድሩ የጡንቻ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ የስፖርተኞችን ስነ-ምግባር፣ ታታሪነትና ትዕግስት የሚፈተንበት መድረክ እንደሚሆን ታውቋል። ስፖርቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድልና መደበኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን ለማስቻልም ሰፊ ጥረት ተደርጓል።
ለዚህ ውድድር በአሸናፊነት ለሚወጡ ስፖርተኞች በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ስፖርተኞች በዘርፉ ተስፋ እንዲኖራቸውና ራሳቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ማበረታቻ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡
ውድድሩ በዕለቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን፣ ታዋቂ ድምፃውያን የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን በማቅረብ ዝግጅቱን እንደሚያደምቁትም ተገልጿል።
ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የውጊያ ስፖርት አፍቃሪዎችና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች አዲስ የትውውቅና የውድድር መድረክ በመሆን በታሪክ ማህደር ሰፍሮ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።
📷 Zemenu Atalay

Sponsored by
Surafel
7 months ago
8 months ago
በስምንት ጎል ትሪለር የታጀበው ጨዋታ
4ለ4 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
#ethiopia | የዩናይትድ ሄድ መለስ ከኦልድትራፎርድ ቀጥሏል ። ምስጋና ለግብ ጠባቂው ሴን ሌሜንስ ይግባና ማንቸስተር ዩናይትድ ከሽንፈት እንደ ምንም ተረፈ ። መከላከልን የረሳው ነፃ አሳላፊ መንገድ የሆነው የዩናይትድ የተከላካይ መስመር ላይ የበርንማውዝ ኮኮቦች እንደ ልብ ተመላለሱ።
በስምንት ጎል ትሪለር የታጀበው ለገለልተኛ ተመልካቾች ብቻ አዝናኝ የነበረው ጨዋታም በ4 አቻ ተጠናቀቀ ።
መላጣው ዳኛ ሳይመን ኹፐር የመሩት ጨዋታም ከ99 ደቂቃ በላይ ዘልቆ ከ40 በላይ ሙከራዎችን አሳየ ። ማንቸስተር ዩናይትድ ከዕሁድ እስከ ዕሁድ ተጫወተ ከሰኞ እስከ ሰኞ ወይ ዐርብ እና ቅዳሜ ቢጫወት በወትሮ የተናፈቀ የታላቅነት ቅርፁ ደረጃ ውሎ ለማደር እንደ ተሳነው ዛሬም አለ ። እየመራ የሚለቀውን ጨዋታ ከሽንፈት ድኖም አጠናቀቀ ።
አንድ ሳምንት ሙሉ እያረፈ የሚጫወተው ዩናይትድ ካለፉት ሶስት በሜዳው ካደረጋቸው የሊጉ ጨዋታዎቹ ማግኘት ከነበረበት ዘጠኝ ነጥብ ሰባት ያህሉንም ጣለ ። ዩናይትድ ካለፉት ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎቹም ማሸነፍ የቻለውም ሁለቱን ብቻ ነው ።
ዩናይትድ ወሳኝ እንደ አማድ ምቤሞ ያለ ተጨዋቾቹን ወደ Afcon ልኮ ከሚያደርጋቸው የBoxing Day እና አዲስ ዓመት ዋዜማ ቀጣይ ተከታታይ የቪላ እና ኒውካስል የሊጉ መከራው በፊት ሌላ ሁለት ነጥብም ጣለ ።
የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በትኩረት የመከላከል ቁምነገር ዋጋ ትርጉሙን የረሳ የሚመስለው የ3-4 -3 የጨዋታ ቅርፅ ዛሬም እንደ ኩናህ ቡሩኖ አማድ ምቤሞ ማውንት የመሳሰሉ ከፍተኛ የማጥቃት አቅምን የተላበሱ የዩናይትድ ተፈጥሮአዊ ኮኮቦችን ግራ ቀኝ ሲያባክን አመሸ ።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ብቸኛው የመሃል ሜዳው ሽፋን ሰጪው ካሲሜሮ ቢጫ ካርድ ካሰጠው እንቅስቃሴው በኋላ በቀጣይ የቪላ ጨዋታ በ5 ተከታታይ ቢጫ ምክንያት እንደማይኖር እያወቀ እንደ ልብ በሚያፈስ የተከላካይ መስመሩ ሽፋን ላይ የተሻለ ከለላ በትግል ይሰጥ የነበረው የብራዚላዊ ታጋይ ኮኮብ ውጤታማ ግልጋሎት ላይ ኮቢ ማይኖን ጨምሮ እንደማጫወት ለምን ካሲሚሮን በማይኖ ቀይሮ እንዳስወጣው ከእራሱ ከአሰልጣኙ ውጭ የሚያውቅ እንደጠፋ ጨዋታው ተጠናቀቀ ።
በስምንት ጎል ትሪለር የታጀበው ጨዋታም 4ለ4 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ።
ሴሜዶ የክላይቨርት ልጅና ጓደኞቹ በነፃነት ከገናናው ሜዳ ኦልድትራፎርድ በበርንማውዝ መለያ ሲመላለሱ አመሹ ። የዩናይትድ የማጥቃት መስመር ጥራት ያላቸው ኮኮቦች በጨዋታው የነበረ ታታሪነት ዕድሎችን የመፍጠር ውጤታማነትና ልፋትም መና ቀረ ።
ማንቸስተርም ምስጋና ለግብ ጠባቂው ሴን ሌሜንስ ከሽንፈትም ለጥቂት ተረፈ ።
በእግር ኳስ ጨዋታ ያውም ማሸነፍን ዘላዓለማዊ ውርሱ አድርጎ በኖረው የዩናይትድ ታሪካዊ መለያ አሸናፊ ቡድኖችን ዳግም ለመገንባት ጥብቅ የመከላከል ቅርፅ መያዝ ከቅያሪ ውሳኔዎች አንስቶ የጨዋታ Game managment ጥያቄዎች ዛሬም የአሰልጣኙ ክፍተት ሆነው ቀጥለዋል ።
ጨዋታዎችን የማሸነፍ ታላቁ አላማ ትርጉምን የዘነጋ የሚመስለው የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የ3-4 -3 የጨዋታ ሲስተም ዛሬም ዩናይትድ ቀድሞ ጎል አገባም መልሶ ተቆጠረበትም ዕንደገና መራ ወይ ተመራ በየትኛውም የጨዋታው ደቂቃ ለደቂቃዎች ፀንቶ የማይቆይ ልፍስፍስ እንደሆነ ወትሮ በካምቦሎጆው መድረክ የፈፀማቸው ህልሞቹ ሁሉ ቅዠት እንደሆኑበትም ከገናናው ክለብ ሜዳ ኦልድትራፎርድ መሻሻል ዕንኳ ብርቅ ሆኖ ቀጠለ ።
የሰኞ ምሽት ባልደረባው መከራም በውድድር ዓመቱ በማይጨበጥ የውጤት ጉጉት ርዶ የታላቁን ክለብ ዕውነተኛ መልክ ረስቶ ሲራኮት ውሎ ማደር ከጀመረ ከከራረመው ዓለም አቀፍ ደጋፊው ጋር ዩናይትድ እንደ ቆንጆ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ፊልም የሄድ መለስ ጉዞው የሚቀጥል ይሆናል ።
tribune sport

Comments