Logo
Getu Temesgen
#የልህቀትና #የትሕትና ##ተምሳሌት# #ዶክተር #ዋቆ #ገዳ !
#ethiopia | በዓል ማለት ለብዙዎቻችን ከቤተሰብ ጋር መሰብሰብ ፣ በሞቀው ማዕድ ዙሪያ መሳቅና መጫወት ማለት ነው ።

እንዲያውም አንድ የቢሮ ሰራተኛ እንኳን ቀኑን ከቤቱ ውጪ ለማሳለፍ በማይፈቅድበት ፣ ትልቁ የፋሲካ ዕለት ነገር ግን ለየት ያሉ መሪዎች "ቤተሰብ" የሚለውን ትርጓሜ ከገዛ ቤታቸው አጥር አሻግረው ያዩታል ።

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አንድ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ተፅፏል ።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዴንት ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ የፋሲካን ዕለት ከገዛ ቤተሰባቸው ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ፣ "ቤተሰቦቼ ናቸው" የሚሏቸውን ተማሪዎቻቸውን በማሰብ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው በዓሉን አብረው አሳልፈዋል ።

ይህ ተግባር እንዲሁ በቀላሉ የመገኘት ጉዳይ ፤ ሳይሆን የእውነተኛ የመሪነት መገለጫ ፣ አመራር ከቢሮ ወንበር በላይ መሆኑን ያሳየ ፤ የአባትነት ፍቅር ፣ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ባሉበት ወቅት ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ያደረገ ፤ የትሕትና ልክ ፣ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ሆኖ ራስን ዝቅ አድርጎ ከተማሪዎች ጋር መሳተፍ ለሌሎች አመራሮችም ትልቅ ትምህርት ነው ።

ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ ተማሪዎችን እንደ ወንድም ፣ እንደ እህትና እንደ ልጅ ተመልክቶ በበዓል ዕለት አብሮ በመሆን የመጀመሪያው ከፍተኛ አመራርና ፕሬዚዴንት በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ፅፈዋል ።

ለዚህ ድንቅ መሪና ፕሬዚዴንት ፣ ለዚህ ትሁት አገልጋይና ለዚህ የለውጥ ሰው ያለንን ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እንገልጻለን ‼️

ኢትዮጵያ እንደ ዶክተር ዋቆ ያሉ ፣ የሕዝባቸውን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ መሪዎች ያስፈልጓታል ።

ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ! 👏🙌

ጌታቸው ባይባ ሚዛን አማን !
#mizantepiuniversity #leadership #inspiration #drwakogeda #ethiopia #serviceaboveself

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.