Logo
Getu Temesgen
የሟች ህፃን ናኦድ አጎት የሞት ቅጣት ተላልፈበት
#ethiopia | ላልተገባ ጥቅም ሲባል ህፃን ናኦድ ተኽላይን በአስቃቂ ጭካኔ የገደሉ አራት ወንጀለኞች ከሞት እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።

ከአራቱ ወንጀለኞች አንዱ በሌለበት የ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲከታተለው የቆየው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ አግኝቷል።

ሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ ሀምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ዙሪያ ነበር አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት።

ግድያው የተፈጸመው ታግቶ ለማስለቀቂያ 2 ሚሊዮን ብር ከተጠየቀበት በኋላ ነው።

የሟች እናት ወ/ሮ ዮርዳኖስ ጋይም " በልጄ ግድያ ቁጥር አንድ ተጠርጣሪ የሆነው የቅርብ ቤተሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ቢሆንም እስከ አሁን የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የለም " በማለት የፍትህ መዘግየቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው መግለፃቸውን አስነብበን ነበር።

" የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል " ሲሉ ነበር የሟች እናት የገለጹት።

ጭካኔ የተሞላበት የግድያ አፈፃፀሙ ከአንድ ዓመት በላይ ሲከታተል የቆየው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በሦስት ወንጀለኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚሁ መሰረት ፦

- የሟች ህፃን ናኦድ እናት #ወንድም በሆነው አንደኛ ተከሳሽ ክብሮም ገ/ማርያም የሞት ቅጣት፤

- ከሰተ ደበብና ፀጋይ የተባሉ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው የ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤

- ወንጀሉን ፈፅሞ የተሰወረው አራተኛ ተከሳሽ ዓንዶም ገ/ሊባኖስ በሌለበት የ25 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተዘግቧል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #rip #deathpenalty #court #tigray #mekelle

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.