20 days ago
ኢትዮጵያ፦ የዓለም ሰላም ተሟጋች እና የፍትህ ፋና ወጊ
******************
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት ስናስብ ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላምና ለፍትህ የከፈለችውን መተኪያ የሌለው መስዋዕትነት ማስታወስ ግድ ይላል።
ኢትዮጵያ ዓለም በጋራ ጉዳዮች ላይ ተሰባስቦ እንዲመክር ካላት ጽኑ አቋም የተነሳ እ.አ.አ በ1923 የመንግሥታቱ ማኅበር አባል ብትሆንም፣ ማኅበሩ ግን ከፋሺስት የመርዝ ጋዝ ጥቃት ሊጠብቃት አልቻለም።
ሀገራችን እ.አ.አ በ1936 በመንግሥታቱ ማኅበር ፊት ቀርባ "ዛሬ በእኛ ላይ የደረሰው ነገ በእናንተ ላይ ይደርሳል" በማለት ያሰማችው ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ በዓለም የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የፍትህ ተሟጋችነታችን ቀዳሚ ማሳያ ነው።
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃም ኢትዮጵያ ከ51 የተመድ መሥራች ሀገራት አንዷ በመሆን የሀገራትን ሉዓላዊ እኩልነት የሚያረጋግጡ ድንጋጌዎች በቻርተሩ እንዲካተቱ ታሪካዊ ሚና ተጫውታለች።
ከቃላት ባለፈም በአፍሪካና በተለያዩ ሀገራት ለሚገኙ የነጻነት ታጋዮች መጠጊያና ደጋፊ በመሆን ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆና ቆይታለች።
በሰላም ጥበቃ ረገድም ከኮሪያ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ወታደራዊና የፖሊስ አባላትን በማሰማራት የዓለምን ሰላም በመስዋዕትነት ስታስጠብቅ ኖራለች።
ዛሬም ኢትዮጵያ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ አፍሪካ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራት ይገባል የሚለውን ጥያቄ በግንባር ቀደምነት በማንሳት ላይ ትገኛለች።
ይህ የዘመናት የፍትህ ተሟጋችነቷ ጉዞ የሰው ልጆች ሁሉ ድምጽ በእኩልነት እንዲሰማ ካላት ጽኑ ራዕይ የሚመነጭ ነው።
በለሚ ታደሰ
ዝርዝር ትንታኔውን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል 🔗
#ethiopian #diplomacy #un80 #globaljustice #peacekeeping #unitedafrica

22 days ago
የጥቁር ሕዝቦች ድምፅ በተመድ አዳራሽ - ኢትዮጵያ ለነፃነት የከፈለችው ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላቸው ትሥሥር እንደ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብቻ የሚታይ ሳይሆን፣ በታሪክ አውድማ ላይ በፅናት እና በሉዓላዊነት የተገመደ የክብር ሰንሰለት ነው።
ከሰማንያ ዓመታት በፊት ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍርስራሽ ላይ ቆማ አዲስ ተስፋን ስትፈልግ፣ ኢትዮጵያ ከ51ዱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ሆና የቻርተሩን ሰነድ ስትፈርም ተራ ተሳታፊ አልነበረችም።
ይልቁንም፣ የዲፕሎማቶቻችን ድምፅ የኃያላንን የበላይነት ለመሞገት እና የደካማ ሀገራትን መብት ለማስጠበቅ የሚተጋ የፍትሕ ጩኸት ነበር።
በወቅቱ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር ለነበሩት ወንድም የአፍሪካ እና የእስያ ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ተሟጋች ሆና መቅረቧ፣ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” የሚለውን ብሂል ወደ ጎን በመተው ለሰው ልጅ ሁሉ ነፃነት መቆሟን ያሳየ ታላቅ የሞራል ልዕልና ነበር።
ይህ የታሪክ አሻራ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈ ይገኛል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ የሰላም ዘቦችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማሠማራት፣ በዓለም ሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ ያላትን የማይናወጥ ሚና በተግባር አሳይታለች።
የሀገራችን ሠራዊት በሄደበት ሥፍራ ሁሉ የሚታወቅበት የጥንካሬ፣ የዲሲፕሊን እና የሕዝባዊነት ገጽታ፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ከሚያዋጡ ሀገራት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርጓታል። ይህ መሥዋዕትነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻችን እና ለመላው ዓለም ሰላም መቆማችንን የሚያረጋግጥ የቆራጥነት ማሳያ ነው።
በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚከናወኑት እነዚህ ተልዕኮዎች፣ የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገውታል።
ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸው እና የድርጅቱን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እዚህ በታሪካዊቷ ከተማችን እንዲከበር መወሰኑ፣ እንዲሁ የተገኘ ድንገተኛ ክስተት አይደለም። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ያበረከተችው ታሪካዊ አስተዋፅኦ እና ለዓለም ሰላም የከፈለችው መሥዋዕትነት የተሰጠው ታላቅ እውቅና ነው።
“መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል” እንዲሉ፣ የሀገራችን የዲፕሎማሲ ጥንካሬ እና የሠራዊታችን አኩሪ ገጽታ ለስምንት ዐሥርተ ዓመታት ተጠብቆ ቆይቶ ዛሬም በዓለም መድረክ ድምፃችን ጎልቶ እንዲሰማ አድርጎታል።
ይህም የአፍሪካን ዳግም መነሣት የሚያበስር ምልክት እና ለጋራ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን የጥንካሬ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ እና ተመድ በዘላቂ ልማት ግቦች ዙሪያ ያላቸው ትብብርም ሌላው የትሥሥሩ ገጽታ ነው። ድህነትን ለማጥፋት፣ ፕላኔቷን ለመጠበቅ እና ለሁሉም ሰው ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት፣ ሀገራችን ከድርጅቱ ጋር ያላትን ስትራቴጂክ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል።
ወደፊትም ቢሆን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ደጀን እና የልማት ተምሳሌት ሆና በመቀጠል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፍትሐዊ ሥርዓት እንዲሰፍን እና የጋራ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የነበራትን የሞራል መሪነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጥርጥር የለውም።
የታሪካችን ጥንካሬ እና የሠራዊታችን ፅናት ዛሬም ለዓለም ሰላም ዋስትና፣ ለትውልድም ኩራት ሆኖ ይቀጥላል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #diplomacy #un #un80

u1260u1265u122du1200u1295 u134du1325u1290u1275 u12a5u12e8u1270u1240u12e8u1228u127d u12e8u121du1275u1308u1298u12cd u12e8u12a0u134du122au12ab u1218u12f2u1293
#un80 #addisababa #ethiopia #musicshow #circusshow #culture #unitednations #ethiopianmusic #entertainment ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
በብርሀን ፍጥነት እየተቀየረች የምትገኘው የአፍሪካ መዲና
#un80 #addisababa #ethiopia #musicshow #circusshow #culture #unitednations #ethiopianmusic #entertainment
22 days ago
"በኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ ጽ/ቤት ዋና ግብ የኢትዮጵያ መንግሥትን ስትራቴጂ መደገፍ ነው" - የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
**************************
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ ጽሕፈት ቤት ዋና ግብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማገልገል እና የኢትዮጵያ መንግሥትን ስትራቴጂ መደገፍ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዋና ጸሐፊው ኢትዮጵያ የተመድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የቴምብር ስብስብ ይፋ ባደረገችበት መርሐ-ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ተገቢ የሆነ ውክልና እንዲኖራቸው በሚያደርጉት ጥረት ከጎናቸው እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ያለንበትን ዓለም እንዲያንጸባርቅ እና በአፍሪካ ላይ የደረሰውን ታሪካዊ በደል ለማረም በምክር ቤቱ የአፍሪካ ቋሚ ወንበር እንዲኖር ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በድጋሚ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ አፍሪካን በመወከል ረገድ ያላትን ታሪካዊ ሚና የገለጹት ዋና ጸሐፊው፣ ለተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ ቋሚ የፀጥታው ምክር ቤት ወንበር መኖር ተገቢ እና ትክክለኛ ጥያቄ እያቀረበች መሆኑን አስረድተዋል።
አዳጊ ሀገራት በተለይም የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ውሳኔ ሰጪ ሚና እንዲኖራቸው የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንሥተዋል።
የአፍሪካ ሀገራት እያሳዩ ያሉት ከፍተኛ የመቋቋም አቅም እና የኢኮኖሚ ስኬት፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ተገቢውን ውክልና ለማግኘት ብቁ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ዛሬ ያስተዋወቀችው ልዩ ቴምብር ከ1945 ዓ.ም ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከናወኑትን ታላላቅ ሥራዎች ማለትም ግጭቶችን ከመከላከል እስከ ረሃብ መቅረፍ፣ የቅኝ ግዛት መጨረሻን ከማረጋገጥ እስከ ሰብአዊ መብቶችን ማስከበር ያሉትን እንድናስታውስ እንደሚጋብዝ ተናግረዋል።
በዛሬው ፈታኝ እና ተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም፣ የፍትህ እና የብልጽግና ተስፋ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ አሁንም አስፈላጊ እና አጣዳፊ መሆኑን ያረጋገጡት ዋና ጸሐፊው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዞ ውስጥ ግንባር ቀደም ሀገር እንደምትሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።
በሔዋን ጌታቸው
#ebc #ethiopia #un #un80

"ተመድ የዛሬውን ነባራዊ ሁኔታ በማንጸባረቅ አፍሪካን በአግባቡ ሊወክል ይገባል"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ በተካሄደ ደማቅ መርሐ ግብር ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ታሪካዊ ንግግራቸው ዓለም አቀፉ ተቋም የዘመኑን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ራሱን ሊያሻሽል እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሀገራት መካከል ያለው የጋራ መተማመን ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁንም ገልጸዋል።
በዓለማችን የሚከሰቱ ግጭቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ውስብስብ እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቃል በሚገባውና በተጨባጭ በመሬት ላይ ባለው ሁኔታ መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩን አስገንዝበዋል።
በመሆኑም ተመድ ይህንን ክፍተት በመድፈን ይበልጥ አካታች፣ ፍትሃዊ እና የዛሬውን ዓለም እውነተኛ ገጽታ የሚያንፀባርቅ ሆኖ መሻሻል እንዳለበት አብራርተዋል።
በተለይም አፍሪካ በራሷ እጣ ፈንታ ላይ በሚወሰኑ ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ላይ ጠንካራና ተሰሚነት ያለው ድምፅ ሊኖራት እንደሚገባ በጽኑ አሳስበዋል።
የአህጉሪቱ ውክልና መረጋገጥ የተቋሙን ውጤታማነትና ተዓማኒነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክረውም ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ ከተመልካችነት ወጥታ የላቀ ኃላፊነት ለመውሰድ እንዲሁም ጠንካራና ተዓማኒነት ያለው ሥርዓት ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አረጋግጠዋል።
ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን የአባል ሀገራት የጋራ ጥረትና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በለሚ ታደሰ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #ebc #un80 #pmabiyahmed #africarepresentation #unitednations #multilateralism

Sponsored by
Surafel
23 days ago
የኢትዮጵያ እና የተመድ የ80 ዓመታት ታሪካዊ ቁርኝት
****************
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስምንት ዐሥርተ ዓመታት ጉዞ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ በጋራ ደኅንነት፣ በሰላም እና በልማት ፅኑ አቋም ይዛ በዓለም አቀፍ መድረክ ደማቅ አሻራዋን አኑራለች።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሻገረው የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዞ ተመድ የተመሠረተበትን በዓል ሲያከብር፣ የድርጅቱ ቀዳሚ መሥራች እና ንቁ ተሳታፊ የሆነችው ሀገራችን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ በሰላም ማስከበር እና በልማት ትብብር ረገድ ያሳለፈቻቸው ዓመታት በክብር ይወሳሉ።
እ.አ.አ በ1945 ተመድ ሲመሠረት፣ ኢትዮጵያ ቻርተሩን ከፈረሙ 51 ቀዳሚ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች።
ይህም በወቅቱ በቀኝ ግዛት ሥር ለነበሩት በርካታ የአፍሪካ እና የእስያ ሀገራት ትልቅ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ ታሪካዊ ክስተት ነበር።
ታዲያ ይህ ግንኙነት ለሌሎች ሀገራት ከተስፋነት በዘለለ፣ ላለፉት 80 ዓመታት ጠንካራ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ኖሮት ቀጥሏል።
በተባበሩት መንግሥታት የታሪክ ድርሳን ውስጥ የኢትዮጵያ ስም ጎልቶ ከሚነሳባቸው ተግባራት ቀዳሚው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ነው።
ከ1950ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ጀምሮ በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በዳርፉር እንዲሁም በቅርብ ጊዜያት በአብዬ እና በደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ኢትዮጵያ ለሌሎች ሀገራት ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚናዋን ተወጥታለች።
ኢትዮጵያ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በርካታ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በመላክ ከግንባር ቀደምት ሀገራት ተርታ የምትሰለፍ ሆና ቀጥላለች፡፡ ይህም ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት ያላትን ፅኑ አቋም በተግባር ያሳየችበት ነው።
አዲስ አበባ የድርጅቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ECA) እና የሌሎች በርካታ የተመድ ኤጀንሲዎች መቀመጫ መሆኗ የኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት ግንኙነት ሌላው ትልቅ መገለጫ ነው።
እ.አ.አ በ1958 የተመሰረተው ይህ ኮሚሽን አዲስ አበባን ከኒውዮርክ እና ከጄኔቫ በመቀጠል የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።
ይህ ትብብር ኢትዮጵያ በአህጉራዊ የልማት አጀንዳዎች እና በኢኮኖሚ ትሥሥር ዙሪያ ያላትን ሚና በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል።
ተመድ 80ኛ ዓመቱን ሲያከብር ኢትዮጵያ የድርጅቱ ቻርተር እንዲከበር፣ የአፍሪካ ድምፅ በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ጉልህ ስፍራ እንዲኖረው እና በዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ዙሪያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ያላትን አጋርነት እያጠናከረች ትገኛለች።
የኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የ80 ዓመታት ጉዞ፣ ለቀጣዩ ትውልድም በጠንካራ መሠረት ላይ ተገንብቶ ዘላቂ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንደሚቀጥል ይታመናል።
በሀና ምንዳሁን
#ethiopia #ebc #un80 #unitednations #peacekeeping #globaldiplomacy #uneca