16 hours ago
#tigray
#mekelle
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል መቐለን ከተቆጣጠሩ በኋላ ስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ቤተሰቦችም እየተገናኙ ነው።
የባንክ አገልግሎትም ተጀምሯል።
በመቐለ ከተማ የፀጥታ ሁኔታው እና የሚፈጸመው ዝርፊያ ካለፉት ቀናት መሻሻል ቢያሳይም ሙሉ በሙሉ ሊቆም እንዳልቻለ ሁለት ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
" ትላንት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከታክሲ እያወረዱ ሞባይልና ገንዘብ ሲዘርፉ ተመልክተናል " ሲሉ አንድ እማኝ ተናግረዋል።
" በቢላዋ እና ትጥቅ በማስፈራራት የግለሰቦች ቤት በመስበር የመሰሉ ዘረፋዎችም በስፋት አሉ " ሲል ሌላኛው ነዋሪ ገልጿል።
በሌላ በኩል፥ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደ መደበኛነት እየመጣ መሆኑን አመልክተዋል። በርካታ ወጣቶች ፣ መኪኖች እና ባጃጆች በከተማዋ በብዛት ወጥተው መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
ይህ በእንዳህ እያለ ከሳምንት በላይ የተቋረጡት በክልሉ የሚገኙ የመንግስትና የግል ሚድያዎች መልሶ ለማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ የውስጥ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥቆማ ሰጥተዋል።
ለ104.4 መቐለ FM አዲስ አስተባባሪ እንደተመደበ ለማውቅ ችለናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
ፎቶ፦ ማኅበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia በትግራይ መቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መመለስን ተከትሎ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። ነዋሪዎቹ " ጭልምልም ብሎብን ነበር። አሁን ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ስለተገናኘን ደስ ብሎናል " ብለዋል። " አሁን በከተማዋ የተሻለ መረጋጋት አለ ፤ አልፎ አልፎ ከሩቅ የተኩስ ድምጽ ይሰማል ተኩሱ የትግራይ ሰላም ኃይሎች ከበረሃ ወደ ከተማ ሲገቡ ስለሚተኩሱ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ትናንት…

2 days ago
#mekelle
ለ10 ቀናት ያህል ተቋርጦ የነበረው የመቐለ የሞባይል እና ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ መልሶ መጀመሩን ተከትሎ ከሳምንት በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦች እየተጠያየቁ ነው።
በተያያዘ፣ የመቐለ 104.4 ኤፍ ኤም ሬድዮ የትግራይ ሰላም ኃይል ተቆጣጥሮ ለከተማው ህዝብ የሚያረጋጉ መልእክቶች እያስተላለፈበት ይገኛል።
ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም መቐለን የተቆጣጠሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል በርካታ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

" እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው " - አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
👉 " ... ሻዕቢያ ሰሞኑን በጦርነት በአካል ተሳትፏል ፤ መልሱ እጥፍ ሆኖ እንደሚመለስ ምንም ጥያቄ የለውም ! "
ዳግም ጦርነት ካገረሸ በኋላ የፌዴራል መንግሥት ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየቱን ሰጠ።
የፌዴራል መንግሥትን ወክለው አስተያየት የሰጡት አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ናቸው።
አብርሃም (ዶ/ር) ፤ ከሰሞኑን በነበረው ጦርነት ከህወሓት ኃይሎች ጋር አብሮ የሻዕቢያ (ኤርትራ) ሰራዊት ተሳትፏል ሲሉ ተናግረዋል።
" የሻዕቢያ መንግሥት የሻዕቢያ ሰራዊት በዚህ ጦርነት በአካል ተሳትፏል። ከነትጥቁ፣ ከነ መሳሪያው ፣ ግምባር ወስዶ ተሳፍቷል። የሞተም፣ መሳሪያዎቹ የተማረኩ መአት ናቸው ያሉት " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይሄ መልሱ እጥፍ ሆኖ እንደሚመለስ ምንም ጥያቄ የለውም " ያሉት አብርሃም (ዶ/ር) " በሰው ሀገር ገብቶ ከሽፍታና ባንዳ ጋር መንግሥትን ለመውጋት ጠምሮ (ጥምረት ፈጥሮ) መምጣት ምን ሊያስከትል እንደሚችል በምላሹ ያገኘዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጠላት ዋና ፍላጎቱ የኢትዮጵያ ትርምስ እንደሆነ ፤ ሻዕቢያም ጎረቤት ሆኖ ሁሌም ኢትዮጵያን በስጋት የሚያይ አካል እንደሆነ አመልክተዋል።
የነዚህ አካላት ፍላጎት " ኢትዮጵያ በትርምስ እንድትኖር ፤ አቅሟ እንዳይዳብር ፤ ሰላሟ የፀና ጠንካራ ሀገር እንዳትሆን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ጠላቶች እራሳቸው ደፍረው ማድረግ ስለማይችሉ ሁሌም ተላላኪ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
በሰሞነኛው ግጭትም " ሰው ሞቶብናል ከወጣቶች ሞተዋል በሁሉም ሳይድ ይሄ ኪሳራ ነው። ለአንድ አገር ብዙ ሃብት ለልማት የምናውለው በዚህ እየፈሰሰ ነው ያለው ይሄም ኪሳራ ነው። ከዚህ በላይ ድል ለነሱ የለም " ብለዋል።
ድል የሚሉት ይሄን ማተራመሱን፣ አቅም ማሳጣቱን፣ ማዳከሙን ነው ሲሉ አክለዋል።
ሻዕቢያ " ሰሜን በተለይም ትግራይን የመጨረሻ ደካማ ካልሆነች በስተቀር ስጋት ነች ብሎ " እንደሚያስብ ጠቁመዋል።
አብርሃም (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምንም አይነት ጥረት ቢያደርጉም ኢትዮጵያ ልትፈርስ እንደማትችል ገልጸዋል። ህዝቡ ጀግንነቱ እንዳልተቀየረና ጀግንነቱ እየባሰበት እንደሆነ ተናግረዋል።
ሰሞነኛው ጦርነት የኢትዮጵያን መንግሥት ለማፍረስ የተቀሰቀሰ መሆኑን የገለጹት አብርሃም (ዶ/ር) ፤ " እራሳቸው ጦርነት ጀምረውብን መከላከል አድርገን መልሰን እነሱ በሄዱበት እና በገቡበት ቦታ እያጸዳን ነው ምንገኘው " ሲሉ ተናግረዋል።
" አሁን ላይ የመጀመሪያ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይን ማጽዳት ነው " ብለው " ከዛ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የመንግስትን አቅጣጫ ምንከታተለው ይሆናል " ብለዋል።
" እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው። ሃገር እየደፈረ ዝም ብሎ የሚመለከተው አካል የለም። ኢትዮጵያዊ እንደዚህ አይነት ባህሪ የለውም መንግሥታችንም ይህንን አይቀበልም " ሲሉ አስገንዝበዋል።
እጁን እያስገባ ያለው አካል እጁን የማይሰበስብ ከሆነ ምላሹ ከባድ እንደሚሆን ፤ ይህም ምላሽ የማይቀርለት እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።
አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ሁኔታን በተመለከተ ሀገር መከላከያው በአብዛኛው ትግራይን እያፀዳ መሆኑን ገልጸው በፍጥነት ሰላምና መረጋጋት የማስፈኑን ስራ እንዲሁም ህዝቡ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የቀበሌ፣ ወረዳ ፣ ዞን አደረጃጀት የመፍጠር ሁኔታ በፌዴራል መንግሥት መጀመሩን ገልጸዋል።
እንዲሁም አሁን ያለው ሁኔታ ቶሎ ተረጋግቶ ፤ የሽግግር ሂደት ኖሮት በፍጥነት ደግሞ ክልላዊ ምርጫ የሚደረግበት ይህም በወራት ውስጥ እንዲሆን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #mekelle ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ መሃል መቐለ ሮማናት አደባባይ መግባታቸው ተረጋግጧል። መላው የከተማዋን ክፍል ሙሉ በሙሉ በቀጥጥራቸው ስር ማድረጋቸውም ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ " የትግራይ ሰላም ለውጥ ምክር ቤት " አካል የሆነው የቃንጪ ሐቂ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጉድፈይ፣ " የመከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ጥምረት ብዙ ቦታዎችን…

3 days ago
#mekelle
ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ መሃል መቐለ ሮማናት አደባባይ መግባታቸው ተረጋግጧል።
መላው የከተማዋን ክፍል ሙሉ በሙሉ በቀጥጥራቸው ስር ማድረጋቸውም ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ " የትግራይ ሰላም ለውጥ ምክር ቤት " አካል የሆነው የቃንጪ ሐቂ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጉድፈይ፣ " የመከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ጥምረት ብዙ ቦታዎችን ይዟል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሀገር መከላከያ ከራያ አካባቢዎች ጀምሮ እስከ መቐለ ፣ ከሰቆጣ ጀምሮ እስከ ኮረምና አዲሸሁ፣ በአፋር ክልል በኩል አብዓላ ወረዳ እስከ መቐለ ያሉትን ቦታዎች እንደያዘ ገልጸዋል።
" በራያ አዘቦ እና ወጀራ በሚባለው አካባቢ ተቆርጠው የቀሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ነበሩ እነርሱም ዛሬ ሌሊት ተሰባስበው እንደወጡ ነው ያለን መረጃ የሚያመላክተው " ሲሉ አክለዋል።
የሕወሓት አመራሮች መቐለን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በከተማው ከነትጥቃቸው የተበተኑ ታጣቂዎች ዝርፊያ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ገልጸዋል።
ጦርነት በሚሆንበት ወቅት እየተከታተሉ የህዝብ ንብረት የሚዘርፉ እንዳሉ ገልጸው፣ " መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው በቶሎ መግባት ነበረበት። አሁን ገብቷል ሁኔታውን ያረጋጋል ብለን እናስባለን። 'ዘረፋ አለ' መባሉ ትክክል ነው " በማለት ገልጸዋል።
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና የአሁኑ የስምረት ፓርቲ አመራር ፕ/ር ክንደያ ገብረሕይወት " መቐለ ከኋላቀር ቡድኑ ነጻ ወጥታለች " ብለዋል። አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑንም አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም

" ታጣቂዎች ለሊት መጥተው በር ሰብረው ነው ይዘዋቸው ይሄዱት " - የቤተሰብ ምንጭ
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደና ሌሎች አብረዋቸው ታስረው የነበሩ አመራሮች ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የቅርብ ቤተሰብ ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጡ።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በመቐለ በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች ትላንት ሌሊት ነው ከመቐለ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸው የተገልጸው።
ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር ከተወሰዱት መካከል የትግራይ ኃይሎች የመረጃና ደህንነት ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ እና የትግራይ ኃይሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ኢሳያስ ታደሰ ይገኙበታል።
እኚሁ የቤተሰብ ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ የሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ጠባቂዎች መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. በተቀየሩ ማግስት ቤተሰቦቻቸው ወደ ቤቱ መግባትም ሆነ ከቤቱ መውጣት እንዳይችሉ ተደርጎ ለ18 ሰዓታት ያህል በቤታቸው ተዘግተው እንደቆዩ ተናግረዋል።
ከዚያም በማግስቱ ከቤታቸው አስወጥተው ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው ገልጸዋል።
በኋላም ከሌሎች የቀድሞ የትግልና የስራ አጋሮቻቸው ጋር በመቐለ ላጪ ክፍለ ከተማ በሚገኘው " HZ ሆቴል " ታስረው እንደነበር አመልክተዋል።
የህወሓት አመራሮች መቐለን ለቀው ለመውጣት በተዘጋጁበት ወቅት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደንና ሌሎች ታሳሪዎችን ከታሰሩበት ቦታ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎ ነበር። ታሳሪዎቹ ግን " አንድሄድም / አንወጣም ከዚህ " በማለት ተከላክለው እንደነበር የቤተሰብ ምንጩ ገልጸዋል።
እስከ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. ሌሊት 9፡00 ሰዓት ድረስ በዚህ ሁኔታ ከቆዩ በኋላ ታጣቂዎች ታሳሪዎቹ የነበሩበትን ክፍል በመስበር ገብተው በኃይል ከሆቴሉ አውጥተዋቸዋል። ታጣቂዎቹ ታሳሪዎቹን ከሆቴሉ አውጥተው ወደ አዲግራት አቅጣጫ እንደወሰዷቸው ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #tigray #mekelle የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመቐለ መግቢያዎችን ፣ ኤርፖርቱን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰማ። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ሰላም ኃይል ጋር በመቀናጀት የመቐለ መግቢያ አካባቢን ፤ ኤርፖርቱን ጨምሮ የክልሉን ሰፊ አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። " ወታደራዊ…

Sponsored by
Surafel
3 days ago
#tigray
#mekelle
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመቐለ መግቢያዎችን ፣ ኤርፖርቱን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰማ።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ሰላም ኃይል ጋር በመቀናጀት የመቐለ መግቢያ አካባቢን ፤ ኤርፖርቱን ጨምሮ የክልሉን ሰፊ አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
" ወታደራዊ ግጭት ዳግም ማገርሸቱ ከተነገረ በኋላ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች የህወሓት ኃይሎች ከነበሩበት አቀማመጥ አፈግፍገዋል " ሲሉ ምንጮቹ አመላክተዋል።
በዚህም መሰረት አላማጣ ፣ ሳምረ፣ ኮረም፣ ተምቤን፣ መኾኒ እና ማይጨው ከተሞችን ለቅቆ ወደ መቐለ አቅጣጫ አፈግፍጎ የነበረው የህወሓት ኃይል፣ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከተማዋን መልቀቁ ተገልጿል።
የፀጥታ ኃይሎቹ (ሀገር መከላከያ እና TPF) ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም የመቐለ ዙሪያ አካባቢዎችን ፣ ኤርፖርትን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸው ታውቋል።
የመቐለ የመግብያ በሮች፦
- ኲሓ መቐለ
- ሳምረ መቐለ
- ተምቤን መቐለ
- ዓዲግራት መቐለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አራቱንም መግብያ በሮች መያዛቸውን ወደ መሃል ከተማ እንደሚገቡ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ወደ ዓዲግራት ከተማ በሚወስድ መስመር ማይመኸደን የተባለች አነስተኛ ከተማም በቁጥጥር ማዋላቸው ተገልጿል።
አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አካል በNGO ሳተላይት ስልክ ከከተማው ነዋሪ ከሆኑ ቤተሰብ በሰሙት መረጃ፥ አሁን ላይ የሀገር መከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል ያለውን ሁኔታ 'Handle' እያደረጉ ነው።
የህወሓት ኃይል ከተማውን ለቆ ሲወጣ እስረኞች መውጣታቸውን ዘራፊዎች መበተናቸውን በዚህም በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ፣ በፓሊስ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ፣ በጦር ጉዳተኞች ሆስፒታል ዘረፋ መፈጸሙን አመልክተዋል።
" የነበሩ አመራሮች የህሙማን አምቡላንስ ሳይቀር እዘው ነው የወጡት " ሲሉ አክለዋል።
" ህዝቡ በየመንደሩ ተደራጅቶ አከባቢውን እየጠበቀ ነው " ሲሉም ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።
አሁንም ዝርፊያ እና የበቀል እርምጃዎች እንዳይፈጸሙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች አስተማማኝ ሰላም እና ህግና ስርዓት እንዲያስከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
ከከተማዋ የወጡ የህወሓት ኃይሎች ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አቅጣጫ (እንደ አክሱም እና ሽረ ላሉ አካባቢዎች) ሊያቀኑ እንደሚችሉ ጉዳዩን የሚከታተሉ ታማኝ አካል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
እስካሁን በትግራይም ይሁን በአዋሳኝ የአፋር እና አማራ ክልል አካባቢዎች ስላለውና ስለነበረው ሁኔታ የፌዴራል መንግሥት ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም።
የአፋር ክልል መንግሥት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ሻዕቢያን ጭምር ባሳተፈውና ህወሓት በከፈተው ጦርነት ተይዘው የነበሩ የአፋር አካባቢዎች ነጻ ወጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ግጭት ካለበት የትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ወደ ሌላ ሥፍራ ማዘዋወሩን አስታውቋል። ዛሬ ሰኞ መስከረም 18/2019 ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ክልል ካስወጣቸው መካከል ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ሠራተኞች፣ - የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ…

2 months ago
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፈጸመ ስለተባለው ስለመቀሌው የድሮን ጥቃት የሕወሐት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሰፋ ምን አሉ? #tigray #geopolitics #ethiopia #mekelle #newsupdate
2 months ago
u1230u1260u122d - u12e8u12a0u1295u12f5 u12a0u1245u1323u132bu12cd u12e8u1218u1240u120c u1260u1228u122bu1361 u12e8u12a0u12e8u122d u1218u1295u1308u12f1 u1218u1228u1303 u12e8u1275u130du122bu12ed u12adu120du120du1295 u12c8u1245u1273u12ca u1201u1294u1273 u12a0u130bu1208u1320 u2708ufe0f #ethiopiannews #tigray #mekelle #ethiopianairlines #addisababa ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ሰበር - የአንድ አቅጣጫው የመቀሌ በረራ፡ የአየር መንገዱ መረጃ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አጋለጠ ✈️ #ethiopiannews #tigray #mekelle #ethiopianairlines #addisababa
6 months ago
የጥበብ ዓምዱ አታኽልቲ ነጋ በአዲስ ስራ ተመለሰ
* "ውሽጥን ደገን" ሊመረቅ ነው
#ethiopia | ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈው፣ መምህር፣ ደራሲና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ ዳግም ወደ ስክሪን ተመልሷል።
በ"ማሾ" እና "ምትሓታዊ ዓለባ" (ብርሆን ገይፀን) የብዙዎችን ልብ የገዛው ይህ የጥበብ ሰው፣ አሁን ደግሞ "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ብቅ ብሏል።
ቀን፦
እሁድ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት።
ቦታ፦
በመቀለ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ።
በሸባ ኢንተርተይመንት አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ በቅርቡ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካች ይደርሳል።
አታኽልቲ ነጋ "ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም" የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየ፣ ለብዙ ወጣት ባለሙያዎች ፈር ቀዳጅ የሆነ የጥበብ መምህር ነው። ይህ አዲስ ስራው የቀድሞውን ጣፋጭ የትግርኛ ድራማ ለዛ ይዞ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። ሁላችሁም እሁድ በመቐለ በመገኘት ይህንን የጥበብ ጀግና እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
(Trailer) ለማየት፦ እዚህ ይጫኑ
ጥበብን በባለቤቱ፣ ታሪክን በፈጣሪው!
ብቸኛ አዘጋጅ
( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት
በክብሮም ገ/መስቀል
የዚህን ተከታታይ ድራማ ማስተዋወቂያ (Trailer) ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://youtu.be/T6zFaqse6...
#getu #atakltinega #tigrayfilm #wishtindegen #shebaentertainment #tigrinyadrama #ethiopianart #mekelle #insideoutside #አታኽልቲነጋ #መቀሌ #ጥበብ #ትግርኛፊልም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የሟች ህፃን ናኦድ አጎት የሞት ቅጣት ተላልፈበት
#ethiopia | ላልተገባ ጥቅም ሲባል ህፃን ናኦድ ተኽላይን በአስቃቂ ጭካኔ የገደሉ አራት ወንጀለኞች ከሞት እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።
ከአራቱ ወንጀለኞች አንዱ በሌለበት የ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲከታተለው የቆየው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ አግኝቷል።
ሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ ሀምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ዙሪያ ነበር አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት።
ግድያው የተፈጸመው ታግቶ ለማስለቀቂያ 2 ሚሊዮን ብር ከተጠየቀበት በኋላ ነው።
የሟች እናት ወ/ሮ ዮርዳኖስ ጋይም " በልጄ ግድያ ቁጥር አንድ ተጠርጣሪ የሆነው የቅርብ ቤተሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ቢሆንም እስከ አሁን የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የለም " በማለት የፍትህ መዘግየቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው መግለፃቸውን አስነብበን ነበር።
" የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል " ሲሉ ነበር የሟች እናት የገለጹት።
ጭካኔ የተሞላበት የግድያ አፈፃፀሙ ከአንድ ዓመት በላይ ሲከታተል የቆየው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በሦስት ወንጀለኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚሁ መሰረት ፦
- የሟች ህፃን ናኦድ እናት #ወንድም በሆነው አንደኛ ተከሳሽ ክብሮም ገ/ማርያም የሞት ቅጣት፤
- ከሰተ ደበብና ፀጋይ የተባሉ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው የ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤
- ወንጀሉን ፈፅሞ የተሰወረው አራተኛ ተከሳሽ ዓንዶም ገ/ሊባኖስ በሌለበት የ25 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #rip #deathpenalty #court #tigray #mekelle

10 months ago
#mekelle
የታጠቁ የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ከጥዋት አንስቶ በመቐለ የሚገኘውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ፅ/ቤትን ከበው ሰራተኞች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ፣ በአካባቢው ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ አግደው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።
ብሬን ፣ ክላሽ የታጠቁት ኃይሎች ከጥዋት አንስተው ወደ ፅ/ቤቱ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ፣ ዙሪያውን በመክበብ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርገው አርፍደዋል።
ሰራተኞችና ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ከውስጥም ሰው እንዳይወጣ፣ ወደ ስፍራው ሰው እንዳይጠጋ በመከልከላቸው የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ውጭ ላይ ቆመው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአይን እማኞች ተረድቷል።
ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች እንቅስቃሴው የነበረው የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት አካባቢ ብቻ እንደነበር ከዛ ውጭ ከተማው ሙሉ ሰላም እንደሆነ ገልጸዋል።
ከግማሽ ሰዓት በፊት ታጣቂዎቹ አካባቢውን ክፍት ማድረጋቸው፣ ሰራተኞችም ወደ ስራ መግባታቸው ፣ መንገዶች ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክፍት መደረጋቸውን ለማወቅ ችለናል።
የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም ከነበረው የደመወዝ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ጋር የተገናኘ ነው።
ከሰዓት በኃላ የሚሰጥ መግለጫ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia

1 year ago
📌" እያንዳንድሽ ትመጫታለሽ”
የፌስቡኩ ሰፈር አድማቂ የመቐለ
ታላቁ ምሁርን እንሰናበተው
ፕሮፌሰር Hassen Mohammed ትቶን ሄደ
#ethiopia | ሁሌም ነገሮችን ቀለል አርጎ ሲያይ በህመሙ እንኳን ሲቀልድ ነው የማውቀው። ከፌስቡክ መራቄን ያወቅኩት ሀሰን ከአንድ ወር በፊት ኩላሊቱ ፌል አድርጎ እርዳታ ጠይቆ እንደነበረ አሁን ካለፈ በኋላ ስሰማ ነው 😭
ሀወይ የመቀሌው ምሁር ደህና ሁን አቦ👋😭
የዛሬ ሁለት አመት በፃፈው ፖስት ልጨርስ
" እያንዳንድሽ ትመጫታለሽ
በፎቶ የምታዩት ኮልፌ የመቃብር ስፍራ ነው። እንዴት "አድጓል"? ከብዙ አመታት በኋላ ብመጣ ምን አክሏል?! ከኔ ብቻ ነፍ ሰው ወስዷል። ከአያቶቼ ጀምሮ፣ የልቤ ክፋይ እናት አባት፣ አጎት አክስት እንዲሁም ብዙ ሌሎች የምወዳቸው ... ሁሉ በዚህ በኩል ነው የሄዱት። አላህ ይራህማቸው! ትናንት እና ዛሬም ተጨማምሯል። መንሱር ወንድማችንን አላህ ይራህመው! የመቐለው ወዳጅና የስራ ባለደረባችን ዶር ያሲንንም አላህ ይራህመው! መቐለ ሆነ አዲሳባ ለአዝራኤል ሁሉም ኮልፌ ነው። በክራንች ስለማያስገባ ከሩቅ ሆኜ ሁሉንም ዘየርኩ። የራሴን ፊውቸርም በዚያው። በምልክት "ደውላለሁ" አልኩት 😀 ሳበሳ
ይቺ ለረመዳኑም ለህማማቱም ትጠቅማለች ብዬ አሰብኩ። መተናነስ ነውና አላማቸው። ኃይል አለኝ ለምትል፣ እንጣጥ እንጣጥ የምትል ሁላ ትመጣታለህ! ወደ ትቢያ ትቀላቀላለህም። እንደማለት ነገር።
ድሮ ያየሁትና የረሳሁት መፅሄት ላይ የሆነ አገር ለአንድ ከተማ ከንቲባ ጥያቄ ቀረበ። የሆነ ታዋቂ ቀራፂ የከተማዋ ክፍት ቦታዎች እንዲሰጡት ጠየቀ። አላማው የመቃብር ሐውልት ቅርፆችን ለመትከል ነበር። ሰዎች ለህይወት ትኩረትም ትርጉምም አይሰጡም፣ በደመነብስ ይራወጣሉ። ቢሰጡም እንኳን ከፍተኛ የዝንጋታ ችግር አለባቸው። የዚህ ቀራፂ አላማ ታድያ ስናልፍ ስናገድም፣ ስንንቀዋለል ስንሮጥ አይተን ደንገጥ እንድንል ነው። እንድናስታውስ ነው። ቅድሚያ ለሚገባው ቅድሚያ እንድንሰጥ ነው። ጥብርር ስንል፣ ስንደነፋ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ ስንል ድንገት ቀና ብለን አይተን "what's the point?!" እንድንል። "ምን ዋጋ አለው?"፣ "ምን ትርጉም አለው?" እንድንል እና ወደ መልካምነታችን እንድንመለስ ነው። የኔም አላማ ይሄው ነው። ሰናይ ምሽት!" #tesfag
***
ሀሰኖ! Hassen Mohammed ወዱ መምህራችን!
የ Mekelle University School of Law ትዝታችን እና ታሪካችን አንዱ አንተ ነበርክ። ቅንነትህን ፍትሐዊነትህን አሰላሳይነትህን እና የቋንቋ ችሎታህን ፉገራና ጨዋታህን (ሳበሳ) አንረሳውም።
በሰላም እረፍ!
ነፍስ ይማር።
ተማሪህ

Comments