2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በስዊድን ጎተንበርግ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ'ጎቲያ ካፕ' የዓለም የወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ካቀኑት የኢትዮጵያ ቡድኖች መካከል፣ 20 የሚሆኑ የአንድ ቡድን ተጫዋቾች እና አጃቢ አዋቂዎች የውድድሩ ማጠቃለያ ዕለት ባልታሰበ ሁኔታ መሰወራቸው ተገልጿል። ይህ ክስተት በስፖርቱ ሽፋን በራሳቸው ፍቃድ የተፈጸመ ህገ-ወጥ ስደት (illegal migration) ሊሆን እንደሚችል የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል።
ከ77 ሀገራት የተውጣጡ ቡድኖች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በአራት ቡድኖች ተወክላ ነበር። ሆኖም የፍጻሜው ውድድር በሚካሄድበት ዕለት የተጫዋቾቹ ማረፊያ የነበረው ትምህርት ቤት አስተናጋጆች፣ አባላቱ እቃቸውን ጠቅልለው መጥፋታቸውን ደርሰውበታል። የጎቲያ ካፕ የፕሬስ ቃል አቀባይ ፍሬድሪክ ቤክማን፣ አዘጋጁ ኮሚቴ ከቡድኑ ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለነበረው ድርጊቱ እንዳስገረማቸው ገልጸው፣ ለጥንቃቄ ሲባል ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ውድድሩ ከተጠናቀቀ አስር ቀናት ቢያልፉም፣ የቡድኑ አባላት እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ አልተመለሱም።
አዘጋጆቹ ከቡድኑ አስተባባሪ በደረሳቸው የኢሜል መልእክት "የተፈጠረው የመግባባት ችግር ነው" የሚል ማስተባበያ ቢሰጥም፣ ተጫዋቾቹ የት እንዳሉ ግን ምንም ዓይነት ፍንጭ አልተሰጠም። የስዊድን ፖሊስ የጠፉ ሰዎችን የመፈለግ ክፍል ኃላፊ ኤሊኖር ሃልዲን እንደገለጹት፣ ከዚህ በፊት በውድድሩ ታሪክ ጥቂት ሰዎች የመጥፋት አጋጣሚ ቢኖርም፣ በአንድ ጊዜ 20 ሰዎች ሲሰወሩ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው።
ፖሊስ ከስደተኞች ኤጀንሲ እና ከድንበር ተቆጣጣሪዎች ጋር በመተባበር ፍለጋውን የቀጠለ ሲሆን፣ ድርጊቱ በሰው አዘዋዋሪዎች የተፈጸመ ሳይሆን አባላቱ አስቀድመው ያቀዱት ስደት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ይህ ክስተት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መድረኮች ላልተገባ የስደት ዓላማ መጠቀሚያ እየሆኑ መምጣታቸውን የሚያሳይ አሳሳቢ አጋጣሚ ሆኗል። ታዳጊ አትሌቶች እና አጃቢዎቻቸው ሀገራቸውን ወክለው በሄዱበት የውድድር መድረክ ላይ መሰወራቸው፣ በሀገራት መካከል ያለውን እምነት ከመፈተኑም በላይ፤ በቀጣይ ሌሎች ወጣት ኢትዮጵያውያን ስፖርተኞች ዓለም አቀፍ የውድድር ዕድሎችን እንዳያገኙ እና የቪዛ ክልከላ እንዲያጋጥማቸው ሊያደርግ የሚችል አደገኛ አዝማሚያ መሆኑ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያጎላዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ፤ "ዓመታዊው የጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ ለመካፈል ወደ ስዊድን ያመሩ ታዳጊዎች እና የቡድን አባላት በስዊድን መጥፋታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። በጉዳዩ ዙርያ ምላሽ ወይም ማብራርያ እንድንሰጥ ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄዎች እየቀረቡ ሲሆን ፌዴሬሽናችን የቡድኑ አባላት መጥፋት ያሳዘነው መሆኑን እየገለጸ ታዳጊ ቡድኖች በመሰል ውድድሮች ላይ በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል ወደ ውድድሩ የሚያመሩ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የወከሉ አለመሆኑን እየገለፅን በአንዳድ አካላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት እንደሆኑ እየተገለጸበት ያለው መንገድ ትክክል አለመሆኑን እናሳውቃለን። " ብሏል።

4 months ago
የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ:
የፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲ መታሰቢያ
* ጣሊያናዊ ምሁር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ናቸው
* ባለቤታቸው ወይዘሮ ሳራ የማነ እና ከልጃቸው ካሌብ ጆርጂ ሌጋሲያቸውን ( Legacy ) ለማስቀጠል እየታተሩ ናቸው
#ethiopia | በአፍሪካና በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በሕክምና ሙያቸው፣ በደራሲነታቸውና በሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎቻቸው ደካማና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች ሲረዱ የቆዩት ታዋቂው ጣሊያናዊ ምሁር ፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲ (ዶክተር) በተወለዱ በ81 ዓመታቸው ሰኔ 10 ቀን 2024 ዓ.ም. ተለይተውናል።
ፕሮፌሰሩ ለአርባ አምስት ዓመታት በዘለቀው ሙያዊ ሕይወታቸው በአርባ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት እየተዘዋወሩ በበጎ ፈቃደኝነት የሕክምና አገልግሎት የሰጡ ሲሆን፣ በኦርቶፔዲክስ (የአጥንት) እና በዴርማቶሎጂ (የቆዳ) ሕክምና ስፔሻሊስት ነበሩ።
በሱዳን የሚገኘውን ትልቅ ሆስፒታል ጣሊያኖች በሚገነቡበት ወቅት ከፍተኛ የገንዘብ ፈንድ በማምጣት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያም ለሀያ ዓመታት ያህል ያገለገሉ ሲሆን፣ የአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታልን በማቋቋም የመጀመሪያው ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም በዳኑ ሆስፒታል፣ በአቤት ሆስፒታል ድንገተኛ አደጋ ክፍል በአጥንት ስፔሻሊስትነት የሰሩ ሲሆን፣ በየዓመቱ ከጣሊያን ወደ ወሊሶ ሆስፒታል እየመጡ ሰፊ የኦፕራሲዮን ሕክምና አገልግሎት በነፃ ይሰጡ ነበር።
ፕሮፌሰር ኤንሪኮ የሰውን ልጅ በዘር፣ በቋንቋ፣ በቆዳ ቀለምና በሃይማኖት የማይለዩ ፍፁም የሰብአዊነት ተምሳሌት ነበሩ። በአውሮፓ የኮሶቮ ጦርነት ወቅት የአንድ ዓመት ደሞዛቸውን በመተው በጦርነቱ መሃል በነፃ የሕክምና አገልግሎት የሰጡ ሲሆን፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅትም በመጀመሪያዎቹ አምስት ጣሊያናውያን የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ውስጥ በመሆን በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራው ያቀኑ ታላቅ ባለውለታ ናቸው።
በጣሊያን ሚላኖ "ናጋ" የተሰኘ የሕክምና ማዕከል በማቋቋምም አፍሪካውያንና የሌሎች ሀገራት ስደተኞችን፣ በተለይም የሕጋዊ ሰነድና የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ወገኖች በነፃ ሲያክሙ ቆይተዋል።
ብዙዎች ስለ ሀገር ሲያነሱ "የአባት ሀገር" ወይም "የእናት ሀገር" ቢሉም፣ ፕሮፌሰሩ ግን ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር ጥልቅ በመሆኑ ሁልጊዜም "የልጄ የካሌብ ሀገር" በማለት በኩራት ይገልጿት ነበር።
ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ወታደራዊ ታሪክ በርካታ ምርምሮችን ያደረጉት ፕሮፌሰሩ፣ በአጠቃላይ ከ46 በላይ መጻሕፍትን በኢንግሊዘኛና በጣሊያንኛ ቋንቋዎች አሳትመዋል።
ከእነዚህም መካከል "The History of Imperial Ethiopian Army" የተሰኘውና ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ምርምር ማዕከል ያበረከቱት መጽሐፍ፣ "ደስታስ ይርስ ኤንድ ላይፍ 1892-1937" እና "Aethiopia la moneta Africana" የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው። የቡና አመጣጥ ከኢትዮጵያ መሆኑን ለአለም ካስተዋወቁበት ስራቸው ባሻገር የዘመነ መሳፍንትን ፍፃሜ የሚያሳይ ታሪካዊ መጽሐፍ ይጠቀሳሉ።
እኝህ ታላቅ ምሁር ስኮላር፣ ዶክተር፣ የሚሊተሪ ኦፊሰር እና ደራሲ ብቻ ሳይሆኑ፣ በሚላኖ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ "ትንሹ ልዑል" የተሰኘውን የሕጻናት መጽሐፍ በ55 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተሙ ተርጓሚና ድንቅ የቅብ ሥራዎችን ያበረከቱ ሰዓሊም ነበሩ።
ምንም እንኳን ሞት በድንገት ከሚወዷቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ ሳራ የማነ እና ከልጃቸው ካሌብ ጆርጂ ቢለያቸውም፣ ያኖሩት ታላቅ አሻራ ግን ከመቃብር በላይ ሁሌም ሕያው ሆኖ ይኖራል።
ባለቤታቸውና ልጃቸው የፕሮፌሰሩን ውርስና ሌጋሲ ለማስቀጠል፣ እሳቸው ሳይታተሙ የተዉትንና ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በአምስት መቶ አምስት መቶ ገጾች የተቀነበቡ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍትን ለሕትመት ለማብቃት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያን የመወደዳቸው ምዕራፍ የተገለጠው፤ የተጀመረው በባለቤታቸውና በልጃቸው እንደሆነ ይናገሩ ነበር። በዚህ መሠረት ቤተሰቦቻቸው በኢትዮጵያ ምድር በስማቸው ሙዚየም ለመክፈት አልያም በእርሳቸው የተሰሩ ሥራዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለማበርከት ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።
የፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲን ሕይወትና ሥራዎች ፤ ለአገርና ለሕዝብ ያበረከቱትን አስተዋጸኦ በክብር የሚዘክር ሥራ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ይጠበቃል።
#ethiopiaheritage #italianscholar #enricopierobossi #ethiopianhistory #humanitarian #enricobossi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Ethiopia’s Great Friend:
In Memory of Professor Colonel Enrico Piero Bossi
Italian scholar and human rights advocate
His wife, Mrs. Sara Yemane, and their son, Caleb Giorgi, are working to preserve and continue his legacy.
#ethiopia | The renowned Italian scholar, Professor Colonel Enrico Piero Bossi (M.D.), who dedicated many years of his life in Africa and Ethiopia through his medical profession, authorship, and humanitarian activities, helping vulnerable and disadvantaged communities, passed away at the age of 81 on June 17, 2024.
During his distinguished 45-year professional career, Professor Bossi volunteered medical services across 42 African countries. He was a specialist in Orthopedics (bone and musculoskeletal medicine) and Dermatology (skin medicine).
He made a significant contribution to securing major funding for the construction of a large hospital in Sudan built by Italian organizations.
In Ethiopia, where he served for nearly twenty years, he played a key role in establishing Adama General Hospital and served as its first director.
Additionally, he worked as an orthopedic specialist at Danu Hospital and in the Emergency Department of Abet Hospital. Every year, he traveled from Italy to Woliso Hospital, where he provided extensive surgical services free of charge.
Professor Enrico was a true symbol of humanity, treating all people equally regardless of race, language, skin color, or religion. During the Kosovo War in Europe, he gave up an entire year’s salary to provide free medical services in the war zone. Likewise, during the Ethio-Eritrean War, he was among the first five Italian medical professionals who flew by helicopter to the conflict area to provide humanitarian assistance.
In Milan, Italy, he founded the medical center known as “NAGA,” where he provided free healthcare services to African immigrants and migrants from other countries, particularly those lacking legal documentation or financial means.
While many people refer to their homeland as their “fatherland” or “motherland,” Professor Bossi’s love for Ethiopia was so profound that he proudly referred to it as “the country of my son, Caleb.”
A dedicated researcher of Ethiopian history, culture, and military history, Professor Bossi authored and published more than 46 books in English and Italian.
Among his notable works are:
The History of Imperial Ethiopian Army
Destas Yirs and Life 1892–1937
Aethiopia la Moneta Africana
His work helped introduce Ethiopia’s role as the birthplace of coffee to the wider world. He also authored historical works documenting the end of the Era of the Princes (Zemene Mesafint).
Professor Bossi was not only a scholar, physician, military officer, and author, but also a translator and artist. At the Catholic University of Milan, he translated and published The Little Prince in 55 international languages and contributed remarkable artistic and illustrative works.
Although death unexpectedly separated him from his beloved wife, Mrs. Sara Yemane, and his son, Caleb Giorgi, the remarkable legacy he left behind will remain alive far beyond his grave.
To preserve Professor Bossi’s legacy, his wife and son are working to complete and publish two previously unpublished manuscripts. These extensive works, each consisting of approximately 500 pages, focus on Ethiopian subjects and were left unfinished by the professor.
The professor used to say that the chapter of his love for Ethiopia was revealed—and indeed began—with his wife and his child. Based on this, his family is actively working either to open a museum in Ethiopia bearing his name or to donate his works, along with various personal artifacts and items, to the Ethiopian National Museum.
It is hoped that the Ethiopian Heritage Authority will undertake initiatives to honor and commemorate Professor Colonel Enrico Piero Bossi’s life, work, and invaluable contributions to the nation and its people.
May his memory and contributions continue to inspire future generations.
#ethiopiaheritage #italianscholar #enricopierobossi #ethiopianhistory #humanitarian #enricobossi

የአራጣ ብድር ምንነት እና ተጠያቂነት
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
ፋንታሁን ደለለው ጠበቃና የህግ አማካሪ
መግቢያ #ethiopia | የአራጣ ብድር በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ የህሊናን ወይም የሰውን ችግር መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ስር የሚካትት ወንጀል ሲሆን አስቀጪነቱም በሕጉ ተደንግጓል። ይህ ድርጊት በማኅበረሰብ ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በሕግም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። በዚህ ጽሑፍ የአራጣን ምንነት፣ በሕግ የተፈቀደን የወለድ መጠን፣ የአራጣ መንስኤዎችንና የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች እና የአራጣ ብድር ተጠያቂነት እና መፍትሄዎችን ጭምር በአጭሩ እንዳስሳለን።
1. የአራጣ ምንነት
የሕግ መዝገበ ቃላት የሆነው ብላክስ ሎው መዝገበ ቃላት 8ኛው እትም እንደሚሰጠው ትርጉም ”USURY is an illegal contract for a loan or forbearance of money, goods, or things in action, by which illegal interest is reserved, or agreed to be reserved or taken.” ይህን ወደ አማርኛ በግርድፉ ስንመልሰው አራጣ ማለት ሕገ-ወጥ በሆነ የብድር ውል ወይም ገንዘብን፣ እቃዎችን ወይም በድርጊት ላይ ያሉ ነገሮችን መስጠት ሆኖ ሕጋዊ ያልሆነ ወለድ ለመጠበቅ ወይም ለመስጠት የሚደረግ ስምምነት ነው። በሌላ በኩል ማሪያም ዌብስተር የተሰኘው መዝገበ ቃላት አራጣን በተጋነነ የወለድ መጠን ገንዘብ ማበደር በማለት ይተረጉመዋል። በመሆኑም ከተለያዩ ትርጉሞች መረዳት እንደሚቻለው አራጣ ያልተገባ የወለድ ስሌት ተበዳሪዎችን በማስከፈል የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡ ተመጣጣኝ የወለድ መጠን ፋይናንስ ገበያው ወይም ብሔራዊ ባንኮች በሚወስኑት መሰረት ማሰብ ተገቢ ቢሆነም በሕግ ከተወሰነው የወለድ ምጣኔ በላይ ገንዘብ ማበደር በብዙ አገሮች ዘንድ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓል፡፡ ወንጀሉም አራጣ በመባል ይታወቃል፡፡
በሀገራችን በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ለአራጣ ቀጥተኛ ትርጉም ባይሰጥም በአንቀጽ 712 በአራጣ ወንጀል የሚያስጠይቁ ተግባራትን ያስቀምጣል። ይኸውም ማንም ሰው የተበዳዩን ችግረኝነት፣ የበታችነቱን፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን፣ ወይም መንፈሰ ደካማነቱን፣ ወይም ልምድ ወይም ችሎታ የሌለው መሆኑን መሰረት በማድረግ፡-
በሕግ ከተፈቀደው ወለድ በላይ ገንዘብ ያበደረው እንደሆነ ወይም
ካበደረው ገንዘብ ጋራ በግልፅ ተመጣጣኝነት የሌለው ንብረት በምትኩ እንዲሰጠው ያደረገው ወይም ቃል ያስገባው እንደሆነ የአራጣ ወንጀል በመፈፀም የሕግ ተጠያቂነት ይኖርበታል።
በመሆኑም በአጠቃላይ አራጣ ማለት በሕግ ከተፈቀደው በላይ የተጋነነ የወለድ መጠን በማስከፈል እና ከገንዘቡ ጋር ተመጣጣኝነት የሌለው መያዣ በመቀበል የሚደረግ የብድር ስምምነት ሲሆን ይህም የተበዳሪውን ሁኔታ ማለትም ችግረኝነቱን፣ የበታችነቱን፣ የገንዘብ ችግሩን፣ መንፈሰ ደካማነቱን... መሠረት በማድረግ የሚፈፀም ብዝበዛ" (Exploitation of distress) ነው፡፡
በኢትዮጵያ በሕግ የተፈቀደውን የወለድ መጠን ስንመለከት የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 1751 ሕጋዊ ወለድ (Legal Rate of Interest) ማለት በውል ያልተወሰነ ወለድ (ጥቅም) ከፋይ የሆነ ሰው በዓመት በመቶ ዘጠኝ (9%) ሂሳብ ይከፍላል ይላል። በተጨማሪም የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2479(1) የብድር ውል ተዋዋይ ወገኖች ተበዳሪው ሊከፍለው የሚገባው የወለድ መጠን በወር ወይም በቀን ሳይሆን በዓመት ከአስራ ሁለት በመቶ (12%) በላይ ሊበልጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ሕጉ የፈቀደው የብድር ውል ወለድ መጠን በዓመት 12% ድረስ ብቻ እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
2. የኢፊድሪ ህግ 1996 እና የኢትዮጵያ ፍትሀብሄር ህግ ተፈጻሚነት ወሰን
ይሁንና ይህ የወለድ መጠን በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ላይ ተፈፃሚነት የለውም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ብድር አቅርቦት በተፈለገው መጠን መገኘትን፣ እንዲሁም የወለድ ተመንና ሌሎች ክፍያዎችን የመወሰንና የመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው ሲሆን ብሔራዊ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 591/2000 ዓ.ም አንቀፅ 5(4) እና በመመሪያ ቁጥር 12/2010 መሠረት የብድር ውል ለደንበኞቻቸው በሚሰጡበት ወቅት ላበደሩት ብድር የወለዱን ምጣኔ በራሳቸው እንዲወስኑ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወለድ ተመን መመሪያ ቁጥር 295/2020 መሰረት በብድር እና በቅድመ ክፍያ ላይ የብድር መጠን በተመለከተ በእያንዳንዱ ባንክ በነፃነት የሚወሰን እንደሆነ ያስቀምጣል። በመሆኑም ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ የሚታሰበው የወለድ ምጣኔ ከላይ በፍትሐብሔር ሕጉ እንደተመለከተው የወለድ ጣራው በዓመት እስከ 12% ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ማድረግ ይችላሉ።
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ ተደርጎባቸዋል። ስለዚህ አራጣ ማለት ሕጉ ከፈቀደው የብድር ወለድ መጠን በላይ ተዋውሎ ማበደር ማለት ነው፡፡
3. የአራጣ ወንጀል የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
አራጣ በተበዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ተበዳሪዎች ለተበደሩት ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የወለድ መጠኑ በጣም የተጋነነ ስለሆነ ብድሩን መልሰው ሳይጨርሱ ጥሪታቸው ወይም በብድሩ ገንዘብ ሰርተው ያገኙትን ትርፍ አበዳሪው ስለሚወስድባቸው ለኪሳራ እና ለከፋ ድህነት ይዳረጋሉ፡፡ ተበዳሪዎች ጊዜያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ብለው በተበደሩት ገንዘብ ድህነትን ሸምተዉ ድሀ ሆነው ሲቀሩ፤ አበዳሪዎችም ምንም እሴት በኢኮኖሚ ውስጥ ሳይጨምሩ ሀብት የሚሰበስቡበት ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
የአራጣ ወንጀል በግለሰቦች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ የድርጊቱ መበራከት ሀገራዊ ጉዳት በማስከተል የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይሆንም። በአራጣ የሚዘዋወረው ገንዘብ ላይ መንግሥት እውቅና ስለማይኖረው ከትርፉ ላይ ግብር ስለማይከፈል መንግሥት ገቢ ሳይሰበስብ ይቀራል፡፡
ሌላው ጉዳት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ እንዳያስቀምጡ ከማድረጉ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም የሚሆነው ጥቂትም ቢሆን ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ አራጣ በማበደር እንዲሰማሩ በማድረጉ ነው፡፡ ገንዘቡ በባንክ ተቀመምጦ ለኢኮኖሚው ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽኦ የሚያስቀረው ሲሆን ወደ ባንኮች የሚገባው ተቀማጭ እየቀነሰ መሄዱ በመጨራሻም ባንኮች አቅም እያጠራቸው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ባንኮች ለብድር የሚውል ተቀማጭ ገንዘብ ሲያጥራቸው በተዘዋዋሪ አራጣ አበዳሪዎች የብድር አማራጭ ይሆናሉ፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በተመጣጣኝ ወለድ መጠን ገንዘብ ተበድረው ሥራ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ብድር ሳያገኙ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።
4. የአራጣ ብድር ተጠያቂነት
በአራጣ ብድር በሚያስከትሉ የወንጀል እና የፍትሀብሄር ተጠያቂነትን በዚህ ክፍል ያካተትን ሲሆን እንደማከተለው ቀርቧል።
4.1 የአራጣ ወንጀል የሕግ ተጠያቂነት
የአራጣ ወንጀል በወንጀል ሕጉ በአንቀፅ 712 ስር ሽፋን አግኝቷል። ከላይ እንደተገለፀው በድንጋጌው ላይ የዘረዘሩትን ተግባራት የፈፀመ ሰው በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ከ5 (አምስት አመት) በማይበልጥ ፅኑ እስራት እና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም ሰው ከላይ በተጠቀሰው ሀሳብ መነሻነት በአራጣ ላይ የተመሰረተ መብት የተቀበለ፣ በመከላከያነት የተጠቀመበት ወይም ለሌላ ሰው ያስተላለፈ እንደሆነ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጣል፡፡
4.2 የአራጣ ብድር የፍትሀብሄር ተጠያቂነት
በፍትሃብሔር ህግ አንቀጽ 1162 መሠረት አላግባብ መበልጸግ በፍትሃብሔር ቀጥታ ወይም በሌላ መንገድ በእርግጥ ተጎጂ የሆነው ሰው ወይም አካል የተበዳሪውን ችግር ውስጥ መግባት ወይም የመንፈስ/ስነ ልቦና ደካማናት በመጠቀም በማበደር ያልተገባ፣በህግ ያልተደገፈ የወለድ ምጣኔን በመተመን የሚያበድሩ አካላት በፍትሃብሔር ውል ህጎቻችን ቁጥር 1676 ጀምሮ እንደሚደነግገው ከፍቃድ ውጪ እንደሆነ ተቆጥሮ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በህገወጥ ስምምነት/1808(2) መሠረት እንዳልነበረ ሊቆጠር የሚችል ወይም ሊፈርስ የሚችል ውል በመሆኑ ተበዳሪው ከተበደረው ክፍያ በላይ በአበዳሪው ተጠይቆ እንደሆነ ይህንን ሊያስመልስ መብት አለው።
5. የአራጣ ብድር ውል ጉዳቶች
5.1 አራጣ በተበዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ተበዳሪዎች ለተበደሩት ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የወለድ መጠኑ በጣም የተጋነነ ስለሆነ ብድሩን መልሰው ሳይጨርሱ ጥሪታቸው ወይም በብድሩ ገንዘብ ሰርተው ያገኙትን ትርፍ አበዳሪው ስለሚወስድባቸው ለኪሳራ እና ለከፋ ድህነት ይዳረጋሉ፡፡ ተበዳሪዎች ጊዜያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ብለው በተበደሩት ገንዘብ ድህነትን ሸምተዉ ድሀ ሆነው ሲቀሩ፤ አበዳሪዎችም ምንም እሴት በኢኮኖሚ ውስጥ ሳይጨምሩ ሀብት የሚሰበስቡበት ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
5.2 የአራጣ ወንጀል በግለሰቦች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ የድርጊቱ መበራከት ሀገራዊ ጉዳት በማስከተል የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይሆንም። በአራጣ የሚዘዋወረው ገንዘብ ላይ መንግሥት እውቅና ስለማይኖረው ከትርፉ ላይ ግብር ስለማይከፈል መንግሥት ገቢ ሳይሰበስብ ይቀራል፡፡
5.3 ሌላው ጉዳት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ እንዳያስቀምጡ ከማድረጉ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም የሚሆነው ጥቂትም ቢሆን ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ አራጣ በማበደር እንዲሰማሩ በማድረጉ ነው፡፡ ገንዘቡ በባንክ ተቀመምጦ ለኢኮኖሚው ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽኦ የሚያስቀረው ሲሆን ወደ ባንኮች የሚገባው ተቀማጭ እየቀነሰ መሄዱ በመጨራሻም ባንኮች አቅም እያጠራቸው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ባንኮች ለብድር የሚውል ተቀማጭ ገንዘብ ሲያጥራቸው በተዘዋዋሪ አራጣ አበዳሪዎች የብድር አማራጭ ይሆናሉ፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በተመጣጣኝ ወለድ መጠን ገንዘብ ተበድረው ሥራ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ብድር ሳያገኙ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።
6. የህግ ምክር
ገንዘብ ተበዳሪዎች ወይም ፈላጊዎች ባስፈለጋቸው የኢንቨስትመንት ወይም የብድር አገልግሎት መስክ በመሰማራት ካልተፈለገ ጉዳትና ኪሳራ እንዲድኑ እንዲሁም በዘመነ የፋይናንስ ስረአት ለመመራት ፤ የፋይናንስ ተቋማት ብድር በተጠየቁ ጊዜ ቀልጣፋና፣ማራኪ በሆነ አገልግሎት የብድር አገልግሎት እንዲያቀርቡ የአሰራር ማሻሻል እንዲኖር ተገቢውን ጥረት ማድረግ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ማለትም ለተበዳሪውም ሆነ ለአበዳሪው
አግባብ ያለው የህግ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስቻል የሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት እና ለዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ማጣቀሻዎች/References/
1. የኢፊድሪ ወንጀል ህግ 1996
2. የኢትዮጵያ ፍተሀብሔር ህግ 1952
3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 591/2002
4. የፍትህ ሚኒስተር የፊት /የፌስቡክ/ ገጽ
45 ሌሎች የባንክ ፥የማይክሮ ፋይናንስ አበዳሪ ተቋማት አዋጅ፣ደንብ፣መመሪያዎች
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
https://t.me/Fantahunlawye...
0929101037

የፍርድ ቤት መር አስማሚነት
ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የሽምግልና ሥርዓት
#ethiopia | የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት አሰራር ይበልጥ ለማጎልበት እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የምክክር መድረክ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የድሬዳዋ ከተማ የባህል ሽማግሌዎች፣ የአባ ገዳዎች፣ የኡጋዞች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርዓት ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የፍትህ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በተለይም ድሬዳዋ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች መኖሪያ እንደመሆኗ፣ ዘመናዊውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ከባህላዊ ሽምግልና እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር አቀናጅቶ መሄድ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ተገኝተዋል።
በቀጣይ ፍርድ ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም፣ ለዘርፉ አዲስ ለሚቀላቀሉ አስማሚዎች የህግ እና የአሰራር ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባራዊ ትግበራ እንደሚገባ ታውቋል።
#ፍርድቤት #ፍትህ #ሽምግልና #ባህል #ሃይማኖት #ድሬዳዋ #ኢትዮጵያ #legal #mediation #culture #religion #diredawa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
⚖️ ስለ"ህግ እና ማህበረሰብ" መረዳት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች!! ⚖️
👤 ታደሰ ተክሌ (የህግ አማካሪና ጠበቃ)
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ "ህግ እና ማህበረሰብ" ያላቸው ቁርኝት ጥልቅና ውስብስብ ነው። ህግ የማህበረሰቡን እሴት የሚያንፀባርቅ መስተዋት ነው። ማህበረሰብን ማጥናትና መረዳትም ህግን ጠንቅቆ ለማወቅ ከማገዙም በላይ በርካታ አለመግባባቶችን በቀላሉ ለመፍታት መንገድ ይከፍታል። በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታም በህግ አውጪው አካል እና በዜጎች ፍላጎት መካከል የሚስተዋሉ ክፍተቶች ይህን እውነታ ካለመረዳት የሚመጡ ናቸው። ማህበረሰቡን ያማከለ ህግ ስለሚወጣበት መንገድ ጽሁፌን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ 👇
🛑 በኢትዮጵያ ህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶች
📌 የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማነስ፦ ብዙ ጊዜ ህጎች የሚረቀቁት በመንግስት አስፈፃሚ አካላት ወይም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሆኖ ለፓርላማ ይቀርባሉ። ይህ ሂደት ህጉ ከመውጣቱ በፊት የህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲቀንስ ሊያደርገው ይችላል። 📉
📌 ውይይቶች በከተማ ላይ ብቻ ማተኮራቸው፦ ፓርላማው አዋጆችን ከማፅደቁ በፊት የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው መድረኮችን ያዘጋጃል። ሆኖም፣ እነዚህ ውይይቶች ብዙውን ጊዜ በከተማ ላይ ያተኮሩ እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ወይም ሰፊውን የአርሶ አደርና አርብቶ አደር የህብረተሰብ ክፍሎችን ሃሳብ ያላካተቱ ሊሆኑ ይችላሉ።
📌 ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን አለማካተት፦ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ማህበረሰብ ለዘመናት ሲመራባቸው የቆዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ህጎች አሉ። መደበኛው ህግ እነዚህን እሴቶች ግምት ውስጥ ሳያስገባ ሲቀር፣ ህጉ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የማጣት ወይም የመጣስ እድሉ ሰፊ ይሆናል። ⚖️
📌 የቋንቋ ተደራሽነት ችግር፦ በሌላ በኩል ህጎች የሚወጡት በፌዴራል የስራ ቋንቋ (አማርኛ) እና እንግሊዝኛ ብቻ እንደመሆኑ ቋንቋውን ለማይረዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ህጉን ተረድቶ ለመተግበር እንቅፋት ይፈጥራል። 🗣️
💡 ማህበረሰቡን ያማከለ ህግ እንዴት መውጣት አለበት?
ህግ የሰላም እና የልማት መሳሪያ እንዲሆን "ማህበረሰብ-ተኮር" መሆኑ የግድ ነው፡፡ 🕊️🏗️ ይህን ለማድረግ የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝ ናቸው፦👇
ሀ. አሳታፊነት (Participation)፤ 👥 ህጉ በቀጥታ የሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች (ገበሬዎች፣ ነጋዴዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች…) በረቂቅ ደረጃው ላይ እንዲሳተፉ መደረግ አለበት። አስተያየታቸውም በህጉ ውስጥ መካተቱን ማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ይፈጥራል።
ለ. የህግ ተፅዕኖ ግምገማ (Impact Assessment)፤ 📊 ህጉ ከመውጣቱ በፊት በማህበረሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ህይወት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ በጥናት ሊለይ ይገባል። "ይህ ህግ ቢወጣ ድሃውን ማህበረሰብ ይጎዳል ወይስ ይጠቅማል?" የሚለው ጥያቄ በቅድሚያ መመለስ አለበት።
ሐ. ነባራዊ እሴቶችን ማክበር፤ ህጉ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሞራል እና የባህል እሴቶች ጋር መጣጣም አለበት። ለምሳሌ በግጭት አፈታት ዙሪያ የሚወጡ ህጎች የማህበረሰቡን የእርቅ ባህል ከግምት ቢያስገቡ ውጤታማ ይሆናሉ።
መ. ግልፅነት እና ተደራሽነት፤ 📢 ህጉ በግልፅ ቋንቋ መፃፍ እና ወደ ተለያዩ የክልል የስራ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለህዝቡ መሰራጨት አለበት። "ህግን አለማወቅ ከቅጣት አያድንም" የሚለው መርህ ትርጉም የሚኖረው ህዝቡ ህጉን እንዲያውቅ በቂ ስራ ሲሰራ ብቻ ነው። 📖
📝 በአጠቃላይ...
ህግ የማህበረሰቡን ፍላጎት ተከተሎ የሚወጣ እንጂ፣ ማህበረሰቡን በግዴታ ወደ አንድ አቅጣጫ ለመንዳት ብቻ የሚወጣ መሆን የለበትም። በኢትዮጵያ "ህግ እና ማህበረሰብ" እንዲጣጣሙ የህግ አውጪው አካል ከፖለቲካዊ ፍላጎት ይልቅ ለማህበራዊ እውነታዎች ቅድሚያ መስጠት ይኖርበታል፡፡
👤 ታደሰ ተክሌ (የህግ አማካሪና ጠበቃ) #የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት #የግል_ዕጩ_ተወዳዳሪ
⚖️ Qabxiilee Murteessoo Waa’ee "Seeraa fi Hawaasaa" Hubatamuu Malan!! ⚖️
👤 Taaddasaa Taklee (Gorsaa fi Abukaatoo Seeraa)
Haala qabatama Itoophiyaa keessatti hidhanni "Seeraa fi Hawaasa" gidduu jiru gadi fagoo fi walxaxaa dha. Seeronni daawwitii duudhaalee hawaasaa calaqqisiisani dha. 🪞 Hawaasa qorachuu fi hubachuun seera gadi fageenyaan beekuuf gargaaruu malees, waldhabdee garaa garaa salphaatti hiikuuf karaa baha. 🤝 Haala qabatama biyya keenyaatiin, qaama seera baasu fi fedhii lammiilee gidduutti hanqinni mul'atu dhugaa kana hubachuu dhabuuf kan maddu dha. Barreeffama koo karaa seeronni hawaasa xiyyeeffannoo godhatan itti ba'an ilaalchisee akka armaan gadiitti nan dhiyeessa: 👇
⚖Adeemsa Seera Baasii Itoophiyaa Keessatti Barsiifatawwan Baramanii fi Hanqinaalee Mul'atan
📌 Hirmaannaan Kallattii Uummataa Gadi Aanaa Ta'uu፦ Yeroo baay'ee seeronni kan qophaa'an qaamolee raawwachiiftuu mootummaafi Mana Marii Minisitirootaatiin ta'ee gara Paarlamaatti dhiyaatu. Adeemsi kun utuu seeronni hin ba'iin dura hirmaannaan kallattii uummataa akka xiqqaatu gochuu danda'a. 📉
📌 Mariwwan Magaalota Irratti Qofa Xiyyeeffachuu፦ Paarlamaan Labsiiwwan raggaasisuun dura uummatni yaada akka irratti kennuuf maddabaroota marii ni qopheessa. Ta'us, mariwwan kun yeroo baay'ee magaalota irratti kan xiyyeeffataniifi yaada hawaasa bal'aa qonnaan bultootaa fi horsiisee bultootaa kan hin dabalanne ta'uu danda'u.
📌 Duudhaalee Aadaa fi Amantii Of Keessaa Dhabuu፦ Uummatni Itoophiyaa akka hawaasaatti seera aadaa fi amantii kanaan dura ittiin bulamaa ture qaba. Seerri idilee duudhaalee kana tilmaama keessa yeroo hin galchine, hawaasicha biratti fudhatama dhabuu ykn cabsuuf carraan jiru bal'aa dha. ⚖️
📌 Afaan Hojii Gufuu Ta'uu፦ Gama biraatiin seeronni kan ba'an afaan hojii federaalaa (Afaan Amaaraa) fi Afaan Ingiliziitiin qofa waan ta'eef, uummata afaanicha hin beekneef seericha hubatanii hojiirra oolchuuf gufuu uuma.
⚖Seeronni
Hawaasa
Xiyyeeffannoo Godhatan Akkamitti Ba'uu Qabu?
Seerri meeshaa nageenyaa fi misoomaa akka ta'uuf "hawaasa-irratti kan hundaa'e" ta'uun isaa dirqama. 🕊️Kana gochuuf qabxiileen armaan gadii murteessoo dha:
A. Hirmaachisummaa (Participation)፤ 👥 Qaamoleen seerichi kallattiidhaan isaan ilaallatu (qonnaan bultoonni, daldaltoonni, dubartoonni, dargaggoonni...) sadarkaa wixineetti akka hirmaatan taasifamuu qabu. Yaadin isaanii seera keessatti dabalamee argamuun isaa miira abbummaa uuma. 🕊
B. Madaallii Dhiibbaa Seeraa (Legal Impact Assessment)፤ 📊 Seerri utuu hin ba'iin dura jireenya hawaasummaa, dinagdee fi xiinsammuu uummataa irratti dhiibbaa inni fidu qorannoodhaan adda ba'uu qaba. "Seerri kun yoo ba'e hawaasa hiyyeessa ni miidha moo ni fayyada?" gaaffiin jedhu dursee deebii argachuu qaba.
C. Duudhaalee Qabatamaa Kabajuu፤ Seerichi duudhaalee amalaa fi aadaa hawaasa Itoophiyaa waliin kan walsimu ta'uu qaba. Fakkeenyaaf, seeronni furmaata waldhabdee irratti ba'an aadaa araaraa hawaasichaa tilmaama keessa yoo galchan bu'a-qabeessa ta'u.
D. Iftoomina fi Dhaqqabamummaa፤ 📢 Seerichi afaan ifa ta'een barreeffamee gara afaan hojii naannolee garaa garaatti hiikamee uummataaf raabsamuu qaba. "Seera beekuu dhabuun adabbii jalaa hin oolchu" jedhu hiika kan qabaatu, uummatni seericha akka beekuuf hojiin gahaan yoo hojjetame qofa. 📖
📝 Walumaagaletti...
Seerri fedhii hawaasaa hordofee kan ba'u malee, hawaasicha gubbaadhaan gara kallattii tokkotti humnaan oofuuf qofa kan ba'u ta'uu hin qabu. Itoophiyaa keessatti "Seeraa fi Hawaasni" akka walsimaniif, qaamni seera baasu fedhii siyaasaa caalaa dhugaa hawaasummaatiif dursa kennuu qaba.
👤 Taaddasaa Taklee (Gorsaa fi Abukaatoo Seeraa) #kaadhimamaaa_dhuunfaa #naannoo_filannoo_ukkaa #mana_maree_bakka Bu'oota_Uummataaf

በዋስትና ከመፈታት አኳያ አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ ያመጣቸው አዳዲስ ነገሮች መካከል:-
By Hailu Hasena (Legal Advocate)
1. "ያለ ዋስትና መለቀቅ (Release without bail/unconditional release)" የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::
በዚህ ድንጋጌ መሠረት ተጠርጣሪው የተጠረጠበትን ወንጀል ስለመፈጸሙ ወይም የተባለው ወንጀል ስለመፈጸሙ አጠራጣሪ (doubtful) በሆነ ጊዜ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፍ/ቤትም ሆነ ቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍ/ቤት ተጠርጣሪውን ያለ ዋስትና እንዲሁ እንዲለቁት ይገደዳሉ:: አንቀጽ 118(4)፣ 137(2)
*በቀድሞው የወ/መሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 59(1) እና 93 መሠረት የጊዜ ቀጠሮ እና የቀዳሚ ምርመራ ፍ/ቤቶች ተጠርጣሪው ወንጀል ስለመፈጸሙም ሆነ ወንጀሉ ራሱ ስለመፈጸሙ ቢጠራጠሩም ስንኳ ተጠርጣሪውን የግድ ዋስትና እንዲያስይዝ ወይም በማረፊያ ቤት እንዲቆይ እንዲያዙ ይገደዱ ነበር:: በአዲሱ መድብለ ሕግ ያ አሠራር ተሽሯል::
*ይህ ድንጋጌ በተለይ ለሚታፈሱ ወይም በመመሳጠር በፍ/ብሔር ወይም ወንጀል ባልሆነ ጉዳይ ለሚታሰሩ ሰዎች ይህ ትልቅ የሕግ ጥበቃ የሚያደርግ ነው::
*ስለዚህ የተያዙ ሰዎች የሚለቀቁባቸው መንገዶች እነዚህ ናቸው—ያለ ዋስትና መለቀቅ፣ ያለ ገደብ መለቀቅ፣ በራስ ዋስትና መለቀቅ፣ በንብረት ዋስትና መለቀቅ፣ በሰው ዋስትና፣ በገንዘብ ዋስትና መለቀቅ፣ በተጨማሪ ዋስትና መለቀቅ::
*ስለሆነም ከእንግዲህ የጠበቆች ሥራ የታሰረን ሰው በዋስትና ማስፈታት ብቻ ሳይሆን ያለ ዋስትና ማስፈታትንም ይጨምራል::
*Note: በፍ/ቤት መደበኛ ክስ (charge) የተከፈተ ከሆነ ያለ ዋስትና የመለቀቅ ጉዳይ አይነሣም::
2. በሕግ ዋስትና የሚያስከለክሉ ወንጀሎች (non-bailable crimes)
* በሞት የሚያስቀጡ ወንጀሎች፣ ወይም
* በ ≥15 ዓመት ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ሰው የሞተባቸው ወንጀሎች ብቻ እንዲሆኑ የተደነገገ ስለሆነ በእንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች ውጭ ያሉ ወንጀሎች በሙሉ በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎች (bailable crimes) ሆነዋል:: አንቀጽ 138(2,3)
ስለሆነም:-
➡️ስለሆነም በሕግ ዋስትናን በማይከለከልባቸው ወንጀሎች በመሉ ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች በዋስትና የመለቀቅ መብት አለው::
➡️በዕድሜ ልክ ወይም የጽኑ እሥራት ጣሪያ በሆነው በ25 ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል ብቻውን ዋስትናን አያስከለክልም::
➡️በማንኛውም የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ/የተከሰሰ ሰው በሕግ ዋስትናን አይከለከልም—all corruption crimes have become bailable.
ከዚህ ቀደም በዐዋጅ ቁ. 434/1997 (በዐዋጅ ቁ. 882/2007 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 4(1) መሠረት "ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው በዋስትና አይለቀቅም በማለት ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጡትን ለይቶ non-bailable corruption crimes ተደርጎ የነበረው ድንጋጌ ቀሪ (abolished) ተደርጎአል::
➡️በአደገኛ ቦዘኔነት ዐዋጅ ቁጥር 384/96 አንቀጽ 6(3) "በአደገኛ ቦዘኔነት ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም:" ተብሎ በወንጀል ዓይነት ዋስትና ይከለከል የነበረው (categorical bail denial) ዘፈቀዳዊ ነው ተብሎ በዚህ ዐዋጅ ተሽሮአል::
➡️በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎችን (bailable crimes) አስመልክቶ ዋስትና መብት (right) ሲሆን ዋስትና ሊከለከልም ሊፈቀድም የሚችለው በዳኞች ፍቅድ ሥልጣን (judicial discretion) ነው::
ፍቅድ ሥልጣኑ የሚመራባቸው መርኆዎችም ደግሞ "ዳኛው ተጠርጣሪውን/ተከሳሹን በዋስትና ይለቃል የሚል ግምት (presumption of release on bail) ይወሰዳል:"፤ "ዋስትናን በሁኔታ የሚያስከለክሉ ሁኔታዎችም አይኖሩም: ተብሎ ይገመታል::"
"ዋስትናን ለመከልከል የሚያበቁ ልዩ ሁኔታዎች በጠባቡ እና ለተከሳሽ/ተጠርጣሪ በሚጠቅም መልኩ ይተረጎማሉ:" የሚሉ ናቸው—ከተመድ የሰብኣዊ መብቶች የዋስትና መብት ትርጉም አኳያ::
ለምሳሌ:- ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጣ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ወይም ማስረጃ ያጠፋል ወይም በተፈለገ ጊዜ አይቀርብም ወይም ቋም አድራሻ የለውም ወይም መውጣቱ ለኅ/ሰቡ ደኅንነት ያሰጋል ወይም የዋስትና ግዴታውን አይወጣም ወዘተ. የሚል ግምት አይያዝም::
ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ እነዚህን መርኀዊ ግምቶች ለማስተባበልና ለመሠረታዊ መብቶች (የነጻነት መብት፣ ንጹሕ ሆኖ የመገመት መብት) የሥነ ሥርዓታዊ ጥበቃ የሆነውን የዋስትና መብት ለመቃወም ሕጋዊ፣ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት ያለ መሆኑን በቂ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዳት ይኖርበታል::
3. የድኅረ ጥፋተኝነት ፍርድ ዋስትና (Post-conviction bail) የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::
አንቀጽ 301(2)
ይህ ድንጋጌ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ነህ ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ የቅጣት ውሳኔ እስኪተላለፍበት ድረስ ባለው ጊዜ በዋስትና እንዲቆይ የሚያደርግ ነው::
ይሁንና ይህ ዋስትና የሚሠራው ወንጀሉ በመቀጮ ብቻ የሚያስቀጣ ሲሆን ነው::
እንደሚታወቀው በነባሩ የወ/ሕ/ሥ/ሥ መሠረት ዳኞች የፈረዱበትን ማንኛውንም ሰው ቅጣቱ እስኪወሰን ድረስ 'ታስሮ' እንዲቆይ ያዙ ነበር—በጣም ጥቂት ሰብኣዊነት ላይ የተመሠረተ ልዩነት ቢኖርም::
ለዚህ እንደ ምክንያት ይጠቀስ የነበረው የዋስትና መብት ንጹሕ ሆኖ ከመገመት መርኅ ጋር ብቻ የተቆራኘ ስለሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሲባል መብቱም ዐብሮ ቀሪ ይሆናል፣ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በዋስትና ቢወጣ ሊጣልበት የሚችለውን ቅጣት ፈርቶ ላይቀርብ ስለሚችል የሚጣለው ቅጣት አፈጻጸም ችግር እንዳይገጥመው የሚል ግምት በመያዝ ነበር::
ይሁንና ሁለቱም ምክንያቶች የተሳሳቱ እና የሕግ ፍልስና መሠረት የሌላቸው ስለሆኑ በሥሡ ለማረም ተሞክሯል::
*ለምሳሌ በፌስታል ዐዋጅ ቁ. 1383/2017 አንቀጽ 25(1/ሀ) ሥር ፌስታል በመጠቀም ወይም ለመጠቀም ይዞ በመገኘት ወንጀል ተከሶ የጥፋተኛነት ፍርድ የተሰጠበት ተከሳሽ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በማረፊያ/በማቆያ ቤት እንዲቆይ አዲሱ ሕግ አይፈቅድም
ተባረኩ!
Hailu Hasena (Legal Advocate)

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የከተማ ይዞታን ለማስመለስ ክስ በይርጋ ይታገዳል?
(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰባት ዳኞች በተሰጠ የህግ ትርጉም የተሰጠ የህግ ትንታኔ)
#ethiopia | በጠበቃና የህግ አማካሪ አልማው ወሌ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
የተከበሩ ጠበቃ እናመሠግናለን መልካም ንባብ
ኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ 1
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ 1
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ 1
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም 3
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ 4
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች 4
ክፍል ሰባት፡ የውሳኔው ማጠቃለያ እና ቀጣይ አንድምታዎች 4
7.1 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል 5
7.2 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት 6
7.3 የክፍል 7 ጥማቂ 8
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ግምገማ 9
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ
ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የሰጠው ይህ ውሳኔ በመ/ቁጥር 210477 ላይ ተሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በመለወጥ ተሰጠው (Overruling) ውሳኔ ሲሆን በአገሪቱ የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገት እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ የራሱ የሆነ አንድምታ ያለው መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለውጥ በችሎቱ የተሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(1) ድንጋጌ እና በሰበር ስነ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀፅ 14(2) በተዘረጋው ስርዓት ሲሆን ችሎቱ የተሰየመበትም ዋነኛ ምክንያትም የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ ቀደም ሲል በሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል ሊታረቅ የማይችል ተቃርኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የጉዳዩ ምንጭ አቶ ጅላሎ ኩመል ሼህረዲ (አመልካች/ተከሳሽ) እና አቶ ታምራት መርከቡ ፍልቾ (ተጠሪ/ከሳሽ) በአዲስ አበባ ከተማ (ለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ፊጋ ሰፈር በሚባል አካባቢ) በሚገኝ 2,000 ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ ላይ ያደረጉት ክርክር ነው፡፡ ጉዳዩ ለሰባት ዳኞች ችሎት መመራቱ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መሠረታዊ የሕግ ይዘት ያለው ጉዳይ ሲሆን ችሎቱም በሕግ አተገባበር ላይ ወጥነት እና ተገማችነትን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን ለመውጣት በተጠቃሽ ውሳኔዎቹ መካከል የታየውን ተቃርኖ አስታራቂ እና ግልጽ አቋም ሊያዝበት የሚገባ መሆኑን በግልጽ አስፍሯል፡፡ ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረኑ አስገዳጅ ውሳኔዎች ሥርዓታዊ የሆነ ችግር እንዳያስከትሉ ችሎቱ ራሱን በራሱ በማረም የወሰደው ዕርምጃ በኢትዮጵያ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ሥርዓት ውስጥ ያለውን ተቋማዊ ብስለት የሚያሳይ ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚገባው ነው፡፡
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ
በመጀመሪያ ደረጃ በሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 ጥር 05 ቀን 2002 ዓ.ም. የተወሰነውንና በቅጽ 10 የታተመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአጭሩ ስንመለከት ጉዳዩ አቶ ዳዊት መስፍን ከተጠሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ጋር ያደረጉት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ዳዊት በአዲስ አበባ ከተማ (የቀድሞ ወረዳ 118፣ ቀበሌ 05) የሚገኝ መኖሪያ ቤት የባለቤትነት መብትን መሠረት በማድረግ ቤቱ እንዲለቀቅላቸው ክስ አቅርበው ነበር፡፡ ለዚህም በጥቅምት 23 ቀን 1985 ዓ.ም. የተሰጠ የከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አቅርበዋል፡፡ ተጠሪው (ኤጀንሲው) በበኩሉ፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845ን ማለትም የ10 ዓመቱን የውል ግዴታዎች ይርጋ ድንጋጌ በመጥቀስ የይርጋ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያውን በመቀበል ክሱን ውድቅ አድርገውት ነበር፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የሰበር ችሎት ግን የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት አግባብ መኖር አለመኖሩን ጭብጥ አድርጎ በመያዝ ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቷል፡፡ የሰበር ችሎቱ ትንታኔውን የጀመረው ማናቸውም ኢትዮጵያዊ የንብረት ባለቤት መሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(1) የተረጋገጠ መሆኑን በማንሳት ሲሆን፣ በመቀጠልም የፍትሐብሔር ሕጉን የንብረት ድንጋጌዎች ማለትም አንቀጽ 1126፣ 1168፣ 1184፣ እና 1186 ደንጋጌዎችን እንዲሁም በፍ/ህ/ቁጥር 1188 እስከ 1192 ድረስ ያሉትን ድንጋጌዎችን ሙሉ ይዘትና መንፈስ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ችሎቱ ወሳኝ ብሎ ያነሳው ነጥብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1192 "ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን" ብሎ ያስቀመጠው ለሚንቀሳቀስ ንብረት ብቻ መሆኑን እና ስለ ማይንቀሳቀስ ንብረት በዝምታ ማለፉን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንቀጽ 1206 ሥር የተደነገገው የመፋለም ክስ የባለቤትነት መብት ከሁሉ የሰፋ መብት መገለጫ መሆኑን፣ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ዘላቂነት (Perpetuity) ያለው መብት በመሆኑ በይርጋ ቀሪ እንዳይሆን የሕግ አውጪው ፍላጎት መሆኑን አብራርቷል፡፡ በዚህም መሠረት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ድንጋጌን ተፈፃሚ ማድረግ የሕጉን አወቃቀርና መንፈስ የሚያፋልስ መሆኑን በመግለጽ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም መብት ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ወደሚል ድምዳሜ ደርሷል፡፡ ይህ ውሳኔ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ ጠንካራ ቢሆንም፣ ዋነኛ ክፍተቱ ትንታኔው ሙሉ በሙሉ ታሳቢ ያደረገው "የግል ባለቤትነት መብት" (Private Ownership) መኖርን መሆኑ ነው፡፡ ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት ስለነበር ይህ አካሄድ ትክክል ቢሆንም፣ የባለቤትነት መብት በሕገ-መንግሥት በተከለከለበት መሬት ላይ ትንታኔው እንዴት ሊተገበር ይችላል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም ትርጉም በሌሎች ልዩ ህጎች ያሉትን የይርጋ ድንጋጌዎችን የማይነካ መሆኑ በማሳሳብ አልፏል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁጥ 69302 ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ስንመለከት፦ ጉዳዩ በአመልካች አቶ ሸለማ ነገሰ እና በተጠሪ አቶ ፋይሣ መንግስቱ መካከል በኦሮሚያ ክልል፣ ኖኖ ቤንጃ ወረዳ በሚገኝ የገጠር እርሻ መሬት ላይ የተደረገ ክርክር ነው፡፡ ተጠሪ አባቴ በሞት ከተለየበትמ 1985 ዓ.ም.
ጀምሮ አመልካች መሬቱን አላግባብ ስለያዘብኝ ይልቀቅልኝ ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካች በበኩሉ መሬቱን ለ18 ዓመታት መያዙን በመግለጽ ተከራክሯል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች መሬቱ እንዲለቀቅ የወሰኑ ቢሆንም የሰበር ችሎቱ ግን አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት የማግኘትና ያለመፈናቀል መብት እንዳላቸው ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(4) መሠረት ማረጋገጡን ጠቅሶ፣ ይሁን እንጂ መሬቱን በሌላ ሰው የተነጠቀ አርሶ አደር ክስ ማቅረብ ስላለበት የጊዜ ገደብ የገጠር መሬት አዋጆች በግልጽ አለመደንገጋቸውን በማንሳት የሕግ ክፍተት መኖሩን አሳይቷል፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉ የሁከት ይወገድልኝ ክስ የ2 ዓመት ይርጋን (አንቀጽ 1149(2)) መተግበር የአርሶ አደሩን ሕገ-መንግሥታዊ መብት አጥብቦ የሚገድብ በመሆኑ ውድቅ በማድረግ፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እንደ ድልድይ በዋቢነት በመጥቀስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ምንም እንኳን ከመዝገብ ቁጥር 43600 ፈጽሞ የተለየ አቀራረብ ይዞ የመሬት ይዞታን ከባለቤትነት መብት ነጥሎ በማየት የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ ያደረገ ቢሆንም፣ የውል ድንጋጌ የሆነውን የፍ/ህ/ቁ 1845 ድንጋጌን በቀጥታ መሬት ላይ ለመተግበር የሄደበት መንገድ በበቂ ሁኔታ ያልተብራራ መሆኑ እንደ ሂሳዊ ድክመት ሊነሳበት ይችላል፡፡
በሦስተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁ 210477 ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የተወሰነውንና አሁን የተሻረውን ስንመለከት፣ ጉዳዩ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ-ከተማ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ በአመልካቾች (የአቶ ነጋሳ ዱቤ ወራሾች) እና በተጠሪዎች (ወ/ሮ ጸሐይ ቹቾ እና ወ/ሮ ሴደሬ ንጉሴ) መካከል የተደረገ ክርክር ነበር፡፡ ተጠሪዎች ቦታውን ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለ19 ዓመታት መያዛቸውን በመግለጽ የይርጋ መቃወሚያ አቅርበው የስር ፍርድ ቤቶችም መቃወሚያውን ተቀብለውት ነበር፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎቱ ይህንን ውሳኔ በመሻር፣ የቀረበው ክስ "የመፋለም ክስ" መሆኑን በመግለጽ የቤትን ባለቤትነት የተመለከተውን የሰ/መ/ቁ 43600 አመክንዮ በቀጥታ በመዋስ "የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም" የሚል አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቶ ነበር፡፡ የዚህ ውሳኔ ዋነኛ ስህተት የባለቤትነት መብትን (Ownership) እና የይዞታ መብትን (Holding rights) አንድ አድርጎ ማየት መቻሉ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(3) መሠረት ግለሰቦች በመሬት ላይ የባለቤትነት መብት እንደሌላቸው እየደነገገ፣ በሰ/መ/ቁ 210477 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ግን የባለቤትነት መብት ጥበቃን (ከይርጋ ነፃ መሆንን) በመሬት ይዞታ መብት ላይ በመተግበሩ መሠረታዊ የሆነ የፅንሰ-ሐሳብ እና የሕግ ስህተት ተፈጽሞበት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
ክፍል ሦስት፡ በውሳኔዎቹ መካከል የነበረው ተቃርኖ እና የሕግ ማዕቀፎች
በእነዚህ ሦስት ውሳኔዎች መካከል የተፈጠረው ተቃርኖ እጅግ የጎላ እንደነበር በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንድ በኩል መዝገብ ቁጥር 43600 በቤት ባለቤትነት ላይ የመፋለም ክስ ይርጋ የለውም ሲል፣ በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁ 69302 በገጠር መሬት ይዞታ ላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ አድርጓል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በሰ/መ/ቁ 210477 የከተማ መሬት ይዞታን አስመልክቶ የቀረበን ክርክር የባለቤትነት ጉዳይ ከሆነው ከሰ/መ/ቁ 43600 ጋር በማመሳሰል የከተማ መሬት ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ወስኗል፡፡ ይህ ሁኔታ በመሬት ይዞታዎች (በገጠር እና በከተማ) ላይ የተለያየ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የይርጋ አተገባበር እንዲፈጠር አድርጎ የነበረ መሆኑ ከውሳኔዎቹ በግልፅ ይታያል፡፡
ይህንን ተቃርኖ ለመፍታት የሰባት ዳኞች ችሎት በርካታ ሕጎችን አንድ ላይ መመርመር ነበረበት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ስለ መሬት የመንግስትና የሕዝብ ንብረትነት፣ አንቀጽ 40(4) ስለ አርሶ አደሮች መብት፣ እና አንቀጽ 40(7) በጉልበትና በገንዘብ ስለሚፈራ ንብረት ያካተቱት ድንጋጌዎች ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1192፣ አንቀጽ 1206 (ስለ መፋለም ክስ)፣ አንቀጽ 1149(2) (የሁከት ክስ ይርጋ)፣ እንዲሁም አንቀጽ 1677(2) እና 1845 ድንጋጌዎች ሙሉ ይዘታቸው ተፈትሸዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2006 እና የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አግባብነት ያላቸው የሕግ ማዕቀፎች በመሆናቸው በችሎቱ ታሳቢ ተደርገዋል፡፡
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም
ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን የተወሳሰበ የሕግ ጥያቄ ለመፍታት የተጠቀሱትን ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎችን በመመርመር ለእያንዳንዳቸው ተገቢ ነው ያለውን ማብራሪ ሰጥቶባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን አልሻረውም፤ ይልቁንም ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት በመሆኑና መኖሪያ ቤት ላይ የባለቤትነት መብት ስላለ፣ ትንታኔው ከዚህ መዝገብ ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ በማስረዳት የጉዳዩን ልዩነት (Distinguishing) በማሳየት ትርጉሙ እንዲፀና አድርጎታል፡፡ በመቀጠልም በሰ/መ/ቁጥር 69302 ለገጠር መሬት የተሰጠውን የ10 ዓመት ይርጋ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ትክክለኛነት የተቀበለ ቢሆንም፣ ይህንን የገጠር መሬት ቀደመት አስገዳጅ ትርጉም በቀጥታ በከተማ መሬት ላይ መተግበሩ ስህተት መሆኑን በማሳየት የስር ፍርድ ቤትን አካሄድ ነቅፏል፡፡ በመጨረሻም በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሻረው ሲሆን ለውሳው ምሶሶ ያደረጋቸው አበይት ምክንያቶቹም የቀደመው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የባለቤትነት መብትን እና የይዞታ መብትን በማምታታት፣ በመሬት ይዞታ መብት ላይ ሊቀርብ የማይችለውን የመፋለም ክስ የይርጋ መቃወሚያ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም የሚሉት መሆናቸውን አዲሱ ትርጉም በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ችሎቱ አዲሱን የሕግ ትርጉም ለመስጠትና ለመተንተን የተከተለው አመክንዮ አራት ደረጃዎችን ያካተተ ነበር፡፡ አንደኛ ትንታኔውን በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(3) ላይ በማስረፅ መሬት የግለሰብ ባለቤትነት ሊኖርበት የማይችል መሆኑን እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 የመፋለም ክስ መሬት ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን አረጋግጧል፡፡ ሁለተኛ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ የሚኖረው መብት (በሊዝም ሆነ በነባር) በነገር ላይ ያለ (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት እንጂ ተራ የኪራይ ውል ግንኙነት አለመሆኑን በማብራራት የመብቱን ህልውና ገልጿል፡፡ ሦስተኛ የሲቪል ሎው (Civil Law) የመፋለም ክስ ፅንሰ-ሐሳብ እና የኮመን ሎው (Common Law) የማስለቀቅ ክስ (Action of ejectment) ፅንሰ-ሐሳቦችን በማነፃፀር፣ ምንም እንኳን ይህ የኮመን ሎው አሠራር ለሕግ ሥርዓታችን እንግዳ ቢሆንም፣ በሕግ የታወቀ መብት እስካለ ድረስ ስያሜው ክሱን ለማስተናገድ እክል እንደማይሆን አብራርቷል፡፡ አራተኛ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን ድልድይ በማድረግ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ሥር የተቀመጠውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት
የከተማ መሬት ይዞታን አላግባብ ከያዘ ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚል አዲስ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ
በዚህ ውሳኔ ተግባራዊ የተደረገው የፍ/ህ/ቁ 1845 "በውል ስለሚመነጩ ግዴታዎች" ሥር የሚገኝ ሲሆን፣ ውልን ስለመፈፀም፣ ባለመፈፀም እና ውልን ስለማፍረስ የሚቀርቡ ክሶች በአስር ዓመት ይርጋ እንደሚታገዱ የሚደነግግ ነው፡፡ የመሬት ይዞታ ክርክር ደግሞ በባህሪው ከውል የሚመነጭ ሳይሆን ከሕገ-ወጥ ይዞታ ወይም ንጥቂያ የሚመነጭ ነው፡፡ ሆኖም ችሎቱ ይህንን ክፍተት ያገናኘው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የውል ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ ያለበት "ግዴታ" ምን ዓይነት እንደሆነ (ከሕገ-ወጥ ድርጊት ወይስ ያለአግባብ ከመበልፀግ የመነጨ መሆኑን) ችሎቱ በግልጽ አላብራራም፡፡ እንዲሁም በፍ/ህ/ቁ 1846 መሠረት የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ ከመቼ እንደሚጀምር፣ በአንቀጽ 1851 መሠረት የይርጋ መቋረጥ እንዴት እንደሚስተናገድ፣ እና በፍ/ህ/ቁጥር 1854 መሠረት መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው ሰው እንኳን በይርጋው መጠቀም የሚችል መሆኑ በመሬት ንጥቂያ ላይ የሚያመጣው ህጋዊ ውጤት/ ተፅዕኖ መኖር ያለመኖሩን በችሎቱ ትንታኔ ሥር በሰፊው ያልተዳሰሱ ግን መሰረታዊ የሆኑ የህግ ጥያቄዎች ሆነው አልፈዋል፡፡
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች
የሰባት ዳኞች ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ የንብረት ሕግ ስነ ህግ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው በርካታ ጥንካሬዎችን ይዟል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ችሎቱ የፍትሐብሔር ሕጉን እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥትን የመሬት መብት ስሪት በአግባቡ በማዋሃድ የግል ባለቤትነትን እና የመሬት ይዞታ መብትን በጥልቀት ለመለየት መቻሉ ሊደነቅ የሚገባው ሕገ-መንግሥታዊ ትንታኔ ነው፡፡ በተጨማሪም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን ሙሉ በሙሉ ከመሻር ይልቅ በሚገባው የሕግ አውድ (በቤት ባለቤትነት ላይ) ብቻ እንዲወሰን በማድረግ ትክክለኛ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም አስተዳደር/አተገባበርን ለማሳየት ችሏል፡፡ እንዲሁም የባለቤትነትን እና የይዞታ መብትን ማምታታት በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአግባቡ በማረም ለአስገዳጅ የሕግ ትርጉም ስርዓት ጥራት እና ታዓማኒነት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት መብቶችን ተራ የውል ግንኙነት ሳያደርግ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው ተጨባጭ መብቶች (In rem) መሆናቸውን ማረጋገጡ እና ጉዳዩን በ7 ዳኞች በማየት ተቋማዊ ቅቡልነትነን (Institutional Legitimacy) ማጠናከሩ የውሳኔው ዐበይት ጥንካሬዎች ናቸው፡፡
ክፍል ሰባት፡ አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ እና አዋጅ ቁጥር 1324/2016፡ የሕግ በጊዜ አተገባበር እና የአመሳስሎሽ ትርጓሜ መነጽር የተደረገ ዳሰሳ
7.1 መግቢያ
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ቁልፍ ትርጉሙ (Ratio decidendi)፤ የከተማ መሬት ይዞታን ሕገ-ወጥ ከሆነ መንገድ ከያዘው ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚለው ሲሆን ፣ "የሕግ በጊዜ አተገባበር" (Intertemporal law፤ ሕጎች በጊዜ ሂደት ያላቸውን ተፈፃሚነት የሚገዛ መርህ) እና "የአመሳስሎሽ ትርጓሜ" (Analogical reasoning) ተቀራራቢ የሕግ ድንጋጌዎችን በመጠቀም የሕግ ክፍተትን የመሙላት ሥነ-ዘዴ) በሚሉት ሁለት መነጽሮች ሲመረመር እጅግ አሳማኝ የሆኑ አካዳሚያዊ እና ተግባራዊ ጥያቄዎችን ሊስነሳ የሚችል ነው፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ ውሳኔ እና ከእርሱ በፊት ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የወጣው የፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016. መገጣጠም፣ የችሎቱን ሥነ-ሥርዓታዊ ትክክለኛነት እና የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) ምርጫዎች ለየብቻ እና በሂሳዊ መንገድ እንድንገመግም ሰፊ የትንታኔ መደላድል የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡ በዚህ ረገድ ሊደረግ የሚችለው ትንታኔ የጉዳዩን ፍሬ-ነገሮች፣ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 ድንጋጌ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች (በተለይም የይርጋ እና የሽግግር ድንጋጌዎችን)፣ እና የፍትሐብሔር ሕጉን የይርጋ ማዕቀፍ መሠረት በማድረግ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡
በሌላ በኩል ውሳኔው አንዳንድ ድክመቶች እና ቀጣይ ማብራሪያ የሚሹ ክፍተቶችም የሚታዩበት መሆኑን የግል ምልክታ አድርጌአለሁ፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተሰጠው ትንታኔ አጠር ያለ እና ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሻ ነው፡፡ ይህንን ይርጋ ተግባራዊ ማድረግ በተለይም ከአገር ውጭ በነበሩ ወይም በተለያዩ አቅም በሚያሳጡ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከፖሊሲ አኳያ አልተገመገመም፡፡ እንዲሁም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን የህግ ትርጉምን በተመለከተ "ተፈፃሚ ለማድረግም ሆነ ተቃርኖ አለው ለማለት አልተቻለም" የሚለው የችሎቱ አገላለጽ የተወሰነ ብዥታን የሚፈጥርና ይበልጥ ግልጽ ቢደረግ ይመረጥ የነበረ ነው፡፡ በዚሁ አስገዳጅ ውሳኔ ውስጥ በሌሎች ልዩ ህጎች የተመለከቱትን የይርጋ ድንጋጌዎችን በሚመለከት የተቀመጠውን አገላለፅ መጠቀም ያልተቻለበትን አግባብ ውሳኔው አያሳይም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመፋለም ክስ ከመሬት ጋር እንደማይሄድ ከተገለጸ በኋላ፣ በትክክል ክሱ በምን ዓይነት የክስ ምክንያት (Cause of action) መቅረብ እንዳለበት ግልጽ አቅጣጫ አለመቀመጡ ለባለሙያዎች ክፍተት ትቷል፡፡ ከገጠር መሬት አዋጅ ድንጋጌዎች ጋር በማነፃፀር ለከተማ መሬት ተመሳስሎሽ ትንታኔ (Analogical reasoning) ያልተጠቀመበትን አግባብም መኖሩን ውሳኔው ማሳየቱን ችሎቱ እንዲህ አይነት የህግ ትርጉም ስልት ተግባር ላይ ለማዋል/ለመውሰድ የነበረውን መልካም አጋጣሚ ማምከኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እንዲሁም ቅን ልቦ የሌለው ወይም መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው የመሬት ነጣቂ የ10 ዓመት ይርጋን ተገን አድርጎ መብት ሊያገኝ የሚችልበትን የፍ/ህ/ቁጥር 1854 ድንጋጌ አንድምታ ችሎቱ አለመመርመሩ እንደ ውሳኔው ድክመቶች ሊነሱ የሚችሉ ነጥቦች ይመስሉኛል፡፡
7.2 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል
ከላይ እንደተጠቀሰው በፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥርዓት እና በሕግ ትርጓሜ መሠረታዊ መርሆች መሠረት፣ አዲስ የወጣ መሰረታዊ ሕግ (Substantive law) የሕግ አውጪው በግልጽ ካልደነገገ በስተቀር ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም፡፡ ይህ ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህ (lex prospicit, non respicit) የሕግ ተገማችነት (Legal certainty) የጀርባ አጥንት ሲሆን፣ የተከራካሪ ወገኖች መብት እና ግዴታ የሚገዛው ድርጊቱ በተፈጸመበት ወይም ቢያንስ ክርክሩ በፍርድ ቤት በተጀመረበት ጊዜ በነበረው ሕግ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ ይህ መርህ እጅግ ግልጽ በሆነ መንገድ ይሠራል፡፡ ተጠሪ (ከሳሽ) ክሳቸውን ያቀረቡት ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.
ሲሆን፣ የክሱ መነሻ (ሕገ-ወጥ የመሬት ይዞታ ንጥቂያ) ተከሰተ የተባለው ደግሞ በ2011 ዓ.ም. (ወይም አመልካች እንደሚሉት በ1980 ዓ.ም.) ነው፡፡ በአንፃሩ አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 ፀድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣው በነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው፡፡ ይህም ማለት ክርክሩ ከተጀመረና በተለያዩ የፍርድ ቤት እርከኖች ሲንከባለል ከቆየ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አዋጁ ራሱ ይህንኑ ሁኔታ የሚገዛ ግልጽ የሽግግር ድንጋጌ (Transitional provision) የያዘ መሆኑ ነው፡፡ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 65(1) በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ይደነግጋል፡- "የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች ይህ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት… ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር እየተደረገባቸው ባሉ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም"፡፡ ይህ ድንጋጌ አዲሱ ሕግ፤ በአዋጁ የተካተቱ ማናቸውንም የይርጋ ጊዜያት ጨምሮ፣ ወደፊት ብቻ የሚሠራ እንጂ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩ ጉዳዮችን ወደኋላ ተመልሶ እንደማያካትት የሕግ አውጪው የሰጠው ግልጽ መመሪያ ነው፡፡
ይህ የሽግግር ድንጋጌ በቀጥታ አግባብነት ያለው፣ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 64(2) ለመሬት ማስለቀቅ ክስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ስለሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት ቢኖረው ኖሮ ውጤቱን ሊቀይረው ይችል ነበር፡- ማለትም ፍርድ ቤቱ በተገበረው የ10 ዓመት ይርጋ ታግዷል የተባለው የተጠሪ ክስ፣ የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ አሰላል ታይቶ በ15 ዓመቱ የይርጋ ጊዜ ሥር ሊድን (ሊቀጥል) ይችል ነበር፡፡ ሆኖም ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን አዲስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ አለማድረጉ ፍፁም ትክክል ነው ሊባል የሚችል ነው፡፡ እንዲያውም በሥነ-ሥርዓት ደረጃ ሲታይም አስገዳጅነት የነበረው ተግባር ነው፡፡ ይህን አድርጎ ቢሆን ኖሮ፣ አጠቃላይ የሆነውን ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህን እና የአንቀጽ 65(1)ን የተለየ የሽግግር መመሪያ በጣሰ ነበር፡፡
ስለሆነም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የተከተለው አካሄድ መገምገም ያለበት ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) በነበረው የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ በዚያን ወቅት፣ የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን በተመለከተ የተለየ የይርጋ ጊዜ ባለመኖሩ የተፈጠረውን የሕግ ክፍተት ለመሙላት በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የነበሩት አማራጮች፣ የፍትሐብሔር ሕጉ (በተለይም አንቀጽ 1677 እና 1845)፣ ወይም ደግሞ ቀድሞ የነበረው የገጠር መሬት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 456/1997) ብቻ ነበሩ (የኋለኛው አዋጅም ቢሆን በሰበር መ/ቁ 69302 እንደተረጋገጠው ለዚህ ክስ የሚሆን ግልጽ የይርጋ ጊዜ አላስቀመጠም ነበር)፡፡ ችሎቱ ክፍተቱን ለመሙላት የፍ/ህ/ቁ 1677(2) እና 1845ን (ጠቅላላ የ10 ዓመት ይርጋን) የመረጠ ሲሆን፣ ይህ ምርጫ የተደረገው በወቅቱ በነበረው የሕግ ሥርዓት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ ለገጠር መሬት ክሶች የተለየ እና የረዘመ የይርጋ ጊዜ ማውጣቱ የችሎቱን ውሳኔ ወደኋላ ተመልሶ ሕገ-ወጥ አያደርገውም፡፡ ይልቁንም፣ ፍርድ ቤቱ ገና ላልወጣ ሕግ እውቅና ሰጥቶ ወደኋላ ተግባራዊ አለማድረጉ የዳኝነት ሥልጣን ያለበትን የጊዜ ገደብ መረዳቱን እና የሕግ አውጪውንና የሕግ ተርጓሚውን የሥልጣን ክፍፍል ማክበሩን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) መርህ የተገበረበት መንገድ ጉድለት የለሽ ነው፡፡ ችሎቱ አግባብነት ያለውን የጊዜ ማዕቀፍ በትክክል ለይቷል፤ ክሱ በቀረበበት ጊዜ የነበረውን ሕግ ተግብሯል፤ እንዲሁም ከዓመታት በኋላ የሚወጣን ሕግ አስቀድሞ ከመገመትና ከመተግበር ታቅቧል ለማለት ያስደፍራል፡፡
7.3 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት
ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግን በጊዜ አተገባበር መርሆችን የተከተለበት መንገድ ተገቢነት ያለው ቢሆንም፣ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ (Analogical) ድልድይ ግን ቀጣይነት ያለው አካዳሚያዊ ክርክር የሚሻ ከባድ የሕግ ፍልስፍና ጥያቄን ማስነሳቱ አይቀሬ መስሎ ታይቶኛል፡፡የዚህ ሂሳዊ ግምገማዬ መነሻም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) ጥረት ማድረጉ አይደለም፤ ለከተማ መሬት ክስ የተለየ ይርጋ ባለመኖሩ ይህን ማድረጉ ተገቢና አስፈላጊ ነበር፣ ነገር ግን ትችቱ የሚያነጣጥረው በአመሳስሎሽ የወሰደውን የይርጋ ጊዜ ባመጣበት የተለየ ምንጭ ላይ በማተኮር ነው፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክርን የሚገዛ የይርጋ ጊዜ በሕግ አለመኖሩን ሲገነዘብ፣ ከፍትሐብሔር ሕጉ ሦስተኛ መጽሐፍ (ስለ ንብረት ሕግ) በመውጣት፣ ወደ አራተኛው መጽሐፍ (ስለ ግዴታዎች) ተሻገረ። በዚያም የውል ሕግ ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ የሚደነግገውን አንቀጽ 1677(2) ድንጋጌን እንደ ማሻገሪያ ድልድይ በመጠቀም በፅሑፍ አቀማመጡ ውልን ለመፈፀም፣ ላለመፈፀም ወይም ለማፍረስ ለሚቀርቡ ክሶች የተዘጋጀውን በቁጥር 1845 ድንጋጌ ሥር የሚገኘውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ አድርጎታል። ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም ለገጠር መሬት ክርክሮች በሰበር መ/ቁ 69302 ከተወሰደው የትንታኔ መንገድ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው፡፡
ሆኖም የሕግ አውጪው በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 የገጠር መሬትን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ በራሱ ጊዜ ምላሽ ሲሰጥ፣ በአንቀጽ 64(2) ሥር ያስቀመጠው ገደብ 15 ዓመት እንጂ 10 ዓመት አልነበረም፡፡ ይህ የሕግ አውጪው ምርጫ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተገቢ ነው ብሎ ያሰበው የጊዜ አድማስ ፍርድ ቤቱ በአመሳስሎሽ ከመረጠው የጊዜ ገደብ በእጅጉ የተለየ መሆኑን ያሳያልና፡፡ ከዚህም በላይ፣ የሕግ አውጪው የ15 ዓመትን ጊዜ መምረጡ የዘፈቀደ አልነበረም፡፡ ይህ ጊዜ በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1168 ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተከታታይ ይዞታ እና ግብር በመክፈል (Adverse possession) ባለሀብት ለመሆን ከሚያስፈልገው የ15 ዓመት ጊዜ ጋር በትክክል ይገጠማል፡፡ ይህ መመሳሰል በግልጽ የሚያሳየው፣ የሕግ አውጪው የመሬት ማስለቀቅ ክስ ይርጋን ከንብረት ሕጉ የይዞታ መብት አሰጣጥ ጋር በማዛመድ (Calibrating) በንብረት መብት ማዕቀፍ ውስጥ ውስጣዊ ወጥነትን መፍጠሩን ነው፡፡
ይህ ምልከታ አንድ መሠረታዊ የስነ-ዘዴ (Methodological) ጥያቄን ቁልጭ አድርጎ ያጋልጣል፡፡ ይኸውም ችሎቱ የከተማ መሬት ማስለቀቅ ክስን (ወደ አንቀጽ 1168 የ15 ዓመት ይርጋ ከሚያመላክተው) የንብረት ሕግ አሠራር ይልቅ፣ (በአንቀጽ 1845 ወደ 10 ዓመት የሚያወርደው) የውል ግዴታ ጋር ማመሳሰል ለምን መረጠ? ጥያቄው አካዳሚያዊ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በሲቪል ሎው የሕግ ሥነ-ዘዴ መሠረት፣ አንድ ፍርድ ቤት በአመሳስሎሽ ትርጓሜ የሕግ ክፍተትን ሲሞላ፣ አመሳስሎሹ መወሰድ ያለበት በጣም የጠበቀ የቅርብ ዝምድና ካለው የሕግ ማዕቀፍ (Nearest cognate legal regime)፣ ማለትም በውስጣዊ መርሆች፣ ዓላማዎች እና መዋቅር ከዋናው ጉዳይ ጋር እጅግ ከሚቀራረበው የሕግ
አካል ሊሆን እንደሚገባው ይታወቃል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት (Holding rights)፣ የሰባት ዳኞች ችሎት ራሱ እንዳመነው፣ ተጨባጭ፣ የሚመዘገቡ፣ የሚተላለፉ እና መያዣ ሊሆኑ የሚችሉ፣ ከሁሉም ስዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው (In rem) የንብረት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ከግለሰቦች ጋር ብቻ ከሚያያዙ (Personal, inter partes) እና ፍጹም የተለየ መርህ ካላቸው የውል ግዴታዎች ጋር በመደባቸው አይገናኙም፡፡ አንድ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ መሬቱን የመመለስ ግዴታ ያለበት፣ በነገር ላይ ያለን (In rem) መብት በመጣሱ እንጂ የውል ቃልን በማፍረሱ (Breach of contractual promise) አይደለም፡፡
ይህ የሕግ ባህሪ ታሳቢ ሲደረግ፣ ይበልጥ ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት (Doctrinal coherence) ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ ሊሆን የሚገባው የፍትሐብሔር ሕጉ የንብረት ድንጋጌዎች፤ በተለይም በአንቀጽ 1168 ሥር ያለው የ15 ዓመት ማዕቀፍ እንጂ የአራተኛው መጽሐፍ የውል ግዴታዎች ክፍል አልነበረም፡፡ የፍ/ህ/ቁ 1168 ድንጋጌ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለ15 ዓመት ከነግብሩ የያዘ ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው በኩል ያለውን አመክንዮ ስናይ (ከመብቱ ለተነጠቀው ሰው አኳያ)፣ ንብረቱን በሕገ-ወጥ መንገድ የተነጠቀ ሰው መብቱን ለማስመለስ የሚችለውም በተመሳሳይ የ15 ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል፡፡ ይህ ሚዛናዊ የሆነን ማዕቀፍ ይፈጥራል፡፡ በሌላ አገላለፅ ሕገ-ወጥ ያዡ መብት ለማግኘት 15 ዓመት ያስፈልገዋል፤ መብቱ የተነጠቀው ሰው ደግሞ መብቱን ለማስመለስ 15 ዓመት አለው ማለት ነው፡፡ በአንፃሩ ሰበር ችሎቱ የ10 ዓመቱን የውል ይርጋ መተግበሩ መዋቅራዊ አለመመጣጠንን (Asymmetry) የሚፈጥር ነው፡፡ ምክንያቱም ሕገ-ወጥ ያዡ ባለመብት ለመሆን አሁንም በአንቀጽ 1168 መሠረት 15 ዓመት ሲያስፈልገው፣ መብት የተነጠቀው ሰው ግን ከንብረት ሕጉ መዋቅር ጋር ምንም ዓይነት መዋቅራዊ ዝምድና በሌለው ሕግ መብቱን በ10 ዓመት ብቻ ያጣል የሚል መልዕክት አለው ማለት ነው፡፡
የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋ ማውጣቱ፣ ከላይ ለተነሳው ሂሳዊ ትንታኔ ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን የማጠናከሪያ ድጋፍ የሚሰጥ ሁኖ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግ አውጪውን ቀጣይ ውሳኔ አስቀድሞ ማወቅ ባይችልም፣ የሕግ አውጪው የወሰደው ምርጫ ግን ለመሬት ማስለቀቅ ክርክሮች ትክክለኛው የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መሠረት የፍ/ህ/ቁጥር 1168 ድንጋጌ የንብረት ሕግ አመክዮ እንጂ የቁጥር 1845 ድንጋጌ የውል ሎጂክ አለመሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የሕግ አውጪው የይርጋ ሥርዓቱን ከውል ይልቅ ከንብረት ሕግ ማዕቀፍ ጋር ማጣመሩ የሚያሳየው፣ የችሎቱ የአመሳስሎሽ ድልድይ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን (Doctrinally suboptimal) ነው፡፡
በመሆኑም አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ (ለከተማ መሬት ክስ የ10 ዓመት ይርጋን ማስቀመጡ) እና ከእርሱ በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1324/2016 (በአንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉ) መገጣጠም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግና የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ ያልታሰበ እና ከፍተኛ አንድምታ ያለው የይርጋ ጊዜ መከፈል (Bifurcation of limitation periods) ይዞ ተከስቷል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን በተጨባጭ ባለው ነባራዊ የሕግ ማዕቀፍ መሠረት፡-የይዞታ መብቱ በሕገ-ወጥ ያዥ የተጣሰበት የገጠር መሬት ባለይዞታ፣ መብቱን ለማስመለስ የሚያስችል የ15 ዓመት ጊዜ አለው (በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት) ሲኖረው ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ባለይዞታ ግን በአዲሱ የሰበር ውሳኔ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) እና 1845 ደንጋጌዎች መሠረት የ10 ዓመት ጊዜ ብቻ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
ይህን ልዩነት በጠንካራ መርህ ላይ ተመሥርቶ ለማስረዳትና አሳማኝ ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ምክንያቱም የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ይዞታ መብቶች የሚመነጩት ከአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት፤ ማለትም መሬት (የገጠርም ሆነ የከተማ) የመንግስትና የሕዝብ ንብረት መሆኑን ከሚያውጀውና የግል ባለቤትነትን ከሚከለክለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ነውና፡፡ የመብቱ ባህሪ (ከባለቤትነት ያነሰ ነገር ግን በነገር ላይ ያለ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቀው የምንችለው (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት መሆኑ) መሬቱ የሚገኘው በከተማ ክልል ውስጥ ሆነም በገጠር፣ በተጠቃሹ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ዕይታ አንድ ዓይነት ነው፡፡
የሕገ-መንግሥታዊ መሠረቱ አንድ ዓይነት ከሆነ፣ ለባለይዞታዎች የሚሰጠው የሕግ ከለላም በመርህ ደረጃ አንድ ዓይነት ሊሆን ይገባል፡፡ ለገጠር መሬት ባለይዞታ 15 ዓመት እየተሰጠ የከተማውን ባለይዞታ በ10 ዓመት መገደብ ምክንያታዊ የሆነ የፖሊሲ መሠረት (Rational policy basis) የሌለው ልዩነትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት የተቃረኑ ውሳኔዎችን በማረም ሊያመጣው የፈለገውን የሕግ ወጥነት (Doctrinal consistency) የሚሸረሽር ነው፡፡
አንድ ሰው የከተማ እና የገጠር መሬት የተለያዩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳላቸው፣ በተለያዩ የቁጥጥር ሥርዓቶች እንደሚመሩ፣ እና የክርክሮቹም ተጨባጭ ሁኔታዎች እንደሚለያዩ በማንሳት፣ ይህ ልዩነት የተለያየ የይርጋ ጊዜን ተገባራዊ ማድረግ እንደሚችል ይሞግት ይሆን ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ መከራከሪያ፣ የከተማ መሬት የይዞታ ሥርዓት ከገጠሩ ይበልጥ መደበኛ፣ በሰነድ የተደገፈ፣ እና በአስተዳደር ሥርዓት የተደራጀ ነው የሚለውን መደበኛ አስተሳሰብ ወደ ጎን ትቶ፣ የከተማ ባለይዞታ መብቱን ለመጠየቅ ከገጠሩ ባለይዞታ ያነሰ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባው ለምንድን ነው? የሚለውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እንዲያውም፣ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ያለው ሰፊ ኢ-መደበኛነት እና የሰነድ አያያዝ ክፍተት፣ መረጃዎች በገጠሩ አካባቢ ቶሎ ስለሚጠፉ፣ ለገጠር መሬት ክስ ከከተማው ያጠረ (ያልረዘመ) የይርጋ ጊዜ ሊያስፈልግ ይችላል ወደሚል ንድፈ-ሐሳባዊ መከራከሪያ ሊያመራን ይችላል፡፡ አሁን በህጉና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም የተወለደው ዥንጉርጉር ሥርዓት ማለትም ገጠር 15 ዓመት፣ የከተማ 10 ዓመት ይርጋ ጊዜ እንዲሆን የተደረገበት ኩነት ይህንን ሎጂክ/አመክንዮ/ የተገላቢጦሽ ያደርገዋል፡፡
7.4 የክፍል 7 ጥማቂ
የሰባት ዳኞች ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) ያስተናገደበት መንገድ እንከን የለሽ (Flawless) ነው ሊባል የሚችል ቢሆንም ችሎቱ ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) የነበረውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር፣ የሕግ ክፍተቱን በወቅቱ በነበሩ የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች በመሙላት፣ እና ገና ፀድቆ ላልወጣ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1324/2016) ወደኋላ ተመልሶ የሚሠራ የተፈፃሚነት ኃይል ላለመስጠት መወሰኑ በሥነ-ሥርዓትም ሆነ በመሰረታዊ ህግ ይዘት ችግር የለውም፡፡ በወቅቱ ላልነበረ ሕግ አልተገበርክም ተብሎ ችሎቱን መተቸት የሚቻልበት የህግ አግባብ የለም፡፡ እንዲሁም የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 የአንቀጽ 65(1)
የሽግግር ድንጋጌ ራሱ አዲሱ ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ እንደማይሠራ በማረጋገጥ ይህንን ያጠናክረዋል፡፡ ሆኖም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ የሕግ አውጪው የገጠር መሬት ይርጋን የ15 ዓመት የይዞታ (Adverse possession) ሥርዓት ከሚደነግገው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1168 ጋር ማጣመሩ፣ ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተፈጥሯዊ እና ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ የሚገኘው በንብረት ሕጉ ማዕቀፍ ውስጥ እንጂ በውል ግዴታዎች ማዕቀፍ ውስጥ አለመሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ ይገኛል ችሎቱ ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 ይልቅ አንቀጽ 1845 ድንጋጌን መምረጡ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ ውስጥ ሁለት የተምታታ እና የሚጋጭ ሥርዓት (Dual and conflicting regime) ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ መሠረታቸው እና የመብታቸው የሕግ ባህሪ አንድ ዓይነት ቢሆንም፣ የከተማ መሬት ክስ በ10 ዓመት፣ የገጠር መሬት ክስ ደግሞ በ15 ዓመት እንዲታገድ ማድረግ የህግ ባለሙያውንም ሆነ ሌላውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያሳምን ሊሆን አይችልም፡፡
ይህ ሥርዓታዊ አለመጣጣም ከሁለት በአንዱ መንገድ ዕልባት እስካላገኘ ድረስ የኢትዮጵያን የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገና የአስገዳጅ ህግ ትርጉም ወጥነት ግብ በፅኑ መፈተኑን የሚይቀጥል መሆኑ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት ለከተማ መሬት የሰጠውን አስገዳጅ ትርጉም ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 መሰረተ ሃሳብና ከተገቢው የህግ አተረጓጎም ስልት አንፃር በድጋሚ በመገምገም በቅርብ ጊዜ በወጣው የገጠር መሬት ህግ ውስጥ ከተደነገገው የ15 ዓመት ማዕቀፍ ጋር ያጣጥመዋል፣ አለበለዚያ ደግሞ የሕግ አውጪው (ፓርላማው) ከገጠር መሬት ሥርዓት ጋር የተናበበ የይርጋ ድንጋጌን ያካተተ አጠቃላይ የከተማ መሬት አስተዳደር አዋጅ ያወጣል፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከላይ ከተጠቀሰው ህገ መንግስቱ ጥበቃ አንፃር አይቶ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ሊሰጠበት ይችላል፡፡ ይህ የእርምት እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ለአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መብት፤ በከተማ 10 ዓመት፣ በገጠር 15 ዓመት ሊሆን ይገባል ተብሎ የተከፋፈለው የይርጋ ጊዜ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ ያልተፈታ ፅንሰ-ሐሳባዊ መዛባት (Doctrinal anomaly) ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በችሎቱ ውሳኔ እንደድክመት ሊነሳ የሚችል ተገቢ ምልክታ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ማጠቃለያ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ ተቃርኖ ያለባቸውን አስገዳጅ የህግ ትርጉሞችን ከማረቅና የስርዓቱን ወጥነትና ተገማችነት ከማስፈን አንፃ እጅግ መሠረታዊ እና አስፈላጊ ቢሆንም በአገሪቱ የንብረት እና የመሬት ሕግ ስነ ህግ ላይ ህገ መንግስታዊ መሰረትን ባልተጎናፀፈ አመክንዮ ተመሳሳይ ጥበቃ ያለውን የባለይዞታነት መብት በተለያዩ የይርጋ ጊዜያት እንዲገዙ ስርዓት ያበጀ በመሆኑ አከራካሪነቱ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ውሳኔው በቀድሞ አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል የነበረውን ጥልቅ ተቃርኖ ሕገ-መንግሥታዊ መሠረትን እና የፍትሐብሔር ሕግን አግባብነት ያላቸውን መርሆች በሚገባ በመመርመር ተገቢውን የዳኝነት ጥበብ በመጠቀም ለመፈታት የተቻለበት መሆኑ ይታመናል፡፡ በተለይም የባለቤትነት መብትን (Ownership) ከይዞታ መብት (Holding rights) በሚገባ በመለየት፣ ለባለቤትነት የተፈጠሩ የሕግ ማዕቀፎችን የግል የመሬት ባለቤትነት በማይፈቅድ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በቀጥታ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ የሕግ ትርጉም በኢትዮጵያ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክሮች ላይ ፅንሰ-ሐሳባዊ ጥራትን፣ ሥርዓታዊ ወጥነትን እና ተገማችነትን በማምጣት ወደፊት ለሚነሱ የንብረት ሕግ ክርክሮች ጠንካራ መሠረት የሚጥል አንፀባራቂ የዳኝነት አሻራ ነው ተብሎ ቢውሰድ ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ሆኖም ከላይ በክፍል 7 ስር በሰፊው እንደተብራራው ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ ስለሆነም ችሎቱ በራሱ አነሳሽነት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይስ የፌዴፌሬሽን ምክር ቤት? ትክክለኛውን መስመስር ይለዩ ይሆን? በዚህ ነጥብ ላይ ሁላችንንም ሊያስተምር የሚችል የምርምር ስራ ወይም የውሳኔ ትችት እይታ በዘርፉ በበቁ በአወቁ የአገራችን ምሁራን ሊከናወን እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
አበቃ!!
ተፃፈ በአልማው ወሌ
መጋቢት 04 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ማስታወሻ፦ ፅሁፉ ጥብቅ የምርምር ዘዴ በመከተል ያልተከናወነ መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅሁ ለወደፊቱ ግን በዚሁ አርዕስትና ተያያዥ የህግ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ከሆነ ሙያዊ እና አካዳሚያዊ ደረጃውን የጠበቀ ስራ ይዠ ለመቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ማናቸውም ስህተቶች የራሴው መሆናቸው እንዲታወቅልኝም እፈልጋለሁ፡፡
https://www.facebook.com/s...

8 months ago
አዲሱ የንግድ ህግ ለኢትዮጵያ ንግድ እድገት ያለው ፋይዳ
የንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
0929101037,0983337690
1. መግቢያ
#ethiopia | በ1952 ዓ.ም የወጣው ነባሩ የንግድ ህግ አዲሱ የንግድ ህግ 2013 ዓ.ም እስኪወጣ ድረስ የኢትዮጲያ የንግድ ስረአትን መስመር በማሥያዝ ረገድ ቀላል የማይባል ሚና የነበረው ሲሆን በዚህም ነጋዴ ማለት ምን ፤ ምን የሚሰራ ስለመሆኑ በነባሩ ንግድ ህግ አንቀጽ 5 ላይ የተቀመጠ ከመሆነኑም ባሻግር በግል እና በማህበር ወይም በመደራጀት እንዴት ሊሰራ እንደሚችል አወቃቀሩን (structures), አመሰራረቱን (formations), መብት ግዴታዎች አጠቃላይ መደንገጋቸውን ማስታወስ ይቻላል፡፡1 ሲሆን በተነጻጻሪም በዚህ በአዲሱ የንግድ ህግም በዚህ ይዘት የተደገገ ሲሆን ተሻሽሎ የተቀመጡ ድንጋጌዎችም ስፍረውበታል፡፡
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውም አዲሱ የንግድ ህግ የወጣበትን ምክንያት ማሰስ እና እነዚህስ ልዩነቶች ምንድን ናቸው፤ ተሻሽሎ በመምጣቱ ይዞ የመጣው ፋይዳ ምንድ ነው የሚሉትን ነጥቦች በአጭሩ ለመዳሰስ ነው፡፡
2. አዲሱ የንግድ ህግ የወጣበት ምክንያት
ከላይ በመግቢያው ለመግለጽ እንደሞከርኩት በንጉሱ አሰተዳደር የኢኮኖሚእድገትን እና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋጥ ለንግድ ስራ ጽኑ የህግ መሰረት መጣል የግድ አስፈላጊ በመሆኑ በ1952 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጲያ የንግድ ህግ ለዚህ ዓላማ ከግብ መድረስ አስፈላጊውን መደላደል ለማድረግ
አንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ይሁን እንጂ ህጉ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ስልሳ አመታት ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ የንግድ እና የመዋእለን ንዋይ ፍሰት እጅግ ከመጨመራቸውም በላይ እያደር አለምአቀፋዊ ባህሪ እየተላበሱ መጥተዋል፡፡
እነዚህ ክስተቶች በተለይ ኢትዮጲያ ገበያ መር ስረአት መከተል ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ህጉ እንዲከለስ ምክነንያትን የፈጠረ ሲሆን ከዚህም የተነሳ በህጉ ውስጥ አንዳንድ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡ ከእነዚህ አለምአቀፍዊ የንግድ እንቅስቃሴ መስተጋብር
እነዲሁም ኢትዮፒያ አሁን ካለችበት ገበያመር የንግድ እንቅስቃሴ አንጻር ለአፈጻጸም የማይመቹ እና ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጡ ድንጋጌዎቸች እንዳሉ ተስተውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ኢትዮጲያ ለደረሰችበት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ደረጃ ህጉ የተሟላ አለመሆኑን ድምዳሜ ላይ ተደርስዋል፡፡
ስለዚህ የኢትዮጲያ አለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስፋፈት፤የነጋዴዎችን፤የባለሃብቶችን እና በህጉ ጥቅማቸው በቀጥታ የሚነካ ባለድርሻ አካላት መብቶችን በሚዛናዊ ሁኔታ ለማስተናገድ ብሎም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ አዲሱን የንግድ ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝትዋል፡፡
3. በአዲሱ ንግድ ህግ የተካተቱ ነጥቦች
በዚህ ክፍል በአዲሱ ንግድ ማለትም በአዋጅ ቁጥር 1243/13 የተካተቱትን ጉዳዮች ከምክንያታቸው ጭምር አጠር አጠር ባለ መንገድ አስቀምጠናል።
3.1. ኀላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር
ኀላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር በአዲሱ የንግድ ህግ ከተካተቱት አዳዲሰ የንግድ ማህበራት አንዱ
ነው፡፡ ሥያሜው ዕንደሚያመለክተው ይህ የሽርክና ማህበር ውስጥ ያ አባላት በሙሉ ለማህበሩ ዕዳ ያለባቸው ኃላፊነት የተወሰነ ሲሆን ይህም በንግድ ህጉ አንቀጽ 221 ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ይሀውም ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰወች የሙያና ለሙያው ደጋፊ ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት
የሚያቐቐሙት ሲሆን የማህበርተኞች ኀላፊነት በመዋጮቹ የተወሰነ የንግድ ማህበር ነው፡፡ ለዚህ ማህበር አላማ፣ የሙያ አገልግሎት ማለት በህግ አግባብ ባለው አካል በተሰጠ የሙያ ፍቃድ መሰረት የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
3.2. ባለአንድ አባል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ
ይህ ኩባንያ ወይም ማህበር ከ534 እስከ 545 ድረስ ባሉት አዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የገባ ሲሆን በአንቀጽ 534 ላይ አእንደተቀመጠው ማህበር ሲል ያሰቀመጠ ቢሆንም በአንድ ሰው የሚቐቐም ነው፡፡ ይህ ማህበር የተካተተበት አላማም በማህበሩ አባል አንድ ብቻ ሊሆን በሚገደድበት ጊዜ ከንግድ ማህበሩ ባህርይ አንጻር በዚህ አግባብ ተዘጋጅቶ የንግድ እንቅስቀሴውን ለማሰቀጠል ሲባል የተመሰረተ መሆኑን የሚሰማሙበት ነው፡፡
3.3. አመሰራረት
በነባሩ የንግድ ህግ የንግድ ማህበራትን ለመመስረት የመመስረጫ እና የመተዳደርያ ጽሁፍ የሚያስፈልግ ሲሆን ነገር ግን በአዲሱ የንግድ ህግ ማህበር የመመስረቻ ጽሁፍ ብጫ አስፈላጊ መሆኑን የተደነገገ ነው፡፡ በህብረት ሽርክና ማህበር አንቀጽ 185፣የአክስዮን ማህበር አንቀጽ 255 ፣
ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር በተመለከተ አንቀጽ 500 ላይ የተደነገገ ነው፡፡ በአጠቃላይ ለንግድ ማህበራት አመሰራረት የመተዳደርያ ደንብን በማስቀረት የመመስረቻ ጽሁፍ በቂ ሲሆን በዚህ ላይ
የንግድ ማህበሩን አላማ ፤ ጥቅም፤መብት፤ግዴታ የመሳሰሉት ሰፋ ያለ ዝርዝር ጉዳዮች የሚሰፍሩበት ነው፡፡
3.4. የአነስተኛ ባለአክስኖች መብት እና ጥበቃ
ቀደም ሲል የነበረው የኢትዮጲያ ንግድ ህግ ለአነስተኛ ባለአክስዮኖች የሚያደርገው ጥበቃ የተለያየ
ጥናት እነንደሚያሳየው ከሌሎች ሀገሮች አንጻር በአማካይ አነስተኛ ሲሆን በአዲሱ ህግ ግን ብዙ ማሻሻዮች የተደረገ ነው፡፡5 ይሀውም አነስተኛ ባለአክስዮን ከቦርድ፣ከከፍተኛ ድርሻ ካላቸው
ባለአክስዮን የሚደርስባቸውን ጭቆና ለመጠበቅ ሲባል መፍቴዎች ተቀምጠዋል፡፡ ይሀውም በአዲሱ ንግድ ህግ አንቀጽ 276/1/፣363፣383፣ 343፣355-361፣400፣402(2)፣ 403፣451(1) እና በመሳሰሉት የተቀመጠ ነው፡፡
3.5. የአክስዮን መመዝገብ
በአዲሱ የንግደ ህግ አንቀጽ 267/1/ አክስዮን በባለአክስዮኑ ስም መመዝገብ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ የቀድሞው የንግድ ህግ ግን በአንቀጽ 325 በአመጭው ጭምር ሊመዘገብ እንደሚችል በአማራጭ ያስቀምጣል፡፡ የአሁን ንግድ ህግ አክሥዮን ቀድሞ ይህ ህግ ከመውጣቱ በፊት ለአምጪው በሚል የወጡ አክስዮኖች ባለቤት የሆነ ቢኖርም ይህ ህግ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት አመት ውስጥ አክስዮኖቹ ስም በሚል መመዝገብ አለበት፡፡
ይህ ሀገራችን
የአክስዮኖችን ሽያጭ በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/13 እና በሌሎች የተሻሸሉ የባንክ፤የፋይናነስ አዋጆች፤ደንቦች፤መመርያዎች ከፍተኛ የህግ እና የተቐማት አወቃቀር (legal and institutional framework) እየተበጀ ሲሆን አዲሱ የንግድ ህጉም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመዋእለሰነዶች ገበያ ሽያጭ (security exchange market) ፣ የአክስዮን ሽያጭ ማሰተላለፍ፣ ጋገር ጠያይዞ ባለአክስዮኖች በገበያ ላይ ጥበቃ እንዲኖራቸው ፍትሀዊ፣ብቁ እና የገበያ ግልጸኝነት እንዲፈጠር አዲሱ የንግድ ሕግ ፣ ከካፒታል አዋጁ በተጨማሪ ከፍተኛ መደላደልን ለአክስዮን ገበያ አመቻችትዋል፡፡
3.6. ሆለዲነግ ካምፓኒ በነግድ ስራ እንዲሰራ ስለመፈቀዱ
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 ስር በተመለከቱት ስራዎች ላይ በመሰማራት በቀጥታ ራሱ ምርትን የንግድ ማህበራት ውሥጥ መዋእለ ንዋይ በማፈሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ወይም ሆለዲነግ
ካምፓኒ እንደ ነጋዴ እንደሚቆጠር አዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 9 ከማመልከቱም በተጨማሪ በቀጠታ ምርትና አገልግሎተ ማቅረብ ይችላል፡፡
3.7. ተራ የሽርክና ማህበር በአዲሱ ህግ ያልተካተተ መሆኑ
በነባሩ የንግድ ህግ ሁለተኛ መጽሀፉ ላይ በሰፊው የተቀመጠ ቢሆንም በንግድ ስራ ውስጥ የማይሳተፍ መሆኑን በግልጽ በነባር ህጉ የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ከሆነ አዲሱ ህግ ከዚህ አመክን
በመነሳት ይመስል ከእነአካቴው ያወጣው ሲሆን ይህ በነባሩ ህግ በመቀመጡ ምክንያት ለሚፈጠሩ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ነው፡፡
3.8. በንግድ ድረጅቶች መካከል የሚፈጠር ዝምድና
በአዲሱ የንግድ ህግ የነግድ ማህበራት እርስ በእርሳቸው የተገዛዙ ከሆነ አንዱ አንድኛውን ከገዛ ፣ እናት(holding)፣ ተቀጽላ (subsidiary )፤group የተዛመዱ(Affiliated) ማህበራት ስያሜ የሚሰጣቸው ሲሆን በአንቀጽ 550-577 የኩባንያዎችን ይዘት፣አቋም፣ስልጣን መብት፣ግዴታ፤ከድምጽ ጋር ተያይዞ ያለው አሰራር እና ውጤት፣ የስራ አመራር ፣ተጠያቂነት
አሰራር ፣ ስለመወሀድ እና ውጤቱ የመሳሰሉት በተመለከተም በዝርዝር የተቀመጠ ነው፡፡
3.9. ማህበራትን መልሶ የማደራጀት ስራ በአዲሱ ህግ የተካተተ መሆኑ
በአዲሱ የንግድ ህግ ሶስተኛ መጽሀፍ ፤ ርእስ አንድ፣ምእራፍ አንድ አንቀጽ 588 ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው የአንድን ማህበር እዳ መልሶ ማዋቀር ጽንሰ ሃሳብ ላይ በሰፊው የተቃኘ ስነስረአቱም
እንዴት ሊሆን እንደሚችልም የተብራራ ሲሆን በተከታዮች ድንጋጌ ላይም የተብራራ ነው፡፡ የእነዚህ ድንጋጌዎች አላማቸው ቀልጣፋና ውጠየታማ በሆነ ጊዜውን ጠብቆ በሚከናወን ስነስረአት
አማካኝነት የኢኮኖሚ መረጋገትን ማሰፋፋት፣የንብረቱን ዋጋ ከፍ ማድረግ እና የህግ ተገማችነትንና ግልጸኝነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ገንዘብ ጠያቂዎችም በተወሰነ አብላጫ ድምጽ የሚፈቅዱ ከሆነ መልሶ በማደራጀት እቅድ አማካይነት ገንዘብ ጠያቂዎችን ተተቃሚ በሚያደርግ መልኩ የባለእዳዎችን እዳዎች እንዲሁም የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን በጠበቀ መልኩ መልሶ በማደራጀት የንግድ ስራ
መሸጥ ነው፡፡
3.10. ለማህበር ቦርድ አባላትነት የአክስዮን ድርሻ የሌላቸውን የሚፈቅድ መሆኑን
በቀድሞው የንግድ ህግ የቦርድ አባላት ከባለአክስዮን ድርሻ ብቻ ሲሆን በአዲሱ ግን ባለ ድርሻ ባይሆኑም እስከ አንድ ሶስተኛው ድረስ የቦርድ አባላቱን ድርሻ መያዝ ይችላሉ፡፡ ይህ ቦርድ ከፍተኛ
ሙያ ባላቸው ፤ልምድ ፣እውቀት ባላቸው የቦረድ ዳይርክተር አባላት የተቀናጀ እና የህጉን አላማ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡አንቀጽ 296/2/ ላይ የተደነገገ ነው፡፡
3.11. በአዲሱ የንግድ ህግ ነጋዴ የሚያስብል የንግድ ስራዎች መጨመር
በቀድሞወ ህግ አንቀጽ 5 ላይ 21 የንግድ ስራዎች ላ የሚሰማራ ነጋዴ የሚያስብል ሲሆን በአዲሱ ግን በተጨማሪነት በማካተት 37 የደረሰ ሲሆን የቀብር ስራ እና ተያያዥነት ስራዎች የሚሰሩ እነደ
አንድ የንግድ ስራ የተካተተ ነው፡፡
4. ማጠቃለያ
ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት በቂ የሆነ የንግድ ህግ ማእቀፍ እና የሚመጥኑ ወይም በቂ የሆነ የንግድ ተቋመት መኖር እጅጉን በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ በቂ የህግ ማዕቀፍ ኖሮ ህግን ወደ
ተግባር ሊቀይር የሚችል በህጎች የተሰናዳ ተቋም፣ አስተዳደር ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጲያ ሃገራችን በገበያ መር ስረአት መመራት ከጀመረች ሁለት አስር አመታትን አልፋለች፡፡ ይሁን እንጂ ተስፋ ሰጪ እና በጊዜው ዘመናዊ የሆኑ የ1952 ዓ.ም የንግድ ህግ ትልቁ የሀገራችን የጀርባ አጥንት የሆነ የንግድ ህግ ማእቀፍ ቢሆንም ሀገራችን አሁን ካላት የንግድ እንቅስቃሴ እድገት ፍላጎት፤የአኮኖሚ እድገት ፣ አለም አቀፍ የገበያ ትስስር ፣ የዜጎችን መሰረታዊ የአኮኖሚ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ከአለምአቀፍ የንግድ ፣ የገንዘብ ተቋማት ህጎች እና የፋይናንስ ስረአት ጋር በማጣጣም የዳበረ ኢኮኖሚ ለሀገር እድገት ለማስመዝገብ ነባሩ የንግድ ህግ ክፍትት ያለበት መሆኑን በመረዳት ይህ አዲሱ ህግ እንደዲሻሻል አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት አዲሱ የንግድ ህግ 1243/2013 ወጥቶ በስራ ለይ ውሏል፡፡ይህ ብቻ በቂ ባለመሆኑ የአኮኖሚ እድገቱን ለማሳለጥ፤ የንግድ ስረአቱን
ለማዘመን ሌሎች የባንክ፤የፋይናንስ፣የካፒታልገበያ ዐዋጅ እነዚህን የሚያስፈጽሙ ደንቦች፣መመሪያዎች ወጥተው ወደ የሚጠበቅባቸው ስራ ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ ሃብት ይዞ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 አዲሱ የንግድ ህግ በወጣበት አመት የወጣ ሲሆን
በ2017 ዓ.ም የንግድ ስራውን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብሳሪነት የተቋቋማለትን አላማ በማብሰር ኢትዮጲያ ይህን ትልቅ የገበያ ሲሳይ ተግባራዊ ለማድረግ የምትችል
መሆኑን ገልጸው በዚህ በካፒታል አዋጅ ስር እንደ ዋና ፈርጅ ስራ የሚቆጠረውን የኢትዮጲያ የሰነዶች መዋለ ነዋይ ገበያ ጥር/2017 ዓ.ም በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን አዲሱ የንግድ አዋጅ መውጣት ለዚህ በር እና መሰረታዊ ነው፡፡
ዋቢ መጽሀፍት
1. የኢትዮጲያ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013፣የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣27ኛ ዓመት ቁጥር 23፣አዲሰአበባ፣ሚያዚያ 4 ቀን 2013
2. የኢትዮጲያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የንግድ ሕግ (ነጋሪት ጋዜጣ፣በተለየ የወጣ፣19ኛኣመት፣ቁጥር 3/1952
ዓ.ም)
3. ፈቃዱ ጴጥሮስ፣የኢትዮጲያ ኩባንያ ህግ፣2014 (3ኛ እትም)
4. የካፒታለ ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 (የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣27ኛ ዓመት ቁጥር 33፤2013፤2013
ዓ.ም.)
5. የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017
6. የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008(የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣22ኛ ዓመት ቁጥር 101፣ሀምሌ
29 ቀን 2002 ዓ.ም)

🏗️ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ ንግድ ላይ መሰማራት ለምትፈልጉ ጠቃሚ መረጃዎች
በኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የከተማ ውበትና የሪል እስቴት ዘርፍ በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት የግንባታ መሣሪያዎች ኪራይ (Special Equipment Rental) ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኝና አስተማማኝ የኢንቨስትመንት አማራጭ ሆኗል። ይህ ዘርፍ በተለይ ለጀማሪ ባለሀብቶችና በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሰፊ የገበያ ዕድል ይዟል።
1. የገበያ ጥናትና ፍላጎትን መለየት (The Power of Demand)
የማንኛውም ቢዝነስ ስኬት የሚጀምረው ከጥልቅ የገበያ ጥናት ነው። በኢትዮጵያ አውድ ሁሉንም መሣሪያዎች በአንዴ ከመግዛት ይልቅ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን መለየት የቀዳሚነት ተግባር ነው።
የትኞቹ መሣሪያዎች ይፈለጋሉ? በአሁኑ ወቅት እንደ ኤክስካቫተር (Excavator)፣ ዶዘር (Dozer)፣ ግሬደር (Grader) እና ሮለር (Roller) ያሉ መሣሪያዎች ለመንገድ ሥራና ለከርሰ ምድር ቁፋሮ በስፋት ይፈለጋሉ።
አካባቢያዊ ፍላጎት፦ ለምሳሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሪል እስቴት ግንባታ ስለበዛ ‘ሎደር’ እና ‘ኤክስካቫተር’ ሲፈለጉ፣ በገጠር የግብርና ልማት አካባቢዎች ደግሞ ‘ዶዘር’ እና ‘ትራክተር’ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።
ወቅታዊነት፦ በኢትዮጵያ ክረምት ወቅት የመንገድ ሥራዎች ስለሚቀዘቅዙ የኪራይ ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል። ይህንን አስቀድሞ ማወቅ ለፋይናንስ አስተዳደርዎ ወሳኝ ነው።
2. የመሣሪያዎች ግዢና የጥራት ደረጃ (Strategic Sourcing)
መሣሪያዎችን ለመግዛት ሲታሰብ የጥራትና የመለዋወጫ አቅርቦትን ማመዛዘን ያስፈልጋል።
አዲስ ወይስ ያገለገሉ? አዳዲስ መሣሪያዎች (ከቻይና እንደ Sany ወይም XCMG፣ ከአውሮፓ እንደ CAT ወይም Komatsu) አስተማማኝ ናቸው። ነገር ግን ከፍተኛ ካፒታል ይጠይቃሉ። ያገለገሉ መሣሪያዎችን ከዱባይ ወይም ከአውሮፓ ማስገባት ለጀማሪዎች ተመራጭ ቢሆንም፣ የመሣሪያውን የሥራ ሰዓት (Working Hours) እና የሞተር ጤንነት በባለሙያ ማስመርመር ግድ ይላል።
የብራንድ ምርጫ፦ በኢትዮጵያ ገበያ መለዋወጫቸው በቀላሉ የሚገኝ ብራንዶችን መምረጥ (ለምሳሌ CAT እና Komatsu) ለወደፊት ጥገናዎ ወሳኝ ነው።
3. የሰለጠነ የሰው ኃይል (Expert Operators)
መሣሪያው የቱንም ያህል ዘመናዊ ቢሆን፣ ብቁ ኦፕሬተር ከሌለው ገቢው ሊቀንስ ይችላል።
ጥንቃቄ የተሞላበት ቅጥር፦ ኦፕሬተሩ የመሣሪያውን ደህንነት የሚጠብቅ፣ ነዳጅ የሚቆጥብና በስራ ቦታ ካሉ መሃንዲሶች ጋር ተግባብቶ የሚሰራ መሆን አለበት።
ጥገናና ክትትል፦ ኦፕሬተሮች በየቀኑ የዘይትና የውሃ ፍተሻ እንዲያደርጉ ማሰልጠን የመሣሪያውን ዕድሜ ያራዝመዋል።
4. የፋይናንስ አስተዳደርና የኪራይ ዋጋ (Financial Planning)
በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበትና የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ በኪራይ ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው።
ግምታዊ የኪራይ ዋጋ (2018 ዓ.ም/2026 እ.ኤ.አ):
ኤክስካቫተር፦ በቀን ከ 18,000 - 30,000 ብር (እንደ ቁፋሮው ጥልቀትና እንደ መሬቱ ሁኔታ)።
ሎደር፦ በሰዓት ከ 1,500 - 2,800 ብር።
ዶዘር፦ በሰዓት ከ 2,500 - 4,500 ብር።
የኪራይ አይነቶች፦
Dry Lease (በደረቁ): ደንበኛው ነዳጅ ያቀርባል፣ እርስዎ መሣሪያና ኦፕሬተር ብቻ። ይህ ለባለቤቱ የተሻለ የትርፍ እርግጠኝነት ይሰጣል።
Wet Lease (ከነነዳጁ): ነዳጁን እርስዎ ያቀርባሉ። ይህ ብዙ ጊዜ ለአጭር ቀናት ስራዎች ይውላል።
5. የጥገና እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም
የመለዋወጫ ክምችት፦ እንደ ፊልተሮች፣ ሃይድሮሊክ ኦይል እና ትናንሽ ቦልቶችን አስቀድሞ መያዝ መሣሪያው ለጥቃቅን ብልሽት ስራ እንዳያቆም ይረዳል።
GPS መከታተያ፦ በኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ መሣሪያዎች ካሉበት ቦታ ሳይንቀሳቀሱ ነዳጅ ሲሰረቅ ወይም ኦፕሬተሮች ከስራ ሰዓት ውጭ በድብቅ ሲያሰሩ ይስተዋላል። የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ መግጠም ይህንን ስርቆት 100% ይከላከላል።
6. የሕግ ማዕቀፍና የኪራይ ውል (Legal & Security)
በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ጠንካራ የኪራይ ውል መኖሩ ለንብረትዎ ዋስትና ነው።
Mobilization (የመጓጓዣ ወጪ): መሣሪያውን ወደ ስራ ቦታ ለመውሰድና ለመመለስ የሚወጣውን ወጪ (ለምሳሌ የሎውቤድ ኪራይ) ደንበኛው እንደሚሸፍን በግልጽ ማስፈር።
ኢንሹራንስ፦ መሣሪያው በስራ ላይ እያለ አደጋ ቢደርስበት ወይም በድንገተኛ አደጋ ቢወድም የሚከፍል አጠቃላይ የመድን ዋስትና (Comprehensive Insurance) መግባት ግዴታ ነው።
የስራ ሰዓት አቆጣጠር፦ በቀን 8 ሰዓት ዝቅተኛ የሥራ ሰዓት (Minimum Hours) ተብሎ ውል መታሰር አለበት። መሣሪያው በደንበኛው ጥፋት ስራ ከቆመ (Idle Time) ደንበኛው ግማሽ ዋጋ ወይም ሙሉ ዋጋ እንዲከፍል በውል መስማማት ብልህነት ነው።
7. የገበያ ትስስርና ማስታወቂያ (Networking)
ዲጂታል ማርኬቲንግ፦ በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌግራም ቻናሎች፣ ፌስቡክ ግሩፖች እና እንደ 2Merkato ያሉ ድረ-ገጾች ላይ መገኘት ደንበኛን በቀላሉ ለማግኘት ይረዳል።
ከኮንትራክተሮች ጋር መወዳጀት፦ ከትላልቅ ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት መፍጠር መሣሪያዎ ዓመቱን ሙሉ ስራ እንዳይፈታ ያደርጋል።
ማጠቃለያ
የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ ቢዝነስ በትክክል ከተመራና የቴክኖሎጂ ቁጥጥር (GPS) ከተጨመረበት፣ በኢትዮጵያ ካሉ ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኙ የንግድ ዘርፎች ቀዳሚው ነው። ዋናው ቁልፍ መሣሪያውን በጥሩ ሁኔታ መያዝ እና ታማኝ ኦፕሬተር መቅጠር ነው።

የጋምቤላው ነዳጅ ቦንጋ ምን ያደርጋል? አሽከርካሪው እና የ5.2 ሚሊየን ብር ነዳጅ ውሳኔ!
ከጅቡቲ ተነስቶ ጋምቤላ መድረስ የነበረበት 46,649 ሊትር ናፍጣ፣ ባልተፈቀደለት የጅማ ዞን መስመር ወደ ቦንጋ ሲጓዝ እጅ ከፍንጅ ተያዘ!
ጉዳዩ ምንድን ነው?
አሽከርካሪ ክፍሌ ዋቁማ የተባለ ግለሰብ ግምቱ 5,207,902 ብር የሆነ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ፣ ህጋዊ መስመሩን በመተው በሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ በኩል አቋርጦ ሲሄድ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሏል።
⚖️ የህግ እይታ (Legal Insight)
በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት፣ ስትራቴጂካዊ የሆኑ ምርቶች (እንደ ነዳጅ) የተፈቀደላቸውን መስመር ስተው መገኘታቸው እንደ ኮንትሮባንድ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እንደተቃጣ ወንጀል ይቆጠራል። ይህም ንብረቱ እንዲወረስና አሽከርካሪው በወንጀል እንዲቀጣ ያደርጋል።
ፍርድ ቤቱ ምን ወሰነ?
የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ትናንት በዋለው ችሎት፦
አሽከርካሪው በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ፣
3,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍል፣
ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ነዳጅ ደግሞ ለጥቅም ሳይውል ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ወስኗል።
https://t.me/Ethio_Zena23

9 months ago
የሕልም ነጋዴዎችና የባዶ ሜዳ ስቃይ፡ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት ቀውስና የፍትሕ ፍለጋ ጉዞ
በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ዘርፍ ታሪክ ውስጥ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የታየው ዕድገት በአንድ በኩል የአገሪቱን ገጽታ ሲቀይር፣ በሌላ በኩል ግን የሺዎችን ሕይወት የቀጠፈ የኢኮኖሚ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል።
ለብዙዎች "ቤት" ማለት መጠለያ ብቻ ሳይሆን የዕድሜ ልክ ጥሪት፣ የልጆች መተማመኛ እና የድካም ውጤት ነው። ሆኖም ይህ ትልቅ ተስፋ በሕገ-ወጥ አልሚዎች እጅ ወድቆ ሲቀጭ ማየት ልብ የሚሰብር ክስተት ሆኗል።
ዛሬ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር የተፈራረመው ስምምነት፣ ይህንን የቆሰለ ተስፋ ለመጠገን የተደረገ ሙከራ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ450 በላይ የሪል ስቴት አልሚዎች እንደሚንቀሳቀሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ከእነዚህ ውስጥ ፕሮጀክቶቻቸውን በገቡት ቃል መሠረት በጥራትና በጊዜ የሚያስረክቡት ከ20% እንደማይበልጡ ይገመታል። ይህ ማለት ከ80% በላይ የሚሆኑ ገዢዎች ለከፍተኛ መጉላላት፣ ለተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ ወይም ለፍጹም ክህደት የተጋለጡ ናቸው። ይህ ዳታ የሚያሳየው ዘርፉ በምን ያህል የውጥንቅጥ አዘቅት ውስጥ እንደሚገኝና በአልሚና በገዢ መካከል ያለው እምነት ደረጃ መውረዱን ነው።
አዲሱ ስምምነት በዋናነት ትኩረት ያደረገው አለመግባባቶችን በግልግል ዳኝነት (Arbitration) መፍታት ላይ ነው። ይህ አሠራር በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚባክነውን ከ3 እስከ 7 ዓመታት የሚፈጅ የሙግት ጊዜ ወደ ጥቂት ወራት ዝቅ ሊያደርገው ይችላል። በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚስተዋለው የዳኞች የቴክኒክ ዕውቀት ማነስ እና የፋይሎች መከመር፣ ብዙ ገዢዎች መብታቸውን ተስፋ ቆርጠው እንዲተዉ ሲያደርጋቸው ቆይቷል። የግልግል ዳኝነት ግን በዘርፉ ዕውቀት ባላቸው ባለሙያዎች ስለሚመራ ሚዛናዊ ውሳኔ የመስጠት ዕድሉ ሰፊ ነው።
ከሌላ አገር ተሞክሮ ጋር ስናነጻጽረው፣ ለምሳሌ በጎረቤት አገር ኬንያ የሪል ስቴት ዘርፉን ለመቆጣጠር የወጣው ሕግና የተቋቋሙት የግልግል ችሎቶች በዘርፉ ላይ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን በ40% ቀንሰዋል። በኬንያ አልሚዎች የገዢዎችን ገንዘብ ለሌላ ዓላማ እንዳያውሉ የሚከለክል ጠንካራ የባንክ ቁጥጥር አለ። በኢትዮጵያ ግን አንድ አልሚ ከአንድ ሺህ ገዢዎች ቅድመ ክፍያ ሰብስቦ፣ ያንን ገንዘብ ለግንባታ ከመጠቀም ይልቅ ሌላ መሬት ለመግዛት ወይም ለንግድ ማዞሪያ ሲያውለው ይታያል። ይህም ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ ለዓመታት እንዲቆዩ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማ እንደገለጹት፣ ለዓመታት የዘርፉን "ወላጅ አልባ" መሆን ተገን በማድረግ ሕገ-ወጥ አልሚዎች የሕዝቡን ገንዘብ ይዘው ሲሰወሩ ቆይተዋል። ይህ አሳዛኝ እውነታ በተለይ በዲያስፖራው ማህበረሰብ ላይ የፈጠረው ጠባሳ ጥልቅ ነው።
በየዓመቱ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ሪል ስቴት ዘርፍ ይፈሳል ተብሎ ቢገመትም፣ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ገዢ ግን በገባው ውል መሠረት ቤቱን አያገኝም። ይህ የአገርን ገጽታ የሚያበላሽና የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን የሚገታ አደገኛ ድርጊት ነው።
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ፣ የግልግል ዳኝነት አገልግሎት "አስቸኳይ ምላሽ" ለሚሹ ገዢዎች መፍትሄ እንደሚሆን ገልጸዋል። ይህ ንግግር የሺዎችን ሰቆቃ የሚያስተጋባ ነው። ብዙ ገዢዎች የቤት ኪራይ እየከፈሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ ወለድ እየገበሩ፣ የከፈሉት ቤት ግን በኮንክሪት አጽምነቱ ቆሞ ማየት የዕለት ተዕለት ሕመማቸው ሆኗል።
ስምምነቱ ይህንን ስቃይ በንግግርና በሕግ አግባብ ለመፍታት መሞከሩ የሚደነቅ ቢሆንም፣ አስገዳጅነቱ ግን ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል።
አዲሱ የሪል ስቴት አዋጅ (ቁጥር 1357/2017) ቢጸድቅም፣ የአፈጻጸም መመሪያው በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል አለመውጣቱ ትልቅ የፖሊሲ ክፍተት ነው።
ስምምነቱ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ቢሞክርም፣ የግል ተቋማት (ማህበራት) የመንግሥትን የቁጥጥር ሚና ሙሉ በሙሉ ሊተኩ አይችሉም። መመሪያው አለመኖሩ አልሚዎች አሁንም በራሳቸው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ውል (Adhesion Contracts) እንዲያዘጋጁ ዕድል ሰጥቷቸዋል።
በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ተሞክሮ፣ አንድ የሪል ስቴት አልሚ ግንባታውን ሳይጀምር ከ5% እስከ 10% በላይ ቅድመ ክፍያ መቀበል አይችልም። በኢትዮጵያ ግን እስከ 100% ክፍያ ተቀብለው ግንባታ የማይጀምሩ አልሚዎች አሉ። ይህ አሠራር ገዢውን ለማጭበርበር ለሚፈልጉ አካላት ወርቃማ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። አዲሱ ስምምነት እንዲህ ዓይነት ዘረፋዎችን ለመከላከል የሚያስችል የቅጣት ሥርዓት ካላካተተ፣ የግልግል ዳኝነቱ "የወረቀት ነብር" ሆኖ የመቅረት ዕድሉ ሰፊ ነው።
ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ነጥብ የጥቅም ግጭት (Conflict of Interest) ጉዳይ ነው። የአልሚዎች ማህበር አባላቱን ለመጠበቅ የቆመ ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣ በአባል አልሚዎች እና በገዢዎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር በገለልተኝነት ለመዳኘት ምን ያህል ብቃት አለው? የሚለው ጥርጣሬ ይነሳል። ንግድ ምክር ቤቱ በመሀል መኖሩ ለገለልተኝነቱ ዋስትና ቢሆንም፣ አሠራሩ ግልጽና ለሕዝብ ክፍት መሆን አለበት። ግልጽነት በሌለበት ቦታ ሙስናና አድልዎ የመስፈን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
የሪል ስቴት ዘርፉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት (GDP) ውስጥ ያለው ድርሻ ወደ 12% ይጠጋል። ሆኖም ይህ ትልቅ ቁጥር በደካማ ሕግ መመራቱ አገሪቱን ለከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ ሊዳርጋት ይችላል። በ2008 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተው የሪል ስቴት ቀውስ (Housing Bubble) መነሻው ደካማ ቁጥጥር እንደነበር ይታወሳል። ኢትዮጵያም ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥማት፣ እንዲህ ዓይነት ስምምነቶች ወደ ጠንካራ የመንግሥት ደንብ ማደግ አለባቸው።
አሳዛኙ እውነታ፣ ብዙ ገዢዎች ወደ ግልግል ዳኝነት ለመሄድ እንኳን ተጨማሪ ወጪ የሚጠይቃቸው መሆኑ ነው። ቀድሞውኑ ጥሪቱን በአልሚ የተበላበት ገዢ፣ ለዳኝነትና ለጠበቃ የሚከፍለው ገንዘብ ማጣቱ ሌላው የችግሩ ገጽታ ነው። ስለዚህ ስምምነቱ ነፃ ወይም ዝቅተኛ ክፍያ የሚጠይቁ የሕግ ድጋፎችን (Legal Aid) ለተጎጂዎች ማመቻቸት ይኖርበታል። ፍትሕ ለሀብታሞች ብቻ መሆን የለባትም።
የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ከተመሰረተ ገና ዘጠኝ ወራት ቢሆነውም፣ እንዲህ ዓይነት ትልቅ ኃላፊነት መውሰዱ የሚበረታታ ነው። ሆኖም ማህበሩ በመጀመሪያ ማድረግ ያለበት አባላቱን ማጥራት (Vetting) ነው። በሕዝብ ገንዘብ የከበሩ፣ ስም ያጠፉና ፕሮጀክት ያጓተቱ አልሚዎችን ከአባልነት በማሰናበት ለገዢዎች የምሥራች ማብሰር አለበት። ስነ-ምግባር የሚጀምረው ከቤት ውስጥ ነውና።
በመደምደሚያው ላይ፣ ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ሪል ስቴት ዘርፍ ላይ የተጋረጠውን ጨለማ ለመግፈፍ የተለኮሰች ትንሽ ሻማ ናት። ነገር ግን ሙሉ ብርሃን እንዲመጣ መንግሥት የፍትሕ ሚኒስቴርን መመሪያዎች ማውጣት፣ ባንኮች የገዢዎችን ገንዘብ የሚጠብቁበትን አሠራር መዘርጋት እና አልሚዎች ለገቡት ቃል በሕግና በንብረታቸው ተጠያቂ የሚሆኑበት ሥርዓት መገንባት አለበት።

ትራምፕ እና አል-ሲሲ በዳቮስ ስለ ሕዳሴው ግድብ "ጠንከር ያሉ" ነጥቦችን ተለዋወጡ
በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን የተገናኙት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት አል-ሲሲበታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ካሁን ቀደም ካልተሰሙ አዳዲስ አቋሞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በዝግ የተካሄደውን ይህን ስብሰባ ተከትሎ በወጡ መረጃዎች መሠረትስለ ግድቡ የተለያዩ ነጥቦች ተነስተዋል
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል በነበራቸው የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሮ የነበረውና ሳይሳካ የቀረው የሦስትዮሽ ድርድር በድጋሚ በአሜሪካ አሸማጋይነት እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ ጉዳዩን ለዓመታት እንዲንከባለል መተው የለብንም እኔ እዚህ ያለሁት ስምምነት እንዲፈጠር ለማድረግ ነው በማለት ለግብፅ አቋም ድጋፋቸውን አሳይተዋል።
በውይይቱ ላይ ግብፅ በድርቅ ወቅት የሚለቀቀው የውሃ መጠን በሕግ አስገዳጅ በሆነ ስምምነት (Legally Binding Agreement) እንዲረጋገጥ ያቀረበችውን ጥያቄ ትራምፕ ደግፈዋል።
ትራምፕ ግብፅ የውሃ ዋስትና ያስፈልጋታል ይህ ለህልውናዋ ወሳኝ ነው በማለት ኢትዮጵያ ግድቡን በምትሞላበትና በምታንቀሳቅስበት ወቅት የግብፅን የውሃ ድርሻ እንዳይቀንስ ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር "የእርዳታ መሣሪያን" (Financial Leverage) የመጠቀም ዝንባሌያቸውን በድጋሚ አንስተዋል።
አሜሪካ ለሀገራቱ የምትሰጠው እርዳታ ከስምምነቱ ጋር መያያዝ አለበት የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ማድረጋቸው ተሰምቷል ይህም ኢትዮጵያ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትመለስ ለማድረግ የቀረበ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ተደርጎ ተወስዷል።
ምንም እንኳን በግልጽ "ጥቃት" የሚል ቃል ባይጠቀሙም ትራምፕ "ግብፅ ይህንን ሁኔታ ዝም ብላ ልትመለከት አትችልም ጉዳዩ እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸዋል።
ይህም ግብፅ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስትል ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ትራምፕ እንደሚረዱላት ማሳያ ተደርጎ ተተርጉሟል።
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በበኩላቸው የናይል ውሃ ለግብፅ ቀይ መስመር ነው የሚለውን አቋማቸውን በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጉዳዩ ላይ ለሚያሳዩት ቆራጥ አቋም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ የዳቮስ ስብሰባ ትራምፕ በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው በአባይ ጉዳይ ላይ ይበልጥ ወደ ግብፅ ያዘነበለ እና ጥብቅ የሆነ ፖሊሲ እንደሚከተሉ አመላካች ሆኗል ይህም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ውጥረት ሊያስገባው እንደሚችል ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ መሪዎች በመካከለኛው ምስራቅ እና በሊቢያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አንስተው ተወያይተዋል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግብፅ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለመጠበቅ እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል።
አሜሪካ ለግብፅ የምታደርገውን ወታደራዊ እና የደህንነት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ቃል ገብተዋል።
ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ባሻገር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መሪዎቹ ተወያይተዋል።
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ የአሜሪካ ኩባንያዎች በግብፅ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስብሰባው በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት አጭር መግለጫ ከፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ጋር ያለን ግንኙነት እጅግ ጠንካራ ነው።
ግብፅ ታላቅ ሀገር ናትበመካከላችን ስላለው ወዳጅነትም ደስተኛ ነኝ" ብለዋልፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በበኩላቸው አሜሪካ ለግብፅ የምታደርገውን ስልታዊ ድጋፍ አድንቀው በተለይም በአባይ ጉዳይ ላይ የምታሳየውን አቋም አመስግነዋል።
ይህ የዳቮስ ስብሰባ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከተመለሱ በኋላ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ከሚያደርጉት ግንኙነት ውስጥ ለግብፅ ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያሳይ እንደሆነ ተንታኞች እየገለጹት ይገኛሉ።

10 months ago
ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል
የሕገመንግስት አንቀጽ 39 እና ዓለም አቀፍ ህጎች
በህግ ባለሙያ ፋንታሁን ደለለው
መግቢያ #ethiopia | በአለምአቀፍ ደረጃ ራስን በራስ ማስተዳደር /self determination/ ጽነስ ሀሳቡ እስከ የት ድረስ እንደሆነ የተለያየ ትርጉም ሲሰጥበት ይስተዋላል። አንዳንዶች የመገንጠልን ጽንሰ ሀሳብን የሚያካትቱ ሲሆን አንዳንዳቹ ደግሞ የመገንጠልን ጽንሰሀሳብ በፍጹም በህገመንግስታቸው ውስጥ ሳያካትቱ እንደውም መገንጠል ላይ በዝምታም ሆነ በግልጽ የሚከለክሉ ሀገራት አሉ።
ራስን በራስ እስከ ማስተዳደር መገንጠል ስረአት በህገመንግስታቸው የሚያካትቱ ሀገራት ደግሞ በግልጽ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በግልጽ አስቀምጠዋል። ከዚህ ውጭ ባለፈም በህጋዊ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተገንጥለው ሀገር ነን የሚሉ እያስተዋልናቸው ያለ ሲሆን እነዚህ ሀገራት "እጣፋንታቸው ምንድነው?" የሚለውን በዚህ አጭር ጽሁፍ የምንመለከተው ይሆናል
1. ራስን በራስ ማስተዳደር ምንድነው?
(self determination)
ራስን በራስ ማስተዳደር አንድ ሀገር ወይም የአንድ ሀገር ክልል የሀገሩን የህገመንግስት እና የህግ የበላይነት በማክበር ያለማንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በራሳቸው እድል የሚያስተዳድረበት ነው። በዚህ ረገድ የተለያየ አይነት ዙርያ ጥምጥም አይነት ትርጉም ቢመላለስም ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ከማንም ከጣልቃገብነት ነጻ በመሆን በህግ የበላይነትና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ነው።
2. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመገንጠል እንዴት ይፈጸማል? self determination to succesion
ራስን በራስ ማስዳደር እስከ መገንጠልን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግ ሀገር ከነበረበት ሀገር ጋር ለመቀጠል የሚያስችለው ዲሞክሪያሳዊ ፣ ህገመንግስታዊ መብትን ፣ አለምአቀፍ የዲሞክሪያሳዊ እና የሰብአዊ መብቶችን ለመጎናጻፍ ከእናት ሀገሩ ያጣ እንደሆና በህዝቡ ላይ ተደጋጋሚ የመብት ጭቆና እና የመብት ጥሰት እየደረሰበት ከሆነ ነው።
በዚህ ጊዜ ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት ጥያቄው ለሀገረ መንግስቱ ለሀገረ መንግስቱ መብት የተሰጠው ሲሆን ይህን በማቅረብ ህጉን ተከትሎ የሚወሰን ይሆናል።
ከዚያም በሀገሩ ህዝብና ህገመንግስት መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ውሳኔ መገንጠል የሚፈልገው ህዝብ ጭምር ተጠይቆ የመጨረሻ መልሱ ያለ ልዩነት የመገንጠል መብትን የሚፈቅድ ከሆነ መገንጠል ተግባራዊ ይሆናል።
ይህ የሚሆነውም የመገንጠል መብት በህጉ በግልጽ የተቀመጠ እንደሆነ ነው። አለበለዚያ ግን መገንጠል አይታሰብም ተገነጠልኩ ቢልም የቅዥት ተግባር ይሆናል እንጂ ህጉን የጠበቀ ተግባር አይሆንም።
3. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል ተግባር እንዴት ይፈጸማል?
በመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያዋ ሀገር የመገንጠል ጥያቄ የሚቀርብባት ህጋዊ ሀገር ልትሆን ያስፈልጋል። ይህም ማለት በአለም አቀፍ ልምድ ህጎች ውሳኔዎች መሠረት ሀገር ለማለት የምትበቃ ልትሆን ያስፈልጋል።
ሀገር ስትሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚ ፣ህገመንግስት፣ህዝብ፣ግዛት፣የውጭ ግንኙነት አቅም ፣ ሉአላዊነት ሊኖራት ያስፈልጋል።
ይህቺ ሀገር በዚህ ልክ ህጋዊ ከሆነች በኋላ ነው የመገንጠል ጥያቄን የተወሰነው ሀገረ ግዛት ወይም ክልል ራስን በራስ ማስተዳደር ወይም እስከ መገንጠል የሚለውን በመጠየቅ በጠያቂው ህዝብ፣ ግዛትና እና በተጠያቂው ሀገር ህዝብ ሙሉ ፍቃድ ተፈጻሚ የሚሆነው።
ለምሳሌ ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚፈልግ ክልል የሁሉም ክልሎች ፣ የፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤ፥ የፌድሬሽን ምክር ቤት እንዲሁም የጠያቂው ክልል ምክር ቤት በሙሉ ያለ ምንም ልዩነት የመገንጠል ይሁንታን ሊገኝ ያስፈልጋል።
አንዱ እንኳን የልዩነት ሀሳብ ካመጣ የመገንጠል ሀሳብ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ይህ በኢፊድሪ ከመንግሥት አንቀጽ 39 ላይ የተቀመጠ ነው።
ለምሳሌ በኢትዮጵያ ይህ ህገመንግስት ሳይወጣ መንግስት ሳይመረጥ የመገንጠል ስረአት የሚከናወንበት ህግና ህገመንግስት ሳይኖር ሀገርንና ህዝብን ወክሎ የውጭ ግንኙነቶች ጋር የድርድርና የማስፈጸም አቅም ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ወደ መንግስት የተቀየረ ሳይኖር ሀገርን በበላይነት የሚገዛ ህመንግስት ሳይመሰረት በተረባበሸ የሀገር ስሜት ውስጥ በመሆን ተገንጥያለው ብሎ በተወሰኑ ቡድኖች ብቻ በተደረገ የማይጸና ውል የመገንጠል ጥያቄ አቅራቢውም ሆነ ተቀባይውም ህጋዊ ቅቡልነት የሌላቸው ናቸው።
3. ቅቡልነት ያለው ህግን ሳይከተሉ መገንጠልን በራሳቸው ህጋዊ ያደረጉ ሀገራት እጣ ፈንታቸው ምን ይሆናል?
እነዚህ ሀገራት by defacfo(ያለ ህግ ቅቡልነት) ያላቸው ቢሆንም ከሌሎች ሀገሮች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነቶች የሌላን ሀገርን ብሔራዊ ጥቅም መብት የሚነካ ከሆነ ጥቅሙ የሚነካበት ሀገር በተለይም ሀገር የሆነበት አካሄድ ህጋዊ ጥያቄን የሚያስነሳ ከሆነ ይህንን በመቃወሚያነት በማንሳት ብሔራዊ ጥቅሙ የተነካበት ሀገር መብቱን ማስከበር ይችላል።
4. መደምደሚያ
ይህ እንደ ጸሀፊው የህግ ምርምርና አስተያየት የቀረበ ቢሆንም ዋናው ነገር እንደ ጸሀፊው አስተያየት ሀገራት እንደ ህጋዊ ሀገር ሆነው ህዝባቸውን በማስተዳደር የዜጎችን እና የሀገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በመጀመረያ ደረጃ በህግ ቅቡልነት ሊኖራቸው ያስፈልጋል።
References/ዋቢ መጽሀፍት/
1. Crawford, J. (2006). The Creation of States in International Law (2nd ed.). Oxford University Press.
2. International Court of Justice (ICJ). (2010). Accordance with International Law of the Unilateral Declaration of Independence in Respect of Kosovo, Advisory Opinion.
3. International Court of Justice (ICJ). (1986). Frontier Dispute (Burkina Faso/Republic of Mali), Judgment.
4. Montevideo Convention on the Rights and Duties of States. (1933).
5. United Nations Human Rights Council (UNHRC). (2022). Report of the Special Rapporteur on the situation of human rights in Eritrea. A/HRC/50/20.
6. United Nations Security Council (UNSC). (1999). Resolution 1244. S/RES/1244.
7. United Nations Security Council (UNSC). (1961). Resolution 169. S/RES/169.
8. Vaughan, S. (2011). The Ethio-Eritrean Conflict and the Algiers Agreement: A Legal Analysis. In A. Jacquin-Berdal & M. Plaut (Eds.), Unfinished Business: Ethiopia and Eritrea at War. Red Sea Press.
9. Woods, T. (2019). The Law of Territorial Integrity and the Eritrea-Ethiopia Boundary Commission. Cambridge Journal of International and Comparative Law.

12 months ago
የኢትዮጵያ ብር ኖት ላይ የነበረው ሐረግ: "ላምጭው እንዲከፈል ህግ ያስገድዳል!"
ይህ ሐረግ ("Pay to the bearer on demand") የብርን ዋጋ ህጋዊ መሰረት የሚያሳይ ነው:
* ታሪካዊ ትርጉም (የወርቅ ደረጃ): በቀድሞው ዘመን መንግሥታት የብር ኖት ሲያትሙ፣ ዋጋው በብሔራዊ ባንክ ውስጥ በወርቅ ወይም በብር ተጠብቆ ይገኝ ነበር። ስለዚህ፣ ኖቱን የያዘው ሰው (ላምጭው) ባንክ ሄዶ የገንዘቡን ዋጋ በወርቅ እንዲቀይርለት የመጠየቅ ህጋዊና ፍጹም መብት ነበረው። ቃሉ ለገንዘቡ አስተማማኝነትና እምነት ለመስጠት ያገለግል ነበር።
* ዘመናዊ ትርጉም (ፍያት ገንዘብ): ዛሬ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛው ዓለም የሚጠቀመው 'ፍያት ገንዘብ' በመሆኑ ብሩ በወርቅ አይቀየርም። ይሁን እንጂ ሐረጉ አሁንም ቢሆን የሚያመለክተው: ብሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሙሉ ዋስትና የተሰጠውና በሀገሪቱ ውስጥ ለግብይት፣ ለክፍያና ለዕዳ መክፈያነት በህግ የተፈቀደ (Legal Tender) ብቸኛው ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ መሆኑን ነው።
seledadotio

1 year ago
በዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ፣ እና ቨርጂኒያ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ነዎት? እንግዲያውስ ይህ ነጻ መድረክ እንዳያመልጦ!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ለአሥርት አመታት ወሳኝ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንዲሁም ለሀገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከተ የቆየ ቢሆንም መሠረታዊ የሕግ ጉዳዮችን ካለመረዳት እና በቂ የሕግ ጥበቃ ባላማግኘቱ የተነሳ በተለያዩ አካላት ለሚፈፀም የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊት እየተጋለጠ በሰው ሃገር ያፈራውን ጥሪት በቀላሉ ሲዘረፍ ይስተዋላል፡፡ ይህንን ለመቅርፍ የሚያስችል ነጻ የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የኢትዮ ሌጋል ሺልድ የጥብቅና ድርጅት መስራች ጠበቆች ከኢትዮ አሜሪካን የንግድ ም/ቤት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶሎታል፡፡
የፊታችን ሀሙስ ሴፕቴምበር 25 ከ 5:00 PM -9:00 PM አድራሻ 1 Veterans Place Silver Spring MD
ዛሬውኑ ቦታ ይያዙ!
ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ
https://www.eventbrite.com...
ይህ አስፈላጊ የህግ ግንዛቤ ፕሮግራም እራስዎን፣ ቤተሰብዎን እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን ለመጠበቅ በሚያስችል እውቀት ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ነው።
ማን መታደም ይችላል?
ይህ ዝግጅት ለሁሉም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት፣ በንብረት ግዥ ላይ ለሚሳተፉ ወይም የህግ ጉዳዮች ላሏቸው ሰዎች ጠቃሚ ነው።
ምን ይማራሉ?
የኢትዮ ሌጋል ሺልድ መስራች እና ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች ተናጋሪዎች ሲሆኑ፣ በወሳኝ የህግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ይሰጣሉ።
የፕሮግራሙ ይዘት፡-
በቅርቡ የጸደቀውን የሪል እስቴት ሕግን እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ችግሮችን፡ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ገበያን ውስብስብ ሁኔታ ይዳስሳል። ባለሙያዎቻችን የንብረት ባለቤትነትን እና ግብይቶችን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎችን ያብራራሉ እንዲሁም የተለመዱ ማጭበርበሮችን እና ህጋዊ መፍትሄዎችን ይጠኡማሉ።
የውክልና ስልጣን (Power of Attorney, PoA)፡- ውክልና ከውጪ ሆነው ጉዳዮችዎን ለማስተዳደር ወሳኝ መንገድ ቢሆንም ብዙዎችን ለምዝበራ የዳረገ የተለመደ የብዝበዛ ምንጭ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዮችዎን ለማስተዳደር ስለሚያስችለው ህጋዊ POA፣ ህጋዊ ወሰኑን፣ በኢትዮጲያ ያሉ ጉዳዮችዎን ለማስፈጸም የሚስያስችል ትክክለኛው ውክልና ለማዘጋጀት እና ለመጠቀም እየሚረዱ ልምዶችን ይማራሉ።
አዲሱን የንብረት ማስመለስ እና መውረስ ህግን መረዳት፡ የኢትዮጵያን ንብረት ማስመለስ እና ንብረት መውረስ አዋጅን (አዋጅ ቁጥር 1364/2025) ማብራራት እና መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመጠቆም የህጉን ወሰን፣ ወደ ኋላ አተገባበር እና "ያልተገለጹ ንብረቶች" የሚለውን ጽንሰ-ሀሳብን ማብረራትን ያካትታል። ይህ ህግ በእርስዎ ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እና ንብረቶችዎን ለመጠበቅ ምን አይነት ቅድመ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብዎት መረጃ ያገኛሉ።
የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ላይ ያለው ለውጥ፡
የኢትዮጵያ የጥብቅና ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ በሕግ ቴክኖሎጂ (Legal-Tech) እንዴት እየተቀየረ እንዳለ ያውቃሉ? ከተለምዷዊ "ራፖርት ወይም ማመልከቻ ጽሀፊዎች" እስከ የህግ ቴክኖሎጂ እድገት እንዲሁም እነዚህ እድገቶች ለዲያስፖራዎች የበለጠ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዴት እንደሚሰጡ እናስረዳለን።
የዲያስፖራውን መብት ለማስጠበቅ በምናደርገው ጉዞ ይቀላቀሉን። ይህ ከተለመደው የተለየ እና በጋራ መፍትሄ ለመፈለግ የምንመክርበት ነው፡፡ እንዲሁም የዲያስፖራውን ማህበረሰባችንን የማንቃት እና ብተናጥል የሚደርስበትን ትቃት በጋራ መፍትሄ እንዲፈልግ እና መብቱን እንዲያስክብር አይን ከፋች ጅምር ነው።
መሠረታዊ የሕግ እውቀትን በማስጨበጥ በዲያስፖራው ላይ የሚፈፀመውን ማጭበርበር(scams targeting the diaspora) ለመዋጋት የታሰበ ነው::

ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ የሕግ ግንዛቤ ማስጭበጫ መድረክ
#ethiopia | በውጭ ሀገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሆነው በትውልድ ሀገረዎ ውስብስብ የሕግና የቢሮክራሲ ፈተናዎች አጋጥሞዎታል?
እንግዲያውስ በዲያስፖራ እና ኢትዮጵያውን ጠበቆች በተመሰረተው፣ በሕግና ሕግ ነክ በሆኑ የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ኢትዮ ሊጋል ሺልድ ኤል ኤል ፒ(የጥብቅና ድርጅት) በኢትዮጵያ ታዋቂ ከሆኑ የህግ ጠበቆች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ነፃ የሕግ ግንዛቤ ላይ በመገኘት በሐገረዎ ስላለው የህግ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ይረዱ ፣ ያቅዱ ፣ ይወስኑ፡፡
የኢትዮጳውያንን ዲያስፖራ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ለርስዎ እንዲስማሙ ሆነው በተሰሩ የሕግ መፍትሄዎች አማካኝነት ዲያስፖራውን በሕግ ጉዳይ የማንቃት እንቅስቃሲያችንን ይቀላቀሉ፡፡
እየተደጋገመ እና እየተስፋፋ ከመጣው የአጭበርባሪያዎች ማባበያ ራስዎን ለመጠበቅ እና በቂ የሕግ ግንዛቤ ኖሮት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያሳልፉ የሚያግዝዎትን መድረግ አዘጋጅትን እየጠበቅንዎት ነው፡፡ የእኛ ተልዕኮ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሕግ ግንዛቤን በማሳደግ ከአደገኛ ዘረፋዎች በመከላከል ባሕበረሰባችንን መጠበቅ ነው፡፡
በተለይ ከፍተኛ ማጭበርበሮች ፣ ክህደቶች እንዲሁም ስጋቶች በሚታይባቸው የሕግ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን፡፡
አዳዲስ አዋጆችና የሰበር ውሳኔዎች ስለወጡ ለመረዳት እንግዳ በሆኑት፤
* የሪል እስቴት ሕግ
* የንብረት ማስመለስና መውረስ ሕግ
* በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (AML) ሕግ
* የቤተሰብ ሕግ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ ለውሳኔ የሚያግዝዎትን በቂ ግንዛቤ እናስጨብጠዎታለን
የዚህ ዝግጅት ዋና አላማ እርስዎን የኛ ደንበኛ ማድረግ ሳይሆን የመሰረታዊ ሕግ ግንዛቤን በማሳደግ ከማን ጋር እንዴት ልስራ ? ከእያዳንዱ የሕግ ጉዳይ ውሳኔ በፊት ምን ላድረግ? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖርዎት በማድረግ ውሳኔዎችን ማገዘ ነው። በተለይ በሐገራችን ከወጡ አዳዲስ ሕጎች እና አዳዲስ የሰበር ውሳኔዎች አኳያ ጉዳዮቹን በማየት በቂ ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተናል፡፡
ይህ በአካልና በበየነ መረቦች አማካኝነት የሚደረገው ዝግጅታችን ከተለያዩ ባለሞያዎች እና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመገናኘትና ራስዎንና ስራዎን ለማስተዋወቅ ያግዝዎታል ፡፡
በተለይም ጠበቆችን ከደንበኞቻቸው ጋር በማገናኘት ብሎም የትኛው ጠበቃ በየትኛው የሕግ ጉዳይ እንደሚሰራ ፤ የጠበቆችን ፕሮፋይልና ይበልጥ የሚያተኩሩበትን የሕግ ዘርፍ በመዘርዘር ስለሕግ አገልግሎት በቂ ግንዛቤ እንዲኖርዎት የሚያደረግውን በኢትዮ ሊጋል ሽልድ የተሰናዳውን የ Legal Talent Cloud and Matching Platform ይተዋወቃሉ፡፡
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም ለመመዝገብ የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ
Text or call direct or WhatsApp: 301-640-9768
* ኢሜይል: adminethiolegalshield.com

ኢትዮ ሊጋል ሺልድ የቴክኖሎጂ የህግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ
#ethiopia | ኢትዮ ሊጋል ሺልድ የተሰኘው የህግ ተቋም በኢትዮጵያ የህግ አገልግሎት ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራውን በይፋ አስመረቀ።
ተቋሙ ያዘጋጀው የቴክኖሎጂ ፈጠራ (https://ethiolegalshield.c... የህግ ባለሙያዎችን እና የህግ አገልግሎት ፈላጊዎችን በቀላሉ የሚያገናኝ ሲሆን፣ ለሁሉም ሰው ፍትህ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።
ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2017 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ በተከናወነው መርሐግብር ላይ፣ ከህግ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከመንግስት ዘርፍ የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመርሐግብሩ ላይ “በኢትዮጵያ የህግ አገልግሎቶች ዲጂታል ሽግግር” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ውይይቱ ቴክኖሎጂ በህግ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን ፋይዳ እና ተደራሽነትን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ላይ ያተኮረ ነበር።
በመድረኩ ላይ በተነሳው ሀሳብ መሰረት፣ ኢትዮ ሊጋል ሺልድ ባህላዊ እሴቶችን ከዘመናዊ የፈጠራ ዘዴዎች ጋር በማዋሃድ የህግ አገልግሎት ዘርፉን ለመቀየር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ተቋሙ ፍትህን ለማስፈን፣ የሙያ ስነምግባርን ለማክበር እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን የህግ አገልግሎት አብዮት ለመፍጠር በጉዞ ላይ መሆኑንም አሳውቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይም፣ በአለም ዙሪያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህግ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀው "የዳያስፖራ የህግ አገልግሎት ጉብኝት" መርሃግብርም ይፋ ተደርጓል። ይህ ጉብኝት በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልጋቸውን የህግ ድጋፍ ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ አዲስ መድረክ፣ በተለይም ገና ለገና ለሙያው አዲስ የሆኑ የህግ ባለሙያዎች እና የህግ ተማሪዎች ከዘርፉ መሪዎች ጋር የሚተዋወቁበት እና ከህግ ፈጠራ ጋር የሚዛመዱ ጠቃሚ ልምዶችን የሚቀስሙበት ልዩ እድል መፍጠሩ በመድረኩ ላይ ተነግሯል።

ለመላው የሕግ ባለሞያ ማህበረሰብ፡ አዲስ የሕግ ምሩቃን እና ተማሪዎች በሙሉ መልካም ዜና!
የሕግ አገልግሎትን የሚያዘምን እና ለሁሉም ተደራሽ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ይፋ ሊሆን ነው!
የሕግ ቴክኖሎጂን(LegTech) በመጠቀም በኢትዮጵያ የጥብቅና አገልግሎትን ዘመናዊ ለማድረግ እና ተደራሽነትን ለማስፋት ያለመ ነው::
ኢትዮ ሌጋል ሺልድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የጥብቅና ማህበር ከገበያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ለብዙዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥርና ባለሞያውን በቀላሉ ከአገልግሎት ፈላጊው ጋር የሚያገናኝ (AI-powered Legal talent cloud and Matching platform) በቴክኖሎጂ የታገዘ የህግ አገልግሎት ይዞላችሁ ቀርቧል።
ይህ አገልግሎት የህግ ባለሙያዎችንና ደንበኞችን በቀጥታ የሚያገናኝ ከመሆኑ ባሻገር የሕግ አገልግሎትን ለሁሉም ማህበረሰብ የመክፈል አቅም እና የቦታ ርቀት ውስንነት ሳይገደብ ተደራሽ የሚያደርግ በመሆኑ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
ይህን ወሳኝ አዲስ ጅምር ለማስተዋወቅ በተዘጋጀው ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ ግብራችን ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል።
በዝግጅቱ ላይ፡
• "በቴክኖሎጅ የታገዘ የህግ አገልግሎት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ፣ የህግ ቴክኖሎጂ ለፍትህ ተደራሽነትና ለዘርፉ እድገት ስላለው አስተዋጽኦ የሚመክር የፓናል ውይይት ይካሄዳል።
• ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ለማገልገል የተዘጋጀውን ልዩ የህግ አገልግሎት ለተሳታፊዎች እናስተዋውቃለን።
• የህግ ባለሙያዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ የመንግስት ባለድርሻ አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በዚህ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ስለህግና ቴክኖሎጂ የወደፊት ሁኔታ ይወያያሉ።
የዝግጅቱ ዝርዝር
• 📅 : ማክሰኞ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
• 🕙: ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00
• 📍: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ 5ኛ ፎቅ፣ አዲስ አበባ
ለመሳተፍ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ በመጫን ፤መረጃዎን የተሳታፊዎች ዝርዝር ወስጥ በማስመዝገብ ወደ ዝግጅቱ ለመታደም ሲመጡ በባንኩ ጥበቃዎች የመግቢያ ይለፍ ያገኛሉ፡፡

" ሀኪሞቹ ከአግባብ ውጪ ከታሰሩበት በአስቸኳይ ይፈቱ የህግ የበላይነት ይከበር " - ማኅበሩ
የትግራይ ህክምና ማኅበር በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚስተምሩና በሞያው ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የስፔሻሊቲ ሀኪሞች ታስረዋል።
ታሳሪዎቹ ዶ/ር ብርሃኑ ጥላሁን እና ዶ/ር ሙሉ ዳኘው እንደሚባሉ የገለፀው ማህበሩ ከስራ ገበታቸው በፓሊስ ቁጥጥር መዋላቸውን አስታውቋል።
ማንኛውም ሰው ሆነ ባለሞያ ከህግ በታች መሆኑ ያስታወሰው ማህበሩ የአባላቱ መታሰር ከህክምና ህግ (Medco legal ) እንደሚያያዝ ጠቁሞ ህጉ የራሱ የሆነ የአፈፃፀም ስርዓት አለው ብሏል።
የኢፌዲሪ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2006 አንቀፅ 37 ቁጥር 1 ና 2 አንድ ባለሞያ በህክምና አሰጣጥ ወቅት ባጋጠመ ስህተት የሚፈፀም ወንጀል ተጠያቂ የሚሆንበት የህግ አገባብ ተቀምጧል ሀኪሞቹ ግን ይህንን የህግ አካሄድ ተጥሶ ነው የታሰሩት ብሏል።
ስለሆነም ሀኪሞቹ ከአግባብ ውጪ ከታሰሩበት በአስቸኳይ እንዲፈቱና የህግ የበላይነት እንዲከበር የትግራይ ህና ማህበር ጥሪውን አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle
@tikvahethiopia

ቤት ሸንሽኖ ማከራየት ያስቀጣል
#ethiopia | የአቡ ዳቢ ከተማ አስተዳደር በመኖሪያ ቪላዎችና አፓርትመንቶች ውስጥ የሚደረጉ ህገ-ወጥ ክፍፍሎችን (ቤት ሸንሽነው የሚያከራዩትን/ illegal partitions) ለመቆጣጠር ጠንካራ እርምጃ መውሰድ ጀመረ፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚፈጠረው ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት እጥረት መፍትሄ የሚሆኑ አማራጮችን እያቀረበ መሆኑን አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ እና የትራንስፖርት መምሪያ (DMT) እንዳስታወቀው፣ በህገ-ወጥ መንገድ ቤት እየሸነሸኑ የሚያከራዩ፣ የህዝብን ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጡ፣ በተለይም የእሳት አደጋ ስጋትን የሚጨምሩ፣ ከመጠን ያለፈ የህዝብ መጨናነቅን የሚፈጥሩ እና የከተማዋን ገጽታ የሚያበላሹ በመሆናቸው የማስወገድ ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
"ቤትዎ የእርስዎ ኃላፊነት ነው" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው ይህ ዘመቻ፣ የንብ ረት ባለቤቶች የከተማዋን የግንባታ ህጎችና መመሪያዎች እንዲያከብሩ ለማሳሰብ ያለመ ነው።
ህገ-ወጥ የክፍል ሽንሸናዎችን (illegal partitions) የሚያደርጉ የንብረት ባለቤቶች እስከ 1 ሚሊዮን ዲርሃም (ከ272,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ) ሊደርስ የሚችል ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ ይህ እርምጃ አነስተኛ ገቢ ባላቸው ነዋሪዎችና ሰራተኞች ላይ የሚፈጥረውን የመኖሪያ ቤት እጥረትና የኪራይ ዋጋ ውድነት ችግር ለመቅረፍ መንግስት አማራጭ መፍትሄዎችን አቅርቧል።
እነዚህ ነዋሪዎች በህገ-ወጥ ክፍፍል በተከፋፈሉ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩት የኪራይ ዋጋቸው ተመጣጣኝ በመሆኑ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህንን ችግር ለመፍታት፣ የአቡ ዳቢ ባለስልጣናት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ተብለው የተሰሩ "ዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች" (low-cost housing) መኖራቸውን አስታውቀዋል።
እነዚህ መኖሪያ ቤቶች በአቡ ዳቢ እና በአል አይን ከተሞች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሲሆን፣ እንደ ሙሳፋህ፣ አል ራሃ እና ሌሎች የሰራተኞች መኖሪያ አካባቢዎችን ያካትታሉ።
ይህ የመንግስት እርምጃ ሁለት አላማዎችን ያካተተ ነው፤ አንደኛው የከተማዋን ደህንነትና ስርዓት ማስጠበቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ማቅረብ ነው።
አቡ ዳቢ፣ ዩናይትድ አረብ ኤመሬት። #zehabesha

Comments