Logo
SeledaPost
የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀላቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው::

ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ አወግዛለሁ::

በአርሲ በተደጋጋሚ ንፁሀኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተበራከተ በየጊዜው ለቅሶ እና ዋይታ ብቻ እየተሰማ ያለ መፍትሄ መቀጠሉ እጅግ ያሳምማል::

ንፁሃን ዜጎች እያለቁ ያለው ከውጪ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን ወንድም ወንድሙ ላይ እየሰነዘረው ባለው አሳዛኝ ከጭካኔ ጥቃት ነው::

በሀገሩ ምድር በድህነት ህይወቱን እየመራ ለሚገኝ ንፁህ ህዝብ ከግራ እና በቀኝ ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎች በማያውቁት አጀንዳ ለሞት፣ ለእልቂት፣ ለስደት መዳረጉ ልብ ሰባሪ ነው::

ይህ የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::

በአርሲ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለው::

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ አላህ እንዲረዳቸው እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው::

አላህ ሀገራችንን እና ወገኖቻችንን ይጠብቅልን::

ሰላም መግባባቱንና መተዛዘኑን በመላው ሀገራችን ሀያሉ ጌታችን አላህ(ሱ.ወ) ያስፍንልን

ኡስታዝ አቡበከር

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.