የጥቁር ሕዝቦች ድምፅ በተመድ አዳራሽ - ኢትዮጵያ ለነፃነት የከፈለችው ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላቸው ትሥሥር እንደ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብቻ የሚታይ ሳይሆን፣ በታሪክ አውድማ ላይ በፅናት እና በሉዓላዊነት የተገመደ የክብር ሰንሰለት ነው።
ከሰማንያ ዓመታት በፊት ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍርስራሽ ላይ ቆማ አዲስ ተስፋን ስትፈልግ፣ ኢትዮጵያ ከ51ዱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ሆና የቻርተሩን ሰነድ ስትፈርም ተራ ተሳታፊ አልነበረችም።
ይልቁንም፣ የዲፕሎማቶቻችን ድምፅ የኃያላንን የበላይነት ለመሞገት እና የደካማ ሀገራትን መብት ለማስጠበቅ የሚተጋ የፍትሕ ጩኸት ነበር።
በወቅቱ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር ለነበሩት ወንድም የአፍሪካ እና የእስያ ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ተሟጋች ሆና መቅረቧ፣ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” የሚለውን ብሂል ወደ ጎን በመተው ለሰው ልጅ ሁሉ ነፃነት መቆሟን ያሳየ ታላቅ የሞራል ልዕልና ነበር።
ይህ የታሪክ አሻራ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈ ይገኛል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ የሰላም ዘቦችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማሠማራት፣ በዓለም ሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ ያላትን የማይናወጥ ሚና በተግባር አሳይታለች።
የሀገራችን ሠራዊት በሄደበት ሥፍራ ሁሉ የሚታወቅበት የጥንካሬ፣ የዲሲፕሊን እና የሕዝባዊነት ገጽታ፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ከሚያዋጡ ሀገራት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርጓታል። ይህ መሥዋዕትነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻችን እና ለመላው ዓለም ሰላም መቆማችንን የሚያረጋግጥ የቆራጥነት ማሳያ ነው።
በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚከናወኑት እነዚህ ተልዕኮዎች፣ የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገውታል።
ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸው እና የድርጅቱን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እዚህ በታሪካዊቷ ከተማችን እንዲከበር መወሰኑ፣ እንዲሁ የተገኘ ድንገተኛ ክስተት አይደለም። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ያበረከተችው ታሪካዊ አስተዋፅኦ እና ለዓለም ሰላም የከፈለችው መሥዋዕትነት የተሰጠው ታላቅ እውቅና ነው።
“መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል” እንዲሉ፣ የሀገራችን የዲፕሎማሲ ጥንካሬ እና የሠራዊታችን አኩሪ ገጽታ ለስምንት ዐሥርተ ዓመታት ተጠብቆ ቆይቶ ዛሬም በዓለም መድረክ ድምፃችን ጎልቶ እንዲሰማ አድርጎታል።
ይህም የአፍሪካን ዳግም መነሣት የሚያበስር ምልክት እና ለጋራ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን የጥንካሬ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ እና ተመድ በዘላቂ ልማት ግቦች ዙሪያ ያላቸው ትብብርም ሌላው የትሥሥሩ ገጽታ ነው። ድህነትን ለማጥፋት፣ ፕላኔቷን ለመጠበቅ እና ለሁሉም ሰው ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት፣ ሀገራችን ከድርጅቱ ጋር ያላትን ስትራቴጂክ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል።
ወደፊትም ቢሆን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ደጀን እና የልማት ተምሳሌት ሆና በመቀጠል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፍትሐዊ ሥርዓት እንዲሰፍን እና የጋራ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የነበራትን የሞራል መሪነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጥርጥር የለውም።
የታሪካችን ጥንካሬ እና የሠራዊታችን ፅናት ዛሬም ለዓለም ሰላም ዋስትና፣ ለትውልድም ኩራት ሆኖ ይቀጥላል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #diplomacy #un #un80

22 days ago