3 days ago
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

10 days ago
#ቤተልሔም_ሸረፈዲን - " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ ያላት "
( የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ )
**********************************************
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
#በመጨረሻም ፦ ጽሑፉ ለፌስቡክ ረጅም ( አረፍ አረፍ እየተባለ ተነቦ የሚያልቅ ) ነው ። አጥሮ ሁሉም ጋ ከሚደርስ ረዝሞ የሚመለከታቸውና የሚያስፈልጋቸው ቢያነቡት መርጬ ነው ። ሆነ ብዬ ነው ማለት ነው ። ይሁን ። እንግዲህ እያረፋችሁም ፣ እያለፋችሁም አንብቡት ።
ለግጥምም ፣ ለዜማም አልፎ ሂያጅ ነኝ። ( በተለይ ) ለግጥም አልፎ ሂያጅ መሆኔ ያስቆጨኛል ። ግጥም ምኞቴ ነው ፤ ጉድለቴም ። ማንም እንደሚሰማውና እንደሚረዳው ነኝ ። አዚያዚያምን መረዳትም ላይ ጨዋ አላዋቂ ነኝ ። ቤተልሔም ሸረፈዲን " ደስተኛ " ብላ ስለሰየመችው አዲሱ አልበሟ የተሰማኝን ልላችሁ ነው ዳር ዳር የምለው ።
እኔ የምለው ፣ ቤተልሔም ሸረፈዲን ግን ስንት ዓመቷ ነው ? በቅርቡ ትንሽ ልጅ አልነበረችም እንዴ ? ከመቼው አደገች ? ከምኔው አብባ አፈራች ? አልበሟ በተለቀቀበት " ኩራ ስትሪም " ላይ ገጣሚው ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) እንደ ገጣሚነቱ ቃላት ቆጥቦና ሀሳቡን አስውቦ " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ አላት
" እንዳላት ሆና ነው የመጣችው ። የጥበብ ስራ አመዛኙን ሁለቱን ይፈልጋል ። እውቀትም ፣ ተሰጥዖም በዝቶ ኖሯቸው የትም ሳይደርሱ የቀሩ " እገሌ ፣ እገሌ " የምንላቸው ጥቂት የማይባሉ የጥበብ ሰዎች በየአልባሌው ወድቀው ቀርተዋል ። እስቲ እነዚህን ሰዎች አስቧቸው ። የህጻን ልብም ፣ የአዋቂ ጆሮም አታገኙባቸውም ።
10 ዘፈኖች የያዘው " ደስተኛ " አልበም ናትናኤል ግርማቸውና ታምሩ አማረ በጥምረት ፕሮዲዩስ ያደረጉት ነው ። ከጀርባቸው ደግሞ ከብዙ ጥበባትና የጥበብ ሰዎች ጀርባ ያለው ዘላለም ኩራባቸው " ኩራ ስትሪም " ን ይዞ አለ ። ቅንብሩን ፣ ሚክሲንግ እና አሬንጅመንቱን ታምሩ አማረ ፣ ግጥሞቹን ( በሙሉ ) ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) ፣ " ባለቤቴ " እና " እንዴት " ዜማዎችን ዮሴፍ በቀለ ( ጆ ) ፣ " አይታለፍም " ዜማ እሱባለው ይታየው ( የሺ ) ፣ የቀሪዎቹን 7 ስራዎች ዜማዎች በምህረተአብ ደስታ ሲፈጠሩ ከእነዚህ ውስጥ የእበሙ መጠሪያ የሆነው " ደስተኛ " ን ዜማ ናቲና ምህረተአብ በጋራ ሰርተዋቸዋል ።
በአሁኑ ጊዜ አንድ ነጠላ ዜማ መስራት የምረቃ ፕሮግራም ያዘጋጃል ፤ ወዳጅ ዘመድ ያጠራራል ፤ " ሰይፉ በኢቢኤስ " ላይ ያስቀርባል ፤ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ አላስቆም አላስቀምጥ ያስብላል ። አልበም መስራት ( አድማጭ ያልተቀበለውም ቢሆን እንኳ ) እንደ አራሷ ሴት " ምጡን ተዪው ፤ ልጁን እዪው " እየተባለና የስቃዩ ጊዜ እየተረሳ እንጂ ደጋግሞ በስሜት ሞቶ መነሳት ነው ። የሚያገጫጭ ፣ የሚያነጫንጭ ፣ የሚያቀያይምንና " ሁለተኛ ብንገናኝ ! " የሚያባብል ነው ። የምጡ ጊዜ አልፎ ልጁ ሲታይ እየተረሳ ነው አንዱ ሙዚቀኛ ከሌላው ጋር የኖረው ። ቤተልሔም መልካሞችና ህልም ያላቸው ሙያተኞች እጅ ላይ አሳርፏት እንጂ ጀምሮ አለመጨረስ ፣ ወድቆ አለመነሳትም አለ ። ገና በመጀመሪያው አልበም ፣ በትንሽ እድሜ ፣ በጀማሪነት አረዳድ እንዲህ ያለ ስኬታማ አልበም መስራት ደጋግሞ የማያጋጥም ነው ። ህብስት ጥሩነህ እነ አየለ ማሞ ( ማንዶሊን ) እና ታንጎ ሙዚቃ ቤትን እንዳገኘችው አይነት እድለኛነት ይጠይቃል ። የናቲ እና ታምሩ ጥምረት ደግሞ የእነ ኤሌክራትን እና አምባሰልን ዘመን ያስታውሰናል ።
ናቲ " ኩራ ስትሪም " ላይ 4 ዓመት ስላለፈው " ደስተኛ " አልበም ሲናገር " አልበሙን ጀምረነው ባልነው ጊዜ ያልጨረስነው እኛ በዚያ ውስጥ እየተሰራን ስለነበረ ነው " ይለዋል ። ፕሮዲዩሰሮቹ በምን በምን እንደተሰሩ አላውቅም ። ቤተልሔምን ግን በእርግጥም ሰርተዋታል ። አፈሩን ቆፍረውና አልመው ፣ አቡክተው ቤተልሔምን እንደ ውቡ ሸክላ አስጊጠው ሰርተዋታል ። እሷ እንደምትለውም ትንሿ ቤተልሔም " ከብዙ ልምምድ በኋላ የመጣ አልበም " ባለቤት እንትሆን አድርገዋታል ። ቤተልሔም ሸረፈዲን የተባለች ጥንቅቅ ፣ ጥፍጥ ያለ ስራ ያላት ድምጻዊትን ለዘመኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ( ? ) አበርክተዋል ። አሁን የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ቤተልሔም ሸረፈዲን የምትባል ብስል ፣ ትክን ያለች ድምጻዊት አለችለት ። ቤተልሔም ስለ አዲሱ አልበሟ ለኩራ ስትሪም ስትናገር " ይሄን አልበም እንደ መጀመሪያም ፣ እንደ መጨረሻም ስራ አድርጌ ነው የማየው ። " ብላለች ።
ናትናኤል ግርማቸው ገጣሚነት ተሰጥቶታል ። ገጣሚነቱ የቃላት ድርደራ ሳይሆን የሀሳብ ስፋት የታደለው ነው ። ናቲን በራሄል ጌቱ " ኢትዮጵያዬ " ነው ያወቅኩት ። የራሷን የራሄል ጌቱን " ያገሬ ሰው " ፣ በኋላም " ወረት " ን ሰርቶ አስደንቆኛል ። ናቲን በራሄል ጌቱ ( በስራዎቿ ) በኩል ነው ያገኘሁት ። ይህ ሰው ነው ደግሞ ከታምሩ አማረ ጋር ሆኖ ቤተልሔም ሸረፈዲንን ያገኛት ። ሁለቱ በፕሮዲዩሰርነት ባይከሰቱ ቤተልሔም ሸረፈዲን ቢያንስ በዚህ ጊዜ አትወለድም ። የጀርባ አቅሟን ባላውቅም የ10 ግጥም ፣ የ10 ዜማ ፣ የ10 ዜማዎች ቅንብር ፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ክፍያን አትወጣውም ( ብዬ እገምታለሁ ) ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ዘላለም ኩራባቸውን አታገኘውም ። ዘላለም ኩራባቸው ወደ ሙዚቃ ማምረት ስራ ሲገባ ከገንዘብ የነፍስ ጥሪ ትርፉን አስቦ እንደሚሆን አምናለሁ ። ካሁን ቀደም በተናጠል ሲያደርግ የነበረውን ሙያውንና ሙያተኛውን እንደ ታላቅ ወንድም አጋር የመሆን ዝንባሌውን ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶት መምጣቱ ይመስለኛል ። ቤተልሔም እድለኛ ናት ። እነ ንዋይ ደበበ ፣ ሀመልማል አባተ ፣ ጸሐዬ ዮሀንስ እና ዘመንኞቻቸው በመጡበት መንገድ ነው የመጣችው ። ሌላም እድለኛነት ( ከችሎታ ጋር ) አላት ።እነ ጠረፍ ካሳሁን ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ለምለም ኃ/ሚካኤል ፣ ዘቢባ ግርማ ተሰርተው የወጡበት " የኛ " ፕሮጀክት ፣ የእነ አይዳ አሸናፊ እጅም አርፎባታል ።
ከአስሩ የ " ደስተኛ " አልበም ስራዎች በተሸከመው ሀሳብ ( ለእኔ ) " ባለቤቴ " ን የሚያህልልኝ አላገኘሁም ። ለዚህ ዘፈን ከ " ባለቤቴ " ይልቅ " አትክልተኛው " ስምም ሆኖልኛል ። ምናልባት ግን " አትክልተኛው " ለዘፈን ርዕስነት ያንስ ( አይሆን ) እንደሆን አላውቅም ። ሙሉ ዘፈኑን ስንሰማው ገጸባሕሪዋ በምናቧ ከዋለለችለት የምናብ ባለቤቷ ይልቅ የሰው ያልሆነ ፣ ለሰው አዕምሮ " ሞኝ " የሚባል ፣ ለፍጽምና የቀረበ በዝናብም ፣ በጸሐይም ስራውን የማያስተጓጉል ፣ ብርሀን መርጦ የማይመጣ ፣ በጭለማ የማይሸሸግ ፣ የማግኘትም ፣ የማጣትም ጊዜ ወዳጅ ፣ እንደ አምላክ ያለ ብርቱ ሰው ነው ። ባለቤትነቱ ህልም ሲሆን ብርቱ አትክልተኝነቱ ግን እውን ነው ። ይህ ሰው ትትርናውና ቸርነቱ እንደ አምላክ ያለ ነው ። ከማንም ፣ ከምንም የማይጠብቅ ። መስጠት ብቻ የሆነ ። በአበቦቹ መሐል ብቻ አይደለም ያለው ። ልብ ባለበት ሁሉ ነው ።
" በዝናብ አካሉም በዶፉ እየረሰረሰ
የአትክልቶቹን ስር ሲያጠጣ የልምዱን ውሀ እያፈሰሰ
አሉት የማን ነው ጅል ያን አትክልተኛ
ሳቁበት እንደሞኝ ወይኔ
አላወቁም የእሱ ዝናብ መጣ ቀረ
ንፍገትን ለልቡ እንዳላስተማረ ።
*************************
አሰብኩት ከሆነ እንዲህ ለአትክልቱ
እንዴት መልካም ይሆን ለሚወዳት ሚስቱ "
ያለችውን ብርቱና ቸር ሰው ነው . . .
" ቢዘንብም ቢያካፋም ከጎኔ የማይጠፋ
እንደ ባለ አጸዱ ጽኑ ለመውደዱ
ሳላውቅህ ልንገርህ የነገ ውሀ አጣጬ
አርገኝ እንዳልከስም ፍቅርን ተጠምቼ "
እያለች ምኞቷን ፣ መሻቷን ፣ የወደፊት ህልሟን ትነግረናለች ። መልካምነት መስጠት ብቻ ሳይሆን መቀበልንም ይፈልጋል ። ምርጥ ዘር ምርጥ አፈርንም ይፈልጋል ። በተዘራበት ሁሉ አይበቅልም ። እንደ እሷ የሚረዳ ካልተገኘ ሌሎቹ እንዳሉት " የማነው ሞኝ ? " ያስብላል ።
በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ የዚህ የወደድኩት ብርቱ አትክልተኛ ተቃራኒ ቢሆንም የእኔ ከ1ኛ - 3ኛ " ቻው ( ዎ ) " ነው ።
" አልነበረም ከዓይን የተሰወረ
መንገድህን ሳላየው መች ቀረ
ሰነባብቷል መንፈስህ ሸፍቷል
ልቤን ልብህ ቻው ካለው ቆይቷል ።
አልታወጀም እንጂ ፊትም የእኛ ነገር
የተለያየነው አብረን ሆነን ነበር ።
እንባዬ ተማጽኖህ እንዳያስታርቀን
ያለቀው ያኔ ነው ልብህ የሄደ ቀን ።
እያንዳንዱን ቀናት በእንባ እየሰፈርኩኝ
ቻው ስልህ ኖሬያለሁ እየሸራረፍኩኝ ።
ዛሬም ለበደልህ አረከኝ ጣል ጣል
ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል ። "
ይኽ መቸም በየፍቅር ጎጆው ፣ በየትዳር ማጀቱ ፣ በየጓደኝነቱና ወዳጅነቱ አደባባይ የሚታይ የወቅቱ እውነታ ነው ። በየግንኙነታችን " ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል " ። አብዛኛዎቻችን አንድ ላይ ቆመናል እንጂ አብረን አይደለንም ። " አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል " እንዳለው ድምጻዊው ። እግሮቻችን ብቻ አብረው ይጓዛሉ ፤ አካላችን አንድ ላይ ይታያል ፤ ነፍስ የሌለው ስጋ ነው ። አብረን ውለን እናድራለን ፤ በልባችን ግን ተለያይተናል ። አልታወቀን ይሆናል እንጂ እንደ ግልም ፣ እንደ ሀገርም እንዲህ ሆነናል ። ለዚህ ነው አሁን ያለንበት ላይ ያለነው ። ለዚህ ነው በየሰበቡ ሕይወት የሚታክተን ። ለዚህ ነው መኖር ትግል ፣ አብሮነት መተናነቅ የሚሆንብን ( የሆነብን ) ። የቤተልሔም ሸረፈዲን " ቻው " ለአንድ ተፈቃሪ ወንድ የተሰራም ቢሆን ሀሳቡ ግን እዚህ ድረስም የሚመጣ ነው ። ናቲ " ቃሉ ከዜማው ጋር ነው የመጣው " ያለውና ራሷን ድምጻዊቷን አስለቅሶ የተገለጠው " ቻው " ገና ብዙውን ልብ የሚነካ ስራ ይሆናል ።
" ልቤን " ን ላልወደው አስቤ ነበረ መሰለኝ ። የእድሜም ፣ የፍላጎትም ጉዳይ ሆኖ ፈጠን ላሉ ምቶች አልደነግጥ ሆኖ ይሆናል እንጂ ምን ሆኜ ነው ዜማው ፣ ምቱ ፣ በተለይ የድምጻዊቷ አዘፋፈን ከፍ ብሎ የታየበትን ይህን ስራ " ይቆየኝ " ያልኩት ? ባልወደውና ደጋግሜ ባልሰማው ይቆጨኝ ነበር ። ( ለነገሩ ካልወደድኩት ለምን ይቆጨኛል ? ) " ደስተኛ " ርዕስና ሀሳቡ ደስተኛ ካልሆነች ፣ " አልወድሽም " ከተባለችና ከተገፋች ገጸባህሪ የተገኘ ነው ። " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ትላለች ። " አልወድሽም " ተብላና " ብትጎዘጉዝ አበባ ዛሬ አይረባ " ያለች ሴት ራሷን ማታለል ሳይሆን " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ስትል ካዋጣትና ከተቻላት ያድርግላት ። ከእሷ እንባና የልብ ስብራት ምን ጉዳይ አለን ? ብቻ ከአፏ ሳይሆን ከልቧ ይሁን ።
" እንደ ውሀ መውረድ ፣ እንደ ጸሐይ መውጣት
እንደ ጊዜው መክነፍ ፣ እንደ አሸዋ መብዛት
እውነታ መሆኑን ቅንጣት ሳልጠረጥር
እኔስ አምነዋለሁ የልብህን ፍቅር "
ያለችበት " አካልዬ " ለረጋ ያለ ሙዚቃ አፍቃሪ ይሁነኝ ተብሎ የተቀመረ ስራ ነው ። በምርጤነት ከተቀበልኳቸው መካከል አንዱ ነው ።
አንደኛው ሙዚቃ አስተያየት መስጫ ውስጥ ገብቼ ሳነብ " የዚህ አልበም ትልቁ ችግሩ ውስጡ ያሉት ዘፈኖች 10 ብቻ መሆናቸው ነው " ሲል " አድናቆቱን " ገልጿል ። እኔም እንደዚያ ሆኖ ይሰማኛል ። ከአስሩ ሰባቱን ስራዎች በልዩ ሁኔታ ወድጃቸዋለሁ ። አንዱ የዋለልኩበትና ሁለቱ ደግሞ ልብ ያልሰጠኋቸው ናቸው ። ይህ በአንድ አለበም ውስጥ ከበቂ በላይ ስኬታማነት ነው ። ከብዙ ዓመት በኋላ ተሟልቶ ያገኙሁት ምርጤ ነው " ደስተኛ " አልበም ።
እዚህ አልበም ላይ ያለኝ አንድ ( ግላዊ ) ቅሬታ አስሩም ስራዎች የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸው ነው ። እንዳይሆኑ የሚከለክል ደንብ የለም ። ፕሮዲዩሰሮቹ የቤተልሔምን እድሜና የፍቅር ጊዜዋን አስበው ያደረጉት ሊሆን ይችላል ። ያም ቢሆን በዚህ ውጥንቅጡ የወጣ የመከራ ጊዜ ፣ በብዙ ሰው ሰራሽና የአስተሳሰብ ሰንሰለት እግር ከወርች ታስረን መሔጃ ባጣንበት ዘመንና ሀገር ፣ ላለንበት ጊዜ ፣ ለስሜታችን ፣ ለህመማችን ፣ ለሰለለው ተስፋችን የሚሆን አንድ ስራ ልናጣ አይገባም ብዬ አስባለሁ ። ናቲና ምህረተአብ ለራሄል ጌቱ እንደሰጧት " ያገሬ ሰው " ያለ ስራ ቢመርቁልን እንዴት መልካም ነበረ ?
ከቀናት በፊት አስቴር አወቀ ( በድጋሚ ስራዎቿም ቢሆን ) በትንሿ ቤተልሔም ሸረፈዲን ላይ ተደርባ አልበሟን መልቀቋ አስፈርቶኝ ነበረ ። ይህን የመሰለ አልበም ፣ የ4 ዓመት የሚነገርና የማይነገር እልህ አስጨራሽ ድካም መና እንዳይቀር ሰግቼ ነበረ ። ስጋቴ ስጋት ብቻ ሆኖ ቀርቷል ። ቤተልሔም የዋርካው ጥላ ሳያርፍባት አልፋለች ። ገና ገና ትቀጥላለች ፤ ትቀጣጠላለች ።

12 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ ቲክቶክ ላይ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ዛሬ ባደረጉት ንግግር፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሚፈጠሩ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትብብሮች (Alliances) ያላቸውን አደጋ፣ አሁን ላይ ሀገሪቱ ስለሚያስፈልጋት የፖለቲካ ራዕይ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ስለሚኖረው ቀጠናዊ ትስስር ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ንጉሡን፣ በመቀጠልም ደርግን ለመጣል የተፈጠሩት የፖለቲካ ትብብሮች ጊዜያዊ ጠላትን ከማስወገድ ባለፈ ዘላቂ መፍትሄ እንዳላመጡ አቶ ጃዋር ተናግረዋል። ደርግን ለመጣል የተፈጠረው ትብብር የአማራውን ልሂቅ በማግለሉ አዲስ የፖለቲካ ትርክት እንደወለደ ሁሉ፤ ከ2018 እስከ 2020 የነበረው ትብብርም ትግራይን በማግለሉ ሀገሪቱን ወደ ጦርነት ማስገባቱን አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅትም የማዕከላዊ መንግሥቱን ውድቀት ተከትሎ "አብይን ለመጣል" ብቻ ተብለው የሚፈጠሩ ትብብሮች ከፍተኛ አደጋ እንዳላቸው ያስጠነቀቁት ፖለቲከኛው፣ የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ከመጣል ባለፈ፣ ከአብይ አህመድ ወይም ከብልጽግና በኋላ የምትመጣው ኢትዮጵያ ምን ዓይነት አስተዳደር እና ማህበራዊ አደረጃጀት ይኖራታል በሚለው ዘላቂ ራዕይ ላይ አስቀድመው ሊወያዩ እና ስምምነት ላይ ሊደርሱ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ ወደ ሌላ አዲስ የትርምስ አዙሪት ውስጥ እንደምትገባ አስጠንቅቀዋል።
የፖለቲካ ምህዳሩ መዘጋት እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ ባነሱት ሀሳብ፣ የፖለቲካ መድረኩ ዝግ በሚሆንበት ጊዜ የሰላማዊ ትግል አማራጭ ቦታውን ለጠመንጃ እንደሚያስረክብ ገልጸዋል። የትጥቅ ትግል የጀመረ ማንኛውም ኃይል ደግሞ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ከሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር ለመተባበር እንደሚገደድ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የውስጥ ቀውሶች ለግብጽ የውጭ ፖሊሲ ትልቅ ክፍተት መፍጠራቸውን የጠቆሙት አቶ ጃዋር፣ ግብጽ የኢትዮጵያን የውስጥ ቀውስ የማባባስ፣ ከጎረቤት ጋር የማጋጨት እና ዓለም አቀፍ ፋይናንስ እንዳታገኝ የማድረግ ስትራቴጂን እየተከተለች መሆኗን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሱዳን ጉዳይ ላይ የተከተለችው የተሳሳተ አካሄድ፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ አማጺያን እና ከኤርትራ ጋር እንድትሰለፍ መግፋቱን ተናግረዋል።
ከኤርትራ ጋር ሊኖር ስለሚገባው ልዩ ግንኙነት ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጃዋር፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን እንደ ባዕድ ሀገር ማየት ስህተት መሆኑን ጠቅሰው፣ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ያላለቀ ፍቺ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት የሀገረ-መንግሥት ግንባታ እና የደህንነት ስጋት እስካልተፈታ ድረስ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ሰላም እውን ሊሆን እንደማይችል አስምረውበታል። የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚ እና ሰላም በእጅጉ የተሳሰረ መሆኑን በማንሳትም፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያድግ በምስራቅ አሰብን፣ በሰሜን ደግሞ ምጽዋን ማግኘት ግድ እንደሚለው ሁሉ፤ በኤርትራ በኩልም ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ የኢትዮጵያን ሰፊ ገበያ ማግኘት የግድ እንደሚያስፈልጋት አስረድተዋል።
ይህ ትውልድ ከቀድሞዎቹ የኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ህወሓት የፖለቲካ ትርክቶች ወጥቶ በሰፊ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ትስስር ላይ ሊያስብ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። አሜሪካ እና እንግሊዝ እንዳላቸው ዓይነት ልዩ ግንኙነት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊገነባ እንደሚገባ ያሳሰቡት ፖለቲከኛው፣ የሁለቱ ሀገራት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የደህንነት ጉዳዮች ቀስ በቀስ ካልተሳሰሩ በስተቀር ሁለቱም ሀገራት የህዝባቸውን ህልም ማሳካት እንደማይችሉ አስጠንቅቀዋል።

13 days ago
የባሕር በር…የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በታሪክ የግዛቷ አካል የነበረውን እና በሴራ ያጣቸውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ ነው፡፡
ታሪክ እንደሚያስረዳው በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የአዱሊስ ወደብ የዓለም አቀፍ ንግድ ማዕከል የነበረ ሲሆን ፥ በቀጣዮቹ ዘመናትም ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷ በምጽዋና አሰብ ወደቦች መዝለቅ ችሎ ነበር።
በቀጣናው የባሕር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ እጅግ ጥንታዊ የታሪክና የስልጣኔ አሻራ አኑራለች፡፡ ሆኖም በታሪክ አጋጣሚ በተወሰነ የፖለቲካ ውሳኔና የጠላቶች ሴራ ምክንያት ከታሪካዊና ሕጋዊ በሯ ከተነጠለች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ በጣም የሚያስቆጭ ፤ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ለፍትሕ የቆመ ማንኛውም ሰው ይህንን ሀሳብ የሚጋራው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ወደብ አልባ ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ እውነታ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና በትውልዱ ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ከዚህ በፊት የነበረው መንግሥት ይህን ጫና ለመከላከል እና የባሕር በር ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ካለመኖሩ በተጨማሪ ትውልዱ ኢትዮጵያ ያጣቸችውን የባሕር በር በተመለከተ ግንዛቤ እንዳይኖረው አድርጎ አልፏል፡፡
በተለይ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የመጣው ትውልድ በልዩ ሁኔታ በራስ ጥረትና ንባብ ከተረዳው ውጪ አብዛኛው ወደብ የባሕር በር፣የባሕር ሃይል እንዲሁም ባሕር ላይ ስላለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግንዛቤ የለውም፤ እንዲያውቅም አልተደረገም፡፡
በዚህም ትውልዱ የወደብ አልባነት ትርክት ሰለባ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይሁን አንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባህር ጉዳይን ፊት ለፊት እንነጋገርበት ብለው በአደባባይ ይፋ ካደረጉ በኋላ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ በመሆኗ የሚቆረቆር ትውልድ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ጥያቄ የራሴ ሉዓላዊ የባሕር በር ይኑረኝ ፤ ወደብና የመተላለፊያ ኮሪደር በሰላማዊ መንገድና በስምምነት ለማግኘት በሚደረግ ጥረት እንጂ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ግዛት ባለቤትነት የመጠየቅ ጉዳይ አይደለም።
በሰጥቶ መቀበል፣ መሬት ወይም ሌላ ሀብት በመለዋወጥ የባሕር በር ያገኙ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ በቅን ልቦና እና በትብብር መንፈስ ለሚረዳ ማንኛውም ወገን የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሸፍጥ እንደሌለበት መገንዘብ ቀላል ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የታሪክ ብቻ ሳይሆን የነባራዊ እውነታ፣የህጋዊ ባለቤትነት እና የሕልውና ጉዳይ ሲሆን÷ ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ፣ የባሕር በር ተደራሽነት የቀን ፖለቲካ ክርክር ሳይሆን የረጅም ጊዜ የልማት ስትራቴጂ እቅድ አካል ሊሆን ይገባዋል።
በመሆኑም ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን በመከተልና ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ፤ ኢትዮጵያውያንን እንደ ሕዝብ አንድ የሚያደርግ አጀንዳ አድርጎ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው

"በዚህ በቀይ ባህር፣ ኤርትራ ረጅም የባህር በር ያላት ሀገር ናት። የቀይ ባህርን ዳርቻ መቆጣጠር የምትፈልግ፣ የወቅቱ የመካከለኛው ምስራቅ ኃያል ለመሆን ግብግብ ውስጥ እየገጠመች ያለች ሀገር አለች፣ አረብ ኤምሬት የምትባል ሀገር። ስለዚህ ኤርትራ ላይ የጠላትነትን እንዲሰለፍ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ሳይሆን የአረብ ኤምሬትስ ኢንተረስት (ፍላጎት) ነው። በዚህ ምክንያት... አረብ ኤምሬት እኮ የአሰብ ወደብን ለማልማት ወስዳ ነበር። በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በሰዓታት፣ 48 ሰዓት እንደዚህ አካባቢ ነው ለቃችሁ ውጡ የተባሉት። ያልሆነ ነገር ሲያደርጉ ተገኝተው ይመስለኛል - ያው ግልጽ ባይደረግም ብዙ ጊዜ። የአረብ ኤምሬትን ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲል ነው ከኤርትራ ጋር እዚህ ውስጥ የገባው"
የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ከኢኤምኤስ ሚዲያ ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ
የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ከኢኤምኤስ ሚዲያ ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ
15 days ago
የአፋር ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአሰብ እውነታ
***************
ከዳህላክ እና ምጽዋ ጀምሮ እስከ ታጁራ ድረስ ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ በተዘረጋው የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ በመሃል ሌላ ማኅበረሰብ ሳይኖር ብቸኛ ነዋሪ የሆነው የአፋር ሕዝብ፣ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ እና ከተፈጥሮ መኖሪያ ምድሩ የተነጠለው በፍላጎቱ አልነበረም።
ይህ ሰፊ የባሕር ጠረፍ የሕዝቡ ተፈጥሯዊ መተንፈሻ እና የህልውናው መሠረት ቢሆንም፣ በፖለቲካዊ ሤራ ከባሕሩ እና ከወንድሞቹ እንዲገነጠል መደረጉን ኢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ያሰናዳው ዘጋቢ ፊልም ይገልጻል።
በወቅቱ የአፋር ሕዝብ መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በጊዜው የተደረገውን አፋርን ለሁለት ቆርጦ የመገንጠል ድርጊት አጥብቀው ተቃውመውት ነበር።
ሱልጣኑ የኤርትራ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት አለው በሚል የአፋርን ሕዝብ ለሁለት በከፈለው የኤርትራ ሪፈረንደም ላይ የአፋር ሕዝብ ጥያቄ እንዳለው ጠቅሰው፣ "አፋር ከኢትዮጵያ ጋር ነው የሚገናኘው" በማለት በግልጽ ሞግተዋል።
የአፋር ቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ እንደሚሉት፣ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በወቅቱ አፋርን ለሁለት ከፍሎ የመገንጠልን ድርጊት በጽኑ ተቃውመዋል።
የአፋሮች መኖሪያ የሆነው የአሰብ አካባቢ እንዳይለማ እና እንዲራቆት መደረጉን የሚጠቅሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ይህ የተደረገው አፋር ኢትዮጵያዊነቱን ስለሚያውቅ አንድ ቀን መመለሱ አይቀርም ብለው ስለሚፈሩ እንደሆነ ይናገራሉ።
የቀድሞ የአሰብ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሊ ኢሳ መሐመድ፣ ሱልጣኑ "ዴሞክራሲ ከሆነ ኤርትራ ላለው የአፋር ሕዝብ ለምን የመምረጥ ዕድል አይሰጠውም?" ብለው ሲናገሩ፤ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተው እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ ምላሽ በማጣቱ ሱልጣኑ ሀገር ለቅቀው እንዲወጡ ተገደዱ፤ አፋርም ሳይወድ በግድ ተከፈለ።
ኤርትራ ነጻ ሀገር ከሆነች በኋላ በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ የደረሰው ሰቆቃ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ከተፈጥሮ ምድሩ ማላቀቅ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ።
አቶ ሀቢብ መሐመድ እንዳብራሩት፣ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የነበራቸው ድብቅ አጀንዳ አፋርን ከቀይ ባሕር ጠረፍ ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ነበር።
የተፈለገው መሬቱ እንጂ ሕዝቡ ባለመሆኑ ማፈናቀል፣ ግድያ እና ንብረት መውረስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተፈጽሟል።
ከማፈናቀል ባለፈ ወጣቶችን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ካምፕ በግድ በመውሰድ፣ ባህላቸውን እንዲረሱ የማድረግ የማንነት ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።
የአፋር ቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን እንደሚሉት፣ ሳዋ የባህል እና የቋንቋ መጥፊያ ሲሆን፤ ሕዝቡ ሀገሩን ለቅቆ እንዲሄድ፣ የቀረው ደግሞ ቋንቋ እና ባህሉን እንዲተው ተገድዷል።
አሊ ኢሳ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በአካባቢው የነበረው የአፋር ሕዝብ ተፈጥሯዊ የዓሣ ማጥመድ ሥራ በማፊያዎች እና በሕገወጥ መረቦች እንዲወድም ተደርጓል።
ዓሣ የሚኖርበትን እና ኮራል ያለበትን አካባቢ ጠራርጎ በሚወስድ መረብ ባሕሩ እንዲቀየር ከመደረጉም በላይ፣ ማፊያዎች ሚሊዮን ዶላሮች እየተቀበሉ መርዛማ ቆሻሻዎችን ባሕሩ ውስጥ እንዲጥሉ ተደርጓል።
አፋሮች በተፈጥሮ ሀብታቸው እንዳይሠሩ መከልከላቸው እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር መዳረጋቸውም የዚሁ ግፍ አካል ነው።
የቀድሞው የአሰብ ምክትል ከንቲባ ለ13 ዓመታት ያለ ፍርድ መታሰራቸውን ገልጸው፣ ጉዳያቸው ለባህላዊው የአፋር ፍርድ (መድዓ) እንዳይቀርብ መከልከሉም የሕዝቡን ሕግ እና ባህል ለማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።
የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌ/ጄኔራል ጻድቃን ገ/ተንሣይ እንዳብራሩት፣ የባህላዊው አውሳ ሱልጣኔት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
ምንም እንኳን አርቲፊሻል ድንበሮች ተሰምረው ሕዝቡን ከባሕሩ ቢያርቁትም፣ የአፋር ሕዝብ ማዕከል ምንጊዜም ኢትዮጵያ መሆኗን ጄኔራል ጻድቃን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህን እውነት ሲያጠናክሩ፣ የኤርትራም ሆነ የጅቡቲ አፋሮች በውክልና መጥተው ባህላዊ መሪያቸውን የሚመርጡት አሳይታ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአውሳ ሱልጣኔት ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አስምረውበታል።
ከሰላሳ ዓመታት ዝምታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰብን ጉዳይ ማንሳታቸው በአፋር ሕዝብ ዘንድ የፈጠረውን ወደር የለሽ ደስታ በተመለከተ ሀቢብ መሐመድ ሲገልጹ፣ "የአፋር ስሜቱ ገንፍሎ ወጥቷል፤ ከልክ በላይም ተደስቷል" ብለዋል።
ጥያቄያችን የዴሞክራሲ አይደለም የሚሉት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን፣ ምክንያቱንም ሲያስረዱ "የአፋር ሕዝብ ይኖራል ወይስ አይኖርም?" የሚል የሕልውና ትግል ውስጥ በመገባቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የተነጠቀውን ጠረፍ በመመለስ የአፋርን አንድነት ማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን እንዲሁም ታሪክን ከመደለዝ መታደግ የአፋር ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ሊቀመንበሩ ያብራራሉ።
የቀይ ባሕር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከማንም በላይ ጥቅሙ የአፋር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ባሕሩ ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ አፋር አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #afar #seaaccess #seaport #redsea #assab #hornofafrica #ebc

Sponsored by
Surafel
18 days ago
u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12a0u1230u1265u1295 u1260u121bu1323u1277 u1265u127b u1260u12e8u1240u1291 u12a85 u121au120au12eeu1295 u12f6u120bu122d u1260u120bu12ed u1273u12c8u1323u1208u127d
#redsea #ethiopia Ethiopian Broadcasting Corporation","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"User","__isEntity":"User","__isActor":"User","id":"100064325666044","url":"https://www.facebook.com/E... Broadcasting Corporation","work_info":null,"__module_operation_CometTextWithEntitiesRelay_textWithEntities":{"__dr":"ProfileGeminiWeakReferenceLink_user$normalization.graphql
ኢትዮጵያ አሰብን በማጣቷ ብቻ በየቀኑ ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች
#redsea #ethiopia Ethiopian Broadcasting Corporation
1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) እ.ኤ.አ ጁን 2026 በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተባባሪነት የተቋቋመው “Pulse of Africa” የተሰኘው ሚዲያ አንድ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ተቋም ከአንድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የዲፕሎማሲ አካዳሚ ጋር ስምምነት መፈራረማቸውን የሚገልጽ ዜና አውጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ዜናው ስምምነት ያደረጉትን ተቋማት ስም ሆን ብሎ የደበቀ እና እጅግ አሻሚ ቃላትን የተጠቀመ መሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። በኤምሬትስ በኩል ያለው ተቋም አንዋር ጋርጋሽ የዲፕሎማሲ አካዳሚ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ የምርምር እና የስልጠና ተቋም የሆነው የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ነበር። ዜናው የተፈረመበትን ሂሊ ክልላዊ የውይይት መድረክ ሳይቀር ዝም ብሎ አንድ ክልላዊ መድረክ በማለት ሸፍኖታል።
በአንጻሩ የኤምሬትሱ ጋርጋሽ አካዳሚ በዲጂታል መድረኮቹ ላይ ስምምነቱን በይፋ እና በዝርዝር አውጥቶታል። የስምምነቱ ዓላማም በሁለቱ ወገኖች መካከል በውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ምርምር እና ጥናቶችን ማካሄድ፣ ስትራቴጂካዊ ውይይቶችን ማደራጀት፣ የዲፕሎማሲ አቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን መስጠት እና የባለሙያዎች ልውውጥ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል። ይህ ክስተት ብዙዎችን ያነጋገረው፣ ሚዲያው የተቋቋመው ስለ አፍሪካ የሚነገሩ አሉታዊ ትርክቶችን ለመቀልበስ እና አህጉሪቱ ከውጭ ሞግዚትነት ነጻ የሆነ የራሷን ትርክት እንድትቀርጽ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ ከተናገሩ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ለኤምሬትስ ጥቅም ሲባል መረጃዎችን መደበቁ ነው።
ተንታኞች እንደሚሉት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ዜናውን የደበቀበት ምክንያት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምርምር ክንፍ ከኤምሬትስ አካዳሚ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያገኘ መሆኑን በይፋ ማመኑ፣ መንግስት ከሚገነባው የብሔራዊ ኩራት እና የነጻ ውሳኔ ሰጪነት ትርክት ጋር ስለሚጋጭ ነው።
ይህም የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግንኙነት ከትብብር አልፎ ወደ ስትራቴጂካዊ ጥገኝነት እያመራ መሆኑን እንደሚያሳይ ባለሙያዎች ይሞግታሉ። ይህ የጥገኝነት መዋቅር በዋናነት የተገነባው በፋይናንስ፣ በወታደራዊ ሎጅስቲክስ እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ነው። በ2018 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ሀገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስትታመስ፣ አቡ ዳቢ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ3 ቢሊዮን ዶላር ተቀማጭ በማድረግ ትልቅ የፋይናንስ ድጋፍ አድርጋለች። በ2021 የትግራይ ጦርነት በተባባሰበት እና የአዲስ አበባ መውደቅ ስጋት በነበረበት ወቅት ደግሞ፣ ኤምሬትስ ድሮኖችን እና ወታደራዊ ትጥቆችን በማቅረብ የጦርነቱን ሚዛን ለመቀልበስ ወሳኝ ሚና ተጫውታለች። ከዚህም በተጨማሪ በኢነርጂ፣ በግብርና፣ እና የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ከኤምሬትስ ወደብ አስተዳደሮች ጋር በማስተሳሰር ረገድ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተደርጓል።
አሁን የተፈረመው የዲፕሎማሲ ስልጠና ስምምነትም፣ የዚህ ጥገኝነት አራተኛው እና ረቂቁ ምዕራፍ መሆኑ ይገለጻል። ይህም ኤምሬትስ የኢትዮጵያን ቀጣይ የዲፕሎማት ትውልድ በመቅረጽ እና የውጭ ፖሊሲዋ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ በማሳረፍ የረጅም ጊዜ ፍላጎቷን እያስጠበቀች መሆኑን ያመላክታል። በተጨማሪም ባለፈው ጥር ወር ሚድል ኢስት አይ ባወጣው የምርመራ ዘገባ፣ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አማካሪ የነበሩ ግለሰብን ጠቅሶ፣ ኢትዮጵያ በሱዳን፣ በቀይ ባህር (አሰብ ወደብ)፣ እና በኤርትራ ጉዳይ ላይ ከኤምሬትስ ውጭ የራሷን ነጻ ውሳኔ ማሳለፍ እስኪያቅታት ድረስ ጫና ውስጥ መውደቋን አስነብቧል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ገለልተኛ የውሳኔ ሰጪነት ሚና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።

2 months ago
ሰላም፣ ደህና አደራችሁ?
ታሪክና መልክዓ ምድር ያቆራኛቸው የኢትዮጵያና የቀይ ባሕር ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ ከቅርብ አሥርት ዓመታት ወዲህ ግን ይህ እውነታ ተቀይሮ ቆይቷል።
በታሪካዊ ስሕተቶችና በሴራ መንገዶች የባሕር በሯን ያጣችው ኢትዮጵያ ጉዳዩን ማንሳት እንኳን እንደ ነውር ወደሚቆጠርበት የስነ-ልቦና ስብራት ውስጥ ገብታ ነበር።
ይህ ሁኔታ ሀገሪቱ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እና ለደህንነት ስጋት እንድትጋለጥ አድርጓታል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የባሕር በር ጉዳይ ከነበረበት የመዘንጋት አዙሪት ወጥቶ የብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ አጀንዳ ወደ መሆን ተሸጋግሯል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለት ውሃዎች (የዓባይ ወንዝ እና የቀይ ባሕር) ፖሊሲን ይፋ በማድረግ ይህንን ታሪካዊ፣ ሕጋዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አዳዲስና ቁርጠኛ እንቅስቃሴዎች በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ይሁንታ እየተቸረው ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባሕር በር ጉዳይን የብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ሀገራዊ አጀንዳ እንዲሆን በማድረግ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እንዲቆሙ መንገድ ጠርገዋል።
የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚበይኑትን የዓባይ ወንዝ እና የቀይ ባሕር ጉዳይን በተመለከተ የሁለት ውሃዎች ፖሊሲን ይፋ አድርገው ኢትዮጵያ በሴራ ያጣችውን የባሕር በር በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለማስመለስ የሚያስችል እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል።
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተዋሳኝነቷን ስታጣ በሰነድ የተደገፈ ምንም ዓይነት ማስረጃ አለመኖሩ ውሳኔው ሕጋዊ እንዳልሆነ እና ኢትዮጵያ በብዙዎች ርብርብ የባሕር በር ማጣቷን ያሳያል።
በባህር በር ጉዳይ መጠየቅ ነውርና ትክክል እንዳልሆነ የሚመለከት ትርክት በመፈጠር የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ መሆኑን ለመጋረድ ቢሞክርም አሁን ላይ በሰከነ መንገድ በውይይት የባሕር በር ማግኘት እንደሚቻል ግልጽ እየሆነ መጥቷል።
5 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የቀይ ባሕር ከ20 ሚሊየን የማይበልጥ ህዝብ ባላቸው ሀገራት መሸፈኑ ፍትሃዊ አለመሆን፥ ቀይ ባሕር እና ኢትዮጵያ ለዘለዓለሙ ተነጣጥለው መኖር እንደማይችሉ የሚያመላክት ነው።
130 ሚሊየን ሕዝብ የያዘችው ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ድርሻ ሊኖራት ግድ በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን ለማረጋገጥ የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ ማግኘት አለበት።
ለዚህ ደግሞ መፍትሔው ጦርነት ሳይሆን ውይይትና ዲፕሎማሲ ቀዳሚው አማራጭ ሆኖ በስፋት እየተሰራበት ይገኛል።
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል የአሰብ ወደብን ለማልማት በተደጋጋሚ ንግግር ቢደረግም ከኤርትራ መንግሥት በኩል ምላሽ ለመስጠት ዝግጁነት የለም።
የባሕር በር ጉዳይ በውይይት እንዲሁም በገበያ ህግ ድርድር እልባት እንዲያገኝ አቋም ያላት ኢትዮጵያ፤ የባሕር በር የማግኘቷ ጉዳይ አይቀሬ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ማንም ፈለገም አልፈለገም ኢትዮጵያ ተዘግታ አትኖርም።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት የሀገርን ኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የሚወስን ቁልፍ የብሔራዊ ጥቅምና የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የቤት ስራ አለባቸው።

ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተገኝተው ጉዳት የደረሰባቸውን ኦርቶዶክሳዊያን የሚያጽናኑ ብፁዓን አባቶችን መደበ።
የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው በችግሩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ፣በብፁዓን አባቶች የሚመራ የቤተ ክርስቲያናችን ልዑካን ቡድን ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቦታ በመሄድ ተጎጂዎችን እንዲጎበኝ፣ እንዲያጽናና እና አሰብ ፈላጊውን ጊዜያዊ ድጋፍ አንዲያደርግ ወስኗል።
ቋሚ ሲኖዶስ በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል በሚቋቋም
ኮሚቴ አስተባባሪነትም በተፈጠረው ችግር ምከንያት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት ጥንታዊው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲያሰራ፣ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በቋሚነት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ፣ በሀገረ ስብከቱ ዳግመኛ መሰል ችግሮች እንዳይፈጠርሩ ጥናት አካሒዶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ዐቢይ ኮሚቴ ተሰይሞ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

3 months ago
የባሕር በር ትንሳዔ፦ የኢትዮጵያ አዲሱ የብልጽግና መንገድ
*************
የባሕር በር ለአንድ ሀገር የሉዓላዊነት፣ የክብር፣ የስትራቴጂክ ጠቀሜታ እንዲሁም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አቅም ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።
የባሕር በር ከሌለ ገበያው የጎረቤት ሀገር ብቻ ሲሆን፣ ወደብ አልባ ሀገራትም የጎረቤቶቻቸው እስረኞች ለመሆን ይገደዳሉ።
ደማቁ የታሪክ ማህደር፦ ከአዱሊስ እስከ ዜይላ
ኢትዮጵያ በረዥም ታሪኳ የባሕር በር ባለቤት የነበረች እና በራሷ ከዓለም ጋር ስትገበያይ የኖረች ሀገር መሆኗን የታሪክ ማስረጃዎች በሚገባ ያሳያሉ።
በሀገራችን ወደብ በተደራጀ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው ገና በአክሱማውያን ዘመን ነበር።
አክሱማውያን እና ከእነሱ በፊት የነበሩት የዳማት ነገሥታት በአዱሊስ ወደብ በመጠቀም ከግሪክ እና ከባዛንታይን ነገሥታት ጋር ይገበያዩ ነበር።
በዚህም የዳማት ልዑላን እና አክሱማውያን ነገሥታት እጅግ እንደከበሩ እና መንግሥታቸውንም ገናና ያደረጉት ከዚህ ንግድ በሚገኝ ገቢ እንደነበር ፕላይኒ ትልቁ በጽሁፉ አብራርቷል።
የአክሱም መንግሥት መዳከም ኢትዮጵያን የባሕር በር አላሳጣትም ነበር። የዛግዌ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ላሊበላን ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቋቋሙት መንግሥታት የምጽዋን ወደብ ለፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ፍላጎታቸው ማሳኪያነት ይጠቀሙበት ነበር።
በኦቶማን ቱርኮች ጫና ሲፈጠር ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፊታቸውን ወደ ሕንድ ውቅያኖሷ ዜይላ ወደብ በማዞር የአርጎባ ሕዝቦችን በመጠቀም ዜይላን የኢትዮጵያ ዋና ወደብ አድርገውት ነበር።
በኋላም ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከፈረንሳይ ጋር ባደረጉት ስምምነት ጅቡቲን በሚገባ ተጠቅመውባታል።
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እ.አ.አ በ1876 ዓ.ም ለንጉሥ ኡምቤርቶ በላኩት ደብዳቤ የዜይላን በር ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ኢትዮጵያውያን በየዘመናቱ የባሕር በር ባለቤትነታቸውን ለማስከበር ያደረጉትን ዲፕሎማሲያዊ ትግል ያመላክታል።
ይህ የሚያሳየው፣ ሀገራችን በውጭ ኃይሎች ወረራ ተግዳሮት ቢገጥማትም፣ በየጊዜው የተፈራረቁት ነገሥታት የባሕር በርን ለማስከበር ሁለገብ ትግል ከማድረግ የቦዘኑበት ጊዜ አለመኖሩን ነው።
የቀይ ባሕር ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍልሚያ
ዛሬ ላይ የቀይ ባሕር አካባቢ ከፍተኛ የዓለም ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚደረግበት እና በርካታ ሀገራት ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ስትራቴጂያዊ ቀጣና ሆኗል።
በቀጣናው ያሉ ኃያላን ሀገራት ከባሕር ውንብድና ጋር በተያያዘ በሚል ሰበብ በጅቡቲ ላይ ወታደራዊ ካምፕ መስርተው ከከተሙ ቆይተዋል።
እነዚህ ኃያላን ሀገራት ግዙፍ ወታደራዊ ሰፈሮችን የገነቡ ሲሆን፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን እና ዘመናዊ የጦር መርከቦችን በቀጣናው አሰማርተዋል።
ከሩቅ ከሚመጡት ኃያላን በተጨማሪም የቅርብ ሀገራትም ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር እጅግ በተወሳሰበ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
ይህ የኃያላኑ ፉክክር በቀጣናው ሊፈጥር የሚችለው ግጭት ለኢትዮጵያና ለመሳሰሉት የአካባቢው ሀገራት ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት የደቀነ ነው።
ፍትሐዊ ያልሆነው እጣ ፈንታ
አሰብ በደቡባዊ ቀይ ባሕር ጫፍ የሚገኝ ወደብ ሲሆን፣ ኤርትራ ነፃ በወጣችበት ጊዜ አሰብ የኤርትራ አካል አልነበረችም፤ ይልቁንም ራስ ገዝ አስተዳደር ነበረች።
ሆኖም ኤርትራ አሰብን በሕገ-ወጥ መንገድ በመጠቅለሏ ኢትዮጵያ የባሕር በሮቿን ተነጥቃ በዓለም በህዝብ ቁጥር ትልቋ ወደብ አልባ ሀገር ሆናለች።
በኢትዮጵያ ወሰን እና በቀይ ባሕር መካከል ያለው ርቀት ከ60 ኪሎ ሜትር ያነሰ ቢሆንም፣ የሀገራችን ወጪ ንግድ እና ስትራቴጂያዊ ደኅንነት ግን በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል።
ፕሮፍሰር ያዕቆብ ኃይለማርያም በመጽሐፋቸው እንደሚያስረዱት፣ በሕዝብ ብዛት ግዝፈቷ እና ለባሕር ባላት ታሪካዊ ቅርበት ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሀገር መሆን አይገባትም።
የአልጀርሱ ሥምምነት የወደብ ባለቤትነት መብትን ለማስከበር ጥሩ አጋጣሚ የነበረ ቢሆንም፣ ጥያቄው ሳይነሳ መቅረቱ ለወደፊቱም የሰላም ጠንቅ ሊሆን የሚችል ጉዳይ ነው።
የማዕበል ሽውታ እና የባሕር ጠረን ለዘመናት የኢትዮጵያ የነፃነት እና የብልፅግና ታሪክ አካል ነበሩ።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ያለፈችባቸው መነሳት እና መውደቆች ከባሕር ጋር ከነበራት ቅርበት እና ርቀት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው።
የባሕር በሮቿ በእጇ በነበሩበት ዘመን የጎለበተች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን መመስረት የተቻለ ሲሆን፣ በሯን በተነጠቀችበት ጊዜ ግን ኢኮኖሚዋ የኮሰሰና ፖለቲካዋ የተናጋ ሆኗል።
በእርግጥም የባሕር በር ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና አለው።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆን የሚገባት ታላቅ ሀገር ናት። ታሪካዊ መብቷን፣ የሕዝብ ብዛቷን እና እየተወሳሰበ የመጣውን የቀይ ባሕር ጂኦ-ፖለቲካዊ ስትራቴጂ ግምት ውስጥ በማስገባት የባሕር በርን ማረጋገጥ የቅንጦት ሳይሆን የሥልውና ጉዳይ ነው።
የአሁኑ ትውልድ ያለፈውን ደማቅ ታሪክ ጠንቅቆ በመረዳት፣ በቀጣናው ካሉ ጎረቤቶቹ ጋር በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርቶ፣ የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ዳግም ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ ተነስቷል።
የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በየብስ ላይ ብቻ ሳይሆን በባሕርም ላይ የተፃፈ ነው። ይህን ታሪካዊ አደራ ከዳር ማድረስ የትውልዱ ጽኑ ቃል ኪዳን ነው።

(ዘ-ሐበሻ ዜና | አዲስ አበባ) የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት፣ ታጣቂዎችን ማገዙ እና ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት አለማስወጣቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና የጋራ ብልጽግና ዋነኛ እንቅፋት መሆኑን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድራፊ አባራያ "የኤርትራ አጣብቂኝ እና የኢትዮጵያ ምርጫ" በሚል ርዕስ ባወጡት አዲስ እና ሰፋ ያለ ትንታኔ፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር በቀጠናው እየተጫወተ ያለውን አፍራሽ ሚና በዝርዝር አጋልጠዋል።
ባለስልጣኑ በትንታኔያቸው እንዳስገነዘቡት፣ ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ህዝቧ የልማት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት እያስመዘገበች ያለውን ከ9 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ይሁን እንጂ የኤርትራ መንግስት ታጣቂዎችን (በተለይም የህወሓትን ጽንፈኛ አንጃዎች) በገንዘብ፣ በሎጂስቲክስ እና በወታደራዊ አቅም በመደገፍ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት እንዲያፈርሱ ከፍተኛ ግፊት እያደረገ ይገኛል።
ዘገባው አክሎም፣ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ልክ እንደ ሀገር መሪ ሳይሆን እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ በኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ላይ መግለጫዎችን መስጠታቸው አባዜ እንደሆነባቸው ጠቅሷል። ከዚህም ባሻገር "የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መንቀሳቀሳቸው እና መሬት ይዘው መቆየታቸው" የሀገሪቱን ድርጊት አደገኛ ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ተመላክቷል።
በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን እንድትጠቀም ኤርትራ ቃሏን ማጠፏ የሎጂስቲክስ አማራጮችን አጥቧል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩቱ ትንታኔ እንደሚያስረዳው፣ ኤርትራ ይህንን ወደብ የዘጋችው ከምክንያታዊ የኢኮኖሚ ስሌት ይልቅ በቂም በቀል ስሜት ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወጣቶቻቸው የባህር በሩን ተጠቅመው በብዛት እንዳይሰደዱ በመስጋት ሆን ብለው የወደቡን አዋጭነት እንዳዳከሙት አብራርቷል።
ከሁሉም በላይ ለቀጠናውም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ ስጋት ተደርጎ የተቀመጠው ግን፣ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህልፈት ወይም ከስልጣን መውረድ በኋላ ያለው የኤርትራ ዕጣ-ፈንታ ነው። ሀገሪቱ የሚሰራ ህገ-መንግስት፣ ፓርላማም ሆነ የተሰየመ ምትክ መሪ የሌላት "ባዶ ሀገር" (Shell state) መሆኗ ተጠቁሟል። ይህ የተቋማት ክፍተት ደግሞ ኤርትራን ለአል-ሸባብ እና አይኤስአይኤስ (ISIS) ጽንፈኛ ቡድኖች መፈልፈያ ሊያደርጋት እንደሚችል እና የቀይ ባህርን ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ምንም እንኳን የኤርትራ አመራር በ20ኛው ክፍለ ዘመን ኋላቀር ትርክት ውስጥ የተቆለፈ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ውጥረቶችን በዲፕሎማሲ እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል። ሆኖም ይህንን እምነት እና መተማመን እንደገና ለመገንባት የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት ሙሉ በሙሉ እንዲያስወጣ በሚል የኢትዮጵያን መንግስት አቋም እና ቅድመ ሁኔታ ትንታኔው አስቀምጧል።

ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ዓለማችን የተከበበች እና 71 በመቶዋም የውኃ አካል ሆኖ እያለ ኢትዮጵያችን ለምን የባህር በር ተነፈገች? ውኃ እንዲህ በበዛበት ዓለም ላይ እያለን፣ ለምን ከባህር በር ተገለልን?
ከቀይ ባህሩ የአሰብ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ እያለን ለምን ውኃውን እንዳናይ ተከልክለን የጂኦግራፊ እስረኛ ሆንን?
ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ ሲነወር የቆየ የባህር በር ጥያቄ አላት፡፡ ጥያቄው የብሔራዊ ጥቅም፣ የደህንነትና ህልውና ጉዳይ ነው፡፡
የባህር በር ከባህር ላይ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶችንና ተጋላጭነትን ለመከላከል ያግዛል፡፡
አሁን አሁን በቀይ ባህር ቀጣና በርካታ ኃያላን የኃይል ፉክክርና ጂኦ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል፡፡
አይበለውና ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር አጥፊ የህልውና ሥጋት የሆነ የጦር መሣሪያ ቢጠመድባት፣ የባህር በር ስለሌላት እንዴት አድርጋ ነው ራሷን መከላከል የምትችለው?
ዓለም የባህር በር ተጠቃሚነት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጋለች፡፡
ለዚህ መፍትሄ ይሆናል የተባለው የዓለምን የባህር በር አጠቃቀም የሚወስነው የተባበሩት መንግሥታት የባህር አጠቃቀም ስምምነት በፈረንጆቹ 1982 ነበር ለሀገራት ፊርማ ይፋ ሆኖ በ1994 ወደ ሥራ የገባው፡፡ ኢትዮጵያም ሕጉን በፈረንጆቹ 1984 ፈርማለች፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ ለሕጉ ተገዢ ብትሆንም እንደ ኤርትራ፣ አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ሶሪያን ጨምሮ 15 የዓለም ሀገራት ስምምነቱን አልፈረሙም፤ በነጻነት ግን ይጠቀማሉ፡፡
በዓለም አቀፉ ሕግ ሀገራት የባህር በር የመጠቀም መብት ቢኖራቸውም፣ በነጻነት ወደብ የመጠቀምም ሆነ በባህር የመንቀሳቀስ መብታቸው ግን በጂኦግራፊ የተገደበ ሆኖ ዘልቋል፡፡
በዚህም ምክንያት የጎረቤት ሀገራትን ወደብ ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራት በሌሎች ፍላጎቶችና ስሜት ጫና ስር እንዲወድቁ አድርጓቸዋል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የብሔራዊ ደህንነት ስጋትም ይደቅናል፡፡
ኢትዮጵያም ይህ ኢ-ፍትሀዊነት ነው በሚል በጠቅላይ ሚኒስትሯ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አማካኝነት ጥያቄ በማንሳት ጉዳዩን የዓለም አጀንዳ አድርጋለች፡፡
ጉዳዩም የዓለም አቀፍ የፍትሓዊ ተጠቃሚነትና የባለቤትነት እንዲሁም የሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዓለም አቀፉ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ፊትም የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
ሀገራችን የባህር በር ስለሌላት፣ የጎረቤት ሀገራት የባህር በሮችን እና ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ ይህ ደግሞ የወጪ እና ገቢ ምርት እንቅስቃሴዋ እና የምርቶች ዋጋ ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና እያስከተለባት ነው፡፡
የባህር በር የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ እና የውጭ ንግድ የሚወስን ወሳኝ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ነው። በርካታ የወደብ፣ የጉምሩክ እና የሎጂስቲክስ የስራ እድሎችንም ለዜጎች ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ ቀጥታ የባህር በር የሌላት ሀገር በመሆኗ በአሁኑ ወቅት አማራጭ ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ የጅቡቲ ወደብ፣ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ ያስተናግዳል።
በሶማሊላንድ ያለው የበርበራ ወደብ ሌላኛው የቅርብ አማራጭ ነው። የታጁራ እና የአሰብ ወደቦችም እንደ ተጨማሪ አማራጭ የሚጠቀሱ ናቸው።
በፈረንጆቹ እስከ 1995 ድረስ ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ በአሰብ በኩል ሲከናወን የነበረ ሲሆን፣ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በምጽዋ ወደብ በኩል ይሳለጥ ነበር።
የባህር በር የሌለው ሀገር ከዓለም የንግድ ሥርዓት እኩልና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ የባህር በር የኢኮኖሚ እድገት እንዲፋጠን ከማድረግ አንጻር ሚናው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ምሁራን የባህር በር ካለህ ዓለምን ታገለግላለህ፣ የባህር በር ከሌለህ ግን የጎረቤት ሀገራት አገልጋይ ትሆናለህ የሚል ብሂል አላቸው፡፡
ይህንን የሚሉት የባህር በር ለአንድ ሀገር እድገትና ብሔራዊ ደህንነት ያለውን ጥቅም በደንብ ስለሚረዱ ነው፡፡
የባህር በር አንድ ሀገር ከዓለም ጋር ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር ይወስናል፡፡
በዓለማችን ላይ ወደ 45 ሀገራት የባህር በር እንደሌላቸው ይነገራል፡፡ ይህም ከዓለም ሀገራት 20 በመቶ እንደ ማለት ሲሆን፤ አዳጊ የሚባሉ ሀገራትን 40 በመቶ የሚሸፍን ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ለማደግና ለመበልፀግ የባህር በር ካላቸው እኩል አይደክሙም፡፡ የባህር በር የሌላቸውና አዳጊ የሚባሉ 32 ሀገሮች በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ሀገራትም ወደ 500 ሚሊየን ሕዝብ አሏቸው፡፡
ይህም የዓለምን ሰባት በመቶ የህዝብ ብዛት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 16ቱ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከእነሱም ትልቋ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እነዚህ ሀገራት የባህር በር ስለሌላቸው በዓለም ንግድ ውስጥ ያላቸው ድርሻ ከአንድ በመቶ ማለፍ አልቻለም፡፡
ይህም የባህር በር ስለሌላቸው ነው፡፡ ይህ ጂኦግራፊ የሀገሮችን እጣ ፈንታ እየበየነ እንዳለ ማሳያ ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በውድ የትራንስፖርት ወጪና በሌሎችም የንግድ እንቅፋቶች የተነሳ ከዓለም ገበያ ያላቸው ትስስር የላላ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ከዚህ የተነሳም በዓለም የፋይናንስ ስርዓት ችግሮችና በብድር እዳ ጫና ይማቅቃሉ፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቅርጽ ይዞ ትግሉ ቀጥላል፡፡
እናማ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ታሪካዊና ሕጋዊ መብት የለንም ትላላችሁ?

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት አይተን የተመኘናቸውን ነገሮች ከአሰብነው በላይ ማሳካት ችለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የቆሻሻ መጣያ የነበረና ያለ አግባብ ተይዞ የቆየ ስፍራ ወደ ዘመናዊ የጋራ መገልገያ ኢኮ ፓርክ በመቀየር ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜና በጥራት ተጠናቅቆ ለውጤት በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት እኛም እንዲህ ባደረግን የሚል ምኞት እንደነበር አንስተዋል።
አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ የራሷን ከተሞች በላቀ ደረጃ በማልማት ላይ መሆኗን አክለዋል።
ታታሪ ሕዝብ፣ ለም መሬትና ያልተጠቀምንበት ሰፊ ሀብት አለን ያሉት ከንቲባዋ፤ በልማት ሥራዎች ሀገራችን አሁን ላይ ከሌሎች ሀገራት የተሻሉ ውጤቶችን እያስመዘገበች መሆኗን ተናግረዋል።
ኢኮ ፓርኩ በውስጡ ፋውንቴይን፣ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የህጻናት መጫወቻ፣ አምፊ ቲያትር፣ ዘመናዊ ካፍቴሪያ፣ ሱቆች፣ የጁስ ባር፣ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት እንዲሁም የእግር ጉዞ የሚደረግበት ሰፊ መንገድ ተሟልተውለት በጥራት መገንባቱን ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት የትውልድ ግንባታ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የመክፈል አቅም የሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችና ሕፃናት በእኩልነት ስሜት የሚዝናኑበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ቀደም ሲል ቦታው የቆሻሻ መጣያና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጠ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ግን ለአእምሮ ምግብ የሚሆን ጤናማ አካባቢ መፈጠሩን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ይህን የጋራ ሀብት እንዲንከባከቡና እንዲጠብቁ አደራ ብለው፤ ለፕሮጀክቱ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የክፍለ ከተማው አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#ethiopia #addisababa #addisecopark #ebc

የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤትነት ጥያቄ ከሀገራዊ ህልውና ጋር የተቆራኘ ነው :- የቀድሞው የአሰብ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሊበን
*******
የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤትነት ጥያቄ በስሜት የሚነዳ ሳይሆን የታሪክ መሠረት ያለውና ከሀገራዊ ህልውና ጋር የተቆራኘ መሆኑን የቀድሞው የአሰብ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሊበን ገለጹ።
አሰብ ከተማ የኢትዮጵያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ደም ስር ከመሆኗም ባለፈ፣ የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ምልክት እንደሆነች ይነገራል።
ዛሬ ላይ በይፋ የቀረበው የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤትነት ጥያቄ፣ ከወቅታዊ ስሜት ይልቅ ተጨባጭ የታሪክ መረጃዎችንና የህልውና አጀንዳን መሠረት ያደረገ ነው።
የቀድሞው የአሰብ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሊበን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአሰብ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ እውነታን የተመረኮዘ መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፣ አሰብ በወቅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ግንባር ቀደም ከተሞች አንዷ ከመሆኗም በላይ የሀገሪቱ ዋንኛ የገቢና ወጪ ንግድ ማዕከል በመሆን ለኢኮኖሚ እድገቱ እንደ ጀርባ አጥንት ታገለግል ነበር።
አቶ ዳንኤል የአሰብ ጥያቄ ዛሬ የተፈጠረ ሳይሆን ጥልቅ የታሪክ መሠረት ያለው መሆኑን ሲያስረዱም፤ አሰብ "የአሰብ ራስ-ገዝ አስተዳደር" (Assab Regional Autonomous) ተብላ ትጠራ እንደነበር አስታውሰዋል። ይህ መዋቅር አሰብን ከኤርትራ ራስ-ገዝ አስተዳደር ነጥሎ በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግስት ተጠሪ የሚያደርግ ነበር።
የዚህ ራስ-ገዝ አስተዳደር ስፋትም ከምጽዋ አቅራቢያ ጀምሮ እስከ ጅቡቲ ጠረፍ ድረስ ያለውን ሰፊ የባህር ዳርቻ የሚያጠቃልል ነበር ይላሉ።
በ1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ ሲመጣ የነበረውን ሁኔታ ያስታወሱት አቶ ዳንኤል፤ የከተማዋ ማህበራዊ ሕይወት፣ የትምህርት ሥርዓት እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ መሃል ሀገር ጋር ፍጹም የተቆራኘ እንደነበር ገልጸዋል።
በወቅቱ አስመራ የነበሩ ነዋሪዎችም ቢሆኑ "አሰብ ለኢትዮጵያ አገልግሎት ካልሰጠች ለእኛም ፋይዳዋ አነስተኛ ነው" የሚል እምነት እንደነበራቸው ጠቅሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት እንድትሆን የሚቀርበው ጥያቄ ወቅታዊና ተገቢ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም ብለዋል።
ከተማዋ የኢትዮጵያ የነዳጅ ማጣሪያ እና የትራንስፖርት ደም-ስር ሆና ለዓመታት ማገልገሏ፣ ዛሬ ለሚነሳው ጥያቄ ትልቅ የሞራልና የታሪክ አስረጂ ነው። ይህም የባህር በር ጥያቄው ህጋዊነት፣ ተገቢነት እና ወቅታዊነት የማይናወጥ መሠረት እንዳለው ያረጋግጣል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopia #assab #redsea #addisababa #ethiopiannews #history

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል፣ የብልጽግና ፓርቲ) በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ እየተከተላቸው ያሉ ፖሊሲዎች እና አቋሞች ቀጣናዊ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ ነው ሲሉ ከሰሱ። ሚኒስትሩ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲዎች "ከእውነታው የራቁ" ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
አቶ የማነ ለክሳቸው ዋነኛ ማሳያ አድርገው ያነሱት፣ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ መንግስት በጥር ወር 2024 (እ.ኤ.አ) ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት (MOU) ህገ-ወጥ እና በድብቅ የተደረገ ነው የሚል ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ ከታህሳስ 2023 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ "በሉዓላዊነት ላይ የተመሰረተ የባህር በር ማግኘት" በሚል መነሻ አሰብን ለመውረር የጦር መሳሪያ ማስፈራሪያዎችን እና ተከታታይ የሚዲያና የዲፕሎማሲ ዘመቻዎችን አካሂዷል ሲሉ ተችተዋል። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ እንደ ዬል ዩኒቨርሲቲ ጥናቶች ያሉ ሪፖርቶችን ዋቢ በማድረግ ኢትዮጵያ በሱዳን ግጭት ውስጥ እጇን አስገብታለች የሚል ክስ አቅርበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊዎች "ኤርትራን እና ሌሎች የቀጠናውን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረት በመፍጠር ሴራ እየጎነጎኑ ነው" በሚል የሚያነሱት ክስ ሀሰተኛ እና የውጥረቱን ትክክለኛ ምንጭ ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ነው ብለዋል።
አቶ የማነ፣ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ፍላጎት "በአንዳቸው የሌላውን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በማክበር ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ሰላም እና ትብብር ማምጣት እንጂ፣ የበላይነትን ለማስፈን በሚደረግ ጥረት ለዘመናት በሚዘልቅ ግጭት ውስጥ መኖር አይደለም" ሲሉ የሀገራቸውን አቋም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራው ማስታወቂያ ሚ/ር በተደጋጋሚ ለሚያቀርቡት ክስ አንድም ቀን ምላሽ ሰጥቶ አያውቅም። ለዚህም ክስ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ የኤርትራ አምባሳደር ሶፍያ ተስፋማሪያም፣ "Eritrea’s Sovereignty Claim and the Insecurity It Conceals" (ኤርትራ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና የሚደብቀው የደህንነት ስጋት) በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በኩል ለወጣው ጽሁፍ ሰፊ እና ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል። አምባሳደሯ በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ፣ የኤርትራ ሉዓላዊነት ታሪካዊ መነሻዎች፣ እንዲሁም የቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶች ላይ የኤርትራን አቋም አንፀባርቀዋል።
ጽሁፉ የኤርትራን የሉዓላዊነት አቋም እንደ "መደበቂያ ወይም የፖለቲካ ስጋት" አድርጎ ማቅረቡን አምባሳደር ሶፍያ አጥብቀው ተችተዋል። ሉዓላዊነት በዘመናዊው ዓለም አቀፍ ህግ (በተባበሩት መንግስታት ቻርተርም ሆነ በአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነድ) የተረጋገጠ መሰረታዊ መብት እንጂ፣ ኤርትራ የምትደበቅበት ሽፋን አይደለም ብለዋል። በተለይ ለኤርትራ ሉዓላዊነት ማለት ከረዥም የፀረ-ቅኝ ግዛት እና የፀረ-ወረራ ትግል፣ ከተደጋጋሚ ጦርነቶች እና መስዋዕትነት የተገኘ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።
"ኢትዮጵያ በኤርትራውያን የታሪክ ትውስታ ውስጥ ተራ ጎረቤት ሀገር ብቻ ሳትሆን የቀድሞ ቅኝ ገዥ ነበረች" ያሉት አምባሳደሯ፣ ይህ ታሪካዊ እውነታ ኤርትራ ለድንበር እና ለሉዓላዊነት ጥያቄዎች የምትሰጠውን ትኩረት እንደሚቀርፀው ገልጸዋል። የአማርኛውን "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም" የሚለውን ምሳሌ በመጥቀስም፣ ጦርነት፣ ወረራ እና ማዕቀብን ያሳለፈ ህዝብ የሉዓላዊነት ጉዳይን በቀላሉ ሊያየው እንደማይችል አስገንዝበዋል።
አምባሳደሯ እንደገለፁት፣ ኤርትራ የባህር በር አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ የንግድ የባህር በር (Maritime Access) የማግኘት መብት አላት የሚለውን መርህ ተቃውማ አታውቅም። ዓለም አቀፍ ህግም ይህንን መብት በድርድር እና በስምምነት እንዲፈፀም ይፈቅዳል። ችግሩ ያለው ግን ይህ ጥያቄ እየቀረበበት ያለው መንገድ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ፣ የባህር በር ጥያቄውን "ታሪካዊ መብት" እና "የህልውና ጉዳይ" አድርገው ማቅረባቸው፣ እንዲሁም "በሰላም ካልሆነ በኃይልም ቢሆን" የሚሉ ዛቻዎች መደመጣቸው በኤርትራ በኩል ስጋት መፍጠሩን አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ አሰብን እና የኤርትራን ግዛቶች ከኢትዮጵያ ጋር ቀላቅለው የሚያሳዩ የተጭበረበሩ ካርታዎች በማህበራዊ ሚዲያ እና በወታደራዊ መድረኮች ላይ መሰራጨታቸው ሉዓላዊነትን የሚጋፋ አስገዳጅ ትርክት መሆኑን አምባሳደሯ ተችተዋል። "ዓለም አቀፍ ህግ (አንቀጽ 2(4)) ጥቃት መሰንዘርን ብቻ ሳይሆን በማስፈራራት እና በዛቻ የሚደረግን ጫናም ይከለክላል፤ ስለዚህ ኤርትራ የወሰደችው የጥንቃቄ እርምጃ ምክንያታዊ ነው" ብለዋል። በ2024 በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስነ-ስነድም በሶማሊያ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ጥሰት በመሆኑ ቀጠናዊ ውጥረቱን እንዳባባሰው ጠቅሰዋል።
አምባሳደር ሶፍያ ጽሁፉ የ1998-2000 (እ.ኤ.አ) የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጦርነትን በተመለከተ ያቀረበውን ሀሳብ "የተዛባ" ብለውታል። የኤርትራ ድንበር በማያሻማ ሁኔታ በ1900፣ 1902 እና 1908 በጣሊያን እና በኢትዮጵያ መካከል በተደረጉ ስምምነቶች ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑን አውስተዋል። የጦርነቱ መነሻ የነበረችውን ባድመን በተመለከተም የድንበር ኮሚሽኑ የማያዳግም ውሳኔ ለኤርትራ የሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል።
ጦርነቱን ተከትሎ ለዓመታት የቀጠለው ፖለቲካዊ ቀውስ የኤርትራ ህግ አለማክበር ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ "የመጨረሻ እና አሳሪ" ነው የተባለውን የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ለሁለት አስርት ዓመታት አልቀበልም በማለቷ የመጣ መሆኑን ሞግተዋል። አክለውም፣ በ2009 በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው የተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ፣ በኢትዮጵያ ጫና ኢጋድን እና አፍሪካ ህብረትን በመጠቀም የተሰራ ፖለቲካዊ ሴራ እንደነበር እና ማዕቀቡ በ2018 መነሳቱ ይህንኑ እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል።
ስለ ኤርትራ ብሄራዊ አገልግሎት የተነሳውን ትችት በተመለከተ፣ አምባሳደሯ ፕሮግራሙ ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ሲቪል እና የልማት ስራዎችንም (እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ እና መሰረተ ልማት) ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል። የብሄራዊ አገልግሎቱ ጊዜ የተራዘመውም ኢትዮጵያ የፈጠረችውን "የሰላምም የጦርነትም የሌለበት" ሁኔታ እና ተያያዥ የፀጥታ ስጋቶችን ለመቋቋም መሆኑን አብራርተዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እያካሄደችው ያለው መጠነ-ሰፊ ጦርነት፣ የድሮን ጥቃቶች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ችላ ተብለው የኤርትራን ብቻ ማጉላት ሚዛናዊነት የጎደለው ትንታኔ ነው ብለዋል።
አምባሳደሯ ሲቀጥሉም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሁሌም በሉዓላዊ እኩልነት፣ ጣልቃ ባለመግባት እና የቀጠናው ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኤርትራ በጋራ ስምምነት እና በዓለም አቀፍ ህግ ላይ የተመሰረተ የንግድ እና የባህር በር ትብብርን እንደማትቃወም ደግመው ያረጋገጡት አምባሳደሯ፣ "የማንቀበለው ግን ትልልቅ ሀገራት በስፋታቸው እና በህዝብ ቁጥራቸው ተማምነው የትናንሽ ጎረቤቶቻቸውን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ጫና ማድረጋቸውን ነው" ብለዋል።
በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ወደፊት ስለሚኖረው ግንኙነትም ሲያብራሩ፤ "እውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም በዲፕሎማሲያዊ መፈክሮች ወይም በውጫዊ ጫና አይመጣም። በጋራ መከባበር፣ መተማመን እና ጊዜን በሚጠይቅ ሂደት ላይ መመስረት አለበት። በተለይም በ2018 የተፈጠረውን ታሪካዊ የሰላም እድል በአግባቡ መጠቀም ያልቻለው የኢትዮጵያ አመራር ባለበት ሁኔታ፣ ሰላምን ማጣደፍ አይቻልም። ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ከራሷ ጋር ሰላም መፍጠር አለባት" በማለት ጽሁፋቸውን አጠናቅቀዋል።

4 months ago
የካሙዙ ካሳ አነጋጋሪ ንግግር!
ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡት ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ፤ ኢትዮጵያ በቅርቡ የባሕር በር እንደምታገኝና አሰብ ላይ የሙዚቃ ስቱዲዮ እንደሚከፍት ገልጿል።
ካሙዙ አክሎም አሁን ያለው መንግሥት ተቃዋሚዎቹን እንደማያስር ገልጾ፣ የብልፅግና ፓርቲን አለመደገፍ ለቁጭት ሊዳርግ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
"መደገፍ አገር ወዳድነት ነው" ያለው አቀናባሪው፤ ሁሉም ዜጋ በመንግሥት የልማት ሥራዎች ላይ እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።
seledadotio

አዲስ አበባን የረገትጥኩ ሰሞን
(ዘላለም ጸጋዬ)
#ethiopia | ምንም እንኩዋን የተወለድኩት ከአንዲት ትንሽዬ የገጠር ከተማ ቢሆንም የልጅነት አይኔን ስገልጥ ግን የማስታውሰው የማርያምን ቤተክርስትያን፣ የመቅድስዋን የእጣን ሽታ፣የንፋስ ሽውታ የሚያስፉዋጨውን የጉዋሮዋን አርዘሊባኖስ፣የደጀ ሰላምዋን መአዛ ፣ካጠገቡም ያለውን ጭው ያለ ገደል እንዲሁም "መልእክተ ዮሀንስ ሀዋርያ ወልደ ዘብድዮስ" እያሉ መርጌታ አየለን የከበቡ የቆሎ ተማሪዎች ድምጽ እና የመሳሰለው ነው።በጥቅሉ የልጅነት አይኔን የገለጥኩት ስልጣኔ ካልጎበኘው እልም ካለ ገጠር ውስጥ ነው ...እናማ አኩፋዳዬን ጣጥዬ አዲስ አበባ የገባሁት የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር።ነፍሱን ይማረውና አባቴ ፈለገ ዮርዲያኖስ ትምህርት ቤት ወስዶ ከተተኝ።አባቴ ቀድሞ ከተማ ገብቶ አስኩዋላት ተምሮ እቀድሞዋ ቺኮዝሎቫኪያ ድረስም ሂዶ ተምሮ ነበር የመጣው።ተያም በሁዋላ እስከ ደርግ ምክርቤት አባልነት ደርሶ ነበር።
ትምህርት የተጀመረ ሰሞን የእርሻ መመህራችን ስለ ስንዴ አበቃቀል ሲያስተምሩ ቆይተው።"ጥያቄያለው አለ?" ሲሉ ከመቅጽበት እጄን እንደ ኢራን ሚሳኤል ዘረጋሁት።እኔ በገጠር አያለሁ የማውቀው ትልቅ ስራ መምህረነት ነው።ከዛ ባለፈ ሁሉም አርሶ ነው የሚበላ።እናም ከተማ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ስትከነክነኝ የከረመችውን ጥያቄ እንዲህ በማለት አቀረብኩ "መምህር የስንዴ አበቃቀልን አላጣሁትም የኔ ጥያቄ ግን... እንዲያው ለመሆኑ ይሄ ሁሉ ከተሜ የት አርሶ ነው የሚበላ" ብዬ ስጠይቅ...የክፍሉ ተማሪ ሁሉ በሳቅ ፈረሰ።ያልሳቀ አንድ ሰው ቢኖር መምህሩ ብቻ ነበሩ።እንዴ ምንድነው አዳሜን ሚያስቀው ብዬ ተገረምኩ።አባቴ በሰው ላይ መሳቅ እና ማላገጥ አይገባም እንዲይ ካደረግክ ነገ ሌሎች በአንተ ላይ ያላግጡብሀል ይለኝ ነበር።በገጠርም ቢሆን ምን አልባት ነጠላችንን አፋችን ላይ ጣል አርገን በትንሹ ብናንጉዋጥጥ ነውይ በሰው ላይ ካካካክ ብለን አንስቅም።
የእርሻ ክፍለ ግዜው እንዳለቀ።መምህሩ ሲወጡ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ እየተከተለ "ዘላለም ገበሬው" ማለት ጀመረ።ምንም አልተደናገጥኩም።ድሮም ደንቆሮ ወሬ አያጣም ብዬ ኮስተር አልኩ።የገጠር ልጅ ልበሙሉ አይደል።እህኔ እኮ የአንዱን ተማሪ የአይን መጋረጃ በዚህ አፈር ሲግፍ በከረመ እጄ ብከድንለት እኮ ሌላው አርፎ ይቀመጥ ነበር ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ከክላስ ስወጣ ወይም ስኔ 30 ጠብቀው ጨርቆስ ጉሊት መሃል ተሰብስበው ዱቄት እንዳያደርጉኝ ደግሞ ፈራሁ።በዛ ላይ ሰፈሩ ብዙ ግዜ በችግር ብዛት በህይወት አረቄ ሰክረው የሚደባደቡ አያጣውም ነበር።
የሆነው ሆኖ እንዲህ አልኩዋቸው...አዎ ገበሬ ነኝ።የገበሬ ምርቱ በትሳስ ነው።ታህሳስ ላይ እንገናኝ አልኩዋቸው።ቅኔ መሆኑዋ ነበር።የተሳዳቢው ተማሪ ቡድን መሪ ደግሞ አንዲት ድፍኑዋን ጨረቃ የመሰለች ዘቢብ የምትባል ቆንጅዬ ልጅ ነበረች።ቆንጆ ሰው አመሉም እንደመልኩ ሸጋ፣ልቡም እንደ እጣን ንጹህ ይመስለኝ ነበር።ገና ያኔ ነው አዬ ውበት ከንቱ ደምግባትም ብላሽ ያልኩት::ዘቢብ ግን ዛሬ የት ነሽ...እነዛ እንደ ቤተመቅደስ ጧፍ የሚያበሩ አይኖችሽ ሰላም ናቸው ወይ??? አቤት ውበታቸው አይን ያስፈነጥዝ ነበር•••
የሆነው ሆኖ በመጨረሻም ታህሳስ የመጀመርያ ሴሚስተር ውጤት ሲመጣ ከክፍሉ አንደኛ ወጣሁ።ያሁሉ ተማሪ እንደ ንጉስ ያየኝ ጀመር።እኔም ቆፍጠን ቄምጨጭ አልኩ "አለም ምንግዜም የቆራጦች ናት" ይል ነበር በዓሉ ግርማ።እናማ በክፍላችን ውስጥ እንግሊዘኛን እንደኔ የሚያነባት አልነበረም።አፌን ያዝ ከሚያደርገኝ የገጠር አማርኛ በስተቀር ምንም የሚወጣልኝ አልነበረም።ከባድ ጥያቄ በተጠየቀ ቁጠር መምህራን አይናቸውን ወደኔ ነበር የሚያቆለቁሉት።
ውሸት የሚባል አላውቅም ነበር።አሁንም ይተናነቀኛል።"እናትክን" የሚል ስድብ የሰማሁት እዛው ከትምህርት ቤታችን ፊትለፊት ከጉሊቱ መካከል ነበር።የዛን ቀን ከሰማይ እሳት እና ምስማር ቀላቅሎ የሚጥል ነበር የመሰለኝ።ያለወላጅ እናት ስላደግኩ በሱዋ ምትክ በልቤ እመቤታችን ንጽህት ድንግል ማርያም እናቴ እያልኩ ስላደግኩ እሱዋ የተሰደበች ያክል ነበር የሰቀጠጠኝ።በዛ ላይ ደግሞ "በእንተ ስሙዋ ለማርያም" ያልኩበት በስሙዋ ተማጽኜ ጎርሼ ያደርኩበት ዘመን ውልብ አለብኝ።
ምንም እንኩዋን አዲስ አበባ አቀባበሉዋ እንደ ደንባራ በቅሎ መንቃራ ቢሆንም።ኢለመንታሪ ፈለገ ዮርዳኖስ፣ ሀይስኩል 9 እና 10 አብዮት ቅርስ፣ 11 እና 12 ቦሌ ሀይስኩል፣ እንዲሁም እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድረስ አንቀባርራ አሳድጋኛለች።ከገጠር ይዤ የወጣሁት ስብእና ለዛሬው ማንነቴ እጅጉን አስተዋጽኦ አድርጉዋል።አንዳንዱም ጎጂ ባህል ነበር ለምሳሌ ሳልደርስበት የደረሰብኝን ሰው ሳልበቀል መተው ሽንፈት ይመስለኛል።እርቅም ከታሰበ ከተመጣጣኝ አጻፋ በቀል በሁዋላ እንጂ እንዲሁ አንተም ተው አንተም ተው አይሰራም።
ለማንኛውም አዲስ አበባ ቤቴ፣አሳዳጊዬ ክፉውንም፣ ደጉንም ያሳለፍኩብሽ፣ የኔ ሁሉን ቻይ ኑሪልኝ።ምንም እንኳን ባህር ብሻገርም ልቤ ግን ያለው ካንቺው ዘንድ ነው።•••የሰው ልጅ ከመኖር የሚያተርፈው ትዝታ ነው።
እኔም እነሆ ትዝታዬን አጋራኋችሁ!
መልካም ሰንበት!

5 months ago
"አሰብ የአባቴ የዘላለም ቁጭት፣ የእኔም የታሪክ ውርስ ነው!” - የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ እውነተኛ ታሪክ
#ethiopia | አሰብ ሲነሳ ለብዙዎች የካርታ ላይ መስመር ወይም የፖለቲካ መነጋገሪያ ሊሆን ይችላል፤ ለእኔ ግን የደም ስሬ፣ የልጅነት ትውስታዬና የአባቴ የዕድሜ ልክ ናፍቆት ነው።
አባቴ ፈንታው አደም በአሰብ ነጋዴ ሰፈር ስሙ ገዝፎ የሚነሳ፣ በንግዱና በሥራ ወዳድነቱ የሚታወቅ ብርቱ ሰው ነበር። አሰብ ለእሱ መኖሪያ ብቻ ሳትሆን ማንነቱ፣ ሀብቱና ክብሩም ነበረች።
የ1983 ዓ.ም የመለያየት ንፋስ ሲነፍስ ወንድሞቼና እህቶቼ በጅቡቲ በኩል ተሰደዱ፤ አባቴ ግን "ሀገሬን ጥዬ አልወጣም" ብሎ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ከአሰብ ጋር ግብግብ ገጠመ። በ1986 ወይም 87 አካባቢ አሰብን ለቆ የወጣው የመጨረሻው ተፈናቃይ እሱ ነበር።
ከአሰብ ቢወጣም ልቡ ግን እዛው ቀርቷል። ኮምቦልቻ ካምፕ ውስጥ ተጠልሎ ሳለ እንኳ በረሃውና የለመደው የንግድ ግርግር እየመጣ ሲቀሰቅሰው "የአሰብ ተፈናቃይ" የሚለውን ስም ሊለምደው አልቻለም። ናፍቆቱ ሲበዛበት ለአሰብ ቅርብ ወደሆነችው ዲቺኦቶ (በአፋር ክልል በአሁኑ የኤሊዳር ወረዳ ውስጥ የምትገኘ የንግድ ቦታ ነች) ተመልሶ መነገድ ጀመረ፤ ሁሌም ግን ከጓደኞቹ ጋር ቁጭታቸው አንድ ነበር "አሰብ ተመልሰን ሄደን የድሮ ሕይወታችንን በኖርን" የሚል፡፡
አባቴ በ2007 ዓ.ም አላህ ይርሃመውና ከዚህ ዓለም ሲለይ፣ ያንን ትልቅ ተስፋና ቁጭት በእኔ እጅ አስቀምጦ አልፏል። ዛሬ እኔ ጋር የአባቴ ንብረት የሆኑ የቤትና የንግድ ቦታዎች ሕጋዊ ካርታዎችና ሰነዶች አሉ። "ይሄ የእኛ ነው" እያለ ያሳየን የነበረው ያ የንግድ ቦታና የመኖሪያ ቤት ዛሬም በዓይነ ሕሊናዬ ይርመሰመሳል።
አሁን የወደብና የአሰብ ጉዳይ ሲነሳ "የአባቴ ምኞት በእኔ ዘመን እውን ይሆን ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በውስጤ በኃይል ይጮኻል።
አሰብ ለኮምቦልቻ፣ ለባቲና ለአካባቢው ሕዝብ የሕልውና መሠረት፣ የንግድ መፍለቂያና የትልቅ ተስፋ ምድር ነበረች። እኔ የአባቴን ታሪክ የምሸከም፣ ሰነዱን የያዝኩ ሕጋዊ ወራሹ ነኝ።
ያ የቁጭት ታሪክ ተቀይሮ፣ አባቴ በሕይወት እያለ ያላየውን ያንን የወደብ ብርሃን እኔ ሄጄ የማየውና ለእናንተም በደስታ የምነግራችሁ ቀን ቅርብ እንደሆነ አምናለሁ። የታሪክ ፍትህ የአባቴንና የሺዎችን ቁጭት የሚያብስበት ጊዜ ይመጣል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #assab #history #identity #ኢትዮጵያ #አሰብ #የወደብጉዳይ #ቁጭት #ትውስታ

''አሰብ በሰላም ካልተመለሰ የአድዋ ልጆች ነን እናሳያቸዋለን ወጣቱ ይዘጋጅ'' ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
በአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት የአዳነች አቤቤ ስለ ባህር በር ይህን ብለዋል "የባህር በር ጥያቄያችን በሰላም ካልተመለሰ የአድዋ ልጆች መሆናችንን በተግባር እናሳያለን ወጣቱ ይዘጋጅ ይህ የዚህ ትውልድ አደራ ነው ሲሉ ያስተላለፉት መልዕክት በብዙዎች ዘንድ ትኩረትን ስቧል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ግብጽ ለኢትዮጵያ የባሕር በር አማራጭ አቀረበች
ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ካለሳለሰች፣ በጎረቤት አገራት በኩል የባሕር በር እንድታገኝ ለማገዝ ግብጽ ፍላጎት እንዳላት "ዘ ናሽናል" ዘገበ።
ጋዜጣው የግብጽ መንግሥት ይህን ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ማቅረቡን ጠቅሷል።
ግብጽ ይህን ሃሳብ ያቀረበችው በጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የሚገኙ ወደቦችን ለማልማት ስምምነት ላይ መድረሷን በሚገልጹ ዘገባዎች መካከል ነው።
በተለይም የዶራሌ፣ የአሰብ እና የፖርት ሱዳን ወደቦችን ለማልማት ያላትን ዕቅድ ለኢትዮጵያ እንደ አማራጭ አቅርባለች ተብሏል።
እስከ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ ጉዳዩ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።

ግብፅ ለኢትዮጵያ አዲስ አማራጭ አቀረበች፦ "ለዓባይ ውሃ ተለዋዋጭ ከሆናችሁ፣ ለባህር በር ድጋፍ እናደርጋለን"
#fastmereja I ግብፅ በዓባይ ውሃ ክፍፍል ላይ ኢትዮጵያ "ተለዋዋጭ" አቋም የምታሳይ ከሆነ፣ ሀገሪቱ ቀይ ባህርን የምታገኝበትን መንገድ ከአፍሪካ ወዳጆቿ ጋር በመሆን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። "ዘ ናሽናል" የካይሮ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ይህ ሃሳብ ባለፈው ሳምንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደርሷቸዋል።
ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለህልውናዋ "ስጋት" እንደሆነ በመግለጽ፣ የውሃ አጠቃቀሙን የሚገዛ ሕጋዊ ስምምነት እንዲኖር ትፈልጋለች።
ኢትዮጵያ በውሃው ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ የምትደርስ ከሆነ፣ ግብፅ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ያላትን የባህር በር ፍላጎት ለማሳካት ከጎኗ እንደምትቆም ገልጻለች።
ይህ የግብፅ ሃሳብ ለዋይት ሃውስ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መላኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ በዓመታት የዘለቀውን ይህንን የውሃ ውዝግብ ለማስታረቅ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ግብፅ ይህንን አማራጭ ስታቀርብ ስውር ማስጠንቀቂያም አክላለች። ኢትዮጵያ ጥያቄውን ውድቅ ካደረገች፣ ግብፅ በሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በጅቡቲ እና በኤርትራ ያላትን ከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ እንዲሁም በቀይ ባህር ደቡባዊ ክፍል ያለውን የባህር ኃይል ኃይሏን በመጠቀም ኢትዮጵያ የወደብ አገልግሎት እንዳታገኝ "እንቅፋት" እንደምትሆን አመልክታለች።
ምንም እንኳን አዲስ አበባ ለግብፅ ጥያቄ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ ባትሰጥም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሀገር የባህር በር ተከልክላ 'የመልክዓ ምድር እስረኛ' ሆና መቀጠል አትችልም" ብለዋል።
ለዓመታት ተቃቅረው የነበሩት ካይሮ እና አንካራ አሁን ላይ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ሲሆን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ እና በሶማሊያ ጉዳዮች ላይ ያላቸው አቋም እየተቀራረበ መጥቷል።
ግብፅ፣ ሶማሊያ እና ቱርክ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባህር በር ለማግኘት ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት እንዲሁም እስራኤል ሶማሊላንድን እውቅና መስጠቷን በጽኑ ተቃውመዋል።
ግብፅ በአሁኑ ወቅት በጅቡቲ እና በኤርትራ (በአሰብ ወደብ) ላይ ያላትን ተጽዕኖ በማሳደግ እና የባህር ኃይል ጦር ሰፈሮችን በማጠናከር፣ ወደፊት በግድቡ ጉዳይ ላይ ለሚደረግ ድርድር እንደ ትልቅ የመደራደሪያ ካርድ ልትጠቀምበት እንደምትችል ተገምቷል።
#ፖለቲካ ዘገባ

6 months ago
❗️"ተወደደም ተጠላም አሰብ ይመለሳል" መከላከያ
"ተወደደም ተጠላም፤ ተዘግቶብን አንኖርም!" በዛሬው ወታደራዊ ትርኢት ላይ የታየ
#ethiopia
seledadotio
seledadotio
"ተወደደም ተጠላም፤ ተዘግቶብን አንኖርም!" በዛሬው ወታደራዊ ትርኢት ላይ የታየ
#ethiopia
seledadotio
seledadotio
6 months ago
"አሰብን በድርድር .. " የኢትዮጵያ ግልጽ ጥያቄ ለኤርትራ
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለወራት የዘለቀው የድንበር ውጥረት አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ደብዳቤ በትናንታናው ዕለት ወጥቷል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤርትራ መንግስት በላከው ይፋዊ ደብዳቤ፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣና ከአማፂያን ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት እንዲያቆም በጥብቅ አሳስቧል።
ቁልፍ ነጥቦች፦
የወታደራዊ እንቅስቃሴ ስጋት፦ የኤርትራ ጦር በሰሜን ምስራቅና ሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ድንበሮች ላይ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ "ቀጥተኛ ወረራና ትንኮሳ" ነው ተብሏል።
የአሰብ እና የባህር በር ጥያቄ፦ ኢትዮጵያ ለሉዓላዊነቷ መከበር አዎንታዊ ምላሽ የምታገኝ ከሆነ፣ ስለ አሰብ ወደብ አጠቃቀም እና ስለ ባህር በር ጉዳይ በቅን ልቦና ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
የሰላም አማራጭ፦ ደብዳቤው "ከግጭት ይልቅ ሰላምን፣ ከትርምስ ይልቅ ብልጽግናን" በሚል መሪ ቃል፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የዘመናት ቅራኔ በውይይት ለመፍታት ጥሪ አቅርቧል።
ይህ የኢትዮጵያ ጥሪ በቀጣናው ላይ ያለውን የኃይል ሚዛንና የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዴት ሊቀይረው እንደሚችል የብዙዎች ትኩረት ሆኗል። ኤርትራ ለዚህ "የሰላም ወይስ የማስጠንቀቂያ" ጥሪ የምትሰጠው ምላሽ ይጠበቃል።

ኤርትራ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ንግግር "የጦርነት አጀንዳን ምክንያታዊ ለማድረግ" የቀረበ ነው አለች
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለ ኤርትራ መንግሥት ያደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ መንግሥት "በኤርትራ ላይ ሊከፍት ያቀደውን የጦርነት አጀንዳ ምክንያታዊ ለማድረግ" የቀረበ ነው ሲሉ ተቹ።
የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባዩ ማክሰኞ ጥር 26/2018 ዓ.ም. ምሽት በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ጦርነት "ወቅት እና ከጦርነቱ ረጅም ጊዜ በኋላ ለኤርትራ ሠራዊት የክብር ሜዳይ" ሲሰጥ ነበር ብለዋል።
የማነ ይህንን ያሉት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች የጅምላ ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ግፎችን ፈጽመዋል በሚል ከወነጀሉ በኋላ ነው።
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት መሻከርን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ግንኙነት ውስጥ ችግር የተፈጠረው መንግሥታቸው በቀይ ባሕር ላይ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄን በማንሳቱ "እንዳልሆነ" ተናግረዋል።
"በትግራይ ውጊያ ሲጀመር በመጀመሪያው ዙር ወጊያ ሽሬን ካስለቀቅን በኋላ የኤርትራ ጦር ከኋላ ኋላ ተከትሎ ሽሬ ገብቶ የአንዳንድ ግለሰቦችን ቤት ማፍረስ፣ ፎቅ ማፍረስ ሲጀምር ፀብ ተጀምሯል፤ አልተናገርንም እንጂ" ሲሉ በሁለቱ መንግሥታት መካከል "ጸብ የጀመረው" ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኤርትራ ወታደሮች አክሱም ውስጥ "ወጣቶችን በጅምላ መረሸናቸውን" እንዲሁም አድዋ እና አዲግራት ከተሞች ውስጥ ፋብሪካዎችን እንዳወደሙ እና እንደዘረፉ ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። እነዚህን ድርጊቶች ለማስቆም ወደ ኤርትራ "በርካታ መልዕክተኞችን መላካቸውን" አክለዋል።
"ይሄ ጸብ ተፋፍሞ ሄዶ የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም 'እንዴት ህወሓት ሳይጠፋ፣ እንዴት ትግራይ ሳይወድም ፊርማ ይደረጋል?' በሚል ነው ጸቡ የመጨረሻ ጫፍ የደረሰው" ብለዋል። "ከዚህ ኃይል ጋር ሆነው ነው እንግዲህ አንዳንድ የህወሓት ሰዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንሥራ ያሉት" ሲሉም ከስሰዋል።
ለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በኋላ በኤክስ ገጻቸው ምላሽ የሰጡት የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ የማነ፤ የብልጽግና ፓርቲ "አስቀያሚ መለያ የሆነው ማጭበርበር እና አታላይነት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ታይቷል" ብለዋል።
በኤርትራ ላይ የቀረበው ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት "ሉዓላዊ የባሕር በር ማግኘት በሚል ሽፋን በኤርትራ ላይ ሊከፍት ያቀደውን የጦርነት አጀንዳ ለመሸፈን እና ምክንያታዊ ለማስመስል በድፍረት የተቀረጸ" ነው ሲሉም ወቅሰዋል።
የማነ አስከትለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓርላማ ንግግራቸው ያነሱትን እስራኤል ከሶሪያ በወረራ የያዘቻቸውን የጎላን ከፍታዎች ጉዳይ ጠቅሰዋል።
ዐቢይ በማብራሪያቸው ስለ መንግሥታቸው የቀይ ባሕር ጥያቄን እንደ የብሔራዊ አጀንዳ እንደሚገነዘበው ተናግዋል። "እስራኤል የጎላን ተራራን የያዘችው ለብሔራዊ ደኅንነቴ፣ ለህልውናዬ ችግር ያጋጥመኛል ብላ ስላመነች ነው" ያሉት ዐቢይ፤ አክለውም "ቀይ ባሕር እና ኢትዮጵያ ለዘላለሙ ተነጣጥለው መኖር አይችሉም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር በር ለማግኘት የምትፈልገው "በቢዝነስ ሕግ" እንደሆነ ተናግረዋል። በባሕር በር ምትክ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ሊቀርብ እንደሚችል ጠቁመዋል። "እስራኤል የጎላን ተራራን የያዘችው ለብሔራዊ ደኅንነቴ፣ ለህልውናዬ ችግር ያጋጥመኛል ብላ ስላመነች ነው" ያሉት ዐቢይ፤ አክለውም "ቀይ ባሕር እና ኢትዮጵያ ለዘላለሙ ተነጣጥለው መኖር አይችሉም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር በር ለማግኘት የምትፈልገው "በቢዝነስ ሕግ" እንደሆነ ተናግረዋል። በባሕር በር ምትክ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ሊቀርብ እንደሚችል ጠቁመዋል። ይህ ካልሆነም "በሊዝ" ወይም "በመሬት ልውውጥ" ሊከናወን እንደሚችልም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ ያለው "በስምምነት በገበያ ሕግ፣ ሳንጠፋፋ አብረን ለማደግ በድርድር እንፍታው እያለ ነው" ሲሉም የመንግሥታቸውን አቋም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ አሰብ ላይ "ወደብ፣ አየር ማረፊያ፣ መንገድ፣ ነዳጅ ማጣሪያ" መገንባቷን አስታውሰዋል።
"ለእኛ የሚገባንን በሆነ በሆነ ምክንያት ዛሬ መከልከል ቢታሰብ በቀጣይነት ማስቀረት ስለማይቻል ወደ ማይፈለግ ነገር ሳይገባ በሰላም በድርድር መጨረስ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ" ብለዋል።
ዐቢይ የጠቀሱትን የጎላን ከፍታዎች ምሳሌ ያነሱት የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር፤ ይህ ጉዳይ መነሳቱ የኢትዮጵያ መንግሥት አሥመራ ላይ ሊከፍት ያቀደውን "ግድየለሽ እና ሕገ ወጥ የጦርነት አጀንዳ ምክንያታዊ ለማድረግ" የቀረበ እንደሆነ ጽፈዋል።
"እንዲያውም [የብልጽግና ፓርቲ] መሪ በኤርትራ ላይ የያዘውን ግድ የለሽና ሕገ-ወጥ የጦርነት አጀንዳ ምክንያታዊ ለማድረግ [በሚል] በዚሁ ንግግሩ ላይ 'የጎላን ከፍታዎች ምሳሌን' ሲያነሳ ጨዋታውን ራሱ አጋልጦታል" ብለዋል።
ከፕሪቶሪያ ስምምነት መፈረም ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው ኢትዮጵያ እና ኤርትራ፤ አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲወነጅሉ ቆይተዋል።
ከሳምንት በፊት የፌደራል ፖሊስ የኤርትራ መንግሥት በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱት ፋኖ ኃይሎች "ልኳቸዋልል" ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ኤርትራ ግን ይህንን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች።
BBC

7 months ago
🎬 በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ታግዶ የነበረው የጥላሁን ጉግሳ "የባሕር በር" ፊልም ለዕይታ ሊቀርብ ነው!
#ethiopia | "ቤቶች ድራማ ከ13 ዓመታት በኋላ በክብር ሊሰናበት ነው"
አርቲስት፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር ጥላሁን ጉግሳ (ዘለቀ) ሁለት ዓበይት ዜናዎችን አሰምቷል።
1️⃣ "ቤቶች" ሊያበቃ ነው!
ለ13 ተከታታይ ዓመታት ያለማቋረጥ በመተላለፍ ከዓለም 3ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን የያዘውና የሁላችንም የሳሎን ትዝታ የሆነው "ቤቶች" የሲትኮም ድራማ፤ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለተመልካች በክብር እንደሚሰናበት ተገልጿል።
2️⃣ ታግዶ የነበረው ፊልም ሊለቀቅ ነው!
ከዓመታት በፊት ተሠርቶ ለጥቂት ጊዜ እንደታየ በኢህአዴግ ባለስልጣናት "ስለ አሰብ የባሕር በር ያወራል" በሚል የታገደውና አርቲስቱንም ለዛቻ እና ማስፈራሪያ ዳርጎት የነበረው "የባሕር በር" ፊልም በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል።
ለምን አሁን?
ጥላሁን እንደገለጸው፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ላለማበላሸት ታግሶ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ የባሕር በር ጉዳይ እንደ አዲስ እየተጠየቀ በመሆኑ ፊልሙን ለመልቀቅ መወሰኑን ተናግሯል።
በተጨማሪም ከሁለተኛ ሴት ልጁ ጋር በመሆን አዲስ ረጅም ተከታታይ ፊልም ይዞ ለመምጣት ዝግጅቱን ጨርሷል።
የቤቶች ድራማን ምን ያህል ይወዱት ነበር? እስኪ ትዝታችሁን አካፍሉን።
#betochdrama #tilahungugsa #yebahirber #ethiopianfilm #artnews #redsea #ethiopia

"ቀይ ባህርን የሚያክል ትልቅ ሀብት ግመል ይጠጣበት ብለው ሰጥተዋል የሚለውን በወቅቱ ብረዳ ኖሮ፣ ለመለስ ዜናዊ የተዘፈነውን የሀዘን ዜማ ላይ አልዘፍንም ነበር ሲል "አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ ተናገረ
ከአርትስ ቲቪ ጋር ባደረገው አነጋጋሪ ቆይታ፣ ስለ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ባወጣው የለቅሶ ዜማ የተሰማውን ቁጭት ገለፇል።
✅ ስለ ይቅርታው፦ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባወጣው ዜማ የኢትዮጵያን ህዝብን ይቅርታ መጠየቁን ገልፇል።
"አሰብን ለካ በአደራ ያስረከቡት እሳቸው መሆኑ አሁን ነው በደንብ እየገባኝ የመጣ" ብሏል።
✅ ስለ ህዳሴ ግድብ፦ ለግድቡ ምረቃ በ3 ቀናት ውስጥ አዲስ ስራ ማቅረቡንና ለዚህም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋና እንደቀረበለት ገልጿል።
✅ የጥበብ ጉዞ፦ ንዋይ እስካሁን ለተለያዩ ድምጻዊያን ከ150 በላይ ዜማዎችንና ግጥሞችን ማበርከቱንም ጠቁሟል።

Comments