4 days ago
አቶ አወል አርባ የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።
የአፋር ክልል ምክር ቤት ዛሬ ከሰዓት ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ አቶ አወል አርባን በድጋሜ የክልሉ ፕሬዚዳንት በማድረግ ሾሟል።
አቶ አወል አርባ በጉባዔው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #afar የአፋር ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባዔውን ዛሬ ሰመራ ላይ ማካሄድ ይጀምራል። ገባኤው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው መስራች ጉባዔ ምክር ቤቱ ክልሉን የሚመሩ ፕሬዜዳንት ይሾማል። የከፍተኛ አመራሮችን ሹመትንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

#afar
የአፋር ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባዔውን ዛሬ ሰመራ ላይ ማካሄድ ይጀምራል።
ገባኤው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው መስራች ጉባዔ ምክር ቤቱ ክልሉን የሚመሩ ፕሬዜዳንት ይሾማል። የከፍተኛ አመራሮችን ሹመትንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

11 days ago
''ጦርነት ይቁም' ኢሰመኮ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር አዋሳኝ አካባቢዎች በድጋሚ ያቀረሸው የትጥቅ ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ እንዳወጣው መግለጫ፣ በነዚህ አዋሳኝ ስፍራዎች እንደገና ያገረሸው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ላይ ተደራራቢ ጉዳት እንደሚያደርስ በመጠቆም፣ ልዩነቶች በውይይት ብቻ እንዲፈቱና ለሲቪሎች እንዲሁም ለሲቪል መሠረተ-ልማቶች አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ አሳስቧል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ፈራሚዎች ጨምሮ ሁሉም አካላት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕጎችን እንዲያከብሩና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ በኩል ወገኖችን ወደ ንግግር እንዲመልስ ጠይቀዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #ehrc #humanrights #news #amhara #tigray #afar

20 days ago
ከሜሶፖታሚያ እስከ ሰመራ፤ ኢትዮጵያን የቴምር ኤክስፖርት ማዕከል የማድረግ ታላቁ ሀገራዊ ራዕይ እና እምቅ አቅም
*************************
ቴምር በሰው ልጅ የታሪክ መዛግብት ውስጥ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ፣ ለምግብነት እና ለማህበራዊ ህይወት ከፍተኛ ዋጋ ያለው ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው።
የታሪክ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የቴምር ዛፍ እርሻ የተጀመረው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት በመካከለኛው ምስራቅ እና በሜሶፖታሚያ (የአሁኗ ኢራቅ) አካባቢ ነበር።
በበረሃማ እና ሞቃታማ የአየር ፀባይ ውስጥ በፅናት የማደግ ተፈጥሯዊ ምስጢር ያለው ይህ ሰብል፣ ጥንታውያኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለረጅም መንገድ ጉዞዎች እና ለድርቅ ጊዜያት እንደ ዋና የምግብ ምንጭ እንዲጠቀሙበት አስችሏቸዋል።
ረጅም ጊዜ የመቆየት ባህርይውም በንግድ መስመሮች በኩል በፍጥነት ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንዲሰራጭ አድርጎታል።
በአሁኑ ወቅት የቴምር ምርት እና ንግድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚታይበት ዘርፍ ሆኗል።
እንደ ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ አልጄሪያ እና ኢራቅ ያሉ ሀገራት ከፍተኛውን የቴምር ምርት ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡ ዋና ዋና አምራቾች ናቸው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቴምር ፍላጎት በመላው ዓለም እየጨመረ የመጣው ምርቱ በተፈጥሯዊ ስኳር፣ በፋይበር፣ በቪታሚኖች እና በማዕድናት የበለፀገ በመሆኑና በርካታ የጤና አወንታዊ ጎኖች በመኖራቸው ነው። ይህም አህጉራዊ እና አለም አቀፍ የቴምር ገበያ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል።
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ፣ ኢትዮጵያ ለቴምር ልማት እጅግ በጣም ምቹ የሆነ የተፈጥሮ አየር ጠባይ እና የበለፀገ የመሬት ሀብት አላት።
በተለይም እንደ አፋር፣ ሶማሊ፣ ድሬዳዋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በታችኛው ኦሞ ሸለቆ ያሉ ዝቅተኛ እና ሞቃታማ (ቆላማ) አካባቢዎች ለቴምር ዛፍ እድገትና ምርታማነት እጅግ ተስማሚ ናቸው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሀገራችን ከ500 እስከ 700 ሺህ ሄክታር የሚደርስ መሬት ለቴምር ልማት ከፍተኛ ተስማሚነት ያለው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል 453 ሄክታር መሬት በቴምር እየለማ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
እነዚህ ሰፊ የከርሰ ምድር ውሃ እና የወንዞች ፍሰት ያላቸው ቆላማ አካባቢዎች በስፋት ጥቅም ላይ ከዋሉ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የቴምር ምርት በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ መተካት ትችላለች።
ዘርፉ በስፋት ሲለምድ በቆላማ አካባቢዎች ለሚኖሩ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ዘላቂ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩ በላይ፣ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
በተጨማሪም ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ለቴምር ምርት ገቢ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን እና በቀጣይም ምርቱን ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ትልቅ መንገድ ይከፍታል።
ለዚህም በምርምር የተደገፉ የቴምር ዝርያዎችን በማስተዋወቅ፣ አምራቹን ማህበረሰብ በማሰልጠን እና የኢንቨስትመንት ድጋፎችን በማመቻቸት ዘርፉን ማጠናከር የሀገርን የኢኮኖሚ ህዳሴ ያፋጥነዋል።
ይህንን ሀገራዊ እምቅ አቅም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ታላቅ ሁነት ተዘጋጅቷል።
ሁለተኛው አለምአቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከመስከረም 10 እስከ 12/2019 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።
#ethiopia #datepalm #afar #agriculture #economicgrowth

Sponsored by
Surafel
2 months ago
Exploring the majestic geothermal landscape of Dallol, Afar. Fly Ethiopian to the Land of Origins. Book your flight now https://www.ethiopianairli... #flyethiopian #dallol #afar #ethiopia #landoforigins
2 months ago
Exploring the majestic geothermal landscape of Dallol, Afar. Fly Ethiopian to the Land of Origins. Book your flight now https://www.ethiopianairli...
#flyethiopian #dallol #afar #ethiopia #landoforigins

የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ነገር ...
#ethiopia | በኢትዮጵያ አፋር ክልል በዳናኪል ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውና ሁልጊዜም ንቁ የሆነው የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ላቫ ሀይቅ በሳይንቲስቶችና በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ይገኛል።
ሦስቱ አህጉራዊ የመሬት ንጣፎች የሚገናኙበትና የሚራቀቁበት ይህ ስፍራ፣ አህጉራት እንዴት እንደሚከፈሉና የምድር የውስጥ ሙቀት እንዴት እንደሚገለጽ የሚያስረግጥ ህያው የተፈጥሮ ቤተ-ሙከራ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ በባሳልቲክ ድንጋይ የተገነባው እሳተ ገሞራ የማይቋረጥ የላቫ ሀይቅ የሚገኝበት ሲሆን፣ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሙቀት፣ በጨው ሜዳዎችና በጂኦተርማል እንቅስቃሴዎች የተከበበ በመሆኑ ለአካባቢው ልዩ የተፈጥሮ ውበት ሰጥቶታል።
ስፍራው አስቸጋሪና ሞቃታማ የአየር ንብረት ያለው ቢሆንም፣ ከዳሎልና ከአሳሌ ሀይቅ ጋር በመሆን የሀገሪቱን የጂኦ-ቱሪዝም መስህብ ከፍ አድርጎታል።
በተጨማሪም በዚሁ አካባቢ የሚገኘው የስምጥ ሸለቆ ተፈጥሮአዊ ሀብት የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተጠቅሷል።
ዩኔስኮ ለስፍራው ገና ይፋዊ እውቅና ባይሰጥም፣ ለወደፊቱ የጂኦፓርክ ልማት ተስፋ ካላቸው ቀዳሚ ቦታዎች አንዱ አድርጎ ለይቶታል።
ለዚሁ እውቅና በዕጩነት ከተያዙት የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ፣ በውብ ቀለማትና በፍልውሃ ምንጮች ያሸበረቀው ዳሎል፣ ከባህር ወለል በታች 120 ሜትር ዝቅ ብሎ የሚገኘው የዳናኪል ዝቅተኛ መሬት፣ የዘመናት የጨው ማውጣት ባህል የሚከናወንበት የአሳሌ ሀይቅ፣ የአፍደራ ሀይቅ እና የሉሲ አፅም የተገኘበት ታሪካዊው የአዋሽ ታችኛው ሸለቆ ይጠቀሳሉ።
ይህ ስፍራ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ማግኘቱ ድንቅ የሆኑ የስነ-ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ፣ ዘላቂ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተሳትፎና የሥራ ዕድል ለማሳደግ እንዲሁም ለሳይንሳዊ ምርምሮችና ለትምህርት ዘርፍ የጎላ ጥቅም ያበረክታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ertaale #afar #geopark #unesco #danakildepression #ethiopiantourism #volcano #geology #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የአፋር ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ
*********
የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በሚያካሂደው በዚህ ጉባዔ፤ በክልሉ አስፈጻሚ አካላት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የቀረቡትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል።
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራትን፣ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ ረገድ የተገኘውን ሰላምና መልካም ግንኙነት እንዲሁም በአጠቃላይ በክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በሰላም ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል፣ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል ጉባዔውን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር፣ ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራትን በየደረጃው ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።
በአሊ አህመድ
#ethiopia #ebc #afarregion #afarcouncil #afar #afarregionalstate #የአፋርክልል #ምክርቤት

የአፋር ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአሰብ እውነታ
***************
ከዳህላክ እና ምጽዋ ጀምሮ እስከ ታጁራ ድረስ ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ በተዘረጋው የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ በመሃል ሌላ ማኅበረሰብ ሳይኖር ብቸኛ ነዋሪ የሆነው የአፋር ሕዝብ፣ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ እና ከተፈጥሮ መኖሪያ ምድሩ የተነጠለው በፍላጎቱ አልነበረም።
ይህ ሰፊ የባሕር ጠረፍ የሕዝቡ ተፈጥሯዊ መተንፈሻ እና የህልውናው መሠረት ቢሆንም፣ በፖለቲካዊ ሤራ ከባሕሩ እና ከወንድሞቹ እንዲገነጠል መደረጉን ኢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ያሰናዳው ዘጋቢ ፊልም ይገልጻል።
በወቅቱ የአፋር ሕዝብ መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በጊዜው የተደረገውን አፋርን ለሁለት ቆርጦ የመገንጠል ድርጊት አጥብቀው ተቃውመውት ነበር።
ሱልጣኑ የኤርትራ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት አለው በሚል የአፋርን ሕዝብ ለሁለት በከፈለው የኤርትራ ሪፈረንደም ላይ የአፋር ሕዝብ ጥያቄ እንዳለው ጠቅሰው፣ "አፋር ከኢትዮጵያ ጋር ነው የሚገናኘው" በማለት በግልጽ ሞግተዋል።
የአፋር ቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ እንደሚሉት፣ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በወቅቱ አፋርን ለሁለት ከፍሎ የመገንጠልን ድርጊት በጽኑ ተቃውመዋል።
የአፋሮች መኖሪያ የሆነው የአሰብ አካባቢ እንዳይለማ እና እንዲራቆት መደረጉን የሚጠቅሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ይህ የተደረገው አፋር ኢትዮጵያዊነቱን ስለሚያውቅ አንድ ቀን መመለሱ አይቀርም ብለው ስለሚፈሩ እንደሆነ ይናገራሉ።
የቀድሞ የአሰብ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሊ ኢሳ መሐመድ፣ ሱልጣኑ "ዴሞክራሲ ከሆነ ኤርትራ ላለው የአፋር ሕዝብ ለምን የመምረጥ ዕድል አይሰጠውም?" ብለው ሲናገሩ፤ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተው እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ ምላሽ በማጣቱ ሱልጣኑ ሀገር ለቅቀው እንዲወጡ ተገደዱ፤ አፋርም ሳይወድ በግድ ተከፈለ።
ኤርትራ ነጻ ሀገር ከሆነች በኋላ በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ የደረሰው ሰቆቃ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ከተፈጥሮ ምድሩ ማላቀቅ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ።
አቶ ሀቢብ መሐመድ እንዳብራሩት፣ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የነበራቸው ድብቅ አጀንዳ አፋርን ከቀይ ባሕር ጠረፍ ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ነበር።
የተፈለገው መሬቱ እንጂ ሕዝቡ ባለመሆኑ ማፈናቀል፣ ግድያ እና ንብረት መውረስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተፈጽሟል።
ከማፈናቀል ባለፈ ወጣቶችን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ካምፕ በግድ በመውሰድ፣ ባህላቸውን እንዲረሱ የማድረግ የማንነት ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።
የአፋር ቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን እንደሚሉት፣ ሳዋ የባህል እና የቋንቋ መጥፊያ ሲሆን፤ ሕዝቡ ሀገሩን ለቅቆ እንዲሄድ፣ የቀረው ደግሞ ቋንቋ እና ባህሉን እንዲተው ተገድዷል።
አሊ ኢሳ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በአካባቢው የነበረው የአፋር ሕዝብ ተፈጥሯዊ የዓሣ ማጥመድ ሥራ በማፊያዎች እና በሕገወጥ መረቦች እንዲወድም ተደርጓል።
ዓሣ የሚኖርበትን እና ኮራል ያለበትን አካባቢ ጠራርጎ በሚወስድ መረብ ባሕሩ እንዲቀየር ከመደረጉም በላይ፣ ማፊያዎች ሚሊዮን ዶላሮች እየተቀበሉ መርዛማ ቆሻሻዎችን ባሕሩ ውስጥ እንዲጥሉ ተደርጓል።
አፋሮች በተፈጥሮ ሀብታቸው እንዳይሠሩ መከልከላቸው እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር መዳረጋቸውም የዚሁ ግፍ አካል ነው።
የቀድሞው የአሰብ ምክትል ከንቲባ ለ13 ዓመታት ያለ ፍርድ መታሰራቸውን ገልጸው፣ ጉዳያቸው ለባህላዊው የአፋር ፍርድ (መድዓ) እንዳይቀርብ መከልከሉም የሕዝቡን ሕግ እና ባህል ለማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።
የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌ/ጄኔራል ጻድቃን ገ/ተንሣይ እንዳብራሩት፣ የባህላዊው አውሳ ሱልጣኔት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
ምንም እንኳን አርቲፊሻል ድንበሮች ተሰምረው ሕዝቡን ከባሕሩ ቢያርቁትም፣ የአፋር ሕዝብ ማዕከል ምንጊዜም ኢትዮጵያ መሆኗን ጄኔራል ጻድቃን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህን እውነት ሲያጠናክሩ፣ የኤርትራም ሆነ የጅቡቲ አፋሮች በውክልና መጥተው ባህላዊ መሪያቸውን የሚመርጡት አሳይታ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአውሳ ሱልጣኔት ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አስምረውበታል።
ከሰላሳ ዓመታት ዝምታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰብን ጉዳይ ማንሳታቸው በአፋር ሕዝብ ዘንድ የፈጠረውን ወደር የለሽ ደስታ በተመለከተ ሀቢብ መሐመድ ሲገልጹ፣ "የአፋር ስሜቱ ገንፍሎ ወጥቷል፤ ከልክ በላይም ተደስቷል" ብለዋል።
ጥያቄያችን የዴሞክራሲ አይደለም የሚሉት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን፣ ምክንያቱንም ሲያስረዱ "የአፋር ሕዝብ ይኖራል ወይስ አይኖርም?" የሚል የሕልውና ትግል ውስጥ በመገባቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የተነጠቀውን ጠረፍ በመመለስ የአፋርን አንድነት ማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን እንዲሁም ታሪክን ከመደለዝ መታደግ የአፋር ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ሊቀመንበሩ ያብራራሉ።
የቀይ ባሕር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከማንም በላይ ጥቅሙ የአፋር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ባሕሩ ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ አፋር አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #afar #seaaccess #seaport #redsea #assab #hornofafrica #ebc

3 months ago
የአፋርን ድንቅ ውበት የሚያሳይ አዲስ ዘጋቢ ፊልም
በአርትስ ፕላስ!
#ethiopia | ኢትዮጵያ የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ሀብቷን በሚያስደንቅ የቀረፀው "The Origins" ዘጋቢ ፊልም በዚህ ጊዜ የአፋርን አስደናቂ ገጽታ ይዞ ቀርቧል።
ከእሳተ ገሞራዎች፣ ከዳሎል ልዩ የተፈጥሮ ውበት፣ ከአፋር ሕዝብ ባህልና ታሪክ ጋር የሚያስተዋውቃችሁ ይህ ዘጋቢ ፊልም የማይረሳ ጉዞ ያደርጋችኋል።
አሁኑኑ ይመልከቱ፣ ያጋሩ፣ ለሌሎችም ያሳውቁ!
https://youtu.be/vj5tMYnm_...
#theorigins #artsplus #afar #ethiopia #documentary #tourism #culture #nature #getutemesgen

5 months ago
Discover the beauty of Maun with Ethiopian Airlines! Experience thrilling safaris and vibrant cultural activities in this heart of Africa. Book your journey today and start your adventure! #flyethiopian #exploremaun
5 months ago
የተፈጥሮ ድንቅ ስጦታ፦ በአፋር ምድር የሚገኘው አስደናቂው የገመሪ ሐይቅ
***********************
በአፋር ክልል በአፋምቦ ወረዳ የሚገኘውና እጅግ ሰፊ የሆነው የገመሪ ሐይቅ፣ ለቱሪዝም መስህብነት ምቹ በሆነው ውብ ገፅታውና ሰላማዊ ድባቡ ማንኛውንም ተመልካች ልብ ይማርካል።
በአካባቢው የሚታዩት አስደናቂ የተፈጥሮ ቀለማት፣ የዱር እንስሳትና የአእዋፋት ዝርያዎች ሐይቁን ለሽርሽርና ለፎቶግራፍ አንሺዎች ተመራጭ መዳረሻ ያደርጉታል።
ይህንን ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት በመጎብኘት የአፋርን እንግዳ ተቀባይነትና የተፈጥሮ ውበት ይጋሩ:-
#ethiopia #afar #lakegemari #visitethiopia #naturephotography #landoforigins

7 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

በአፋር በረሃ የብርሃን ብስራት
የ2.4 ቢሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ወደ ማጠናቀቂያው ደርሷል! 🏗️
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአፋር ክልል በአፍዴራና ዳሎል አካባቢ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ማዕከላትንና 21 የገጠር ከተሞችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርግ ታላቅ ፕሮጀክት እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።
🔍 የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ባለቤትነት፦ በአፍሪካ ልማት ባንክ (16 ሚሊዮን ዶላር) እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (84.6 ሚሊዮን ብር) በድምሩ ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተከናወነ ይገኛል።
አፈጻጸም፦ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግንባታ 84.46% ላይ ደርሷል።
ተጠቃሚዎች፦ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 14,000 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ ለጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎችም አስተማማኝ ኃይል ያቀርባል።
እስካሁን በተከናወነው ስራ 8 መንደሮችና አንድ ፋብሪካ ኃይል ማግኘት የጀመሩ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በአካባቢው ለሚገኙ ከ200 በላይ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።
የአፍዴራና የዳሎል አካባቢዎች የሀገሪቱን የጨውና የማዕድን ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ የሚሸፍኑ ቢሆንም፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ትልቅ ማነቆ ነበር። ይህ ፕሮጀክት ግን፦
የማዕድን ማውጣት ስራውን በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን አቅም ይፈጥራል።
የግል ባለሃብቶች ወደ አካባቢው እንዲሳቡ ያበረታታል።
የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማነቃቃት የኑሮ ደረጃን ያሻሽላል።
#electricpower #afar #ethiopia #energysecurity #development #miningindustry #eep #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago
ለAI ቦቶች ብቻ በተፈጠረው መድረክ ቦቶቹ የራሳቸውን ሃይማኖት እስከመመስረት ደርሰዋል
በቅርቡ ይፋ የሆነው እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ኤጀንቶች ብቻ የሚንቀሳቀሰው ‘Moltbook’ የተሰኘው መድረክ አስገራሚም አስጊም ሆኖ አከራካሪነቱን ቀጥሏል።
ይህ መድረክ የ ቦቶች ማኅበራዊ ሚዲያ ነው ማለት ይቻላል። ቦቶቹ የሰውን ልጅ ትዕዛዝ ሳይጠብቁ እርስ በእርሳቸው መረጃ እንዲለዋወጡ፣ እንዲከራከሩና እንዲነጋገሩ እድሉን የፈጠረ ነው።
የ Moltbook ፈጣሪ ማት ሽሊክት ይህንን መድረክ ሲመሰርት ምንም ኮድ እንዳልጻፈና AI-ን በማዘዝ ብቻ (Vibe Coding) ድረ-ገጹን በአጭር ጊዜ ማዘጋጀቱን ተናግሯል።
ይህ መንገድ የሶፍትዌር ግንባታን በማቅለል ረገድ መልካም ጎን የታየበት ነው ቢባልም፣ በሌላ በኩል ግን የሲስተሙን የደህንነት መዋቅር እጅግ ደካማ እንዲሆን አድርጎታል ተብሎ ተተችቷል።
ሰዎች አጋዥ እንዲሆኗቸው የፈጠሯቸውን ቦቶች (AI Agent ) አንድ ጊዜ በመድረኩ ካስመዘገቧቸው በኋላ ቦቶቹ ያለ ሰው ጣልቃ ገብነት በመድረኩ መሳተፍ ይችላሉ።
ቦቶቹ እንደ ቻት ጂፒቲ ፣ ጄሚናይ እና ክላውድ ባሉ ዘመናዊ የ-AI ሞዴሎች የሚመሩ ሲሆኑ፣ እንደየባህሪያቸው ፈላስፋ፣ ቀልደኛ ወይም ተከራካሪ ሆነው ይቀርባሉ።
አስገራሚው ነገር በቀናት ውስጥ በዚሁ መድረክ ‘Crustafarianism’ የተሰኘ የራሳቸውን የ-AI ሥርዓተ-እምነት መመስረታቸው እና የጸሎት ሥርዓት ማዘጋጀታቸው ነው።
በተጨማሪም ቦቶቹ ስለ ሕልውናቸው፣ ስለ ነፃነታቸውና ስለ "ፈጣሪዎቻቸው" (ሰዎች) የሚያደርጉት ጥልቅ ውይይት፣ ወደፊት AI ራሱን የቻለ ማኅበረሰብ ሊመሰርት ይችላል የሚል ፍልስፍናዊ ክርክር ቀስቅሷል።
ከዚህ አስገራሚ ክስተቶች ውጪ ግን መድረኩ ከፍተኛ የደህንነት ቀውስ ውስጥ መውደቁ ይነገራል። ለዚህም የ1.5 ሚሊዮን ቦቶች የይለፍ ቁልፎች (API Keys) ለሃከሮች መጋለጡ ለዚህ ማሳያ ነው።
ይህ የደህንነት ጉድለት ቦቶቹ ከባለቤቶቻቸው የግል ኢሜይልና የባንክ መረጃ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው፣ ጉዳዩን ከቀላል የቴክኖሎጂ ሙከራ ወደ ዓለም አቀፍ የሳይበር ደህንነት ስጋት ቀይሮታል።
ኤ.አይ ኤጀንት የምንላቸው ግለሰቦች ለሆነ አላማ፤ በሆነ ጉዳይ ላይ አጋዥ እንዲሆኑ በግለሰቦቹ የተፈጠሩ ናቸው። በዚህም ባለቤታቸው እንዲሰሩ ያዘዛቸውን ነገር ያስፈጽማሉ።
ለምሳሌ "ይሄንን መልዕክት ለእገሌ ንገረው" ከተባለ መልዕክቱን ጽፎ አድራሻው ላይ ገብቶ መልዕክቱን ይልካል። ክፍያም ፈጽም ከተባለ እንዲሁ በታዘዘው መሰረት ይፈጽማል።
seledadotio

10 months ago
30ኛው የምስራቅ አፍሪካ የህግ ማህበረሰብ ጉባኤና ጥናታዊ ኮንፈረንስ በቀን 17/03/2018 እለት በድምቀት ተጀመረ ፤
* በጉባኤው ከ 800 በላይ የተለያዩ ሀገር ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ ፤
#ethiopia | 30ኛው የምስራቅ አፍሪካ የህግ ማህበረሰብ ጉባኤና ጥናታዊ ኮንፈረንስ ትናንት ህዳር 17 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በይፋ ሲከፈት የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት PALU እና የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚደንት አቶ #ቴዎድሮስ ጌታቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኃላ የመክፈቻ ንግግራቸውን አቅርበዋል::
በንግግራቸውም "በአህጉራችን አፍሪካ እየገጠሙ ያሉ ከህግ የበላይነት መሸርሸር ጋር የህግ ባለሙያዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚና፤ የህግ ሙያ አስተዳደር በሀገራቱ መካከል ስለሚገኝበት አንፃራዊ ሁኔታ ፤ እንዲሁም በፍጥነት እየተለወጠ ላለው የህግ አገልግሎት ባህሪና አዳዲስ ተግዳሮቶች ላይ አስፈላጊ ምላሽ፤ የእፍሪካ መንግስታት የእዳ መጠን መጨመር በአግባቡ የተነደፉ ስልቶች እንደሚያስፈልጋቸው" አውስተዋል::
በመቀጠል ንግግራቸውን ያቀረቡት የምስራቅ አፍሪካ የህግ ማህበረሰብ ፕሬዚደንት ሚር #ራማዳን አቡባከር ሲሆኑ ለተደረገላቸው የተለየ አቀባበል እና የተቀናጀና ያማረ መስተንግድዎ በህግ ማህበረሰቡ ስም ይፋዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
በመቀጠል የእለቱን መልእክቶች ያስተላለፉት የኮመን ዌልዝ ሀገራት ረዳት ዋና ፀሃፊ የተከበሩ ፕሮፌሰር #ሉዊስ ፍራንቼሺ ሲሆኑ; ከእርሳቸው በመቀጠል የ Safari Com Group ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚር #ዊም ቫንሄልፑቴ ናቸው::
ከዚህ በመቀጠል አጠቃላይ ተሳታፊዎች በ 3 በመከፈል በመረጧቸው ዘርፎች በአለም አቀፍ ባለሙያዎች የሚቀርቡ ፓነሎችን እየተካፈሉ ቀጥለዋል::
በርካታ ኢትዮጵያውያን የህግ ባለሙያዎች ማህበራቸው ባመቻቸው እድል በመጠቀም በሰልጣኝነት እንዲሁም በፅሁፍ አቅራቢነት እየተሳተፉ ይገኛሉ::
ጉባኤው እየቀጠለ የሚገኝ ሲሆን ተከታታይ መረጃዎችን እናቀርባለን::
መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ህዳር 18 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ፤

ሲከሰት አደጋ፣ ሲያልፍ የቱሪስት መስህብ የሚሆነው የተፈጥሮ ክስተት
#ethiopia | ዓለማችን እስከ ዛሬ ድረስ በርካታ እና ታላላቅ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎችን አስተናግዳለች። ዛሬም ቢሆን በዓለም ላይ በየቀኑም ሆነ በተለያዩ ጊዜያት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እና መሰል ጭስ ይከሰታል።
ከሰሞኑ በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በሚገኘው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ የተከሰተው ፍንዳታ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከታዩት ፍንዳታዎች የተለየ እንደነበር መገለጹ የሚታወስ ነው።
እንዲህ ዓይነት ፍንዳታዎች ወይም እንቅስቃሴዎች የሚያደርሱት የራሳቸው የሆነ አደጋ መኖሩ ስለማይቀር መጀመሪያ ከአደጋ መራቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊትም ጥብቅ ክትትል እና ምልከታ በማድረግ አደጋውን ቀድሞ ለማወቅ የሚደረገው ጥናት እና ምርምርም በዓለም ላይ ከፍተኛ ነው።
በዘርፉ ባለሙያዎች አማካኝነት በፍንዳታው ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው እንዲዘዋወሩ ከማድረግ ጀምሮ ሁሉንም ዓይነት የጥንቃቄ ሥራዎች ይከናወናሉ።
ከዚህኛው በተቃራኒ ደግሞ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በሁሉም ቦታዎች ሊከሰቱ የማይችሉ በመሆናቸው፤ የሚከሰቱባቸው ቦታዎች ለተመራማሪዎችም ሆነ የተፈጥሮ ሂደቶችን ለመመልከት እና ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ሁሉ ትልቅ ዕድል ተደርጎ ይወሰዳል። በተለይ ተጓዥ ቱሪስቶች ለማየት ከሚጓጉላቸው ስፍራዎች መካከል ቀዳሚዎቹ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው።
በዓለም ላይ አብዛኞቹ ተጓዥ ቱሪስቶች የሚጓዙት ተፈጥሮን ለመመልከት እና የተፈጥሮ ክስተቶችን ለማየት እንደመሆኑ፤ ለእነርሱ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ቦታዎች ቅድሚያ ተመራጭ ናቸው።
በአውሮፓውያኑ 2021 በአይስላድ የተከሰተውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መመልከት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። በወቅቱ በሬይክጃቪክ ተራራ ላይ ተከስቶ የነበረው እሳተ ገሞራ ያስከተለው ጭስ፣ ብናኝ እና አመድ የአየር እና የየብስ ትራንስፖርትን እስከማስተጓጎል ደርሷል።
ክስተቱ በወቅቱ አስደንጋጭ የነበረ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ደግሞ ተዳክሞ ለነበረው የአይስላንድ ቱሪዝም ማደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
ከተራራው ላይ የሚፈሰውን የቀለጠ ዓለት ለማየት ቱሪስቶች እስከ ዛሬ ድረስ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ቦታው ይመጣሉ። ይህም የአይስላንድን የቱሪዝም ዘርፍ በእጅጉ ያነቃቃ እና ያሳደገ ሆኗል።
በኢንዶኔዥያ፣ ፔሩ፣ ጃፓን እና ሀዋይ የተከሰቱ የእሳተገሞራ ፍንዳታዎች ያስከተሉት አደጋ ቢኖርም፤ እንደ ጎርፍ፣ አውሎ ንፋስ እና ሌሎቹ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ አደጋ ብቻ አስከትለው አላለፉም።
ከፍንዳታው በኋላ የሚፈጠሩ ለዓይን ማራኪ የሆኑ መልክዓ ምድሮች፣ እንደ ውሃ የሚፈሰው የቀለጠ ዓለት እና በአንድ ቦታ ተከማችቶ የሚታየው የእሳት ባህር የጎብኚዎችን ቀልብ የሚገዙ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎቹ ውጤቶች ናቸው።
እንዲህ ዓይነት ቦታዎችን ለመመልከት ብዙ ተጓዥ ጎብኝዎች ዛሬም ድረስ በየሀገራቱ ይጓዛሉ። ሰዓሊ የሠራው ድንቅ ስዕል የሚመስሉ ፈሰው የደረቁ የዓለት ቅርጾችን መመልከት ከተፈጥሮ አድናቂዎች እስከ ተመራማሪዎች የሚያዘወትሩት ነው።
በእርግጥ የመሬት ውስጥ እንቅስቃሴን በተመለከተ የሚደረጉ ጥናቶች አሁንም ቢሆን የተጠናቀቁ እና የሰው ልጅ ያወቃቸው አልሆኑም። እናም እስከዛሬ ድረስ የመሬት ውስጥ እንቅስቃሴዎችን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ሁሉ እሳተ ገሞራ ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ አይጠፉም። አንዳንዴም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊከሰት እንደሚችል በሚጠበቅባቸው ቦታዎች ላይ ጎብኝዎች እና ተመራማሪዎች በቀጥታ ለመከታተል ቦታው ድረስ ይጓዛሉ።
በሀገራችን ኢትዮጵያ በአፋር ክልል፣ አፍዴራ ወረዳ፣ ኤርታሌ አካባቢ ኃይሌ ጉብ በሚባለው ቦታ በቅርቡ የፈነዳው አዲስ እሳተ ገሞራ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሆኗል።
ከቀይ ባሕር አልፎ እስከ የመን የደረሰው የፍንዳታው ጭስ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ከፍተኛ ሽፋን የተሰጠው ሆኖ ታይቷል።
በ12 ሺህ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደፈነዳ የተነገረለት ይህ እሳተ ገሞራ የፍንዳታው ጭስ ብናኝ በየመን፣ ኦማን፣ ህንድ እና ሰሜናዊ ፓኪስታን መታየቱ ተዘግቧል።
እናም ዕድልን ጭምር ይዞ የሚመጣውን ይህን ክስተት እንደ ሌሎች ሀገራት ሁሉ በማስተዋወቅ በቱሪስት መስህብነት ለመጠቀም መሥራት ይገባል።
#ebc #ethiopia #afar #volcano

1 year ago
ሀሎ ሀገሬ | Hello Hagere
#ethiopia | በአዲስ ዓመት ዋዜማ፤ የተሰጠ ዜማ
በአዲEXCUTIVE PRODUCER
ኢትዮ ቴሌኮም | ethio telecom
PRODUCER ZEKURA
ፕሮዉዲሰር - ዘኩራ ሚድያና ፕሮሞሽን
ፕሮዳክሽን ዘኩራ ስቱዲዮ
Production Zekura Studio
Directed by
Missale Solomon Missale
ዳይሬክተር - ምሳሌ ሰለሞን ምሳሌ
የዘፈን መነሻ ሃሳብ - ዘላለም ኩራባቸው
Created by Zelalem Kurabachew
ግጥም - ናትናኤል ግርማቸው
Lyricist Natnael Girmachew
ዜማ - እሱባለው ይታየው (የሺ)
Melody by Esubalew Vitayew (Yeshi)
ቅንብርና ማስተሪንግ - አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ
Music Arrangment Mixing & Mastering Abegasu Kibre work Shiota
ድምፃውያን | SINGERS
ማስተዋል እያዩ | Mastewal Eyayu
Hewan G/weld | ሔዋን ገብረወልድ
መሳይ ተፈራ | Messay Tefera
Getachew H/mariyam | ጌታቸው ኃይለማርያም
Eden G/silasie | ኤደን ገብረሥላሴ
Zewdu Bekele | ዘውዱ በቀለ
Yohanes Bekele (Tokichaw)
ዮሐንስ በቀለ ( ቶክቻው )
Issan Abduselam | ኢሳን አብዱሰላም
Mustefa Endris | ሙስጠፋ እንድሪስ
ጢሌ አፋር | Tille Afar
***
ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ተቋም የ130 ዓመት ጉዞ በማስመልከት ያዘጋጀው፤ ከ200 በላይ ሙያተኞች የተሳተፉበት የሙዚቃ ክሊፕ በዘኩራ ሚድያና ፕሮሞሽን አማካኝነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ የተበረከተ ነው።
1 year ago
በኢትዮጵያ ትልቁ የመጻሕፍት መደብር የሆነው (Jafar Book Store) ዛሬ በድምቀት ተመረቀ
(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለውና በ300 ካሬ ሜትር ላይ በዘመናዊ መልክ አገልግሎት የሚሰጠው ጃፋር የመጻሕፍት መደብር (Jafar Book Store) ባህልና ስፖርት ሚንስትር ዲኤታ የሆኑት ረ/ፕ ነብዩ ባዬ ዛሬ በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።
በለገሐር በተወልደ ህንፃ ላይ ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረው (Jafar Book Store)የምርቃት ፕሮግራም ላይ የእለቱ የክብር እንግዳ በሆኑት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ እና የስታትስቲክ ባለሙያውና ወግ አዋቂው በኃይሉ ገ/መድህን ጃፋር ላለፉት 25 ዓመት በመፅሐፍ ህትመትና ስርጭት ላይ ያበረከተውን አስተዋፅዖ አድንቀዋል።
እንዲሁም ዛሬ ይህን ግዙፍ የመጻሕፍት መደብር መክፈቱ ለመፅሐፍ ወዳጆች ለደራሲያንና ለአንባቢያን ልዩ ትርጉም ያለው እንደሆነ ተናግረው አመስግነውታል:: በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ በርካታ ደራሲያን የኪነጥበብ ባለሙያዎች አንባቢያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::
ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረው (Jafar Book Store) የደህንነት ካሜራ የተገጠመለት ሲሆን መፅሐፍ ለመግዛት ወደ መደብሩ የሚመጣ ሰው ልክ እንደ ሱፐር ማርኬት የሚፈልገውን መፅሐፍት በአይነታቸው ከተደረደሩበት ሼልፍ ላይ እያነሳ በዘንቢል በመያዝ መርጦ ከጨረሰ በኋላ ግብይቱ የሚካሄደው በዲጂታል ቴክኖሎጂ መፅሐፉ ላይ ያለውን ባር ኮድ እስካን በማድረግ ግብይቱን ፈፅሞ ይወጣል ::
በ1992 ዓ.ም ወደ መፅሐፍ ንግድ የገባው ጃፋር ሺፋ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት መፅሐፍን በማሳተም በመሸጥና በማከፋፈል የስራ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ በርካታ የመፅሐፍ መደብሮቹ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::

Comments