14 days ago
የአፋር ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአሰብ እውነታ
***************
ከዳህላክ እና ምጽዋ ጀምሮ እስከ ታጁራ ድረስ ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ በተዘረጋው የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ በመሃል ሌላ ማኅበረሰብ ሳይኖር ብቸኛ ነዋሪ የሆነው የአፋር ሕዝብ፣ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ እና ከተፈጥሮ መኖሪያ ምድሩ የተነጠለው በፍላጎቱ አልነበረም።
ይህ ሰፊ የባሕር ጠረፍ የሕዝቡ ተፈጥሯዊ መተንፈሻ እና የህልውናው መሠረት ቢሆንም፣ በፖለቲካዊ ሤራ ከባሕሩ እና ከወንድሞቹ እንዲገነጠል መደረጉን ኢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ያሰናዳው ዘጋቢ ፊልም ይገልጻል።
በወቅቱ የአፋር ሕዝብ መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በጊዜው የተደረገውን አፋርን ለሁለት ቆርጦ የመገንጠል ድርጊት አጥብቀው ተቃውመውት ነበር።
ሱልጣኑ የኤርትራ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት አለው በሚል የአፋርን ሕዝብ ለሁለት በከፈለው የኤርትራ ሪፈረንደም ላይ የአፋር ሕዝብ ጥያቄ እንዳለው ጠቅሰው፣ "አፋር ከኢትዮጵያ ጋር ነው የሚገናኘው" በማለት በግልጽ ሞግተዋል።
የአፋር ቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ እንደሚሉት፣ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በወቅቱ አፋርን ለሁለት ከፍሎ የመገንጠልን ድርጊት በጽኑ ተቃውመዋል።
የአፋሮች መኖሪያ የሆነው የአሰብ አካባቢ እንዳይለማ እና እንዲራቆት መደረጉን የሚጠቅሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ይህ የተደረገው አፋር ኢትዮጵያዊነቱን ስለሚያውቅ አንድ ቀን መመለሱ አይቀርም ብለው ስለሚፈሩ እንደሆነ ይናገራሉ።
የቀድሞ የአሰብ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሊ ኢሳ መሐመድ፣ ሱልጣኑ "ዴሞክራሲ ከሆነ ኤርትራ ላለው የአፋር ሕዝብ ለምን የመምረጥ ዕድል አይሰጠውም?" ብለው ሲናገሩ፤ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተው እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ ምላሽ በማጣቱ ሱልጣኑ ሀገር ለቅቀው እንዲወጡ ተገደዱ፤ አፋርም ሳይወድ በግድ ተከፈለ።
ኤርትራ ነጻ ሀገር ከሆነች በኋላ በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ የደረሰው ሰቆቃ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ከተፈጥሮ ምድሩ ማላቀቅ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ።
አቶ ሀቢብ መሐመድ እንዳብራሩት፣ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የነበራቸው ድብቅ አጀንዳ አፋርን ከቀይ ባሕር ጠረፍ ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ነበር።
የተፈለገው መሬቱ እንጂ ሕዝቡ ባለመሆኑ ማፈናቀል፣ ግድያ እና ንብረት መውረስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተፈጽሟል።
ከማፈናቀል ባለፈ ወጣቶችን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ካምፕ በግድ በመውሰድ፣ ባህላቸውን እንዲረሱ የማድረግ የማንነት ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።
የአፋር ቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን እንደሚሉት፣ ሳዋ የባህል እና የቋንቋ መጥፊያ ሲሆን፤ ሕዝቡ ሀገሩን ለቅቆ እንዲሄድ፣ የቀረው ደግሞ ቋንቋ እና ባህሉን እንዲተው ተገድዷል።
አሊ ኢሳ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በአካባቢው የነበረው የአፋር ሕዝብ ተፈጥሯዊ የዓሣ ማጥመድ ሥራ በማፊያዎች እና በሕገወጥ መረቦች እንዲወድም ተደርጓል።
ዓሣ የሚኖርበትን እና ኮራል ያለበትን አካባቢ ጠራርጎ በሚወስድ መረብ ባሕሩ እንዲቀየር ከመደረጉም በላይ፣ ማፊያዎች ሚሊዮን ዶላሮች እየተቀበሉ መርዛማ ቆሻሻዎችን ባሕሩ ውስጥ እንዲጥሉ ተደርጓል።
አፋሮች በተፈጥሮ ሀብታቸው እንዳይሠሩ መከልከላቸው እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር መዳረጋቸውም የዚሁ ግፍ አካል ነው።
የቀድሞው የአሰብ ምክትል ከንቲባ ለ13 ዓመታት ያለ ፍርድ መታሰራቸውን ገልጸው፣ ጉዳያቸው ለባህላዊው የአፋር ፍርድ (መድዓ) እንዳይቀርብ መከልከሉም የሕዝቡን ሕግ እና ባህል ለማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።
የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌ/ጄኔራል ጻድቃን ገ/ተንሣይ እንዳብራሩት፣ የባህላዊው አውሳ ሱልጣኔት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
ምንም እንኳን አርቲፊሻል ድንበሮች ተሰምረው ሕዝቡን ከባሕሩ ቢያርቁትም፣ የአፋር ሕዝብ ማዕከል ምንጊዜም ኢትዮጵያ መሆኗን ጄኔራል ጻድቃን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህን እውነት ሲያጠናክሩ፣ የኤርትራም ሆነ የጅቡቲ አፋሮች በውክልና መጥተው ባህላዊ መሪያቸውን የሚመርጡት አሳይታ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአውሳ ሱልጣኔት ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አስምረውበታል።
ከሰላሳ ዓመታት ዝምታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰብን ጉዳይ ማንሳታቸው በአፋር ሕዝብ ዘንድ የፈጠረውን ወደር የለሽ ደስታ በተመለከተ ሀቢብ መሐመድ ሲገልጹ፣ "የአፋር ስሜቱ ገንፍሎ ወጥቷል፤ ከልክ በላይም ተደስቷል" ብለዋል።
ጥያቄያችን የዴሞክራሲ አይደለም የሚሉት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን፣ ምክንያቱንም ሲያስረዱ "የአፋር ሕዝብ ይኖራል ወይስ አይኖርም?" የሚል የሕልውና ትግል ውስጥ በመገባቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የተነጠቀውን ጠረፍ በመመለስ የአፋርን አንድነት ማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን እንዲሁም ታሪክን ከመደለዝ መታደግ የአፋር ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ሊቀመንበሩ ያብራራሉ።
የቀይ ባሕር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከማንም በላይ ጥቅሙ የአፋር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ባሕሩ ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ አፋር አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #afar #seaaccess #seaport #redsea #assab #hornofafrica #ebc

1 month ago
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሌሎችን ሉዓላዊነት የማይጋፋ፣ ይልቁንም የጋራ ሰላምና ልማት ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረገ ነው - ምሁራን
*****************************
ኢትዮጵያ ከባሕር በር መራቋ ለኢኮኖሚ ዕድገቷ ትልቅ ፈተና መደቀኑን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የባሕር በር ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም እና የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ፣ በመደመር እሳቤ ታግዞ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈጸም እንዳለበት ተመላክቷል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ኢትዮጵያ ከባሕር በር መራቋ ታሪካዊ መዘዝ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም፣ በውስጥም በውጪም የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ አካላት በመደራጀት ሀገራችን ወደብ እንዳትጠቀም የተለያዩ መሰናክሎችን ሲፈጥሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት መምህር የሆኑት በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣ በአሁኑ የዓለም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የባሕር በር ወይም ወደብ ማግኘት ለአንድ ሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በአፅንዖት ገልጸዋል።
የባሕር በር ከሌለ የሀገር ዕድገት ውስን እንደሚሆን የገለጹት ዶ/ር በለጠ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅም ማደጉና የሕዝብ ቁጥር መጨመሩ ደግሞ ጉዳዩን አንገብጋቢ አድርጎታል ብለዋል።
አክለውም፣ መፍትሄው በመደማመጥ እና በዲፕሎማሲያዊ አካሄድ የምስራቅ አፍሪካን ቀጣናዊ ውህደት ማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ መምህሩ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከፖለቲካዊ ጠቀሜታው ባሻገር ለኢትዮጵያም ሆነ ለኤርትራ ሕዝቦች የጋራ ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የባሕር በርን በጋራ ማልማት እና መጠቀም ለሁለቱም ሀገራት የወደፊት ዕድገት ቁልፍ መፍትሔ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣውን የባሕር በር ጥያቄ አሁን ላይ በዲፕሎማሲያዊ ጥበብ እንደ አዲስ እያነሳችው ትገኛለች።
ይህ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት የማይጋፋ፣ ይልቁንም ቀጣናዊ የጋራ ሰላምና ልማት ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #seaaccess #seaport #nationalinterest #redsea #hornofafrica #diplomacy #regionalintegration #ebc

3 months ago
u12d8u1218u1293u12ca u12e8u1263u1215u122d u1215u130d u12e8u1290u1260u122bu1275 u12a2u1275u12eeu1335u12eb
#ebcdotstream #ethiopianbroadcastingcorporation #seaport ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዘመናዊ የባሕር ሕግ የነበራት ኢትዮጵያ
#ebcdotstream #ethiopianbroadcastingcorporation #seaport
6 months ago
🌊 "የባህር በር ተደራሽነት ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው!"
— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 🇪🇹📢
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በድጋሚ በዓለም አቀፍ መድረክ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ቁልፍ መልዕክቶች፦
⚓️ የህልውና ጉዳይ፦
ኢትዮጵያ በሰላማዊ አማራጮች አስተማማኝ የባህር በር ተደራሽነትን ማረጋገጥ መሠረታዊ እና የማይታለፍ ጉዳይ መሆኑን በጽኑ ገልጸዋል።
📈 መሰረተ ልማት እና ብልጽግና፦
ሀገሪቱ በአየር መንገድ፣ በቴሌኮምና በመንገድ ዘርፎች የገነባቻቸው ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ሙሉ ትርጉም እንዲኖራቸው የባህር በር ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
🤝 ሰላማዊ አማራጭ፦
የባህር በር ጥያቄው ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላማዊ መንገድ እና በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ ተመስርቶ ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
🌍 ቀጣናዊ ትስስር፦
ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዊ ትስስርና ለጋራ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ይህ ጥረት አህጉራዊውን ‘አጀንዳ 2063’ ግቦችን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
#pmabiyahmed #ethiopia #africanunion #ausummit #seaport #redsea #regionalintegration #agenda2063 #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
How did Ethiopia lose its seaport?
https://fidelpost.com/how-... did Ethiopia lose its seaport?✍️ By Mohammed Siraje {Journalist and social science researcher for over twenty years The question of Ethiopia’s coastline has become central to the country’s sustainable development and survival strategy. To…

Comments