(ዘ-ሐበሻ ዜና | አዲስ አበባ) የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት፣ ታጣቂዎችን ማገዙ እና ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት አለማስወጣቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና የጋራ ብልጽግና ዋነኛ እንቅፋት መሆኑን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድራፊ አባራያ "የኤርትራ አጣብቂኝ እና የኢትዮጵያ ምርጫ" በሚል ርዕስ ባወጡት አዲስ እና ሰፋ ያለ ትንታኔ፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር በቀጠናው እየተጫወተ ያለውን አፍራሽ ሚና በዝርዝር አጋልጠዋል።
ባለስልጣኑ በትንታኔያቸው እንዳስገነዘቡት፣ ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ህዝቧ የልማት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት እያስመዘገበች ያለውን ከ9 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ይሁን እንጂ የኤርትራ መንግስት ታጣቂዎችን (በተለይም የህወሓትን ጽንፈኛ አንጃዎች) በገንዘብ፣ በሎጂስቲክስ እና በወታደራዊ አቅም በመደገፍ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት እንዲያፈርሱ ከፍተኛ ግፊት እያደረገ ይገኛል።
ዘገባው አክሎም፣ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ልክ እንደ ሀገር መሪ ሳይሆን እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ በኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ላይ መግለጫዎችን መስጠታቸው አባዜ እንደሆነባቸው ጠቅሷል። ከዚህም ባሻገር "የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መንቀሳቀሳቸው እና መሬት ይዘው መቆየታቸው" የሀገሪቱን ድርጊት አደገኛ ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ተመላክቷል።
በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን እንድትጠቀም ኤርትራ ቃሏን ማጠፏ የሎጂስቲክስ አማራጮችን አጥቧል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩቱ ትንታኔ እንደሚያስረዳው፣ ኤርትራ ይህንን ወደብ የዘጋችው ከምክንያታዊ የኢኮኖሚ ስሌት ይልቅ በቂም በቀል ስሜት ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወጣቶቻቸው የባህር በሩን ተጠቅመው በብዛት እንዳይሰደዱ በመስጋት ሆን ብለው የወደቡን አዋጭነት እንዳዳከሙት አብራርቷል።
ከሁሉም በላይ ለቀጠናውም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ ስጋት ተደርጎ የተቀመጠው ግን፣ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህልፈት ወይም ከስልጣን መውረድ በኋላ ያለው የኤርትራ ዕጣ-ፈንታ ነው። ሀገሪቱ የሚሰራ ህገ-መንግስት፣ ፓርላማም ሆነ የተሰየመ ምትክ መሪ የሌላት "ባዶ ሀገር" (Shell state) መሆኗ ተጠቁሟል። ይህ የተቋማት ክፍተት ደግሞ ኤርትራን ለአል-ሸባብ እና አይኤስአይኤስ (ISIS) ጽንፈኛ ቡድኖች መፈልፈያ ሊያደርጋት እንደሚችል እና የቀይ ባህርን ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ምንም እንኳን የኤርትራ አመራር በ20ኛው ክፍለ ዘመን ኋላቀር ትርክት ውስጥ የተቆለፈ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ውጥረቶችን በዲፕሎማሲ እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል። ሆኖም ይህንን እምነት እና መተማመን እንደገና ለመገንባት የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት ሙሉ በሙሉ እንዲያስወጣ በሚል የኢትዮጵያን መንግስት አቋም እና ቅድመ ሁኔታ ትንታኔው አስቀምጧል።

13 days ago