Logo
FIDEL POST NEWS
ግብጽ ለኢትዮጵያ የባሕር በር አማራጭ አቀረበች

​ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ካለሳለሰች፣ በጎረቤት አገራት በኩል የባሕር በር እንድታገኝ ለማገዝ ግብጽ ፍላጎት እንዳላት "ዘ ናሽናል" ዘገበ።

ጋዜጣው የግብጽ መንግሥት ይህን ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ማቅረቡን ጠቅሷል።

​ግብጽ ይህን ሃሳብ ያቀረበችው በጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የሚገኙ ወደቦችን ለማልማት ስምምነት ላይ መድረሷን በሚገልጹ ዘገባዎች መካከል ነው።

በተለይም የዶራሌ፣ የአሰብ እና የፖርት ሱዳን ወደቦችን ለማልማት ያላትን ዕቅድ ለኢትዮጵያ እንደ አማራጭ አቅርባለች ተብሏል።

እስከ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ ጉዳዩ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.