የባሕር በር…የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በታሪክ የግዛቷ አካል የነበረውን እና በሴራ ያጣቸውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ ነው፡፡
ታሪክ እንደሚያስረዳው በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የአዱሊስ ወደብ የዓለም አቀፍ ንግድ ማዕከል የነበረ ሲሆን ፥ በቀጣዮቹ ዘመናትም ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷ በምጽዋና አሰብ ወደቦች መዝለቅ ችሎ ነበር።
በቀጣናው የባሕር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ እጅግ ጥንታዊ የታሪክና የስልጣኔ አሻራ አኑራለች፡፡ ሆኖም በታሪክ አጋጣሚ በተወሰነ የፖለቲካ ውሳኔና የጠላቶች ሴራ ምክንያት ከታሪካዊና ሕጋዊ በሯ ከተነጠለች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ በጣም የሚያስቆጭ ፤ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ለፍትሕ የቆመ ማንኛውም ሰው ይህንን ሀሳብ የሚጋራው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ወደብ አልባ ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ እውነታ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና በትውልዱ ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ከዚህ በፊት የነበረው መንግሥት ይህን ጫና ለመከላከል እና የባሕር በር ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ካለመኖሩ በተጨማሪ ትውልዱ ኢትዮጵያ ያጣቸችውን የባሕር በር በተመለከተ ግንዛቤ እንዳይኖረው አድርጎ አልፏል፡፡
በተለይ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የመጣው ትውልድ በልዩ ሁኔታ በራስ ጥረትና ንባብ ከተረዳው ውጪ አብዛኛው ወደብ የባሕር በር፣የባሕር ሃይል እንዲሁም ባሕር ላይ ስላለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግንዛቤ የለውም፤ እንዲያውቅም አልተደረገም፡፡
በዚህም ትውልዱ የወደብ አልባነት ትርክት ሰለባ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይሁን አንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባህር ጉዳይን ፊት ለፊት እንነጋገርበት ብለው በአደባባይ ይፋ ካደረጉ በኋላ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ በመሆኗ የሚቆረቆር ትውልድ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ጥያቄ የራሴ ሉዓላዊ የባሕር በር ይኑረኝ ፤ ወደብና የመተላለፊያ ኮሪደር በሰላማዊ መንገድና በስምምነት ለማግኘት በሚደረግ ጥረት እንጂ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ግዛት ባለቤትነት የመጠየቅ ጉዳይ አይደለም።
በሰጥቶ መቀበል፣ መሬት ወይም ሌላ ሀብት በመለዋወጥ የባሕር በር ያገኙ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ በቅን ልቦና እና በትብብር መንፈስ ለሚረዳ ማንኛውም ወገን የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሸፍጥ እንደሌለበት መገንዘብ ቀላል ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የታሪክ ብቻ ሳይሆን የነባራዊ እውነታ፣የህጋዊ ባለቤትነት እና የሕልውና ጉዳይ ሲሆን÷ ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ፣ የባሕር በር ተደራሽነት የቀን ፖለቲካ ክርክር ሳይሆን የረጅም ጊዜ የልማት ስትራቴጂ እቅድ አካል ሊሆን ይገባዋል።
በመሆኑም ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን በመከተልና ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ፤ ኢትዮጵያውያንን እንደ ሕዝብ አንድ የሚያደርግ አጀንዳ አድርጎ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው

12 days ago