አዲስ አበባን የረገትጥኩ ሰሞን
(ዘላለም ጸጋዬ)
#ethiopia | ምንም እንኩዋን የተወለድኩት ከአንዲት ትንሽዬ የገጠር ከተማ ቢሆንም የልጅነት አይኔን ስገልጥ ግን የማስታውሰው የማርያምን ቤተክርስትያን፣ የመቅድስዋን የእጣን ሽታ፣የንፋስ ሽውታ የሚያስፉዋጨውን የጉዋሮዋን አርዘሊባኖስ፣የደጀ ሰላምዋን መአዛ ፣ካጠገቡም ያለውን ጭው ያለ ገደል እንዲሁም "መልእክተ ዮሀንስ ሀዋርያ ወልደ ዘብድዮስ" እያሉ መርጌታ አየለን የከበቡ የቆሎ ተማሪዎች ድምጽ እና የመሳሰለው ነው።በጥቅሉ የልጅነት አይኔን የገለጥኩት ስልጣኔ ካልጎበኘው እልም ካለ ገጠር ውስጥ ነው ...እናማ አኩፋዳዬን ጣጥዬ አዲስ አበባ የገባሁት የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር።ነፍሱን ይማረውና አባቴ ፈለገ ዮርዲያኖስ ትምህርት ቤት ወስዶ ከተተኝ።አባቴ ቀድሞ ከተማ ገብቶ አስኩዋላት ተምሮ እቀድሞዋ ቺኮዝሎቫኪያ ድረስም ሂዶ ተምሮ ነበር የመጣው።ተያም በሁዋላ እስከ ደርግ ምክርቤት አባልነት ደርሶ ነበር።
ትምህርት የተጀመረ ሰሞን የእርሻ መመህራችን ስለ ስንዴ አበቃቀል ሲያስተምሩ ቆይተው።"ጥያቄያለው አለ?" ሲሉ ከመቅጽበት እጄን እንደ ኢራን ሚሳኤል ዘረጋሁት።እኔ በገጠር አያለሁ የማውቀው ትልቅ ስራ መምህረነት ነው።ከዛ ባለፈ ሁሉም አርሶ ነው የሚበላ።እናም ከተማ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ስትከነክነኝ የከረመችውን ጥያቄ እንዲህ በማለት አቀረብኩ "መምህር የስንዴ አበቃቀልን አላጣሁትም የኔ ጥያቄ ግን... እንዲያው ለመሆኑ ይሄ ሁሉ ከተሜ የት አርሶ ነው የሚበላ" ብዬ ስጠይቅ...የክፍሉ ተማሪ ሁሉ በሳቅ ፈረሰ።ያልሳቀ አንድ ሰው ቢኖር መምህሩ ብቻ ነበሩ።እንዴ ምንድነው አዳሜን ሚያስቀው ብዬ ተገረምኩ።አባቴ በሰው ላይ መሳቅ እና ማላገጥ አይገባም እንዲይ ካደረግክ ነገ ሌሎች በአንተ ላይ ያላግጡብሀል ይለኝ ነበር።በገጠርም ቢሆን ምን አልባት ነጠላችንን አፋችን ላይ ጣል አርገን በትንሹ ብናንጉዋጥጥ ነውይ በሰው ላይ ካካካክ ብለን አንስቅም።
የእርሻ ክፍለ ግዜው እንዳለቀ።መምህሩ ሲወጡ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ እየተከተለ "ዘላለም ገበሬው" ማለት ጀመረ።ምንም አልተደናገጥኩም።ድሮም ደንቆሮ ወሬ አያጣም ብዬ ኮስተር አልኩ።የገጠር ልጅ ልበሙሉ አይደል።እህኔ እኮ የአንዱን ተማሪ የአይን መጋረጃ በዚህ አፈር ሲግፍ በከረመ እጄ ብከድንለት እኮ ሌላው አርፎ ይቀመጥ ነበር ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ከክላስ ስወጣ ወይም ስኔ 30 ጠብቀው ጨርቆስ ጉሊት መሃል ተሰብስበው ዱቄት እንዳያደርጉኝ ደግሞ ፈራሁ።በዛ ላይ ሰፈሩ ብዙ ግዜ በችግር ብዛት በህይወት አረቄ ሰክረው የሚደባደቡ አያጣውም ነበር።
የሆነው ሆኖ እንዲህ አልኩዋቸው...አዎ ገበሬ ነኝ።የገበሬ ምርቱ በትሳስ ነው።ታህሳስ ላይ እንገናኝ አልኩዋቸው።ቅኔ መሆኑዋ ነበር።የተሳዳቢው ተማሪ ቡድን መሪ ደግሞ አንዲት ድፍኑዋን ጨረቃ የመሰለች ዘቢብ የምትባል ቆንጅዬ ልጅ ነበረች።ቆንጆ ሰው አመሉም እንደመልኩ ሸጋ፣ልቡም እንደ እጣን ንጹህ ይመስለኝ ነበር።ገና ያኔ ነው አዬ ውበት ከንቱ ደምግባትም ብላሽ ያልኩት::ዘቢብ ግን ዛሬ የት ነሽ...እነዛ እንደ ቤተመቅደስ ጧፍ የሚያበሩ አይኖችሽ ሰላም ናቸው ወይ??? አቤት ውበታቸው አይን ያስፈነጥዝ ነበር•••
የሆነው ሆኖ በመጨረሻም ታህሳስ የመጀመርያ ሴሚስተር ውጤት ሲመጣ ከክፍሉ አንደኛ ወጣሁ።ያሁሉ ተማሪ እንደ ንጉስ ያየኝ ጀመር።እኔም ቆፍጠን ቄምጨጭ አልኩ "አለም ምንግዜም የቆራጦች ናት" ይል ነበር በዓሉ ግርማ።እናማ በክፍላችን ውስጥ እንግሊዘኛን እንደኔ የሚያነባት አልነበረም።አፌን ያዝ ከሚያደርገኝ የገጠር አማርኛ በስተቀር ምንም የሚወጣልኝ አልነበረም።ከባድ ጥያቄ በተጠየቀ ቁጠር መምህራን አይናቸውን ወደኔ ነበር የሚያቆለቁሉት።
ውሸት የሚባል አላውቅም ነበር።አሁንም ይተናነቀኛል።"እናትክን" የሚል ስድብ የሰማሁት እዛው ከትምህርት ቤታችን ፊትለፊት ከጉሊቱ መካከል ነበር።የዛን ቀን ከሰማይ እሳት እና ምስማር ቀላቅሎ የሚጥል ነበር የመሰለኝ።ያለወላጅ እናት ስላደግኩ በሱዋ ምትክ በልቤ እመቤታችን ንጽህት ድንግል ማርያም እናቴ እያልኩ ስላደግኩ እሱዋ የተሰደበች ያክል ነበር የሰቀጠጠኝ።በዛ ላይ ደግሞ "በእንተ ስሙዋ ለማርያም" ያልኩበት በስሙዋ ተማጽኜ ጎርሼ ያደርኩበት ዘመን ውልብ አለብኝ።
ምንም እንኩዋን አዲስ አበባ አቀባበሉዋ እንደ ደንባራ በቅሎ መንቃራ ቢሆንም።ኢለመንታሪ ፈለገ ዮርዳኖስ፣ ሀይስኩል 9 እና 10 አብዮት ቅርስ፣ 11 እና 12 ቦሌ ሀይስኩል፣ እንዲሁም እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድረስ አንቀባርራ አሳድጋኛለች።ከገጠር ይዤ የወጣሁት ስብእና ለዛሬው ማንነቴ እጅጉን አስተዋጽኦ አድርጉዋል።አንዳንዱም ጎጂ ባህል ነበር ለምሳሌ ሳልደርስበት የደረሰብኝን ሰው ሳልበቀል መተው ሽንፈት ይመስለኛል።እርቅም ከታሰበ ከተመጣጣኝ አጻፋ በቀል በሁዋላ እንጂ እንዲሁ አንተም ተው አንተም ተው አይሰራም።
ለማንኛውም አዲስ አበባ ቤቴ፣አሳዳጊዬ ክፉውንም፣ ደጉንም ያሳለፍኩብሽ፣ የኔ ሁሉን ቻይ ኑሪልኝ።ምንም እንኳን ባህር ብሻገርም ልቤ ግን ያለው ካንቺው ዘንድ ነው።•••የሰው ልጅ ከመኖር የሚያተርፈው ትዝታ ነው።
እኔም እነሆ ትዝታዬን አጋራኋችሁ!
መልካም ሰንበት!

2 months ago