Logo
Getu Temesgen
🎬 በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ታግዶ የነበረው የጥላሁን ጉግሳ "የባሕር በር" ፊልም ለዕይታ ሊቀርብ ነው!
#ethiopia | ​"ቤቶች ድራማ ከ13 ዓመታት በኋላ በክብር ሊሰናበት ነው"

​አርቲስት፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር ጥላሁን ጉግሳ (ዘለቀ) ሁለት ዓበይት ዜናዎችን አሰምቷል።

​1️⃣ "ቤቶች" ሊያበቃ ነው!

ለ13 ተከታታይ ዓመታት ያለማቋረጥ በመተላለፍ ከዓለም 3ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን የያዘውና የሁላችንም የሳሎን ትዝታ የሆነው "ቤቶች" የሲትኮም ድራማ፤ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለተመልካች በክብር እንደሚሰናበት ተገልጿል።

​2️⃣ ታግዶ የነበረው ፊልም ሊለቀቅ ነው!

ከዓመታት በፊት ተሠርቶ ለጥቂት ጊዜ እንደታየ በኢህአዴግ ባለስልጣናት "ስለ አሰብ የባሕር በር ያወራል" በሚል የታገደውና አርቲስቱንም ለዛቻ እና ማስፈራሪያ ዳርጎት የነበረው "የባሕር በር" ፊልም በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል።

​ለምን አሁን?

ጥላሁን እንደገለጸው፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ላለማበላሸት ታግሶ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ የባሕር በር ጉዳይ እንደ አዲስ እየተጠየቀ በመሆኑ ፊልሙን ለመልቀቅ መወሰኑን ተናግሯል።

​በተጨማሪም ከሁለተኛ ሴት ልጁ ጋር በመሆን አዲስ ረጅም ተከታታይ ፊልም ይዞ ለመምጣት ዝግጅቱን ጨርሷል።

​የቤቶች ድራማን ምን ያህል ይወዱት ነበር? እስኪ ትዝታችሁን አካፍሉን።

​#betochdrama #tilahungugsa #yebahirber #ethiopianfilm #artnews #redsea #ethiopia

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.