3 days ago
የአስዋን ግድብ ያለ ተፋሰስ ሀገራት ስምምነት የተገነባና በርካቶችን ለጉዳት የዳረገ ፕሮጀክት መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ እንደተናገሩት፣ ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው የአስዋን ግድብ ከማንኛውም ቅድመ ውይይትና የጋራ ስምምነት ውጭ በራሷ ውሳኔ ብቻ የተከናወነና የጥፋት አሻራ ያረፈበት ስራ ነው።
ካይሮ የዓባይ ውሃ ዋነኛ ምንጭ የሆነችውን ኢትዮጵያን ሳታማክርና ፈቃድ ሳታገኝ ግድቡን በመገንባቷ፣ ሌሎች ሀገራት ከወንዙ ፍትሃዊ ጥቅም እንዳያገኙ እንቅፋት ሆና ቆይታለች ብለዋል።
ግንባታው በተካሄደበት ወቅት ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኑቢያ ማህበረሰብ አባላት ከቀያቸውና ከተወለዱበት መኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉን ታሪካዊ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
ይህም በዜጎች ላይ ከፍተኛ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሏል።
በተቃራኒው ኢትዮጵያ የገነባችው የታላቁ ህዳሴ ግድብ እ.ኤ.አ በ2015 በተፈረመው የመርሆች መግለጫ መሠረት በግልጽ ውይይት የተከናወነ ነው።
በመሆኑም ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታቀርበው ትችት ምንም ዓይነት የሞራልም ሆነ የምክንያታዊነት መሠረት የለውም።
በመጨረሻም ሚኒስትሩ አክለው እንደተናገሩት፣ ግብፅ የሌሎችን ፍትሃዊ የልማት ጥያቄ ከመኮነኗ በፊት፣ የአስዋን ግድብን ያለ ተፋሰሱ ሀገራት ፈቃድ ለምን እንደገነባችና ንጹሃን ኑቢያውያንን ለምን ለስደትና ለእንግልት እንዳዳረገች ግልጽ ምላሽ መስጠት አለባት።
#ህዳሴግድብ #አባይ #የአስዋን_ግድብ #ኢትዮጵያ #ግብፅ #gerd #nile #aswandam #ethiopia #egypt #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 days ago
በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤት ላይ በፈጸሙት የድሮን ጥቃት 5 ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ቆሰሉ
የሱዳን የሃኪሞች መረብ እንደገለጸው፣ ጥቃቱ በማዕከላዊ ሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚገኘውን የኮርዶፋን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኖሪያ ቤት ዒላማ ያደረገ ሲሆን፣ ድርጊቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግን የጣሰ ነው ሲል ኮንኖታል።
እንደ ሱዳን የሃኪሞች መረብ ዘገባ ከሆነ ረቡዕ ዕለት ፓራሚሊታሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) በማዕከላዊ ሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ በሚገኘው የኮርዶፋን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ በፈጸሙት የድሮን ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በተጨማሪም በሰላማዊ ሰዎች እና በሕዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸውን አስጠንቅቋል። ቡድኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በሰላማዊ ሰዎች መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያወግዙ፣ ተጠያቂዎችን ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ለተጎዱት አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
የሱዳን ባለስልጣናት እና የሰብአዊ መብት ቡድኖች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሰላማዊ ሰዎች ተቋማት ላይ ጥቃት ያደርሳሉ ሲሉ የሚከሱ ሲሆን፤ ፓራሚሊታሪ ቡድኑ ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ እንሰራለን ከማለት ባለፈ ለክሶቹ ቀጥተኛ ምላሽ አይሰጥም።
ሱዳን ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሰራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በሚካሄድ ውጊያ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ ይህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት እና ሚሊዮኖችን ደግሞ ስደት ዳርጓል።
ሰላማዊ ነጋሲ

7 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የዳኛው ፊሽካ የ90 ደቂቃውን ፍልሚያ መጠናቀቅ ሲያበስር፣ በባህር ዳር ስታዲየም የውጤት ሰሌዳ ላይ «ኢትዮጵያ 0 - 1 ሴኔጋል» የሚል ጽሑፍ ደምቆ ይታይ ነበር። አዎ፣ ኳስ እና መረብ ተገናኝተው የቴራንጋ አንበሶቹ በ10ኛው ደቂቃ በኢብራሂም ምባዬ አማካኝነት ባስቆጠሯት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። ነገር ግን፣ በዚህ ታሪካዊ ምሽት እውነተኛዋ አሸናፊ ሴኔጋል ሳትሆን ኢትዮጵያ ነበረች!
ይህ ምሽት የግብ ሳይሆን የክብር ምሽት ነበር። ለበርካታ የጨለማ ዓመታት በስታዲየም እገዳ ምክንያት ከሜዳው፣ ከሀገሩ እና ከደጋፊው ርቆ በባዳ ሀገር «የሜዳዬ» እያለ ሲንከራተት የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ዛሬ አቧራውን አራግፎ ወደ ራሱ ምድር ተመልሷል። ከረጅም የናፍቆት ዓመታት በኋላ በገዛ ሀገሩ፣ በገዛ ሜዳው እና በገዛ ደጋፊው ፊት መጫወቱ ከምንም በላይ ትልቁ አሸናፊነት ነው።
የባህር ዳር ስታዲየም በደጋፊዎች ሆታ ሲናወጥ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በአየር ላይ ሲያውለበልብ ማየት፣ ከማንኛውም ግብ በላይ ልብን በሀሴት የሚሞላ እና የእግር ኳስን እውነተኛ ትርጉም የሚመልስ ድል ነበር።
በሜዳ ላይ የነበረው ፉክክርስ ቢሆን? በፓትሪክ ቪዬራ የሚሰለጥኑትና እንደ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኢድሪሳ ጋና ጌዬ ያሉ የአውሮፓ ታላላቅ ሊግ ኮከቦችን ያሰለፉት ሴኔጋላውያን፣ በባህር ዳር ሜዳ ላይ በቀላሉ አልተንሸራሸሩም። ምንም እንኳን የኒኮላስ ጃክሰንን ኳስ ተቀብሎ ምባዬ በ11ኛው ደቂቃ መረብ ላይ ቢያሳርፈውም፣ ዋልያዎቹ ግን በቀላሉ እጅ የሚሰጥ ትከሻ አልነበራቸውም።
ጋቶች ፓኖም ከመሃል ሜዳ ኳሶችን ሲያከፋፍል እና ጨዋታውን ሲያረጋጋ፣ ቢንያም ፍቅሩ እና ቸርነት ጉግሳ የሴኔጋልን ተከላካዮች ሲፈትኑ አምሽተዋል። በተለይም ከነዓን ማርክነህ በሁለተኛው አጋማሽ በግንባር ገጭቶ የሞከራትና ግብ ጠባቂው ዲዮፍ በግሩም ሁኔታ ያዳናት ኳስ፣ ዋልያዎቹ እጅ ላለመስጠት ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ማሳያ ነበረች። በግብ ጠባቂው ኑራ በኩልም የኒኮላስ ጃክሰንን አደገኛ ሙከራ በማዳን የቡድኑን የጀርባ አጥንት አጠናክሯል።
ሴኔጋል ጫና ሲበዛባት ተጫዋቾች በመቀየር (እነ ፓፕ ጌዬን እና አሳን ዲያኦን በማስወጣት) ማስተካከያ ለማድረግ ብትገደድም፣ የኢትዮጵያ ልጆች ግን እስከ ጨዋታው መጠናቀቅ ድረስ የአቻነቷን ግብ ፍለጋ መታገላቸውን አላቆሙም ነበር።
በእርግጥ በ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ... ከሱዳኑ 1ለ0 ሽንፈት በኋላ ይህ ውጤት ለነጥብ ሰንጠረዡ ጥሩ ላይሆን ይችላል። ሆኖም፣ ከዓመታት ስደት በኋላ ወደ ሜዳችን መመለሳችን፣ ደጋፊው ዳግም ስታዲየም ገብቶ ሀገሩን መደገፍ መቻሉ፣ እና ወጣቶቹ ተጫዋቾቻችን በአፍሪካ ግዙፍ ቡድን ፊት ጀግንነታቸውን አለማጠፋቸው፣ ዛሬ ተሸንፈን እንድናሸንፍ አድርጎናል።
ስለዚህ ውጤቱን እርሱት፤ ኢትዮጵያ ዛሬ ክብሯን መልሳለች። እግር ኳሳችን ወደ ቤቱ፣ ወደ ባህር ዳር ተመልሷል። የዛሬዋ ኢትዮጵያ በኩራት እና በክብር አሸንፋለች!

11 days ago
በእስራኤል የሚኖሩ የኤርትራ ተቃዋሚዎች በሀገራቸው ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ሰፊ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እየገነቡ መሆናቸውን ገለጹ
#fastmereja I በእስራኤል የሚኖሩ የኤርትራ ተቃዋሚ ተንቀሳቃሾች በፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚመራውን መንግስት ለመለወጥና በሀገራቸው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመትከል ያለመ ሰፊ ህዝባዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እየገነቡ እንደሚገኙ አስታወቁ። ተቃዋሚዎቹ በቴል አቪቭ በሚገኝ ዋና ማዕከላቸው እንቅስቃሴያቸውን እያፋጠኑ ሲሆን፣ ልጆቻቸውን በእስራኤል እያሳደጉ ቢሆንም ዋና አላማቸው ግን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ቀን ማዘጋጀት እንደሆነ ገልጸዋል።
እንደ ጄሩሳሌም ፖስት እና ሚድል ኢስት አየ ዘገባዎች፣ ከዚህ ቀደም "ብሪጌድ ንሐመዱ" በመባል ይታወቅ የነበረው እና አሁን ወደ "ኤርትሪያን ብሉ ሬቮሉሽን ፍሮንት" (EBRF) የተሸጋገረው ይህ ስብስብ፣ በስደት የሚኖሩ ኤርትራውያንን በማስተባበር ላይ ይገኛል። የተንቀሳቃሽ ቡድኑ አስተባባሪዎች በቅርቡ በእስራኤል ነስ ጽዮና ከተማ ባካሄዱት ጉባኤ ከ1,300 በላይ ኤርትራውያን መሳተፋቸውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመረጠ 51 አባላት ያሉት ምክር ቤት ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል።
በእስራኤል የቡድኑ አስተባባሪ የሆኑት አታክልቲ አብርሃም (ሚካኤል) እና ሙሉእ ሱልጣን እንደገለጹት፣ በእስራኤል የተወለዱና ያደጉ ልጆቻቸው ዕብራይስጥ ቋንቋ የሚናገሩና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የተቀላቀሉ ቢሆንም፣ የኤርትራን ማንነትና ታሪክ እንዲያውቁ እየተደረገ ነው። "ማንም ሰው ለዘላለም ስደተኛ ሆኖ መኖር አይፈልግም" ያሉት አስተባባሪዎቹ፣ ህጻናቱን በእስራኤል በጥሩ ሁኔታ እያሳደጉ ያሉት በሀገራቸው ለውጥ ሲመጣ ወደ ኤርትራ የመመለስ ተስፋቸውን ሰንቀው እንደሆነ ተናግረዋል።
እንቅስቃሴው ከመንገድ ላይ ተቃውሞዎችና ግጭቶች ወጥቶ ወደ ተደራጀ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ክንፍ እየተቀየረ መሆኑን የዘገቡት የውጭ መገናኛ ብዙሃን፣ ቡድኑ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ከሚገኙ አጋሮቹ ጋር በመሆን ተፅዕኖውን ለማስፋት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

Sponsored by
Surafel
11 days ago
ታዋቂው ድምፃዊ ዳዊት መኮንን ከ27 ዓመታት የስደት ህይወት በኋላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ
#fastmereja I ከ27 ዓመታት በላይ በአሜሪካ በስደት ሲኖር የቆየው ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አርቲስት ዳዊት መኮንን፣ ዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ወደ ሀገሩ ተመልሶ አዲስ አበባ ገብቷል።
አርቲስት ዳዊት መኮንን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሲደርስ በአባ ገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች፣ በባልደረባ የጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

14 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዕይታ) የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና የሰርከስ ጅምናስቲክ ባለሙያዎች አንድ የሚያመሳስላቸው ድንቅ ጠባይ አለ፤ ሁለቱም አየር ላይ ይገለበጣሉ፣ ግን መሬት ላይ ሲያርፉ እግራቸው አይሰበርም። ልዩነቱ የሰርከስ ባለሙያው ሲገለበጥ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ሲጥል፣ ፖለቲከኛው ግን ሲገለበጥ የህዝብን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉ ነው።
ዛሬ በኒውዮርክ ከተማ፣ በ81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) ደጃፍ ላይ የታየው ትዕይንት ይህንኑ የፖለቲካችንን የሰርከስ ትርዒት በሚገባ ያሳያል። አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከአስር ዓመታት በኋላ ተገናኝተው ተቃቅፈዋል። አቶ ጌታቸውም በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ጥርሳቸው እስከ መንጋጋቸው እስኪታይ በደስታ ተሞልተው፣ "ወንድሜን ዶ/ር ቴድሮስን ከአስር ዓመት ገደማ በኋላ በኒውዮርክ ማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው" ብለው ጻፉልን።
አስር ዓመት! ለፖለቲከኛ አስር ዓመት ማለት አንዲት የቡና እረፍት ያህል አጭር ናት። ለኢትዮጵያ ምስኪን እናቶች ግን አስር ዓመት ማለት... አያሌ የጦርነት፣ የምጥ፣ የረሃብ እና የስደት ዘመን ነው። ምስኪኑ የትግራይ ወጣት "አንተም ሙት፣ እኔም ልሙት" ተብሎ እንደ ደረቅ ቅጠል በጦርነት እሳት ሲማገድ፣ መንደሩ ሲፈርስ እና ሚሊዮኖች ሲራቡ፣ የጦርነቱ ጠባሳ ገና ሳይሽር፣ መሪዎቹ ግን በኒውዮርክ ንጹህ አየር እየተነፈሱ፣ ሙሉ ሱፍ ለብሰው ለካሜራ "ቺዝ" ይላሉ። አቤት የሰማይ እና የምድር ርቀት! አቤት የህዝብ እውነታ እና የልሂቃን ቅንጦት!
የፖለቲካችንን ነገር ይበልጥ አስቂኝ የሚያደርገው የአቶ ጌታቸው የትናንት እና የዛሬ ሚና ነው። ትናንት የፌደራል መንግስቱን በጠላትነት ፈርጀው፣ ህዝብን ወደ ጦርነት ሲያመሩ አልነበረም? ዛሬ ደግሞ የዚያኑ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ሹመት ተቀብለው ዲፕሎማሲ ሲሰሩ ማየት፣ ፖለቲካችን ምን ያህል የልብስ ቅያሪ እንጂ የልብ ቅያሪ እንደሌለው ያሳያል። ዶ/ር ቴድሮስም ቢሆኑ፣ በጄኔቫ ሆነው የኢትዮጵያን መንግስት አጥብቀው ሲተቹ እና ሲያወግዙ አልነበሩም? ዛሬ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀኝ እጅ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ጋር ሞቅ ያለ የናፍቆት ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ "እስስትም የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች ቢያይ ቀለሙን መቀየር ያቆማል" ያሰኛል።
ከዚህ ፎቶግራፍ ተራው ዜጋ የሚማረው አንድ መራራ ሀቅ አለ... የፖለቲካ ልሂቃን ደማቸው አይቃባም፤ ጥቅማቸው ሲነካ ይጣላሉ፣ አቋራጭ ሲያገኙ ደግሞ ይተቃቀፋሉ። እሳቱን የሚያቀጣጥሉት እነሱ፣ ማገዶው ደግሞ በስሜት የሚነዳው ምስኪኑ ህዝብ ነው። ጦርነቱ ሲያልቅ ማገዶው አመድ ይሆናል፤ አቀጣጣዮቹ ግን ኒውዮርክ ሄደው ይተቃቀፋሉ። ስለዚህ የኒውዮርኩ ፈገግታ የትግራይን ብሎም የኢትዮጵያን እናቶች እንባ የሚያብስ አይደለም፤ የልሂቃኑን ምቾት እና ግድየለሽነት በታሪክ መዝገብ ላይ የሚያሰፍር አሳዛኝ የካሜራ ብልጭታ እንጂ።
ከአበጀ በለው

15 days ago
“ኢትዮጵያ ጎዳና” — በኢየሩሳሌም የሚኖር የኢትዮጵያ ታሪክ አሻራ
ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል
#ethiopia | በእስራኤል ቅዱስት ከተማ ኢየሩሳሌም መሃል ላይ አንድ አጭር ጎዳና አለ። በዓይን ሲታይ ከከተማዋ ብዙ ጎዳናዎች የተለየ ላይመስል ይችላል፤ ስሙን ግን ሲያነቡት የሩቅ አገር ስም ያስተጋባል።
“Ethiopia Street — የኢትዮጵያ ጎዳና”።
ይህ ጎዳና በኢየሩሳሌም መሃል፣ ከStreet of the Prophets (HaNevi'im Street) የሚወጣ ሲሆን ከብሉይ ከተማዋ ውጭ በተገነቡት ታሪካዊ አካባቢዎች መካከል ይገኛል። የጎዳናው ስም ግን በቀጥታ ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተቋማት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው።
ከ“ሐበሻ” ወደ “ኢትዮጵያ”
ዛሬ “Ethiopia Street” የሚባለው ይህ ጎዳና በቀድሞ ዘመን Abyssinian Street ወይም Habashim Street ተብሎ ይጠራ ነበር። በአካባቢውም “Habashim” የሚለው ስም ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጋር ተያይዞ ይጠቀም ነበር።
በብሪታንያ ማንዴት ዘመን ጎዳናው Abyssinian Street በመባል ይታወቅ ነበር። በኋላ ግን የስያሜው አጠቃቀም ተቀይሮ፣ በታኅሣሥ 1968 “Ethiopia Street” ተብሎ ተሰየመ። የዚህ ለውጥ ዋና ትርጉም የ“Habashim/Abyssinian” የቆየ ስያሜን በአገሪቱ የዘመኑ ስም “Ethiopia” መተካት ነበር።
በእርግጥም የጎዳናው ስም ለውጥ የተመዘገበበት የ1968 የጋዜጣ ማስረጃም በእስራኤል ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የጋዜጣ ስብስብ ውስጥ እንዳለ ምንጮች ያመለክታሉ።
የጎዳናው ስም ከመጣበት በላይ የሚነግረው ታሪክ
“Ethiopia Street” የሚለው ስም በዘፈቀደ የተሰጠ አይደለም።
ከ19ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ተወካዮች በኢየሩሳሌም ከብሉይ ከተማዋ ውጭ መሬት መግዛትና ሕንፃዎችን መገንባት ጀመሩ። የንጉሥ ምኒልክ ዳግማዊ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ ብጡልና ራስ መኮንን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ ባለሥልጣናት በአካባቢው በርካታ ሕንፃዎች እንዲገነቡ አድርገዋል።
ስለዚህ ጎዳናው የኢትዮጵያ ስም ብቻ የተሰጠው ቦታ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን በኢየሩሳሌም ያላቸውን የረጅም ዘመን መገኘት በሕንፃና በተቋማት የሚያሳይ ታሪካዊ አካባቢ ነው።
ኪዳነ ምሕረት — በጎዳናው ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምልክት
ከጎዳናው በጣም የሚለየው ታሪካዊ ሕንፃ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ነው።
ቤተክርስቲያኑ በደብረ ገነት ገዳም ግቢ ውስጥ ይገኛል። የግንባታው ሥራ በአፄ ዮሐንስ አራተኛ ዘመነ መንግሥት በ1880ዎቹ መጀመሩን ምንጮች ያመለክታሉ፤ በ1893 በአፄ ምኒልክ ዳግማዊ ዘመን ተመርቋል።
የኪዳነ ምሕረት ሕንፃ በባህላዊ የኢትዮጵያ ክብ ቤተክርስቲያን አሠራር የተገነባ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። በደብረ ገነት ገዳምም የኢትዮጵያ መነኮሳት ሃይማኖታዊ ሕይወታቸውን ይቀጥላሉ።
በዚህም ምክንያት ጎዳናው ከቤተክርስቲያኑ ታሪክ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።
ኢትዮጵያውያን ከብሉይ ከተማ ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መገኘት በኢየሩሳሌም ከEthiopia Street በጣም የሚረዝም ታሪክ አለው።
የኢትዮጵያ መነኮሳት በኢየሩሳሌም ከቀደምት ዘመናት ጀምሮ እንደነበሩ ምንጮች ይጠቁማሉ። በብሉይ ከተማዋም Deir al-Sultan የተባለው የኢትዮጵያ ገዳም ከቅዱስ መቃብር ቤተክርስቲያን አጠገብ የኢትዮጵያውያን የረጅም ዘመን መገኘት ምልክት ነው።
በ19ኛው መቶ ዘመን ግን የኢትዮጵያ መገኘት ከብሉይ ከተማዋ ውጭ በአዲሲቱ ከተማ እየተስፋፋ መጣ። ይህም ኪዳነ ምሕረትን፣ ደብረ ገነትን፣ የመኖሪያ ሕንፃዎችን እና በኋላ የኢትዮጵያ ቆንስላን የመሳሰሉ ተቋማትን ያካተተ ሆነ።
የንጉሥ ምኒልክ ዳግማዊ ሕንፃ
በEthiopia Street ቁጥር 8 ላይ የሚገኘው ሕንፃም ከኢትዮጵያ ንጉሣዊ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው።
ሕንፃው በአፄ ምኒልክ ዳግማዊ ተነሳሽነት እንደተገነባ የታሪክ ምንጮች ያስረዳሉ። የኪራይ ገቢውም ለቤተክርስቲያኑና በኢየሩሳሌም ለሚከናወኑ የኢትዮጵያ ሥራዎች ለመዋል የታሰበ ነበር።
ይህ የሚያሳየው ደግሞ የኢትዮጵያ መገኘት በኢየሩሳሌም በሃይማኖት ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን ነው፤ መኖሪያ፣ ንብረት፣ ዲፕሎማሲ እና ማኅበራዊ ተቋማትንም ያካተተ ነበር።
የኢትዮጵያ ቆንስላና የዲፕሎማሲ አሻራ
በአቅራቢያው በProphets Street የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ሕንፃ ሌላው የኢትዮጵያ ታሪካዊ አሻራ ነው። ሕንፃው በ1928 እንደተቋቋመ ምንጮች ይጠቁማሉ። የኢየሩሳሌም ታሪክ ምንጮችም በዚያ ወቅት ኢትዮጵያ በከተማዋ የዲፕሎማሲ መገኘት ያላት ልዩ የአፍሪካ አገር እንደነበረች ያስታውሳሉ።
ይህም Ethiopia Street እና አካባቢው በኢትዮጵያ–ኢየሩሳሌም ግንኙነት ውስጥ ሃይማኖታዊ ቦታ ብቻ ሳይሆን የዲፕሎማሲና የማኅበራዊ ታሪክ ማስረጃም መሆኑን ያሳያል።
አፄ ኃይለ ሥላሴና ኢየሩሳሌም
የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ቤተሰብ ከኢየሩሳሌም ጋር የነበረው ትስስር በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመንም ቀጥሏል።
እ.ኤ.አ. በ1936 ጣሊያን ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ አፄ ኃይለ ሥላሴ በስደት ወቅት ኢየሩሳሌምን ጎብኝተው ከተማዋ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ እንደቆዩ የታሪክ ምንጮች ይመዘግባሉ።
ይህ የሚያሳየው ኢየሩሳሌም ለኢትዮጵያ የእምነት መዳረሻ ብቻ ሳትሆን፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የንጉሣዊ ታሪክ ውስጥም ልዩ ቦታ እንደነበራት ነው።
አንድ ጎዳና፣ ብዙ ታሪኮች
ዛሬ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን Ethiopia Street ስንመለከት፣ አንድ የጎዳና ስም ብቻ አናይም።
በዚያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅርስ አለ፤
የንጉሣዊ ቤተሰብ አሻራ አለ፤
የዲፕሎማሲ ታሪክ አለ፤
የኢትዮጵያውያን መነኮሳትና ምዕመናን የረጅም ዘመን መገኘት አለ፤
እንዲሁም በኢየሩሳሌም የተገነባ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ሕንፃ ቅርስ አለ።
የከተማዋ ታሪክ ምንጮችም Ethiopia Street ከProphets Street ጋር በመያያዝ ከብሉይ ከተማ ወደ አዲሲቱ ከተማ የሚዘረጋ ታሪካዊ፣ ሥነ-ሕንፃዊና ሃይማኖታዊ የከተማ አካባቢ እንደሆነ ይገልጻሉ።
የዛሬው ትርጉም
በ1968 ከ“Abyssinian Street” ወደ “Ethiopia Street” የተቀየረው ስም ዛሬም በኢየሩሳሌም ይገኛል።
ይህ የጎዳና ስያሜ ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም ያላትን ታሪካዊ መገኘት በከተማዋ የሚያስታውስ የቦታ ስም ሆኖ ቀጥሏል። ዛሬም በEthiopia Street ላይ የሚገኘው ኪዳነ ምሕረት እና ደብረ ገነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታሪክ በኢየሩሳሌም በሕያው ተቋም መቀጠሉን ያሳያሉ።
ኢየሩሳሌምን ለሚጎበኝ ኢትዮጵያዊ፣ “Ethiopia Street” የሚለው ስም በካርታ ላይ ያለ ስም ብቻ አይደለም። የቀደሙት ትውልዶች በኢየሩሳሌም ያሳረፉትን አሻራ የሚያስታውስ ታሪካዊ ምልክት ነው።
አንድ ጎዳና — ከሐበሻ ስም ወደ ኢትዮጵያ ስም፤ ከቤተክርስቲያን ወደ ዲፕሎማሲ፤ ከታሪክ ወደ ዛሬ።
Ethiopia Street — Jerusalem
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#jerusalem #ethiopiastreet #ethiopianhistory #kidanemihret #debregenet #israel #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

17 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤርትራን የነጻነት ትግል በግንባር ቀደምትነት ከመሩት ታዋቂ የጦር አዛዦች እና ባለስልጣናት መካከል አንዱ የነበረው ጴጥሮስ ሰሎሞን እና ባለቤቱ አስቴር ዮሐንስ፣ ያለ አንዳች የፍርድ ሂደት ከታሰሩ 25 ዓመታት አልፈዋል። የ10 ዓመት ልጅ እያለች ወላጆቿን ያጣችው እና ዛሬ በ35 ዓመቷ አሜሪካ የምትኖረው ልጃቸው ሀና ጴጥሮስ፣ "ወላጆቼ በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ እንኳን እስካሁን አላውቅም" ስትል የብዙዎችን ልብ የነካ ሰቆቃዋን ታጋራለች።
እ.ኤ.አ በ1993 ኤርትራ ነጻነቷን እንድትቀዳጅ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት የጦር አዛዦች መካከል ጴጥሮስ ሰሎሞን እና ባለቤቱ አስቴር ዮሐንስ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ከነጻነት በኋላም ጴጥሮስ ሰሎሞን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እንዲሁም የዓሳ ሀብት ሚኒስትር በመሆን አገልግሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበረበት ወቅትም ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን እና ከባለቤታቸው ሂላሪ ክሊንተን ጋር ተገናኝቶ እስከመነጋገር የደረሰ ከፍተኛ ባለስልጣን ነበር።
ይሁን እንጂ የጴጥሮስ እና የቤተሰቡ መከራ የጀመረው፣ በግንቦት 2001 ከሌሎች 14 ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ጋር በመሆን (ጂ-15 በመባል የሚታወቁት)፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሕገ-መንግሥቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ በመፈረማቸው ነው። ይህን ተቃውሞ በጸጋ ያልተቀበሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ እ.ኤ.አ መስከረም 18, 2001 ዓለም በአሜሪካው የ9/11 የአሸባሪዎች ጥቃት ተደናግጦ በነበረበት ወቅት፣ በ11 ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ አስደንጋጭ የእስር ዘመቻ ከፈቱ።
የጴጥሮስ ልጅ ሀና ጴጥሮስ ለቢቢሲ እንደተናገረችው፣ አባቷን ለመጨረሻ ጊዜ ያየችው እንደተለመደው ጠዋት ስፖርት ለመሥራት በፎጣ አንገቱን ጠምጥሞ ሲወጣ ነበር። በዚያው ከቤት እንደወጣ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ተወሰደ። በወቅቱ የሀና እናት፣ አስቴር ዮሐንስ ለትምህርት አሜሪካ ትገኝ የነበረ ሲሆን፣ ሀና እና ሦስት ወንድሞቿ ከአያታቸው ጋር መኖር ጀመሩ።
አስቴር ልጆቿን ለማሳደግ ስትል፣ ከመንግሥት ባለስልጣናት የደህንነት ዋስትና በማግኘቷ ታህሳስ 11, 2003 ወደ አስመራ ብትመለስም፣ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ቤተሰቦቿ እየጠበቋት በጸጥታ ኃይሎች ተይዛ ወደ 'ካርሼሊ' ወደሚባለው እስር ቤት ተወሰደች። ጴጥሮስን ጨምሮ ሌሎች የታሰሩት ባለስልጣናት ደግሞ፣ ከአስመራ ሰሜን ምሥራቅ በሚገኘው እና እጅግ ሚስጥራዊና አስከፊ በሆነው 'ኤላ-ኤሮ' (Ela-Ero) በተባለው እስር ቤት እንደሚገኙ ይታመናል። ሁሉም የሀገር ክህደት ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን፣ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረቡም፤ ቤተሰብም እንዲጠይቃቸው አልተፈቀደም።
ሀና ብቻ ሳትሆን፣ በተመሳሳይ ዕለት እናቱን እና አባቱን ያጣው ኢብራሂም ሸሪፎም የዚህ ሰቆቃ ሰለባ ነው። የኢብራሂም አባት፣ ማህሙድ አህመድ ሸሪፎ፣ የሀገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትር እና በተጨባጭ የፕሬዚዳንቱ ምክትል የነበሩ ሲሆን፣ እናቱ አስቴር ፍስሐጽዮን ደግሞ ገዥው ፓርቲ (PFDJ) ከፍተኛ አመራር ነበሩ። "መስከረም 18 ለኔ ብቻ ሳይሆን ሕግ እና ዲሞክራሲ የታሰረበት የኤርትራ የጨለማ ቀን ነው" የሚለው ኢብራሂም፣ አሁን በኔዘርላንድስ በስደት እየኖረ በአባቱ ፈለግ የፖለቲካ ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን እየተከታተለ ይገኛል።
"ወላጆቻችን በሕይወት መኖር አለመኖራቸውን ማወቅ የቤተሰብ መብታችን ነው" ሲል የኤርትራን መንግሥት የሚወቅሰው ኢብራሂም፣ ወላጆቹ ለዲሞክራሲ ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት በኩራት ያነሳል።
በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ውስጥ በስነ-ልቦና ቀውስ (Trauma) ስፔሻሊስትነት የምትሠራው ሀና፣ ራሷ በወላጆቿ መጥፋት ከፍተኛ የስነ-ልቦና ስብራት ውስጥ ትገኛለች። "ሀዘኑ አንዳንድ ጊዜ እንደ ማዕበል መጥቶ ያሰጥመኛል" የምትለው ሀና፣ ለወላጆቿ መልእክት ማድረስ ብትችል ምን እንደምትላቸው ስትጠየቅ፣ "ስለ እኛ አትጨነቁ! የትጥቅ ትግሉን በጽናት እንዳለፋችሁት ሁሉ፣ ይህንንም ችግር አልፋችሁ ወደ እኛ እንደምትመለሱ ተስፋ አደርጋለሁ" ስትል በእንባ ገልጻለች።
የኤርትራ መንግሥት እና በእንግሊዝ የሚገኘው ኤምባሲው፣ እስረኞቹን በተመለከተም ሆነ በሕይወት መኖር አለመኖራቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጡም።

19 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ እጅግ ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያ አወጣ። ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ፣ ማናቸውም ኢትዮጵያውያን ለ"ጽንፈኛ ኃይሎች" የገንዘብ ድጋፍ ሲያሰባስቡ ከተገኙ በሳዑዲ አረቢያ ሕግ ጥብቅ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል።
ከገንዘብ ማሰባሰብ በተጨማሪ፣ ሕገ-ወጥ የፖለቲካ ስብሰባዎችን ማዘጋጀትም ሆነ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣ በልገሳ ወይም በእርዳታ ስም የገንዘብ መዋጮ ማድረግ፣ እንዲሁም በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ መሳተፍ በሳዑዲ መንግሥት ሕግ የሚያስጠይቁ ከባድ ወንጀሎች መሆናቸውን ኤምባሲው አብራርቷል። በመሆኑም እነዚህን ክልከላዎች ጥሰው በመሠል ድርጊቶች በሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም የእስር፣ የቅጣት ወይም ከሀገር የመባረር ችግር ግለሰቦቹ ራሳቸው ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ እና ኤምባሲው ምንም ዓይነት ከለላ እንደማይሰጥ በአጽንኦት አስጠንቅቋል።
ይህ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማስጠንቀቂያ ከዲፕሎማሲያዊ መግለጫነት ባለፈ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥ ለሚዋጉት ታጣቂ ኃይሎች (መንግሥት "ጽ -ንፈኛ" እያለ ለሚጠራቸው አካላት) ከዳያስፖራው የሚላከውን የፋይናንስ ምንጭ ለማድረቅ የጀመረው ሰፊ ዘመቻ አካል ነው። በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖረው በርካታ ኢትዮጵያዊ ለሀገር ውስጥ የፖለቲካ እና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች ትልቅ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል።
ኤምባሲው ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የሳዑዲ አረቢያን ጥብቅ የጸጥታ እና የፀ ረ-ሽ ብር ሕጎች እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም ነው። ሳዑዲ አረቢያ ያልተፈቀዱ የፖለቲካ ስብሰባዎችን እና የገንዘብ ማሰባሰብን ፈጽሞ የማትታገሥ ሀገር መሆኗ ይታወቃል። በመሆኑም መንግሥት የተቃዋሚ ደጋፊዎችን የገንዘብ እንቅስቃሴ በመከታተል የዳያስፖራውን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማፈን እና የተቃዋሚዎችን የፋይናንስ የደም ሥር ለመበጠስ ያቀደ መሆኑን ያመላክታል። ይህ አካሄድ በስደት እና በከባድ የጉልበት ሥራ ላይ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ የሀገሪቱን የጸጥታ ሕግጋት ጥሳችኋል በሚል ሰበብ ለባሰ እስራት እና እንግልት ሊያጋልጠው የሚችል አደገኛ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው።

21 days ago
ድምፃዊ ዳዊት መኮንን ከ27 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ ሀገር ቤት ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው
ታዋቂው ድምፃዊ ዳዊት መኮንን ከ27 ዓመታት የውጭ ሀገር ስደት በኋላ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ ነው። አርቲስቱ በመጪው የኢሬቻ በዓል ላይ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ “አን-ዱፌን ጂራ” በተሰኘ ርዕስ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል።
ለረጅም ዓመታት ከሀገሩ ርቆ የቆየው አንጋፋው ድምፃዊ ዳዊት መኮንን፣ ለመላው ሙዚቃ አፍቃሪዎች እና ለደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መግለጫ ከ27 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጀቱን ገልጿል።
እንደ ድምፃዊው መግለጫ ከሆነ፣ የመጀመሪያው የሙዚቃ ድግስ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ “AN-DHUFEEN JIRA Concert” በሚል ርዕስ የሚቀርብ ይሆናል። ይህ ኮንሰርት አርቲስቱ ከአድናቂዎቹ ጋር ከተለያየ በኋላ በይፋ የሚያገኝበት ትልቅ መድረክ እንደሚሆን ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ድምፃዊ ዳዊት መኮንን የኢሬቻ በዓል ዝግጅትን ተከትሎ በሌሎች የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በመዘዋወር ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርብ ቃል ገብቷል። በቅርቡ ዝግጅት ከሚደረግባቸው ከተሞች መካከል አዳማ፣ ነቀምቴ፣ ሻሸመኔ እና ጂማ እንደሚገኙበትና ከአድናቂዎቹ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

24 days ago
የቀድሞ ንጉሥ የልጅ ልጅ የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት
#ethiopia | የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከ፳፻፲፰ ዘመነ ማርቆስ ወደ ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ እንኳን በሰላም አሸጋገራችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ልዑሉ በመልእክታቸው እንደገለጹት አዲስ ዓመት ሲባስ ያለፈውን የስኬትና የመማሪያ ጊዜያት እያሰቡ ፈጣሪን ማመስገንና የሚመጣውን ዘመን ደግሞ በተስፋና በጸሎት መቀበል የቆየ ባህላችን መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የእንቁጣጣሽ በዓል ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የሀገራችን ልዩ ባህልና የኢትዮጵያዊነት ኩራት መሆኑን ያሳሰቡት ልዑል ኤርሚያስ በአዲሱ ዓመት ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከጦርነት፣ ከወገን መከፋፈልና ከስደት ይታደግ ዘንድ ሰላምና አንድነትን ፈጣሪ እንዲሰጠን ጸሎት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አክለውም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፈነው የኑሮ ውድነትና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት በጉዳት ላይ የሚገኙ ወገኖችን በቻሉት መጠን መርዳትና በሐሳብም ሆነ በጸሎት መደገፍ የሁላችንም ሰብአዊ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከሁለት ዓመት ህጻን ልጇ አጠገብ ህይወቷ አልፎ የተገኘችው ወጣት እዱት (ፍጹም) ስሞን ማሉዋል (የክርስትና ስሟ ወለተ ሩፋኤል) አሳዛኝ ህልፈት፣ በሚኒሶታ እና በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጥልቅ ሀዘን ፈጥሯል። አሁን ደግሞ የዚች ወጣት የቀብር ስነ-ስርዓት፣ እናቷ በሌሉበት ሊፈጸም መሆኑ ሀዘኑን ይበልጥ መሪር አድርጎታል። የማሕጸን ፍሬን በሞት ማጣት ከባድ ሀዘን ሲሆን፤ የራስን ልጅ አስከሬን በአካል ተገኝቶ መሸኘትና አፈር ማልበስ አለመቻል ደግሞ ከሞትም የከፋ ስብራት ነው።
የሟች እናት በስደት የካናዳን ድንበር አቋርጠው ከገቡ ገና አንድ ዓመታቸው ነው። የልጃቸውን ድንገተኛ ሞት ሲሰሙ የመጨረሻውን ስንብት ለማድረግ ወደ ሚኒሶታ ለመጓዝ ያደረጉት ጥረት በቢሮክራሲ እና የህግ ማዕቀፍ ተሰናክሏል። በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ እናቷ በቀብሩ ላይ እንዲገኙ በማሰብ የተለያዩ ደጋፊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ወደ ካናዳ ቢልክም፣ እናትየዋ በቅርቡ ስደተኛ ሆነው የገቡ በመሆናቸው አስቸኳይ የመጓጓዣ ሰነድ ማግኘት አልቻሉም። ከዚህም ባሻገር፣ ሟች እውነተኛ ልጃቸው መሆኗን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ ከሀገር ቤት ማቅረብ ባለመቻላቸው እና በአሁኑ ወቅት ጡት የሚጠባ ህጻን ልጅ የታቀፉ በመሆናቸው ጉዟቸው ፈጽሞ የማይታሰብ ሆኗል። በመጨረሻም አቅም ያጡት እናት፣ በምሬት እና በእንባ ታጅበው፣ እርሳቸው በሌሉበት በሚኒሶታ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህቶቿ አማካኝነት ቀብሯ እንዲፈጸም ከባድ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።
እናቱ ህይወቷ ሲያልፍ አጠገቧ የነበረው እና ይህን አሰቃቂ ክስተት ያስተናገደው የሁለት ዓመቱ ህጻን፣ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል ክትትል እየተደረገለት ይገኛል። በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ደምሴ ከበደ እንዳረጋገጡት፣ የልጁ አባት በቴነሲ ግዛት የሚገኝ ሲሆን፤ አሁን በሆስፒታል ያለውን ልጁን ለመረከብ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር የህግ ሂደቶችን በመነጋገር ላይ ይገኛል።
የወጣት እዱት ሲሞን ጸሎተ ፍትሀት እና የቀብር ስነ-ስርዓት የኮምዩኒቲው አባላት እናት እና ቤተሰብ ሆነው ባጀቧት ሁኔታ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይፈጸማል። የጸሎተ ፍትሀት ስነ-ስርዓቱ ሚኒያፖሊስ በሚገኘው ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደ አሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ደግሞ በሴንት ፖል ከተማ በሚገኘው የኦክላንድ መካነ መቃብር ይፈጸማል።
በሰው ሀገር ላይ ያለ እናት የመጨረሻ ስንብት አፈር ለምትለብሰው ወጣት እዱት ፈጣሪ ነፍሷን በገነት እንዲያሳርፍ፣ ለእናቷ፣ ለቤተሰቦቿ እና ለቀረው ህጻን ልጇ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። በሚኒሶታ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት እንድትሸኟት ጥሪ ቀርቧል።

ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለመገደብ ያደረጉት አዲስ ጥረት በዳኛ ውድቅ ተደረገ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለመገደብ በድጋሚ ያደረጉት ሙከራ በፍርድ ቤት ዳኛ ውሳኔ ታገደ።
ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም ያሳለፉት መሰል ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከተሻረ በኋላ ነበር እንደ አዲስ እርምጃውን ለመውሰድ የወሰኑት።
የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ፣ ትራምፕ "የውጭ ጠላቶች" ላሏቸው ልጆች እና ለመውለድ ብለው ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ሰዎች ለሚወልዷቸው ህጻናት ዜግነት እንዳይሰጥ የሚደነግግ አድማሱ የጠበበ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ፈርመዋል።
ይህም ትዕዛዝ ቢሆን ግን በዩናይትድ ስቴትስ የሚወለዱ ህጻናት በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነት እንደሚያገኙ የሚደነግገውን ሕገ-መንግሥታዊ መብት ሊጥስ የሚችል ነው ሲሉ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ዲቦራ ቦርድማን ተናግረዋል።
ቦርድማን፣ ረቡዕ ዕለት ባሳለፉት ውሳኔ የስደተኞች ተሟጋች ቡድኖች ያቀረቡት ክስ እስኪፈታ ድረስ የትራምፕን ትዕዛዝ ለጊዜው አግደዋል። የትራምፕ አስተዳደር ይግባኝ ሊያቀርብ ይችላል።
"የ2026ቱ ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ በእርግጠኝነት ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ነው" ሲሉ ቦርድማን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትራምፕ የቀደመ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን የመገደብ ጥረት ላይ የሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ ተናግረዋል።
"ይህ ፍርድ ቤት አሁንም በድጋሚ የፕሬዝዳንቱን የዜግነት መብት የመንጠቅ አዲስ ሙከራ ተፈጻሚ እንዳይሆን በጊዜያዊነት ማገድ አለበት" ብለዋል።
የስደተኞች ተሟጋች ቡድኖች የትራምፕን ውሳኔ በመቃወም ክስ ከፍተዋል። ክሱን ያቀረቡት፣ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ለሚወልዷቸው ልጆች ዜግነት እንዳይሰጥ በሚል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዚህ ቀደም የፈረሙት ትዕዛዝ እንዲቀለበስ ለማድረግ ነው።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰኔ ወር ላይ የትራምፕን ትዕዛዝ ከሻረ በኋላ፣ ፕሬዝደንቱ ይዘቱን በማጥበብ አዲስ ትዕዛዝ የፈረሙት ብዙም ሳይቆዩ ነሐሴ ወር ላይ ነው። አዲሱ ትዕዛዝ፣ በአሜሪካ የተወለዱ ልጆች በቀጥታ ዜግነት ስለሚያገኙ ነፍሰጡር ሴቶች ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚሄዱበትን "የመውለድ ቱሪዝም" ዒላማ ያደረገ ነው።
ለመውለድ ብቻ በሚል ወደ አሜሪካ መጓዝ አስቀድሞም ቢሆን በአሜሪካ ሕግ አይፈቀድም። አዲሱ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ይህንን ልምምድ ለማስቀረት የሚያስችሉ ደንቦችን ማጥበቅ እና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ያተኩራል።
ትዕዛዙ በተጨማሪም፣ "የውጭ ጠላቶች" ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ወላጆች ለሚወልዷቸው ልጆች የዜግነት መብትን ይነፍጋል። "የውጭ ጠላቶች" የሚለው አገላለፅ ለአሸባሪ ድርጅ አባላት እና ለዕፅ አዘዋዋሪዎች የሚውል ነው።
የነሐሴው ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ፣ ወላጆቻቸው በአሜሪካ ውስጥ ለውጭ መንግሥታት የሚሰሩ ልጆችም ዜግነት እንዳያገኙ ይከለክላል።
የመንግሥት ጠበቆች፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሰኔ ወር ያሳለፈው ውሳኔ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብትን መገደብ የሚያስችሉ ሌሎች ጠባብ አማራጮችን እንደማያግድ ተከራክረዋል።
አስቀድሞም የዲፕሎማት ልጆችን እና የውጭ ጠላቶችን ጨምሮ በልዩ ሁኔታ ገደብ ሊጣልባቸው እንደሚችል የተፈቀዱ አሉ በማለት አስረድተዋል።
የቢቢሲ የሚዲያ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው "ይህ በባይደን የተሾሙ አክቲቪስት ዳኛ የተላለፈ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ምክኒያታዊ አጀንዳ የሚደናቅፍ ሌላ ውሳኔ ነው" ሲሉ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ሐሙስ ዕለት ተናግረዋል።
በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን በተመለከተ የወጣው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ "ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይዘቶች እና ትንታኔዎች ጋር የሚጣጣም ነው" ሲሉም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ነቅፈዋል።
በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ የሚደረጉት የትራምፕ ተደጋጋሚ ሙከራዎች፣ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ስደትን እና ፍልሰትን ለመቀነስ የሚተገበረው ትልቅ ስትራቴጂ አካል ናቸው።
ይህ ስትራቴጂ ለብዙ አገሮች የተሰጠውን ጊዜያዊ ከለላ ማቆም እና በተለያየ ምክንያት የውጭ ዜጎችን ከአገር ማባረርን ያካትታል።
BBC

ባለፉት አምስት ዓመታት የፖለቲካ ምሕዳሩን ለማስፋት የተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት አስገኝተዋል - አቶ ከማል ሃሺ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የመገፋፋትና የሴራ ፖለቲካን ወደ ሃሳብ የበላይነት ለማሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች አስመዝግበዋል አሉ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የምክር ቤቱ ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባል አቶ ከማል ሃሺ።
አቶ ከማል ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ረጅም እድሜ ያለውና የተለያዩ የሥርዓት ለውጦችን ያስተናገደ ቢሆንም የስክነትና የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እጥረት ግን ይስተዋልበታል፡፡
በፖለቲካው ውስጥ የነበረው መጠላለፍ እና ለሕዝብና ለሀገር ከመቆም ይልቅ ለጊዜያዊ ሥርዓት የማደላት አባዜ ጠንካራ ሀገራዊ ተቋማት እንዳይገነቡ አድርጓል ብለዋል።
ይህም በኢኮኖሚው ላይ ምዝበራን፣ የሃብት ብክነትን እና የልሂቃንን ስደት ያስከተለ ሲሆን ÷ ማህበራዊ መስተጋብሩን በማላላት ረገድም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ነው ያሉት።
ይሁን እንጂ ባለፉት አምስት ዓመታት ከተከናወነው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ሀገሪቱን ወደ ሃሳብ የበላይነት ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ለአብነትም የተለያዩ አቋም ያላቸው የፖለቲካ ኃይሎች በነፃነት ወደ ሀገራቸው ገብተው በሃሳብ እንዲፎካከሩ መደረጉን ጠቅሰዋል።
ይህም የመደመር ዕይታ ልዩነትን አቅፎ የጋራ ሀገራዊ አንድነትንና ብዝኃነትን ማዕከል ያደረገ አዲስ የፖለቲካ ባህል መፍጠሩን አብራርተዋል።
በቀደሙት ሥርዓቶች «አጋር» ተብለው ይጠሩ የነበሩት አካባቢዎች በሀገር ጉዳይ ላይ ሙሉ ውክልናና ውሳኔ ሰጪነት ተነፍገው እንደነበር ያነሱት አቶ ከማል ÷ አሁን ላይ ያ ዘመን ማብቃቱን አስረድተዋል።
እነዚህ ክልሎች አሁን በራሳቸው ጉዳይ ሙሉ በሙሉ የመወሰን መብታቸው ከመከበሩ ባሻገር እንደ ማዳበሪያና ጋዝ ልማት ያሉ በቢሊየን የሚቆጠሩ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑባቸውና በሀገሪቱ የወደፊት ዕድል ላይ እኩል የመወሰን አቅም ያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሃሳብ የበላይነትን በተግባር ለማረጋገጥ በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ገዢው ፓርቲ ሙሉ ስልጣን የመያዝ እድል እያለው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በፌዴራልና በክልል የካቢኔ አባል በመሆን ትላልቅ ተቋማትን እንዲመሩ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
በቅርቡ በተካሄደው ምርጫም ተፎካካሪዎች ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸውና የተሻለ ወንበር እንዲያገኙ እድል የሚያሰፋ አሰራር መዘረጋቱን ገልጸው÷ ይህም በምክር ቤት ውስጥ የተለያዩ ድምፆች እንዲሰሙ የሚያስችል አቅም መፍጠሩን አብራርተዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያሉ ገለልተኛ ተቋማት መመሥረታቸውና የቀደመውን የመሳሪያ ውጊያ ወደ ምክክር መድረክ እንዲሸጋገር ማድረጋቸው የዚሁ የሃሳብ ፖለቲካ ፍሬ መሆኑን ጠቁመዋል።
አሁንም የተጀመረው የሰለጠነ የፖለቲካ ጉዞ ግቡን እንዲመታ ከሀገሪቱ የፖለቲካና የአካዳሚክ ልሂቃን ትልቅ ሚና እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
ልሂቃኑ ሁልጊዜ በመተቸትና በጎራ መከፋፈል ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ ጥናቶችን በማድረግ፣ ገንቢ ሃሳቦችን በማፍለቅና አስፈጻሚውን አካል በእውቀት በመመገብ ለሀገር ልማት፣ ሰላምና ብልጽግና የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት

የመደመር አንቀጽ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወረት ቆጥረን ዛሬን በትጋትና ጥበብ ሠርተን ለትውልድ የበለጸገ ሀገር የማሻገር ራዕይን ሰንቀናል።ራእያችንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጋሩን እንፈልጋለን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡
በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer

"ከአምባሳደር እስከ ጅቡቲ ያልተጠናቀቀው የሰርጉአለም ህይወት!"
*በወጣትነቱ የተለየን የአምባሳደሩ ኩሩ ሰርጉአለም ተገኝ ሲታወስ!
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ነገር ግን የህይወት መንገዳቸው በወጣትነት እድሜያቸው በአሳዛኝ ሁኔታ ከተቀጩ ድምፃውያን መካከል አንዱ ሰርጉአለም ተገኝ ነው።
የሙዚቃ አፍቃሪያን ልብ ውስጥ በሰራቸው ጥቂት ግን ጥልቅ ስራዎቹ ትልቅ ቦታ ማግኘት የቻለው ይህ ወጣት አርቲስት ህይወቱ እና የጥበብ ጉዞው አጭርና ያልተጠናቀቀ ህልም ሆኖ አልፏል።
ሰርጉአለም ተገኝ የተወለደውና ያደገው የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶች መፍለቂያ በሆነችው አዲስ አበባ ልዩ ስሙ አምባሳደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ገና በለጋ እድሜው ለሙዚቃ የነበረው ፍቅር እና ስጦታ ግልጽ ሆኖ ይታይ ነበር።
ህይወት ወደ ስደት በገፋችው ወቅት በጅቡቲ ይኖር በነበረበት ጊዜ በወቅቱ ስመጥር በነበረው "ምኒልክ የምሽት ክበብ" ውስጥ በመስራት ሙያውን ሀ ብሎ ጀመረ።
ያ መድረክ ለቀጣይ ትልቅ የስኬት መንገዱ መሰረት ሆነው።
ወደ ሀገር ቤቱ ከተመለሰ በኋላ በወቅቱ ከነበሩት አንጋፋ እና ድንቅ የሙዚቃ አቀናባሪዎች አንዱ ከሆነው ከሙሉጌታ አባተ ጋር በመሆን ተቆጣጠረችኝ የተሰኘውን የመጀመሪያ የግል አልበሙን ለአድማጮች አቀረበ።
አልበሙ በብዙኃኑ ዘንድ አዎንታዊ ምላሽን ያገኘ ሲሆን ሰርጉአለምን በኢትዮጵያ ሙዚቃ መድረክ ላይ በጉልህ አስተዋወቀው።
የስኬት መንገዱን የቀጠለው ሰርጉአለም በወቅቱ ዝነኛ ከነበሩት ከዳዊት መለሰ እና ኅብስት ጥሩነህ ጋር በመሆን የጋራ አልበም በመስራት አድናቆቱን አጎናጸፈ።
ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የሙዚቃ አፍቃሪዎች መሰብሰቢያ በነበሩት በሜጋ አምፊ ቲያትር እና በአይቤክስ ሆቴል የመድረክ ድምፃዊ ሆኖ በመስራት አድማጮቹን በልዩ ድምፁ ያዝናና ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የሙዚቃ አፍቃሪዎች መሰብሰቢያ በነበሩት በሜጋ አምፊ ቲያትር እና በአይቤክስ ሆቴል ድምፃዊ ሆኖ በመስራት አድማጮቹን በልዩ ድምፁ ያዝናና ነበር።
ሁለተኛ እና የመጨረሻ የግል አልበሙ የሆነው "ሳላያት አመሸሁ" ሲወጣ የሰርጉአለም የሙዚቃ ህይወት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ነበር።
የአልበሙ መጠሪያ የሆነችው ዜማ እና ሌሎችም በውስጡ የተካተቱት ስራዎች የብዙዎችን ልብ የነኩ የኢትዮጵያ ሬዲዮን አየር ነተቆጣጠረ ሙዚቃ ነበር።
ይህ አልበም የሰርጉአለምን የዜማ አጣጣል የድምፅ ውበት እና የጥበብ ብስለት አጉልቶ ያሳየ ታላቅ ስራ እንደሆነ እሱን የሚያውቁ የሙያ አጋሮቹ ይመሰክሩለታል።
ሰርጉአለም ለሦስተኛ አልበሙ ዝግጅት ማድረግ ጀምሮ ነበር።
ለቀጣዩ ስራው የሚሆኑ ድንቅ ዜማዎች እና ግጥሞችን አሰባስቦ ወደ ስቱዲዮ በመግባት የድምፅ ቀረፃ ለመጀመር ደፋ ቀና በሚልበት ሰአት ነበር ባደረበት ህመም በወጣትነቱ ህይወቱ ያለፈው።
ሰርጉአለም የጀመረው ሦስተኛ አልበም ሳይጨርስ በወጣትነቱ ከዚህ አለም በሞት ቢለይም ጥሎት ያለፈው ስራው ግን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #ኢትዮጵያ #ሰርጉአለምተገኝ #ሙዚቃ #ጥበብ #አምባሳደር #ሳላያትአመሸሁ #ተቆጣጠረችኝ

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት በራስ ዐቅም ያከናወናቸው ተግባራት ኢትዮጵያ አሳታፊና አካታች ልማትን እያረጋገጠች ያለች ሀገር መሆኗን የሚያሳዩ ናቸው።
ዛሬ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት በራስ ዐቅም ያከናወነውን ውጤታማ ተቋማዊ ሪፎርም በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ተገኝተን ተመልክተናል። ይህ ሪፎርም የሥራ ቦታን ከማሻሻል ባለፈ፣ የሥራ ባህልን፣ የአገልግሎት ጥራትንና ተቋማዊ ዐቅምን የሚያጎለብት ለውጥ ነው።
የአገልግሎቱ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ስደተኞች በመቀናጀት በዋና መሥሪያ ቤቱ፣ በ8 ክልሎች በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና በ25 መጠለያ ጣቢያዎች ያከናወኑት ሥራ፣ በራስ ዐቅም ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያሳየ ጥሩ ተሞክሮ ነው።
በተለይም የመደመር መንግሥት የግብርና እመርታ ማሳያ የሆነውን የሌማት ትሩፋትን በመጠቀም በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮና እንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብና በተለያዩ የዕጽዋት ልማት ዘርፎች የተጀመሩ ሥራዎች፣ ተቋማዊ ሪፎርም የሚለካው በተሻለ የሥራ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሚፈጥረው ምርታማነትና ውጤት ጭምር መሆኑን ያሳያሉ።
ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ዓለም አቀፍ ስደተኞችን በመቀበል፣ መብትና ክብራቸውን በማስጠበቅ ከተቀባዩ ማኅበረሰብ ጋር በማስተሣሠር በልማት ዕድሎች ተጠቃሚ እያደረገች ነው። ስደተኞቹ የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸውም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸውን እያሳደገ ይገኛል።
በራስ ዐቅም የሚመጣ ለውጥ የተቋምን ዐቅም ያጎለብታል፤ ይህ ደግሞ የሀገርን ዐቅም ይገነባል። በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ያየነው ስኬታማ ጉዞ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

የኤርትራውያን አንድነት ለሀገር ክብር፡ በሚስ ወርልድ 2026 ታሪክ የሰራው የህዝብ ድምጽ
#fastmereja I በሚስ ወርልድ 2026 (Miss World 2026) ውድድር ላይ ኤርትራን ለመጀመሪያ ጊዜ በመወከል ላይ የምትገኘው ተወዳዳሪ ስኒት ሀብተአብ፣ በህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ክፍለ አህጉራዊ መሪነቱን በከፍተኛ ልዩነት መያዟን ተከተሎ፣ በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ያሳዩት አገራዊ ደጋፊነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። በፖለቲካዊ አመለካከትም ሆነ በስደት ምክንያት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ በሀገራቸው ብሄራዊ ክብር እና መድረክ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት እንደሌላቸው በግልጽ አሳይተዋል።
በቪየትናም አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ75ኛው ሚስ ወርልድ ውድድር ላይ ስኒት ሀብተአብ ከአፍሪካ ክፍለ አህጉር በህዝብ ድምጽ የመሪነቱን ቦታ የያዘች ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ ነጥቦችን በማሰባሰብ የሁሉንም ቀልብ ስባለች። በነቭሮሳይንስ እና በልዩ ፍላጎት ትምህርት የተሰማራችው ይህች ተወዳዳሪ፣ የሀገሯን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ወደ ሚስ ወርልድ መድረክ በማውጣት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውታለች።
የፖለቲካ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኤርትራውያን በዲጂታል ድምጽ መስጫ ኮምፒውተሮች እና ስልኮች አማካኝነት ያደረጉት የተቀናጀ የድምጽ ማሰባሰብ ዘመቻ ለውጤቱ መገኘት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል። የውድድሩ የመጨረሻ ምዕራፍ እና የህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን፣ የስኒት ሀብተአብ ስኬት የኤርትራውያንን ጠንካራ አገራዊ አንድነት እና ለሀገራዊ መድረኮች ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያስመሰክር እንደሆነ ተገልጻል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በእስራኤል ውስጥ ከ15 ዓመታት በላይ የኖሩ እና ቤተሰብ የመሰረቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የእስራኤል መንግሥት የጥበቃ መብታቸውን ማንሳቱን ተከትሎ አዲስ የህግ እና የህልውና ፈተና ውስጥ መውደቃቸው ተገለጸ። በቅርቡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የመባረር ውሳኔ ለመቀልበስ፣ 'ሃያስ' የተሰኘው ታሪካዊ የአይሁድ የሰብዓዊ መብት ተቋም መንግሥትን ፍርድ ቤት መክሰሱ ታውቋል።
እንድልካቸው የማነ ተስማ በ2005 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ ወደ እስራኤል በሚያደርገው አደገኛ ጉዞ ምን እንደሚገጥመው አላወቀም ነበር። በሱዳን፣ በሊቢያ፣ ዳግም በሱዳን እና በግብጽ የሲና በረሃ አቋርጦ በ2008 እስራኤል ከገባ በኋላ፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ ሰፍሮ ትዳር መስርቷል። ዛሬ ላይ ስድስት ልጆች ያሉት ሲሆን፣ ልጆቹ ያደጉት በእስራኤል ትምህርት ቤቶች፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውም ዕብራይስጥ ሆኖ ነው። ይሁን እንጂ የዜግነት መብት ስለሌላቸው "ለምን እኛ እንደሌሎች እስራኤላውያን ዜጎች ወታደራዊ አገልግሎት አንሰጥም?" የሚለው የልጆቹ ጥያቄ ሁሌም እንደሚረብሸው አባታቸው እንድልካቸው ይገልጻል።
እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ኮሚሽን መረጃ የእስራኤል የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ምጣኔ እጅግ አነስተኛ እና 0.1 በመቶ ገደማ (በዓመት አምስት ሰዎችን ብቻ የሚቀበል) ነው። በአንጻሩ በአውሮፓ ህብረት በ2025 ከቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄዎች ውስጥ 39 በመቶዎቹ ተቀባይነት አግኝተዋል። በአሁኑ ወቅት 1,334 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውሳኔ እየጠበቀ የሚገኝ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የ2(a)5 ቪዛ (የስራ ፍቃድ የሌለው የመኖሪያ ፍቃድ) ይዘው የሚኖሩ ናቸው።
እስራኤል በህዳር 2021 በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጊዜያዊ የቡድን ጥበቃ ሰጥታ ነበር። ሆኖም በጥር 2024 የወቅቱ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሼ አርቤል፣ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል በሚል ይህንን ጥበቃ አንስተዋል። በታህሳስ 2025 ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍትህ ሚኒስቴርን ውሳኔ በማጽደቅ፣ ስደተኞቹ በ4 ወራት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ወስኗል።
ይህንን ውሳኔ በመቃወም በ1881 በሩሲያ ኢምፓየር ስደት ለገጠማቸው አይሁዶች እርዳታ ለመስጠት የተቋቋመው 'ሃያስ' የተሰኘው ድርጅት፣ አሁን ላይ ፊቱን ወደ አፍሪካውያን ስደተኞች በማዞር የእስራኤልን መንግሥት ለፍርድ ቤት አቅርቧል። ድርጅቱ በመስከረም 22 በቴል አቪቭ አውራጃ ፍርድ ቤት በሚሰማው ችሎት፣ መንግሥት ስደተኞችን ወደ አደገኛ ቀጠና እንዳይመልስ የሚከለክለውን የዓለም አቀፍ ህግ እየጣሰ ነው በሚል ይከራከራል።
የእስራኤል የህዝብ ብዛት እና የኢሚግሬሽን ፖሊሲ በበኩሉ፣ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ቢኖርም፣ ስደተኞቹ አዲስ አበባ ሄደው መኖር ይችላሉ የሚል አቋም ይዟል። ነገር ግን ስደተኞቹ፣ አገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ እና የጸጥታ አውድ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነጻነት ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እንዳልሆነ ይሞግታሉ።
በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ በተለይም የጥቅምት 7ቱን የሃማስ ጥቃት ተከትሎ፣ ለተጎዱ ቤተሰቦች የምግብ እርዳታ በማቅረብ እና በእርሻ ስራዎች ላይ በነጻ በማገልገል አጋርነታቸውን ቢያሳዩም፣ ከሶስት ወራት በኋላ የመባረር ውሳኔ መተላለፉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ይገልጻሉ። አንዳንዶች ይህ የመባረር ጫና፣ ጥቅምት 27 ከተያዘው ሀገራዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ ቀኝ-ዘመም ፖለቲከኞች የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ካርድ ነው ብለው ያምናሉ።
ምንም እንኳን የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን እና የመባረር ዛቻዎችን በየዕለቱ ቢጋፈጡም፣ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከእስራኤል ውጪ ሌላ መሄጃ እንደሌላቸው እና ዕጣ ፈንታቸው በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑን የ'ሃያስ' ድርጅት ተወካዮች ያስገነዝባሉ።

በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል። በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወረት ቆጥረን ዛሬን በትጋትና ጥበብ ሠርተን ለትውልድ የበለጸገ ሀገር የማሻገር ራዕይን ሰንቀናል።ራእያችንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጋሩን እንፈልጋለን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል። በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer
Sponsored by
Surafel
1 month ago
ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን
ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል
ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስቸጋሪ ድርድር ወቅት የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በፅናት የተሞገቱትንና የዲፕሎማሲያዊ ግምባር መሪ የነበሩትን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዛሬ በስደት ሀገር በተራ የመኪና ማቆሚያ ስራ ላይ ተሰማርተው ማየት በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነው።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ የነበሩ ሰዎች የህዝብን ሀብት ዘርፈው በውጭ ሀገር ባንኮች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አካብተው በቅንጡ ህይወት ሲኖሩ ማየት በተለመደበት በዚህ ዘመን፣ አቶ ገዱ በስልጣን ዘመናቸው እጃቸውን ከሙስና እና ከሀገር ሀብት ምዝበራ ያቀቡ ታማኝ መሪ መሆናቸውን ዛሬ በራሳቸው ላብና ጥረት ለመኖር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህያው ምስክር ነው።
ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት እና ሀገር ወደድ ወገኖች፣ ይህንን የታማኝነት እና የህሊና ንጽህና አርአያ የሆነ ታላቅ ሰው በሰው ሀገር በጉልበት ስራ እንዲንገላታ መተው የለብንም።
ሀገራቸውን በቆራጥነት ያገለገሉ እና የህዝብን አደራ ያልበሉ ንጹሃን መሪዎችን ማከበርና መደገፍ የታማኝነትን ዋጋ የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለሌሎች ባለሥልጣናት ትልቅ አስተምህሮ የሚሰጥ ነው።
እኒህ ክቡር ሰው ያላቸውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና የአመራር ልምድ ተጠቅመው የሚገባቸውን የክብር ቦታ እንዲያገኙ፣ ባሉበት ሀገር የግል ቢዝነሳቸውን ማስጀመር የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ እና ተገቢውን የሞራልና ቁሳዊ ድጋፍ በመስጠት ከጎናቸው እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በናይጄሪያ የዲኤንኤ ምርመራ ካደረጉ አራት ወንዶች መካከል አንዱ የልጁ ባዮሎጂካዊ አባት አለመሆኑ ተረጋገጠ
#fastmereja I በናይጄሪያ በግል ተቋም የዲኤንኤ (DNA) የምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡት ዋነኛው የሆነው "ስማርት ዲኤንኤ" ይፋ ባደረገው የ2025/2026 አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ የአባትነት ማረጋገጫ ከተደረገላቸው ወንዶች መካከል 23.6 በመቶ የሚሆኑት የልጆቹ እውነተኛ ባዮሎጂካዊ አባት እንዳልሆኑ ተረጋገጠ። ይህም አሃዝ ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው 24 በመቶ እና በ2023 ከነበረው 26.1 በመቶ ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ቅናሽ ያሳየ ነው።
ሆኖም ዋና መሥሪያ ቤቱን በሌጎስ ያደረገው ይህ ተቋም፣ ይህ ውጤት በጠቅላላው የናይጄሪያ ሕዝብ ውስጥ ከሚገኙ አራት ሕፃናት አንዱ የሌላ አባት ልጅ ነው ማለት እንዳልሆነ በጽኑ አስጠንቅቋል። ተቋሙ እንዳብራራው ምርመራውን ለማድረግ ወደ ተቋሙ የሚመጡት ሰዎች አስቀድመው ጥርጣሬ ያደረባቸው በመሆናቸው መላውን የናይጄሪያ ሕዝብ በዘፈቀደ የሚወክሉ አይደሉም።
ከተደረጉት የዲኤንኤ ምርመራዎች መካከል አብዛኞቹ ማለትም 87 በመቶ የሚሆኑት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ለስደት (ኢሚግሬሽን) ጉዳይ ሳይሆን ሰዎች ለግል የአእምሮ እፎይታና ጥርጣሬን ለማጥፋት ያደረጉት እንደሆነ ተገልጻል። በተጨማሪም የዲኤንኤ ምርመራ ጥያቄዎችን ከሚያቀርቡት መካከል 79 በመቶ ያህሉ ወንዶች ሲሆኑ፣ ምርመራውን ካደረጉት ወንዶች መካከል ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጉት ዕድሜያቸው 41 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ናቸው።
የዲኤንኤ ምርመራ ፍላጎት በሌሎች የናይጄሪያ ግዛቶችም እየጨመረ የመጣ ቢሆንም፣ ከተመዘገቡት የዲኤንኤ ምርመራዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም ሶስት አራተኛው (75%) የተካሄደው የሀገሪቱ ትልቁ የንግድ ማዕከል በሆነችው ሌጎስ ከተማ ውስጥ ነው።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ በፓርኪንግ ስራ
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ የነበራቸው፣ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ መሪ ነበሩ።
በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ በነበሩበት ወቅት የህዝብን ሀብት አለመመዝበራቸው እና ዛሬ በባህር ማዶ በሚደረግ ማንኛውም ህጋዊ ስራ ተሰማርተው በላባቸው ለመኖር አለመሸማቀቃቸው የሚያስደንቅ እና ትልቅ አስተምህሮ ያለው ጉዳይ ነው።
በሀገራችን የፖለቲካ ባህል ውስጥ ስልጣን ላይ የሚወጡ ሰዎች ህዝብን ከመጥቀም ይልቅ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ሀብት ሲያካብቱ ማየት የተለመደ በሆነበት ሁኔታ፣ በንጹህ እጅ ወጥቶ በቅንነትና በክብር በራስ ላብ መኖር የስነ-ምግባር አርአያነትን ያሳያል።
ስራ ምንም ይሁን ምን በህጋዊና በሃቅ መንገድ የሚገኝ ገቢ ሁልጊዜም ኩራት እንጂ ውርደት አይደለም።
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት፣ በኋላም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በስደት ሀገር አሜሪካ ውስጥ በተራ የመኪና ማቆሚያ (Parking) ስራ ላይ ተሰማርተው አየኋቸው።
በመጀመሪያ ደረጃ ውስጤ አዘነ፤ ነገር ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ማህበራዊ እውነታ ጠለቅ ብዬ ስቃኝ አግራሞቴና አክብሮቴ በዛ።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ስልጣን ላይ የወጣ ሰው የህዝብና የሀገር ሀብት ዘርፎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በውጭ ሀገር ባንክ አካብቶ፣ በቅንጡ ህይወት ሲኖር ማየት የተለመደ ሆኖ ነበር።
አቶ ገዱ ግን በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ በነበሩበት ወቅት በሙስና ሳይጨማለቁ፣ የህዝብን አደራ ጠብቀው መውጣታቸውን ዛሬ የሚያደርጉት ጥረት ህያው ምስክር ነው።
በሁለተኛ ደረጃ፣ ከከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ወርዶ ማንኛውንም ህጋዊ ስራ ለመስራት አለመሸማቀቅ፣ ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እና የሞራል የበላይነትን ይጠይቃል። በላብ አድርቆና ጥሮ ግሮ መብላት እንጂ የሰረቁትን መብላት ነው የሚያፍረው።
ስራ አይናቅም፤ በሃቅ የሚኖር ህይወት ደግሞ ሁልጊዜም ዘላለማዊ ክብር አለው። ከዚህ አጋጣሚ የምንማረው ትልቅ ትምህርት አለ፦
ስልጣን ጊዜያዊ ነው፦ ዛሬ የተቀመጥንበት ወንበር ነገ የለም፤ ዋናው ነገር በንጽህና ማገልገል ነው።
ሃቅ አይወድቅም፦ በሙስና ያልተበከለ እጅ በማንኛውም የህይወት አጋጣሚ ቀና ብሎ ይሄዳል።
ስራን አለመናቅ እና በራስ ላብ መኖር የትኛውም ቦታ የሰው ልጅ ትልቅነት መለኪያ ነው። ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላሳዩት የሞራል ብቃት፣ የህሊና ንጽህና እና የስራ አክብሮት ትልቅ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ!
Via Ephrem guesh
#ገዱአንዳርጋቸው #የስራክብር #ኢትዮጵያ #ፖለቲካ #ህሊና
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ የነበራቸው፣ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ መሪ ነበሩ።
በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ በነበሩበት ወቅት የህዝብን ሀብት አለመመዝበራቸው እና ዛሬ በባህር ማዶ በሚደረግ ማንኛውም ህጋዊ ስራ ተሰማርተው በላባቸው ለመኖር አለመሸማቀቃቸው የሚያስደንቅ እና ትልቅ አስተምህሮ ያለው ጉዳይ ነው።
በሀገራችን የፖለቲካ ባህል ውስጥ ስልጣን ላይ የሚወጡ ሰዎች ህዝብን ከመጥቀም ይልቅ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ሀብት ሲያካብቱ ማየት የተለመደ በሆነበት ሁኔታ፣ በንጹህ እጅ ወጥቶ በቅንነትና በክብር በራስ ላብ መኖር የስነ-ምግባር አርአያነትን ያሳያል።
ስራ ምንም ይሁን ምን በህጋዊና በሃቅ መንገድ የሚገኝ ገቢ ሁልጊዜም ኩራት እንጂ ውርደት አይደለም።
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት፣ በኋላም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በስደት ሀገር አሜሪካ ውስጥ በተራ የመኪና ማቆሚያ (Parking) ስራ ላይ ተሰማርተው አየኋቸው።
በመጀመሪያ ደረጃ ውስጤ አዘነ፤ ነገር ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ማህበራዊ እውነታ ጠለቅ ብዬ ስቃኝ አግራሞቴና አክብሮቴ በዛ።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ስልጣን ላይ የወጣ ሰው የህዝብና የሀገር ሀብት ዘርፎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በውጭ ሀገር ባንክ አካብቶ፣ በቅንጡ ህይወት ሲኖር ማየት የተለመደ ሆኖ ነበር።
አቶ ገዱ ግን በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ በነበሩበት ወቅት በሙስና ሳይጨማለቁ፣ የህዝብን አደራ ጠብቀው መውጣታቸውን ዛሬ የሚያደርጉት ጥረት ህያው ምስክር ነው።
በሁለተኛ ደረጃ፣ ከከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ወርዶ ማንኛውንም ህጋዊ ስራ ለመስራት አለመሸማቀቅ፣ ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እና የሞራል የበላይነትን ይጠይቃል። በላብ አድርቆና ጥሮ ግሮ መብላት እንጂ የሰረቁትን መብላት ነው የሚያፍረው።
ስራ አይናቅም፤ በሃቅ የሚኖር ህይወት ደግሞ ሁልጊዜም ዘላለማዊ ክብር አለው። ከዚህ አጋጣሚ የምንማረው ትልቅ ትምህርት አለ፦
ስልጣን ጊዜያዊ ነው፦ ዛሬ የተቀመጥንበት ወንበር ነገ የለም፤ ዋናው ነገር በንጽህና ማገልገል ነው።
ሃቅ አይወድቅም፦ በሙስና ያልተበከለ እጅ በማንኛውም የህይወት አጋጣሚ ቀና ብሎ ይሄዳል።
ስራን አለመናቅ እና በራስ ላብ መኖር የትኛውም ቦታ የሰው ልጅ ትልቅነት መለኪያ ነው። ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላሳዩት የሞራል ብቃት፣ የህሊና ንጽህና እና የስራ አክብሮት ትልቅ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ!
Via Ephrem guesh
#ገዱአንዳርጋቸው #የስራክብር #ኢትዮጵያ #ፖለቲካ #ህሊና
1 month ago
የመደመር አንቀጽ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወረት ቆጥረን ዛሬን በትጋትና ጥበብ ሠርተን ለትውልድ የበለጸገ ሀገር የማሻገር ራዕይን ሰንቀናል።ራእያችንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጋሩን እንፈልጋለን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወረት ቆጥረን ዛሬን በትጋትና ጥበብ ሠርተን ለትውልድ የበለጸገ ሀገር የማሻገር ራዕይን ሰንቀናል።ራእያችንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጋሩን እንፈልጋለን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ላይቤሪያ፣ ከአሜሪካ የተባረሩ የ"ሶስተኛ ሀገር" ስደተኞችን የመጀመሪያ ቡድን ሀሙስ ዕለት መቀበሏን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። የላቲን አሜሪካ ስደተኞችን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወደ 20 የሚጠጉ ስደተኞች ከአሜሪካ ከተባረሩ በኋላ ላይቤሪያ አርፈዋል።
ይሁን እንጂ ስደተኞቹን አሳፍራ የነበረችው አውሮፕላን ላይቤሪያ ከደረሰች በኋላ፣ ከስደተኞቹ መካከል ጥቂቶቹ ከአውሮፕላኑ አንወርድም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግዳጅ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ ዳግም ወደ አውሮፕላኑ መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አልታወቀም።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ-ወጥ ስደትን ለመግታት እየወሰዱት ባለው ጠንካራ እርምጃ እና ስደተኞችን ምንም ዓይነት ትስስር ወደሌላቸው "የሶስተኛ ሀገራት" ለማባረር ኋይት ሀውስ በጀመረው ዘመቻ መሰረት፣ ዜጎቿ ያልሆኑ ስደተኞችን የተቀበለች የቅርብ ጊዜ ሀገር ላይቤሪያ ሆናለች። የላይቤሪያ መንግስት በቀጣዩ ዓመት ከአሜሪካ የሚባረሩ እስከ 1,200 የሚደርሱ የሶስተኛ ሀገር ስደተኞችን ለመቀበል ማቀዱን እና አዲስ መጪዎቹም በሀገሪቱ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል። በዚህም መሰረት የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው ዓመት በስህተት ወደ ኤልሳልቫዶር ተባርሮ ወደ አሜሪካ የተመለሰውን ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያ የተባለውን ግለሰብ ወደ ላይቤሪያ ለማባረር እየሞከረ መሆኑ ተጠቁሟል።
የትራምፕ አስተዳደር በታጠቁ ግጭቶች፣ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከሚታመሱት ደቡብ ሱዳን፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ካሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ጋር የሶስተኛ ሀገር የስደተኞች ስምምነቶችን ተፈራርሟል።
ጋና፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በተመሳሳይ ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማምተው መደበኛ የማባረር በረራዎችን እያስተናገዱ ይገኛሉ።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይህንን የሶስተኛ ሀገር የስደት ማስወጣት እርምጃ ኢ-ሰብአዊ እና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ህገ-ወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል። በተለይም አንዳንዶቹ ሀገራት ስደተኞቹን ከጭቆና ወደ ሸሹበት ሀገር መልሰው ሊልኳቸው ይችላሉ የሚል ከባድ ስጋት አላቸው። በአንጻሩ የትራምፕ አስተዳደር እርምጃው ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ውጤታማ መንገድ ነው በማለት ህጋዊነቱንና ጠቀሜታውን ይሟገታል። በአብዛኛው ይህ የአስተዳደሩ ጥረት ያነጣጠረው የትውልድ ሀገራቸው ከአሜሪካ የሚባረሩ ዜጎቻቸውን በማይቀበሉ ወይም ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ህጋዊ ጥበቃ ባገኙ ስደተኞች ላይ ነው።

ከተጎጂነት ወደ ሀገር ሀብትነት፣ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና የመደመር ፍልስፍና ፍሬዎች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ከተከናወኑት ሀገራዊ የለውጥ ርምጃዎች መካከል የመደመር ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ፍልስፍና ማዕከል ያደረገው "ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ" ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
ይህ ፍልስፍና ዜጎች በየትኛውም የዓለም ጥግ ቢኖሩ ክብራቸው፣ ደህንነታቸውና መብታቸው እንዲከበር የማስቻል አቅም ያለው በመሆኑ በዲፕሎማሲው መስክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
ከመብት ማስከበር ባሻገርም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ወጥተው የተመለሱ ዜጎችን እንደ ተጋላጭ ወይም ጥገኝነት ፈላጊ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ትልቅ "የሀገር ሀብት" በመቁጠር መልሶ የማቋቋምና በሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳታፊ የማድረግ ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በ2018 በጀት ዓመት በርካታ ከስደት ተመላሾች በሀገሪቱ የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ድጋፍና ማቋቋሚያዎችን አግኝተዋል።
የመደመር መንግስት ተመላሾቹን በግብርና፣ በትናንሽና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም በክህሎት ስልጠናዎች የስራ እድል እንዲፈጥሩላቸው አድርጓል።
"ለሀገር በቀል ችግር ሀገር በቀል መፍትሔ" በሚለው መርህ መሰረት፣ ከስደት ተመላሾችን እንደገና ለማቋቋም ሁለገብ አቀራረብን ተከተሏል።
ዜጎች ከስደት መልስ የሚገጥሟቸውን ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች ተቋቁመው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ልዩ ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን፣ ከውጭ ሀገራት የቀሰሙትን የስራ ክህሎት፣ እውቀትና የፋይናንስ አቅም አስተባብረው በኢንቨስትመንትና ንግድ ስራዎች እንዲሰማሩ አመች የልማትና የስራ ምህዳር ተፈጥሮላቸዋል።
ዛሬ ላይ የተመላሾች ስኬት በግልጽ በሚታዩ ውጤቶች እየተደገፈ ይገኛል።
ተመላሾች በሰፊው ከተሰማሩባቸውና ተጨባጭ ውጤት ካስመዘገቡባቸው ዘርፎች መካከልም የከተማ ግብርና፣ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ለአካባቢው ኢኮኖሚ አዲስ ህይወት የሰጠ ዘርፍ ሆኗል።
የፀጉርና የውበት ሙያ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይልና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰቡ በማቅረብ በኢኮኖሚው የራሳቸውን ድርሻ መጫወት እንዲችሉ አድርጓል።
እንዲሁም የሳሙናና ውበት መጠበቂያ ሀገር በቀል ምርቶችን በማስተዋወቅ ከውጭ የሚገቡትን የመተካት ድርሻ እየተጫወቱም ነው።
የባህልና የሙያ ክህሎትን አዋህዶ በዕደ ጥበብና ፈጠራ ስራዎች፡በመሰማራትም ውጤታማ በመሆን ላይ ይገኛሉ።
የመደመር መንግሥት የመስሪያ ቦታ፣ የካፒታልና የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ በማመቻቸቱ ምክንያት፣ ትናንት በስደት እንግልት ያስተናገዱ ዜጎች ዛሬ የራሳቸውን ጥሪት ማቋቋም ችለዋል። ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ወጣቶች የነገ ተስፋ በመሆን የሥራ እድል እስከ መፍጠርም ደርሰዋል።
መንግሥት በግብርና፣ በቱሪዝም እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያስመዘገባቸው ተጨባጭ ስኬቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በማህበራዊ ዘርፍ የዜጎችን ሕይወት የቀየሩ "ሰው ተኮር" ልማቶች አንጸባራቂ ውጤት አስመዝግበዋል።
ሕጋዊና ክብር ያለው የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ከማመቻቸት ጎን ለጎን፣ ተመላሾችን የሀገር የእድገት ሞተር ማድረግ መቻሉ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲው የታየበት ህያው ምስክር ነው።
በትዕግስት ግዛቸው

የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እና አትሌቶች ኮብለላ
#ethiopia | የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እና አትሌቶች ኮብለላ ለአትሌቲክሱ ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ ገለጹ
µ በአሜሪካ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ከተጓዘው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ውስጥ ሶስት አሰልጣኞች እና አራት አትሌቶች ወደ ሀገር ሳይመለሱ መቅረታቸውን ተከትሎ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ ጥበቃና ክብካቤ ካልተደረገላቸው ተመሳሳይ ክስተቶች እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል።
በፖርትላንድ እና ቺካጎ አየር መንገድ አባላቱ ተለይተው የቀሩ ሲሆን የቡድኑ መሪዎች ለፖሊስ አመልክተው ቢፈልጉም ሊያገኟቸው አልቻሉም።
የፌዴሬሽኑ አመራሮች አግኝተው ለማነጋገር ቢሞክሩም እስካሁን የተመለሰ የለም።
ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ በሁኔታው ማዘናቸውን ገልጸው አሰልጣኞቹ ከፍተኛ የትምህርትና የሙያ ደረጃ ያላቸው በመሆናቸው ማጣታቸው ለአትሌቲክሱ ትልቅ ጉድለት ነው ብለዋል።
ከአሰልጣኞች አያያዝ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ መሆናቸውን በመጥቀስ እንደ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ያሉ ትልልቅ ባለውለተኞች እንኳን ተገቢውን ክብር ሳያገኙ ማለፋቸውን አስታውሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ለአሰልጣኞች የሚከፈለው ደሞዝ ከጊዜው የኑሮ ውድነት ጋር የማይመጣጠንና ዝቅተኛ መሆኑን የተናገሩት አሰልጣኙ ቀደም ሲል ይሰጡ የነበሩ ማበረታቻዎች መቅረታቸው አሰልጣኞችን ወደ ስደት እንደሚገፋ ገልጸዋል።
የአሰልጣኞችን አያያዝ የማያሻሽልና ተገቢውን ክብር የማይሰጥ አሰራር ካልተቀየረ አትሌቶችና አሰልጣኞች የተሻለ ህይወት ፍለጋ መሰደዳቸው የሚቀጥል መሆኑን አሳስበዋል።
በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#athletics #ethiopianathletics #sports #husseinshebo #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በአሜሪካ የሺዎች ኢትዮጵያውያን የመኖር ተስፋ ተዘጋ
#ethiopia | በአሜሪካ የሚገኝ የፌደራል ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር በሰብአዊ ምክንያት ለ5 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያውያን ሰጥቶት የነበረውን ጊዜያዊ የጥበቃ ሁኔታ (TPS) እንዲያበቃ የሚፈቅድ ውሳኔ አሳለፈ።
የዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ብሪያን ኢ. መርፊ ለአፍሪካውያን ስደተኞች መብት የሚታገለው "አፍሪካን ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር" የተሰኘው ድርጅት የሕግ ክሱ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ጥበቃው እንዳይቋረጥ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።
ውሳኔው በአሜሪካ ሕጋዊ የመኖርና የመሥራት መብት ተሰጥቷቸው የነበሩ በርካታ ሰዎችን ለስደት መባረር ስጋት የሚያጋልጥ ነው።
በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ የባይደን አስተዳደር በ2022 ለኢትዮጵያውያኑ የ18 ወራት ጊዜያዊ ጥበቃ መስጠቱ ይታወሳል።
ይህ ጥበቃ በ2024 በወቅቱ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አሌሃንድሮ ማዮርካስ ተራዝሞ የነበረ ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ጥበቃውን ለማቋረጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።
የኢትዮጵያውያኑ ጠበቆች የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሯ ክርስቲ ኖኤል ጥበቃውን የመሰረዝ ስልጣን የላቸውም እና ውሳኔው ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥሰት አለበት በሚል ያቀረቡትን አዲስ መከራከሪያ ዳኛ ውድቅ አድርገውታል።
የመጠለያ ጥበቃው (TPS) ከጦርነት እና ሰብአዊ ቀውሶች ለሸሹ ሰዎች ያለመባረር ስጋት እንዲኖሩ የሚያስችል ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር ግን አሰራሩ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ አለመሆኑን በመግለጽ የቀደሙ አስተዳደሮች ጥበቃውን በተደጋጋሚ ማራዘማቸውን ይነቅፋሉ።
በአሁኑ ወቅት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሀይቲ ስደተኞች ይሰጥ የነበረውን ተመሳሳይ ጥበቃ እንዲያበቃ መንገድ የከፈቱ ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔም የሶሪያ እና የሀይቲ ስደተኞች ጥበቃ እንዲነሳ መፍቀዱ ይታወሳል።
📸 CNN

በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡
በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል።
ችግሩን በተመለከተ እስከ ክልል ድረስ አቤቱታ መቅረቡን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ከየቀበሌው የተመደቡ አካላት የሞቱ ሰዎችን፣ የተሰደዱ አባወራዎችን እና ያለቁ እንስሳትን ቁጥር መዝግበው ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቁም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከመንግሥት የተደረገው ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች ብቻ የተሰጠ የሴፍቲኔት እርዳታ እንደነበርም አክለው ጠቁመዋል።
እየከፋ የመጣውን የረሃብ አደጋ ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የድንገተኛ እርዳታ ጥያቄ በማንሳት ሰልፍ መውጣታቸውን የገለጹት ጥላሁን፤ አሁንም አስቸኳይ ድጋፍ ካልቀረበ የአካባቢው ሕዝብ በረሃብ የሚያልቅበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲደርሱላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።(አዲስ ማለዳ )
Seledadotio

በሱዳን ኡም አርዳ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ 14 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን አንድ የአካባቢው ሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ። ባለፉት ጥቂት ቀናት የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) በኮርዶፋን ክልል የምትገኘውን ይህቺኑ ስልታዊት ከተማ መቆጣጠሩን ገልጾ ነበር።
የአካባቢው የህግ ባለሙያዎች ቡድን ባወጣው መግለጫ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ትናናት አርብ በሰነዘረው ጥቃት ንጹሃን መገደላቸውንና በአካባቢው ከፍተኛ የስደት ማዕበል መከሰቱን አረጋግጧል።
በሌላ በኩል የሱዳን የመንግስት ብሔራዊ ጦር የአማጺያኑን ጥቃት መክከቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቢገልጽም፣ በግንኙነት መቋረጥ ምክንያት መረጃውን በተናጠል ማረጋገጥ እንዳልተቻለ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በከተማዋ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ህጻናትን ጨምሮ ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች ወደ ኤል ኦቤድ ከተማ በመሸሻቸው በዚያም ከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት አጋጥሟቸዋል ነው የተባለው።
የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው በአካባቢው የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት በመቋረጡ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች በመጥፋቱ በአካባቢው ያለው የረሃብ አደጋ እየከፋ መምጣቱ ተገልጿል።
አራት ዓመታት ያስቆጠረው አ,ስከፊው የሱዳን ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ ሚሊዮኖችን ደግሞ ከቀያቸው አፈናቅሏል።
DW Amharic #amharicmezmur

Comments