የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የቅዳሴ ቤት በዓል እና 85ኛው የድል ቀን በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ የሚገኘው የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ዓመታዊ የቅዳሴ ቤት በዓል ከ85ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል ጋር በመሆን በከፍተኛ ስነ ስርዓት በመከበር ላይ ይገኛል።
በዚህ ታላቅ ሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓል ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተክህነት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በርካታ ምእመናን ታድመዋል።
የገዳሙ በዓል በየዓመቱ ሚያዚያ 27 ቀን በልዩ ሁኔታ የሚከበርባቸው አምስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስደት እንግሊዝ ሀገር በነበሩበት ወቅት የገዳሙ ቅዳሴ ቤት የተከበረው በዚህ ዕለት በመሆኑ ነው።
ሁለተኛው በ1933 ዓ.ም የኢትዮጵያ ነጻነት ታውጆ የድል በዓል መከበር የጀመረው ሚያዚያ 27 በመሆኑ ሲሆን፣ ሦስተኛው ደግሞ ከጃንሆይ ጋር ወደ ሀገር የተመለሰው ታቦተ ሕጉ በቤተ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ አሁን የካቲት 12 ሆስፒታል በሚገኝበት ስፍራ ወደ ተሠራው መቅደስ የገባው በ1935 ዓ.ም ሚያዚያ 27 በመሆኑ ነው።
በተጨማሪም አሁን ያለው ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ በ1940 ዓ.ም የተጣለውና በ1942 ዓ.ም ታቦቱ ወደ አዲሱ ሕንፃ የገባው በዚሁ ታሪካዊ ቀን በመሆኑ ዕለቱ በገዳሙ ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
#መድኃኔዓለም #ምስካየኅዙናን #ሚያዚያ27 #የድልበዓል #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago