የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለክርስቲያን ማህበረሰብ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
#fastmereja I የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በመካከለኛው ምስራቅ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ክርስቲያኖች ስደትና እንግልት እየደረሰባቸው ቢሆንም፣ እስራኤል ግን የክርስቲያን ማህበረሰቡ በነጻነት የሚያድግባትና የሚበለጽግባት ቀጠና ሆና ትቀጥላለች ብለዋል።
ወቅታዊውን ቀጣናዊ ውጥረት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ በዋና ከተማቸው ኢየሩሳሌም ላይ የሚሳኤል ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ቢሆንም እስራኤልና አሜሪካ የኢራንን አገዛዝ እና የሽብር ተላላኪዎችን በጋራ እንደሚመክቱ አረጋግጠዋል። በተለይም በዚህ የተቀደሰ ወቅት የሁሉም እምነት ተከታዮች የማምለክ ነጻነታቸው እንዲጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
እስራኤል በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆና የዜጎችን ሕይወት የመጠበቅ፣ ነጻነትን የማስከበር እና እያንዳንዱ አማኝ በሰላም ጸሎቱን የሚያደርስበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነቷን እንደምትወጣ ሪፖርቱ ያመለክታል። በመጨረሻም የትንሳኤው የምስራች፣ የተስፋ እና የእምነት ብርሃን በሁሉም ቤቶችና ልቦች ውስጥ እንዲበራ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

2 months ago