3 hours ago
ፔንታጎን በጦር ኃይሉ እውቅና ከተሰጣቸው ሃይማኖቶች ዝርዝር ውስጥ ከ180 በላዩን ቀነሰ
#ethiopia | ፔንታጎን በጦር ኃይሉ እውቅና ከተሰጣቸው ሃይማኖቶች ዝርዝር ውስጥ 180 እምነቶችን መቀነሱን ፎክስ ኒውስ ከውስጥ ማስታወሻ ተመለከትኩት ባለው ዘገባ ላይ ጠቅሷል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴት በወታደራዊ ተቋማት ውስጥ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች የጦር ሠራዊቱን አርበኝነት እና ዲሲፕሊን እየሸረሸሩ ነው የሚል አቋም በመያዛቸው ነው ተብሏል።
ቀደም ሲል ከ200 በላይ ለሚሆኑ ሃይማኖቶች እወቅቅና አግኝተው በሰራዊቱ አባላት ዘንድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ሲባል፣ አሁን ይህ ቁጥር ወደ 31 ብቻ ዝቅ ብሏል።
ውሳኔው ወታደራዊ ተቋሙን ከፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ አክራሪነት ለመከላከል አስፈላጊ እንደሆነ ቢገለጽም፥ በሌላ በኩል በሠራዊቱ ውስጥ የሚያገለግሉ አባላትን የሃይማኖት ነፃነት የሚገድብ እና ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ነው በሚል ቅሬታ ቀርቦበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #fox News #tikvahethmagazine

21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቤጂንግ ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉባኤ እንዳጠናቀቁ፣ ታይዋን ከቻይና ተገንጥላ ይፋዊ ነፃነቷን ከማወጅ እንድትቆጠብ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጡ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ አርብ ዕለት ለ 'Fox News' በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ "ማንም አካል ነፃነቱን ሲያውጅ ማየት አልፈልግም" ብለዋል። ታይዋን እራሷን እንደ ሉዓላዊት ሀገር ስለምትቆጥር ይፋዊ የነፃነት አዋጅ ማውጣት እንደማያስፈልጋት የታይዋኑ ፕሬዚዳንት ላይ ቺንግ-ቴ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወቃል። ዩናይትድ ስቴትስ በሕግ በተደነገገው መሠረት ለታይዋን ራስን የመከላከል አቅም እንድትገነባ ለረጅም ጊዜ ስትደግፍ የቆየች ቢሆንም፣ ይህንን ጥምረት ከቻይና ጋር ካላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጋር ማመጣጠን ፈተና ሆኖባት ቆይቷል።
ትራምፕ ወደ ዋሽንግተን ሲመለሱ በነበራቸው የበረራ ጉዞ ላይ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ከፕሬዚዳንት ሺ ጋር ስለ ደሴቲቱ "በስፋት" መወያየታቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን አሜሪካ ታይዋንን በወታደራዊ ኃይል ትከላከልላት እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ለ 'Fox News' በሰጡት ማብራሪያ ላይ ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካ ፖሊሲ እንዳልተቀየረ አጽንኦት ሰጥተዋል። "እንደምታውቁት ጦርነት ለመዋጋት 9,500 ማይል (15,289 ኪ.ሜ) ርቀት መጓዝ ይጠበቅብናል። እኔ ይህንን አልፈልግም። እነሱ (ታይዋኖች) እንዲረጋጉ እፈልጋለሁ፤ ቻይናም እንድትረጋጋ እፈልጋለሁ" ብለዋል።
በቻይና መንግሥታዊ ሚዲያዎች ዘገባ መሠረት፣ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በውይይቱ ወቅት "የታይዋን ጉዳይ በቻይና እና አሜሪካ ግንኙነት ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊው ጉዳይ ነው፤ በአግባቡ ካልተያዘ ሁለቱ ሀገራት ሊጋጩ ወይም ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ትራምፕ ከቻይና ጋር ጦርነት ይፈጠራል ብለው እንደማያስቡ እና ፕሬዚዳንት ሺም ጦርነት ማየት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
ቻይና በቅርብ ዓመታት በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምዶቿን ማጠናከሯ በቀጠናው ውጥረትን አባብሷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ የትራምፕ አስተዳደር ለታይዋን የ11 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ (የላቁ ሮኬት ማስወንጨፊያዎችን እና ሚሳኤሎችን ያካተተ) ለመሸጥ ማቅረቡ ቻይናን ክፉኛ አስቆጥቷል።
ትራምፕ ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ይቀጥል አይቀጥል በቅርቡ እንደሚወስኑ እና ከሺ ጋርም "በጥልቀት" እንደተወያዩበት ገልጸዋል። አክለውም፣ "በአሁኑ ጊዜ ታይዋንን ከሚያስተዳድረው ሰው ጋር መነጋገር አለብኝ" ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከታይዋን ጋር ይፋዊ ያልሆነ ጠንካራ ግንኙነት ቢኖራትም፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ከታይዋን መሪ ጋር በቀጥታ መነጋገራቸው የተለመደ አይደለም። እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ የቻይና መንግሥት "አስቸጋሪ እና የሰላም አፍራሽ" ብሎ ከሚጠራቸው የታይዋኑ ፕሬዚዳንት ላይ ቺንግ-ቴ ጋር በቀጥታ መነጋገርን ስለሚያስከትል፣ በቤጂንግ በኩል ከፍተኛ ቁጣን ሊጭር ይችላል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊን ቺያ-ሉንግ በበኩላቸው፣ ቡድናቸው የአሜሪካ እና ቻይናን የመሪዎች ጉባኤ በቅርበት ሲከታተል እንደነበር እና የታይዋንን ጥቅም ለማስጠበቅ ከአሜሪካ ጋር ጥሩ ግንኙነት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ታይዋን በቀጠናው "የሰላም እና መረጋጋት ጠባቂ" መሆኗን በማንሳት፣ ቻይናን "በጥቃት አዘል ወታደራዊ እርምጃዎቿ እና በአምባገነናዊ ጭቆናዋ" አደጋን እያባባሰች ነው ሲሉ ከሰዋል።

5 months ago
ቅብጥብጥ ተለቀቀ።
የድምፃዊት ቃልኪዳን_አሸብር አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቋል።
#ቅብጥብጥ 🔥 የተሰኝው አዲስ ቆንጆ የሙዚቃ ቪዲዮ በአንጋፋው ናሆም ሪከርድስ ነው ለተመልካቾችና አድማጮች የደረሰው።
ግጥሙ በእዮቤል ብርሀኑ ሲደረስ
በዜማ ደግሞ አህመድ_ተሾመ (ዲንቢ) ተጠቦበታል።
በአብርሀም_ኪዳኔ የሙዚቃ ቅንብር ሲከወን
ማስተሪንግ ላይ ሰለሞን ሀ/ማርያም ለጆሮ ተስማሚ አድርጎ አቅርቦታል።
https://youtu.be/B3YTxMwrc... ሙሉ ሙዚቃውን በዚህ ያገኛሉ።

7 months ago
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር-በር ጥያቄን የሚደግፉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት መሠረት ሲታይ ምን ይመስላል፤የሚለውን በዛሬው አጭር ፁሁፍ በሪያሊዝም፣በሊበራሊዝም፣እንዲሁም በኮንስትራክቲቪዝም በዋናነት በሦስት ትልልቅ የትንተና ማዕቀፎች ለማብራራት እሞክራለሁ፤በእርግጥ እነኝህ ንድፍ ሀሳቦች በእጅጉ ሰፊ ናቸው። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሊቃውንት በጉዳዩ ላይ ልዩ ልዩ የክርክር እና ሀሳብ መር ውይይት እና መነሻ ፁሁፍ በማቅረብ የሀሳቡን ደርዝ እንዲያሰፉት እጠይቃለሁ ።
🔴ሪያሊዝም ህልዮት(Realism Theory):-
ይህ ህልዮት ቀዳሚ እና የነገረ-ሀሳብ ማንጠሪያ መነፀር ነው፤ዓለም አቀፍ ሥርዓት(International System) የትርምስ ዓለም የሰፈነበት (Anarchic World)ሲሆን፣መንግሥታት ዋነኛ ዓላማቸው ህልውናን ማስጠበቅ እና ኃይልን ማሳደግ ነው።መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የኃይል ምንጭ ወይም ድክመት ነው ብለው ያምናሉ።የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ ሪያሊዝም ንድፈ-ሀሳብ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ እንደ ምክንያታዊነት የደህንነት እርምጃ ይደግፈዋል።
የደህንነት ስጋት እና የተዘጋ-መሬት (የመልካ-ምድር እስረኝነት) መሆን የአንድን ሀገር ደህንነት በጎረቤቶች ጥገኛ ስለሚያደርግ "የህልውና አደጋ ነው።የባህር-በር ማግኘት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና ስትራቴጂካዊ ራስን የመወሰን አቅም ያጠናክራል።የኃይል ሚዛን( Power of Balance)የቀይ ባህር አካባቢ ወሳኝ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውድድርና ፉክክር ቀጠና ስለሆነ፣የባህር በር ማግኘት የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ኃይል ያሳድጋል እና የውጭ ጫናን የመቋቋም አቅም ያጎለብታል ።
🔴ሊበራሊዝም ህልዮት (Liberalism Theory):-የዚህ ዋና መርህ በዓለም አቀፍ ትብብር፣በኢኮኖሚ ትስስር እና በዓለም አቀፍ ሕግና ተቋማት አማካኝነት የጋራ ጥቅምን ማሳደግ ይቻላል የሚል ትንታኔ ያቀርባል።የጥያቄው ድጋፍ በሊበራሊዝም የኢትዮጵያን ፍላጎት በኢኮኖሚና በዓለም አቀፍ ትብብር አንፃር ይደግፋል፤ያበረታታል።ከኢኮኖሚ ጥቅም(በጋራ ማደግ) አንፃር ስንመለከተው የባህር-በር ማግኘት የንግድ ወጪን በእጅጉ በመቀነስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያፋጥናል፣ይህም በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ውስጥ የተሻለ ተሳትፎ እንድታደርግ ያስችላታል።
የጋራ ተጠቃሚነት መሰረት ያደረገ ችግሩ በኃይል ሳይሆን( Bilateral and Multilateral በሁለትዮሽ ወይም በብዙ ወገን ስምምነቶች፣በጋራ ልማት እና በኢኮኖሚ ትብብር(ለምሳሌ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ኮሪደርን በመፍጠር ለዚህም ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚያዊ ውህደት እያበረከተች ያለውን ተግባራት መመልከት ይቻላል) አለመግባባቶችን በመፈታት በመጠቆም ጥያቄውን ሰላማዊ መፍትሔ ይሰጣል የሚል አስረጅ ያቀርባል ።
🔴ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት (Constructivism Theory ):-የዚህ ህልዮት ስለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች የሚያቀነቅነው የሀገር ማንነትን የሚቀርጹት በቁሳዊ ኃይል ሳይሆን በሀሳቦች፣ በማንነት፣ በባህልና በማኅበራዊ ትርክቶች ነው የሚል እሳቤ ያነሳል የጥያቄው ድጋፍንም ይህ ንድፈ-ሀሳብ የጥያቄውን መነሻ ከብሔራዊ ስሜት አንፃር ያብራራል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ስሪት ቀዳሚ እና ከቅድመ-አያቶቻችን ጀምሮ በስፍራው የነበረን የላቀ ተሳትፎ እና ኢትዮጵያ የነበራት የንግድና መርከቦች እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን እንመለከታለን ይህን የታሪክ ድልድይ ከአሁን ዘመን ትውልድ ጋር የማንነት ግንባታ ይፈጥራል።መንግስት የባህር በርን እንደ "ታሪካዊ መብት" እና "የህልውና ጉዳይ" አድርጎ ማቅረቡ የዜጎችን የህብረት ስሜት እና የጋራ ማንነት ይቀርጻል፤ፍላጎቱ የሚፈጠረው በሀይል ስሌት ሳይሆን በታሪክ እና በብሔራዊ ክብር ትርክት እንደሆነ ያሳያል።
🖊እንደ መውጫ:-
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዋናነት በሪያሊዝም(ለደህንነትና ኃይል) እና በሊበራሊዝም(ለኢኮኖሚ ትብብር እና በጋራ መልማት) ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት(የሀገር ማንነትን መቅረፅ) ንድፈ-ሀሳቦች ጠንካራ ድጋፍ ያገኛል።በመሆኑ የብሔራዊ ጥቅም እሴቶችን በመያዝ በትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ በዜጎች ትብብር እና አንድነት ጥያቄው ወደ ልማት እና ኢትዮጵያን ወደ ሃያልነት የሚመልስ እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፀሃፊውን የኤክስ(X)ገፅ ይከታተሉ :-
https://x.com/HDebasu?t=Bz...

Sponsored by
Surafel
8 months ago
ግራንድ አፍሪካን ረን : የአፍሪካውያን ድምፅ አግኝቷል
🇺🇸 FOX5 - ታዋቂው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግራንድ አፍሪካን ረን ዝግጅት ለማብሰር እንግዳ በመጋበዝ የሚዲያ አጋርነቱን አሳይቷል።
👉 🏃🏾♀️🏃🏽🏃🏼♂️
ግራንድ አፍሪካን ረን ከሩጫም በላይ ነው!
💕 አልፋ የጡት ካንሰር ማዕከልን ይደግፉ 💕
HELP - Alpha Breast Cancer Support Service (ABCSS)
💕 Family and friends 💕
🎊Come and support our fight against Breast Cancer and support our efforts to raise awareness on October 11 🎊
#grandafricanrun #countdown #registertoday #grandafricanrun5k #breastcancerawareness #
9 months ago
ተማሪ ህሊና ፍቅሩ በ6 አመቷ The red fox country የሚል ርእስ ያለው በእንግሊዘኛ የተጻፈ የልጆች መጽሀፍ ለንባብ ያበቃች በሀገራችን የመጀመሪያዋ ህፃን ጸሀፊ ያደርጋታል:(ከተሳሳትኩ እርማት እቀበላለሁ):።
አሁን ደግሞ በ14 አመትዋ Anna's story hood በሚል ሁለተኛ የልጆች መጽሀፏን በደማቅ ሁኔታ አስመርቃ ለንባብ አብቅታለች።
ማንኛውም ወላጅ ለልጁ ይህን ምርጥ መጽሀፍ ገዝቶ ሙሉ ሠው የሚያደርገውን ስጦታ ለልጆቹ ያበርክት:
መጽሀፎቹን እራሷ በከፈተችው Halin books and Amazon ላይ ያገኙታል:ሊንኮቹን ከታች አስቀምጫለሁ:ተማሪና ጸሀፊ የወደፊት የሀገር ተስፋ የሆነችው ህሊና ፍቅሩን በማበረታታ አብረን ልጆቻችን ላይ እንስራ እላላሁ:ልጆች ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ስለሆነ።
አመሰግናለሁ🙏🥰
👇 https://youtube.com/halin...
👉https://halinbooks.fws.sto...
👇 https://www.pinterest.com/...
👉https://t.me/halinbooks

Comments