(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚኒሶታ ትዊን ሲቲ እና አካባቢው በሚኖረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማህበረሰብ ውስጥ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የአእምሮ ጤና ችግር ለመቅረፍ ያለመ አዲስ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ ይፋ ተደረገ። የግንዛቤ እጥረትንና አጉል ባህላዊ ተፅዕኖዎችን ለመስበር ያለመው ይህ ንቅናቄ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የማህበረሰብ ተወካዮች በሚተባበሩበት ታስክ ፎርስ (ግብረ-ኃይል) የሚመራ ይሆናል።
የኢስት አፍሪካ ዌልነስ ኤንድ ሪሶርስ ሴንተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበባየሁ አበበ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ወጣቶች እና ቤተሰቦች በአእምሮ ጤና እክል ክፉኛ እየተጎዱ ይገኛሉ። "ባለፉት አንድና ሁለት ወራት ብቻ ራሳቸውን ያጠፉ ወደ አራት የሚጠጉ ወጣቶችን አጥተናል፤ ይህ ለማህበረሰባችን ትልቅ የልብ ስብራት ነው" ያሉት ዶ/ር አበባየሁ፣ ሌሎች በርካታ ወጣቶች ወደ አልኮልና አደንዛዥ እፅ እየገቡ መሆናቸውንና ብዙ ቤተሰቦችም የችግሩ ሰለባ ሆነው ዲስፋንክሽናል እየሆኑ መምጣታቸውን አስረድተዋል።
በሚኒሶታ የብራይት ኒኖ ኦቲዝም ሴንተር ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰብለ ለማ በበኩላቸው፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ስለ አእምሮ ጤና በቂ ግንዛቤ አለመኖሩ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሯ አክለውም፣ "ህብረተሰቡ ስለ ልብ በሽታ በግልጽ እንደሚያወራው ሁሉ ስለ አእምሮ ጤናም ያለ አንዳች ፍርሃት እንዲያወራ ማበረታታት እና ተጎጂዎችን ከማግለል ይልቅ ድጋፍ ሆነን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ዋነኛ አላማችን ነው" ብለዋል።
በአሜሪካ የግንቦት (May) ወር "የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር" መሆኑን ተከትሎ የተጀመረው ይህ ንቅናቄ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን መገለል (Stigma) እና እርዳታ ከመጠየቅ ወደ ኋላ የማለት ባህላዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት ይሰራል።
ይህ ማህበረሰቡን መሰረት ያደረገ ንቅናቄ፣ ፖለቲካን ያላካተተና ሁሉንም ማህበረሰብ በእኩልነት የሚያሳትፍ ነው። የፊታችን ሜይ 9 የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት እና የእስልምና የሃይማኖት ተቋማትን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያና የኤርትራ ማህበረሰቦችን በአንድነት በማሰባሰብ ሰፊ ውይይት እንደሚያካሂድ እና አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት አዘጋጆቹ ገልጸዋል። እስካሁንም ከማህበረሰቡ እጅግ አዎንታዊ የሆነ ምላሽ ማግኘታቸው ተጠቁሟል።
ዶ/ር አበባየሁ አበበ የንቅናቄውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ ቀጣይ እቅዶችን አብራርተዋል/ልል የአጭር ጊዜ እቅዶች... ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ግብረ-ኃይል በማቋቋም፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ወይም በሀምሌ መጀመሪያ ትልቅ 'የአእምሮ ጤና የእግር ጉዞ' (Mental Health Walk) ማካሄድ። በተጨማሪም ባለሙያዎች እና ተሞክሮ ያላቸው ሰዎች ምስክርነታቸውን የሚሰጡበት ሰፊ የፓናል ውይይት እና ወርክሾፕ ማዘጋጀት ሲሆን የረጅም ጊዜ እቅዶች ደግሞ ስለ አእምሮ ጤና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ አጫጭር መረጃዎችን በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች አዘጋጅቶ በየማህበረሰቡ መገልገያ ቦታዎች ማሰራጨት። እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች በአእምሮ ጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ልዩ ስልጠና መስጠት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ይህ እንቅስቃሴ፣ በስደት በሚኖረው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ነውር የሚቆጠረውን የአእምሮ ጤና ጉዳይ ወደ አደባባይ በማውጣት ትውልድን ለመታደግ የተወሰደ ትልቅ እና ወቅታዊ እርምጃ መሆኑ ታምኖበታል።

1 month ago