(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኬንያ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራዊያን ቁጥር በእጥፍ መጨመሩ ተገለፀ፡፡ ‹‹ኢኮኖሚክ ሰርቬይ 2026›› ባወጣው አዲስ ሪፖርት በኬንያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ብዛት እያደገ መምጣቱን ጠቅሶ በዚህም ኤርትራዊያን ግንባር ቀደም ደረጃ መያዛቸውን አስረድቷል፡፡ እንደሪፖርቱ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2021 በአጠቃላይ በኬንያ የተመዘገቡ ስደተኞች ብዛት 540,068 የነበረ ሲሆን በ2025 ግን ይህ ወደ 835,793 አድጓል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራዊያን ወደኬንያ የሚያደርጉትን ስደት መጨመራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ በ2024 ወደኬንያ የገቡት ኤርትራዊያን 3,259 መሆናቸውን አውስቷል፡፡ ነገር ግን በ2025 ወደኬንያ ተጉዘው ጥገኝነት የጠየቁት 7,839 መሆናቸውን ገልፆ ይህም የ99.8 ፐርሰንት እድገት እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምንም እንኳ የኤርትራዊያን ፍልሰት እየጨመረ የመጣ ቢሆንም በኬንያ ከሚገኙት ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ግን ሱማሊያዊያን ናቸው፡፡ እንደሪፖርቱ በ2025 በኬንያ የተመዘገቡት ሱማሊያዊያን ስደተኞች 459,131 ሲሆን ቀጣዩን ደረጃ የያዙት ደቡብ ሱዳናዊያን ቁጥር ደግሞ 202,863 ነው፡፡ እንዲሁም 66,043 ስደተኞች ከዲሞክራቲክ ኮንጎ የሄዱ መሆናቸውን የገለፀው ሪፖርቱ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ 42,897 መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

1 month ago