3 months ago
እስከ 5 ዓመት እስራት የሚያስቀጣው አዲሱ
የመረጃ ነጻነት አዋጅ
#ethiopia | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረውን አዲሱን “የመረጃ ነጻነት አዋጅ” በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ይህ አዲስ ሕግ ቀደም ሲል ከነበረው አሠራር በተለየ መልኩ ከመንግሥት አካላት በተጨማሪ የግል ድርጅቶችም መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዲኖርባቸው አድርጎ ያሻሻለ ሲሆን፣ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ዝርዝር አፈጻጸምና ውጤት ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ድንጋጌ አካቷል።
በተጨማሪም፣ መገናኛ ብዙኃን የሕዝብ ጥቅም መረጃዎችን ሲጠይቁ ከማንኛውም የማባዣ ወጪ ክፍያ ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል።
የዚህ አዋጅ ትልቁ መነጋገሪያ ጉዳይ መረጃን በደበቁ ወይም ባሻጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የጣለው ጠንካራ የወንጀል ቅጣት ነው።
ሆን ብሎ መረጃን ያጠፋ፣ ያበላሸ፣ የደበቀ፣ ሙስናን ለመሸፈን በሚስጥር የያዘ ወይም የሀሰት ሰነድ ያዘጋጀ ኃላፊ ጥፋተኝነቱ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ (ወይም በሁለቱም) ይቀጣል።
እንዲሁም ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ የሰጠ፣ ያለበቂ ምክንያት ትዕዛዝ ያልፈጸመ ወይም የመከላከያ ምስጢር አሳልፎ የሰጠ አካል እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል።
በተጨማሪም መረጃ የመጠየቅ መብትን በቸልተኝነት ለሚያደናቅፉ አካላት ማለትም የቃል ጥያቄን በቅጽ ለመሙላት ፈቃደኛ ካለመሆን፣ መረጃን አትሞ ካለማውጣት፣ እና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በሆነ መንገድ መረጃን ተደራሽ ካለማድረግ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች እስከ 1 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣሉ።
ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትን እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ትልቅ እመርታ መሆኑ ተገልጿል።
Ethiopia Insider
#ethiopia #informationfreedom #breakingnews #transparency #accountability #ethiopianparliament #mediafreedom #lawandjustice

5 months ago
በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር ተፈጥሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር መፈጠሩን ገለጹ። ሆኖም ይህ ነጻነት ከሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ኃላፊነት ጋር ተጣጥሞ የመሄድ ክፍተት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ የለውጡን መንግሥት የመጀመሪያ እርምጃዎች የጠቀሱ ሲሆን፣ "የመጀመሪያው ሥራችን በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን መፍታት ነበር" ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ታግደው የነበሩ ብሎገሮች እና ድረ-ገጾች እንዲከፈቱ መደረጉን፣ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሚዲያ ስርጭቶች ላይ ይደረግ የነበረው የጃሚንግ (የሞገድ እገዳ) ሥርዓት መቅረቱን፣ በስደት የነበሩ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ወደ ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ መፈቀዱን፣ እንዲሁም ለሚዲያ ነጻነት እንቅፋት የነበረው የፀረ-ሽብር ሕግ እንዲሻሻል መደረጉን ዘርዝረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚዲያው ዘርፍ የታየውን የሽግግር ወቅት በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ሁኔታውን "ታስሮ እንደቆየ ጥጃ" በማለት ገልጸውታል።
"የታሰረ ጥጃ ሲፈታ ሁለት ባህሪያት ይታዩበታል፤ አንደኛው እንቅስቃሴ ስላልለመደ እግሩ እየተሳሰረ መቸገር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ያገኘውን ነጻነት በአግባቡ መቆጣጠር አቅቶት ዝም ብሎ በመዝለል ንብረት መስበር ነው" ብለዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በሚዲያው ዘርፍ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት ነጻነቱን በአግባቡ የማስተዳደር እና የሙያ ሥነ-ምግባርን የመከተል ክፍተት እንደታየባቸው ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን የሚዲያ አውዱ አሁንም ድረስ ከመረጃ አቅርቦት፣ ከገንዘብ እና ከተለያዩ ጫናዎች ጋር ተያይዞ እንከኖች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በመጨረሻም፣ ባለሙያዎች የተፈጠረውን የነጻነት ዕድል በመጠቀም ረገድ ራሳቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ አሳስበዋል።
"ሙያተኞች ሕግንና ሙያን እንዴት አጣጥመው እንደሚሠሩ ራሳቸውን መፈተሽ ይኖርባቸዋል" ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በሀይማኖት ከበደ
#ethiopia #mediafreedom #abiyahmed #journalismethics #pressfreedom #narrativebuilding

"u121au12f2u12eb u12e8u1200u1308u122d u1218u1295u1348u1235 u1290u12cd"u1366 u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u12a8u1218u1308u1293u129b u1265u12d9u1203u1295 u1263u1208u1219u12ebu12ceu127d u130bu122d u12ebu12f0u1228u1309u1275 u12cdu12edu12edu1275 #pmabiyahmed #mediareform #ethiopianmedia #journalismethics #nationalinterest #the4ps #technology #ai #ethiopianpolitics #mediafreedom #u121au12f2u12eb #u12a2u1275u12eeu1335u12eb #u12d0u1262u12edu12a0u1205u1218u12f5 ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
\
Comments