ሆርን ኒውስ ሃብ በኢትዮጵያ ሚዲያ ባለሥልጣን በይፋ ተመዘገበ
#fastmereja I ቀደም ሲል "ትግራይ ሄራልድ" በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ሆርን ኒውስ ሃብ (Horn News Hub) በኢትዮጵያ ሚዲያ ባለሥልጣን የኦንላይን ሚዲያ የሥራ ፈቃድ ማግኘቱንና የኤዲቶሪያል ስፋቱን ማሳደጉን ገለጸ። ተቋሙ በይፋ መመዝገቡ በሀገሪቱ ሕጋዊ እውቅና ካላቸው የሚዲያ ተቋማት ተርታ እንዲሰለፍ አድርጎታል።
እንደ ተቋሙ መግለጫ፣ ሚዲያው እ.ኤ.አ በ2021 በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በናይሮቢ ስደት ላይ በነበሩት ጋዜጠኛ ቸኮለ አለሙ የተመሰረተ ሲሆን፤ በወቅቱ የትግራይን ድምፅ ለማሰማት አልሞ ይንቀሳቀስ ነበር። ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፈረምን ተከትሎ፣ ተቋሙ ስሙንና የዘገባ አቅጣጫውን በመቀየር አድማሱን ወደ አገር አቀፍና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከፍ ማድረጉ ተመልክቷል።
የሆርን ኒውስ ሃብ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋዜጠኛ ቸኮለ አለሙ እንደገለጹት፣ አዲሱ የኤዲቶሪያል ፖሊሲ የትግራይ መረጋጋት ከኢትዮጵያ አንድነት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ያምናል፡፡ በዚህም መሠረት ሚዲያው በቀጣይ እንደ ቀይ ባሕር፣ የሕዳሴ ግድብ፣ የሀገር ሉዓላዊነትና የክልሎች ውህደት ባሉ ቀጠናዊና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አስታውቋል።
ተቋሙ "የቀንዱን ድምፅ ማሰማት፣ ለዓለም ማሳወቅ" የሚል አዲስ መሪ ቃል የቀረጸ ሲሆን፣ በቅርቡ የሥራ ጅማሮውን በይፋዊ ሥነ-ሥርዓት እንደሚያበስር ተገልጿል። ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ የዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ውስጥ የሕጋዊነትና የሙያ ስታንዳርድን ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል።

2 months ago