2 months ago
በምሽት ክበብ ውስጥ በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገለጸ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ቱሉ ዲምቱ በሚገኝ ሆልስቴ ሆቴል ውስጥ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በሰዎች መካከል ጠብ ተነስቶ ነበር።
በዚህ ግጭት ወቅት አቡሽ ባዩ የተባለ ግለሰብ በሽጉጥ ተመትቶ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደታወቀው ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 12 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን በስፋት እየገፋበት ይገኛል።
ከተያዙት ግለሰቦች መካከል በፀቡ ላይ በቀጥታ የተሳተፈ አንድ ሰው፣ ከዋናው ገዳይ ጋር አብሮ ሲዝናና የነበረ ሌላ ተጠርጣሪ እንዲሁም ለግጭቱ መነሻ እንደሆነች የተጠረጠረች አንዲት አስተናጋጅ ይገኙበታል።
በወቅቱ በነበረው አለመግባባት ሳቢያ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ ሟች ታጥቆት የነበረውን ሽጉጥ ቀምቶ እንደተኮሰበት የሚያሳዩ ፍንጮችን ማግኘቱን ፖሊስ ጠቁሟል።
የጉዳዩን ዝርዝር የምርመራ ውጤት ወደፊት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
በሌላ በኩል ፖሊስ ከዚህ ድርጊት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የከተማዋን ነባራዊ የሰላም ሁኔታ የማይገልጽ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል።
ህብረተሰቡ የሀሰት ወሬዎችንና አሉባልታዎችን ወደ ጎን በመተው ትክክለኛውን መረጃ ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ የመቀበል ልምዱን ሊያሳድግ እንደሚገባ ያሳሰበው መምሪያው፣ የስጋት ድባብ ለመፍጠር የሚሰሩ አካላትን በተባበረ ክንድ ለማክሸፍ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ
#addisababapolice #crimeinvestigation #ethiopiannews #security #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
በአዲስ አበባ በውጭ ሀገር ዜጋ ላይ ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዜጋን በማዋከብ ስልክ የሰረቁ ሁለት ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን ክትትል በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጠ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ ልዩ ስሙ ኢሰመኮ (ባምቢስ) አካባቢ ነው። ተበዳዩ ኢብራሂም ሀሰን የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሱፐር ማርኬት ዕቃ ገዝተው ወደ አረፉበት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በእግራቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ጥቃቱ የደረሰባቸው።
አብዲ ሀሰን እና ቃልዓብ ወርቁ የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ግለሰቡን ግራና ቀኝ በመሆን ካዋከቡ በኋላ፣ አንደኛው "ሄድፎን ግዛን" በማለት ትኩረት ሲሰርቅ፤ ሁለተኛው ተጠርጣሪ ግምቱ 200 ሺህ ብር የሚሆን iPhone 15 Pro Max ስልክ ከኪሳቸው ሰርቆ ለመሰወር መሞከሩ ተመልክቷል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የባምቢስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከአቤቱታው መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፈጣን ኦፕሬሽን፣ ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች ስልኩን እንደያዙ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባስተላለፈው መልእክት፣ በወንጀል ተግባር ራስን ለማበልጸግ የሚሞክሩ አካላት ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #መናኸሪያfm #addisababapolice #crimenews #ethiopia #publicsafety #kirkossubcity #newsupdate

"ታፍነናል" በማለት 300 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው የጠየቁት ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | በከተማችን አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ (የካ አባዶ) የሚኖሩ የ15 እና የ16 ዓመት ሴት ታዳጊዎች፣ ለስደት መሄጃ ገንዘብ ፍለጋ ሲሉ የፈጠሩት "የታፈንን" ድራማ በፖሊስ ክትትል ከሸፈ።
የክስተቱ ዝርዝር፦
ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት የወጡት ታዳጊዎች ሳይመለሱ ቀርተው፣ "300 ሺህ ብር ካልተላከ ገዳዮቹ ጉዳት ሊያደርሱብን ነው" በማለት ቤተሰቦቻቸውን አስጨንቀዋል።
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታዳጊዎቹ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ ተገኝተዋል። አራቱም ታዳጊዎችና የመኝታ ክፍል ያከራያቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ታዳጊዎቹ ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው ገንዘብ ለማግኘት ድርጊቱን እንዳቀነባበሩት ለፖሊስ ቃል ሰጥተዋል።
ልጆቻችሁ የት እንደሚውሉ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉና ምን እያቀዱ እንደሆነ የመከታተል ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።
ሆቴሎችና የመኝታ ቤቶች ለታዳጊዎች አልኮል ከመሸጥና ክፍል ከማከራየት እንዲቆጠቡ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ልጆቻችንን እንከታተል፤ ከስደትና ከጥፋት እንታደጋቸው!
#getu #addisababapolice #lemikura #teenagecrime #safetyfirst #ethiopianfamily #awareness #socialissue #አዲስአበባፖሊስ #ለሚኩራ #የልጆችጥበቃ #ማስጠንቀቂያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
የ3.8 ሚሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ኬብል የዘረፉ ግለሰቦች ተያዙ!
#ethiopia | የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ በመሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ከዘረፉት ንብረት ጋር በቁጥጥር ስር አውሏል።
የተያዘበት ቦታ፦
በየካ ክፍለ ከተማ፣ ኮተቤ ኪዳነ-ምህረት አካባቢ።
የንብረቱ መጠን፦
4 ሺህ 895 ሜትር የኤሌክትሪክ ኬብሎች (ABC እና UG) እንዲሁም 350 ኪ.ግ የሚመዝኑ አልሙኒየምና መዳቦች።
ግምታዊ ዋጋ፦
የተያዙት ንብረቶች በአጠቃላይ 3 ሚሊዮን 895 ሺህ 81 ብር ያወጣሉ ተብሏል።
የተወሰደው እርምጃ፦
ፖሊስ ምስክሮችን በማቅረብ ጉዳዩ በአፋጣኝ በፍርድ ቤት እንዲታይ ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ኬብሎቹ ከየትኛው አካባቢ ተዘርፈው እንደመጡ ለማወቅ ጥልቅ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል።
አሳሳቢ መልዕክት፦
እንዲህ ያሉ የስርቆት ወንጀሎች ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ ከመዳረጋቸው ባለፈ፣ ደንበኞችን ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና ለደህንነት ስጋት እየዳረጉ በመሆኑ ማህበረሰቡ መሰል አጠራጣሪ ድርጊቶችን ሲመለከት በፍጥነት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #crimealert #addisababapolice #electricinfrastructure #cabletheft #yeka #kotebe #ethiopiaelectricutility #lawenforcement #አዲስአበባ #ፖሊስ #መሠረተልማት #ስርቆት #የካ #ኮተቤ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
🚨 የተቀነባበረው ዘረፋ መጨረሻ
#ethiopia | በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ አፓርታማ 8ኛ ፎቅ ላይ በመስኮት በመግባት ከ6 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት የሰረቀው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ። ጌቱ ተስፋዬ የተባለው ይህ ግለሰብ፣ ወንጀሉን የፈፀመው ባሳለፍነው የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 5:00 ገደማ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
🔍 የወንጀሉ አፈፃፀም በዝርዝር
ተጠርጣሪው በዚያው አፓርታማ ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በአስተናጋጅነት የሚሰራ ሲሆን፣ የስራ እድሉን ተጠቅሞ መረጃ በማሰባሰብ ነው ስርቆቱን የፈፀመው::
* የመግቢያ መንገድ፦ የግል ተበዳይ ወይዘሪት እልፍነሽ አሰፋ የመኝታ ክፍል መስኮት አለመዘጋቱን በማረጋገጥ፣ በ8ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኝ መስኮት ዘሎ በመግባት።
* የተዘረፉ ንብረቶች፦
* ከወርቅና ከዳይመንድ የተሰሩ ልዩ ልዩ የአንገት ሀብሎች።
* የጣት ቀለበቶች፣ የእጅ ብራስሌቶችና የጆሮ ጌጣጌጦች።
* 2,800 የአሜሪካ ዶላር።
* 2 ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች።
👮♂️ የፖሊስ ክትትልና አያያዝ
ተጠርጣሪው ወንጀሉን ፈፅሞ ከአካባቢው ቢሰወርም፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ግን አላስመለጡትም። የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ (አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ) የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦
* የደህንነት ካሜራ (CCTV): በህንፃው ላይ የተገጠመውን ካሜራ በመመርመር የተጠርጣሪውን ማንነት አረጋግጧል።
* ክትትል፦ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ተጠርጣሪው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ አንድ አልጋ ቤት ውስጥ ተደብቆ ሳለ ከነ ንብረቶቹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
> "ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ማምለጥ አይችልም" — የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
💡 ለህብረተሰቡ የተላለፈ መልዕክት
ፖሊስ ህብረተሰቡ በመኖሪያ ቤቱም ሆነ በሚያርፍባቸው ቦታዎች የበርና መስኮት ደህንነታቸውን በአግባቡ እንዲያረጋግጡና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አዲስአበባፖሊስ #የወንጀልምርመራ #ደህንነት #ኢትዮጵያ #bolecity #addisababapolice

6 months ago
ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ፖሊስ በእንጦጦ ፓርክ አካባቢ ጎብኝዎችንና ስፖርተኞችን ኢላማ በማድረግ ወንጀል ለመፈጸም የሞከሩ ሶስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
የክስተቱ ዝርዝር
ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው ዕለት በሽሮ ሜዳ ቁስቋም በኩል ወደ እንጦጦ ፓርክ በመግባት ላይ የነበሩ የሆላንድ ዜጎችን ለመዝረፍ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ክትትል ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ማሳደድ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፣ በወቅቱ ተጠርጣሪዎቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል።
ፖሊስ በምርመራው የደረሰባቸው ነጥቦች፦
* የማንነት ማጭበርበር፦ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል አንዱ የፎርጅድ የመከላከያ መታወቂያ ይዞ ተገኝቷል።
* የወንጀል ስልት፦ ወንጀለኞቹ እንደ ስፖርተኛ ወይም ጎብኝ በመምሰል እንዲሁም በአሳቻ ቦታዎች በመደበቅ ጥቃት እንደሚያደርሱ ተጠቁሟል።
* የቀጠለ ምርመራ፦ ፖሊስ የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ማንነትና የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ እያጣራ ይገኛል።
> "ህብረተሰቡ መሰል ጥርጣሬዎችን በመከታተል ትብብር እንዲያደርግ፣ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #addisababapolice #crimeprevention #entotopark #publicsafety #ethiopia

7 months ago
🛑 በማታለል ወንጀል የተጠረጠሩት የ"ሄሎ ታክሲ" ስራ አስኪያጅና ግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | "በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ የመኪና ባለቤት እናደርጋችኋለን" በሚል የ127 ዜጎችን ተስፋ እና ጥሪት የበሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
🔍 የወንጀሉ ዝርዝር፦
ተጠርጣሪዎቹ የዜጎችን የትራንስፖርት ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ መኪና እናስመጣለን በሚል ከእያንዳንዱ ተበዳይ ከ130 ሺህ እስከ 350 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብለዋል።
የተያዙት ተጠርጣሪዎች፦
አቶ ዳንኤል ዮሐንስ (የሄሎ ታክሲ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ)
ወይዘሪት እንግዳ የሺጥላ እና ሌሎች ተባባሪዎች።
⚠️ የፖሊስ ማስጠንቀቂያ
ፖሊስ እንደገለጸው፣ እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ጊዜያት ዜጎችን በማደራጀት እና የሀሰት ተስፋ በመስጠት የበርካታ ሰዎችን ህይወት ለአደጋ አጋልጠዋል።
"በአቋራጭ ለመክበር በማሰብ ከድሃው ዜጋ ገንዘብ የሚሰበስቡ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል" ያለው ፖሊስ፤ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን በመከታተል ረገድ ህጋዊ እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል።
#ethiopia #addisababapolice #hellotaxi #scamalert #legalaction #transportnews #crimeupdate

8 months ago
" ስልክ የተሰረቀባችሁ ግለሰቦች በአካል በመቅረብ ስልካችሁን ለይታችሁ ውሰዱ " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ውድ ዋጋ ያላቸው ስልኮች ላይ ትኩረት በማድረግ የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ከ30 አይፎን ስልኮችን ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም. ሲ 5 መቶ ቤቶች አካባቢ አንድ ግለሰብ የዋጋ ግምቱ 100 ሺ ብር የሚያወጣ ኤስ 23 አልትራ ሳምሰንግ ሞባይል እንደተቀሙ ለሲ. ኤም.ሲ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ፡፡
ፖሊስ ጣቢያው የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ክትትል ያደርጋል። ወንጀሉ ከተፈፀመበት ስፍራ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ በሁለተኛው ቀን የግል ተበዳይን ሞባይል ስልክ የቀሙትን ምስጋናው አለማየሁ፣ ሄኖክ ወርቁ እና ኢዮብ ወርቁን የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያውላል።
በቀጣይነት በተሰራ ምርመራን የማስፋት ተግባር በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 አያት ዞን አምስት ኮንዶሚኒየም 3ኛ ፎቅ ላይ ምስጋናው አለማየው የተባለው ተጠርጣሪ ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ የግል ተበዳይን ስልክ ጨምሮ 41 ስማርት ስልኮች ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊድ ከዚህ በፊት ስልክ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ስልካቸውን እንዲለዩ ጥሪ አስተላልፏል።
አያይዞም ባሰራጨው መልዕክት መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራት የተከራዮችን ማንነት የማጣራት ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝቧል፤ ግዴታቸው በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስቧል።
#addisababapolice

Sponsored by
Surafel
9 months ago
ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ
ነገ ለ25ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ይካሄዳል። በዚህም ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።
ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-
- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
- ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
- ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
- ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
- ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
- ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
- ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
- ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
- ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ) ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ይዘጋሉ።
በተገለፁት መስመሮች ላይ ከዛሬ ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ፖሊስ አሳውቋል።
ለውድድሩ ተሳታፊዎች ፦ " ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ " ሲል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
ማሳሰቢያ ፦ ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳስቧል።
የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 0111110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም ይቻላል።
AddisAbabaPolice

10 months ago
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።
ነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ከሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አደርጓል።
በዚህም መሠረት ፦
- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣
- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣
- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣
- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣
- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣
- ከሐራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት፣
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣
- ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ፣
- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ ይዘጋል።
በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ተላልፏል።

11 months ago
በጥናት ላይ በተመሠረተ ኦፕሬሽን የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ሀሠተኛ ሠነዶችን ማዘጋጀት፣ ማሠራጨትና መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ህገ ወጥ ድርጊት የሚገቡ ግለሠቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተደረገም ይገኛል። በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጎማ ቁጠባ ፖሊስ ጣቢያ በክ/ከተማው ወረዳ 7 ቀጠና 1 አካባቢ ሀሠተኛ ሠነዶችን በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ የወንጀለኞች ጥናት አድርጓል።
ፖሊስ ጥናቱን መነሻ በማድረግና የፍርድ ቤት የቤት መበርበሪያና የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ
👉ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ፣
👉ፖስፖርት፣ የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎች፣
👉የ10ኛና የ12ኛ መልቀቂያ
👉የትግራይ ክልል መታወቂያ
👉የአማራ ክልል መታወቂያ
👉የየአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ፣
👉የተሽከርካሪ ቦሎ፣
👉የተለያዩ ሪሲቶች፣
👉የልደት ካርድ፣
👉ሊሰራ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ መታወቂያ፣
👉የፖለቲካ ጥገኝነት ለሚጠይቁ ግለሰቦች የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እነዚህኑ ሠነዶች ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው፦
👉1018 የተለያዩ ማህተሞች፣
👉1 ፕሪተር፣
👉1 ህትመት ማሽን፣
👉2 ላፕቶፕ ፣
👉2 ስካነር፣
👉1አጉሊ መነፅር፣
👉2 ማሸጊያ ማሽን፣
👉8ሲዲዎች፣
👉1 መጠረዣ፣
👉1የፖስፖርት ማሽን፣
👉11የማህተም መርገጫ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።
ህብረተሠቡ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛና ትውልድ ገዳይ መሆኑን ተረድቶ መሠል ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ተሳትፎውን እንዲያጎለብት የአዲሰ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ተቋማትም ሠራተኞችን በሚቀጥሩበት ወቅት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸው ላይ ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርጉም ጠቅላይ መምሪያው መልዕክቱን ያስተላልፋል።
Addisababapolice

12 months ago
የ4 ዓመት ህጻን ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ
#ethiopia | ፖሊስ የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቀጠና አራት እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው ብሏል።
ተጠርጣሪ መታደል ታደሰ በቤት ሰራተኝነት ነሀሴ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአቶ መልካሙ ረዳቴ እና በወ/ሮ መሠረት አየለ ቤት በአራት ሺህ ብር የወር ደመወዝ ተስማምታ ትገባለች። በኋላ በ10ኛ ቀኗ የቀጣሪዎቿን የአራት አመት ህፃን ዮሴፍ መልካሙ የተባለውን ይዛ ትሰወራለች።
የህፃኑ ወላጆች ልጃቸው እንደጠፋ ለፖሊስ ያመለክታሉ።
ፖሊስ የምርመራና ክትትል ቡድን በማደራጀት ባከናወነው የክትትል ስራ ተጠርጣሪ መታደል ታደሰ እና በወንጀሉ ተሳታፊ የሆነውን የትዳር አጋሯ መሠረት አየለን በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ ጫጫ ክፍለ ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ ፖሊስ ጋር ተባብሮ ይይዛቸዋል።
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ህፃኑን አግተው " 5 ሚሊዮን ብር ካላስገባችሁ ልጃችሁን በሕይወት አታገኙትም " በማለት እየተደራደሩ እያለ ነው ዛሬ ነሀሴ 17 ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ፖሊስ ታግቶ የነበረው ህፃን ዮሴፍ መልካሙን ከነ ሙሉ ጤንነቱ ለወላጆቹ ማስረከቡን ገልጿል። በተጠርጣሪዎቹም ላይ ቀጣይ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብሏል።
የህጻኑ ቤተሰቦች ተጠርጣሪዋን ያለ በቂ ተያዥ በእምነት ብቻ ወደ ቤታቸው እንዳስገቧት የገለጹ ሲሆን በዚህም ትክክል እንዳልነበሩ ተናግረዋል።
" ማንኛውም ሰው የቤት ሰራተኞችን ሲቀጥር በኛ የደረሰው እንዳይደርስበት በሕግ አግባብ መቅጠር ይኖርበታል " ሲሉም ተናግረዋል።

ቲክቶክን በመጠቀም ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ
ብቁጥጥር ስር ዋሉ
ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የከተማችንን ሠላም ለማወክ እና በህብረተሰቡ ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደማይታገስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ቲክቶክን በመጠቀም ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ከተማችን አዲስ አበባ ከወንጀል የፀዳች እንድትሆንና ዜጎች በሠላም ወጥተው በሠላም እንዲገቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የመዲናዋን ነዋሪዎች ባሳተፈ መልኩ ቴክኖሎጂ መር የሆኑ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን በማከናወን በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ዜጎች ሠላምና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን በተከናወኑ አመርቂ ስራዎችም ባሳለፍነው በጀት ዓመት በከተማዋ የወንጀል ምጣኔን በ43 በመቶ መቀነስ ተችሏል፡፡ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እጅ ከፍንጅ የመያዝ አቅሙን በማሳደግ እና ዜጎች በቀጥታ ለፖሊስ መረጃ የሚሰጡበትን መንገድ (የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ አፕሊኬሽን ) በማመቻቸት ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ፕላትፎርምን በመጠቀም የከተማችንን ሠላም ለማወክ እና በህብረተሰቡ ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር በተደራጀ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነም አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በክትትል ከደረሰባቸው መረጃዎች በተጨማሪ የህብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ እና በከተማችን ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር በማሰብ ቲክቶክን በመጠቀም የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያሰራጩ የነበሩ ኪሩቤል መላኩ ፣ አህመድ ሻሂር ፣ ምኺኤል አብይ፣ በረከት ዳንኤል እና አብዩ ደግአረገ የተባሉ አምስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
ይህንን የቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ስነ ልቦና ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ከነበሩት እና በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ክትትል እየተደረገባቸው ከሚገኙት መካከል አንዱ ብሩክ ተስፋዬ አርአያ የሚባል ግለሰብ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ይህ ግለሰብ ነዋሪነቱ በየካ ክ/ከተማ ሲግናል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲሆን ከዚህ ቀደም በህግ የተከለከለን "ካናቢስ" የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ቀርቦበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የዋስትና መብት ከተፈቀደለት በኋላ በቀጠሮ ቀን ሳይቀርብ ተሰውሮ በመቆየቱ ፍርድ ቤቱ በሌለበት ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛነቱን በማረጋገጥ በአንድ ዓመት ጽኑ እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ተከሳሹ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላም ራሱን በመሰወር በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) የቀጥታ ስርጭት በተደጋጋሚ ጊዜ ከህብረተሠቡ ስነ ልቦና ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን እያስተላለፈ የሚገኝ በመሆኑ ጭምር በፖሊስ እየተፈለገ ይገኛል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች የመዲናችንን ነዋሪዎች ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከቱና ድርጊቱ በቸልታ ከታለፈም ትልቅ አደጋ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ የድርጊቱን ፈፃሚዎች እንደማይታገስ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፤ መሠል እንቅስቃሴ በሚያደርጉ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ነን ባዮች ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።
Via Addisababapolice

Comments