26 days ago
"ጥፋት ሳናጠፋ ይቅርታ አንጠይቅም!"
የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ
#ethiopia | በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ምንም አይነት ወንጀል ስላልፈጸሙ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲፈቱ የቀረበላቸውን ሀሳብ አለመቀበላቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ወይም ሲፒጄ አስታወቀ።
ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ ሲሆኑ በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2023 የተያዙ ናቸው። ከዚያም በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰው የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ እንደገለጹት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች ታሳሪዎች በመለየትና በማስፈራራት መንግስት ያዘጋጀውን የይቅርታ ወረቀት ፈርመው ከእስር እንዲወጡ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ስራቸውን እንዲተዉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር። ነገር ግን ጋዜጠኞቹ ምንም ያጠፉት ጥፋት በሌለበት ሁኔታ ራሳቸውን እንደ ወንጀለኛ አድርገው መቁጠርና ማመንን ባለመቀበል የቀረበላቸውን ጥያቄ ፈፅመው ውድቅ አድርገውታል ብለዋል።
የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞቹን ለረጅም ጊዜ ካሰሩ በኋላ በፍርድ ቤት ማረጋገጥ ያልቻሉትን ወንጀል በግዴታ አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ የሚያደርጉትን አካሄድ ኮንነዋል።
አስተባባሪዋ አክለውም በጋዜጠኞቹ ላይ የሚፈጸመው ያልተገባ ጫና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የተመሰረተባቸው ክስ ተነስቶ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንዲሁም ሙያቸውን በነጻነት ማከናወን እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በሽብርተኝነት የተከሰሱ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የተለያዩ ግለሰቦች የይቅርታ ቅጽ እንዲፈርሙ መጠየቃቸው ተመልክቷል። ነገር ግን ከነዚህ መካከል 30 የሚሆኑ ተከሳሾች ጉዳያቸው ገና በህግ ሂደት ላይ እያለ ራሳቸውን ጥፋተኛ አድርገው እንደማይፈርሙ በመግለጽ ጥያቄውን አለመቀበላቸው ታውቋል።
መንግስት ለጋዜጠኞቹ ያቀረበው ጥያቄ የተለመደ የይቅርታ አሰራር እንደሆነ ቢገልጽም ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ግን በሃገሪቱ ሕግ መሰረት ይቅርታ ሊደረግ የሚችለው አንድ ግለሰብ በስርዓቱ ፍርድ አግኝቶ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።
የጋዜጠኞቹ የችሎት ጊዜ በተደጋጋሚ በመሰረዙ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ለኖቬምበር 19 ተቀጥሯል።
#journalism #pressfreedom #ethiopianews #cpj #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago
የሮይተርስ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ታግዶ የነበረው የሥራ ፈቃድ ታደሰ
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላለፉት ስድስት ወራት ታግደው የነበሩ የሦስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ ማደሱን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ከዓለም አቀፉ የዜና ተቋም ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ኒክ ታተር እና የአፍሪካ ኤዲተር ሲልቪያ አሎይሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት ተቋሙ ባለፉት ሰባት ወራት ያሰራጫቸው አንዳንዶቹ ዘገባዎች የሀገሪቱን ሕግ፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንዲሁም ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ያልጠበቁ እንደነበሩ የክትትል ውጤቶችን በማስደገፍ አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክቷ አክለውም የሮይተርስ ዘገባዎች ሚዛናዊነት፣ ትክክለኝነትና ተአማኒነት ጎድሏቸው ወደ አንድ ወገን ያደሉ እንደነበሩ በመጠቆም ለተፈጠሩት የሕግና የሙያ ጥሰቶች የዜና ተቋሙ አስፈላጊውን እርማትና ማስተካከያ ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
የሮይተርስ ኃላፊዎች በበኩላቸው ተቋማቸው ገለልተኛ መሆኑን በመግለጽ ዘገባዎችን ከአድልዎ በጸዳ መልኩ ለመሥራት ጥብቅ መመሪያዎችን እንደሚከተል አስረድተዋል።
አልፎ አልፎ ለተከሰቱ ስህተቶች ይቅርታ በመጠየቅ ማስተካከያ እንደሚያደርጉና የኢትዮጵያን ሕግ፣ ባህላዊ እሴቶችና ብሔራዊ ጥቅም አክብረው ለመሥራት እንደሚጉ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይም ታግዶ የቆየው የሮይተርስ ዘጋቢዎች ፈቃድ እንዲታደስ የተደረገ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለጋዜጠኞቹ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።
#reuters #ethiopiamedia #journalism #pressfreedom #ema #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
54 የሚዲያ ተቋማት፤ 461 ጋዜጠኞች የምክክሩን ሂደት እየዘገቡ ነው
#ethiopia | ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለመዘገብ ፍላጎት ኖሯቸው ከኮሚሽኑ ጋር ግንኙነት የፈጠሩ 54 የሚዲያ ተቋማት 461 ዘጋቢዎችን በጉባኤው ቦታ አሰማርተው የጉባኤውን ሂደት ለህዝብ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡
የሚዲያ ተቋማትን የዘገባ ተሳትፎ እና የመረጃ ተደራሽነትን በተመለከተ ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ሪፖርት እንዳመለከተው ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክሩ ከመካሄዱ በፊት በርከት ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአጋርነት ማጠናከሪያ መድረኮችን ከመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎችና ባለሙዎች ጋር አካሂዷል፡፡
በእነዚህ መድረኮች በተፈጠረው ግንዛቤና በተደረሰው መግባባት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በርካታ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መደላድል ከመፍጠሩ ባሻገር መረጃዎች በሙያዊና ሀገራዊ ሃላፊነት እንዲሰራጩ ማስቻሉን በዚሁ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡
ተሳትፎው ሁሉንም የመገናኛ ብዙሃን አይነቶች እንዳካተተ እንዲሁም የተቋማቱን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ባከበረ መልኩ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርጉበት ነፃነት በኮሚሽኑ በኩል የተረጋገጠ መሆኑንም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡
ኮሚሽኑ በምክክሩ ቦታ ተገኝተው እንዲሁም ከኮሚሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እና በስፍራው ከሚገኘ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን እየተጋሩ ለህዝብ እያደረሱ ላሉ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርቧል፡፡ ይህንን ተሳፎ እስከ ድህረ ምክክር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠይቋል፡፡
ህብረተሰቡ ወደ ምክክሩ ቦታ እየገቡ መረጃዎችን ተደራሽ ከሚያደርጉ መገናኛ ብዙሃንና ባለሙያዎች መረጃዎችን በማግኘት ከተዛቡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅም ኮሚሽኑ አስገንዝቧል፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ሪፖርት ያስደመጠው ከተለያዩ የዘርፉ ተቋማት ለተውጣጡና ኮሚሽኑን እየደገፉ ላሉ የሚዲያ ስራዎች አጋዥ አካላት ነው፡፡
#ethiopiannationaldialogue #mediacoverage #pressfreedom #ethiopia #journalism #nationalconsultation #mediainethiopia #informedcitizens #journalists #ethiopiannews

5 months ago
በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር ተፈጥሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር መፈጠሩን ገለጹ። ሆኖም ይህ ነጻነት ከሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ኃላፊነት ጋር ተጣጥሞ የመሄድ ክፍተት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ የለውጡን መንግሥት የመጀመሪያ እርምጃዎች የጠቀሱ ሲሆን፣ "የመጀመሪያው ሥራችን በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን መፍታት ነበር" ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ታግደው የነበሩ ብሎገሮች እና ድረ-ገጾች እንዲከፈቱ መደረጉን፣ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሚዲያ ስርጭቶች ላይ ይደረግ የነበረው የጃሚንግ (የሞገድ እገዳ) ሥርዓት መቅረቱን፣ በስደት የነበሩ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ወደ ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ መፈቀዱን፣ እንዲሁም ለሚዲያ ነጻነት እንቅፋት የነበረው የፀረ-ሽብር ሕግ እንዲሻሻል መደረጉን ዘርዝረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚዲያው ዘርፍ የታየውን የሽግግር ወቅት በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ሁኔታውን "ታስሮ እንደቆየ ጥጃ" በማለት ገልጸውታል።
"የታሰረ ጥጃ ሲፈታ ሁለት ባህሪያት ይታዩበታል፤ አንደኛው እንቅስቃሴ ስላልለመደ እግሩ እየተሳሰረ መቸገር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ያገኘውን ነጻነት በአግባቡ መቆጣጠር አቅቶት ዝም ብሎ በመዝለል ንብረት መስበር ነው" ብለዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በሚዲያው ዘርፍ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት ነጻነቱን በአግባቡ የማስተዳደር እና የሙያ ሥነ-ምግባርን የመከተል ክፍተት እንደታየባቸው ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን የሚዲያ አውዱ አሁንም ድረስ ከመረጃ አቅርቦት፣ ከገንዘብ እና ከተለያዩ ጫናዎች ጋር ተያይዞ እንከኖች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በመጨረሻም፣ ባለሙያዎች የተፈጠረውን የነጻነት ዕድል በመጠቀም ረገድ ራሳቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ አሳስበዋል።
"ሙያተኞች ሕግንና ሙያን እንዴት አጣጥመው እንደሚሠሩ ራሳቸውን መፈተሽ ይኖርባቸዋል" ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በሀይማኖት ከበደ
#ethiopia #mediafreedom #abiyahmed #journalismethics #pressfreedom #narrativebuilding

Sponsored by
Surafel
7 months ago
ሲፒጄ በኢትዮጵያ የታሰሩ ሴት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ (CPJ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ።
የሲፒጄ መግለጫ ጋዜጠኞች መስከረም አበራ እና ገነት አስማማው መሆናቸውን አስታውቋል።
ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ በሰሯቸው ዘገባዎች ሳቢያ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለሦስት ዓመታት ያህል በእስር ላይ ይገኛሉ።
ሁለቱ ጋዜጠኞች በመጪው ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የእነዚህ ጋዜጠኞች መታሰር በተለይ በፖለቲካና በግጭት ዙሪያ የሚዘግቡ ሴት ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅ የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ሲፒጄ ገልጿል።
ሙያዊ ዘገባዎችን እንደ ወንጀል የመቁጠር አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተቋሙ በጽኑ ተችቷል።
የሴት ጋዜጠኞች መታሰር በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ወደ ኋላ የሚመልስ መሆኑ ተመልክቷል።
በሙያው ላይ በተሰማሩ ሴቶች ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና እና የስራ ዋስትና ስጋት እንደሚፈጥር ሲፒጄ አስገንዝቧል።
ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፕሬስ ነፃነትና ለሴት ጋዜጠኞች መብት ክብር በመስጠት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጋዜጠኞቹን እንዲፈታ አሳስቧል።
#cpj #pressfreedom #ethiopia #journalismisnotacrime #meskereabber #genetasmamaw #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

8 months ago
🎙️ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ዝግጅቱን አጠናቀቀ!
🌍
#ethiopia | ለጋዜጠኞች የቪዛ፣ የባጅ እና የካሜራ መሳሪያዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ድጋፍ እየተደረገ ነው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን (EMA)፤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሔደዉን 39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ለሚዘግቡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የሚሰጡት ልዩ ድጋፎች:
ባለሥልጣኑ ከመደበኛው የቪዛ እና የመግቢያ ባጅ አገልግሎት በተጨማሪ፤ በተለይ ከውጭ ለሚመጡ ጋዜጠኞች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ ነው።
✅ ከቀረጥ ነፃ:
ጋዜጠኞች ይዘዋቸው ለሚገቡ የሙያ መሳሪያዎች (ካሜራ እና ፕሮዳክሽን እቃዎች) ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ እየተደረገ ነው።
✅ ቅንጅታዊ አሰራር:
ይህንን ለማሳለጥ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን እና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ለጉባኤው ሽፋን ለሚሰጡ አካላት መልካም የስራ ጊዜ እንመኛለን!
#ema #ausummit #mediasupport #ethiopia #pressfreedom #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

"ውሳኔው ይነሳ! የዋዜማ ሬዲዮ ፈቃድ ይመለስ!"
- የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#ethiopia | "ባለስልጣኑ የወሰደው እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ የሚዲያ ምህዳሩን በፍርሃት ይሞላል!"
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በዋዜማ ሬዲዮ ላይ ያሳለፈውን የሥራ ፈቃድ እግድ በተመለከተ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል።
የማኅበሩ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች:
🛑 እግዱን መቃወም:
ማኅበሩ ባለስልጣኑ በዋዜማ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በጽኑ የተቃወመ ሲሆን፤ የሚዲያ ተቋሙ ላይ የቀረበው "ሚዛናዊነት ይጎድለዋል" የሚለው ውንጀላ ከእውነታው የራቀ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
🛑 የመፍትሔ አግባብ:
ስህተቶች ቢኖሩ እንኳን በ "ሚዲያ ካውንስል" ደንብ መሰረት መታረም ሲገባቸው፤ ፈቃድ መንጠቅ ግን ለዲሞክራሲ ግንባታው ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሚፈጥር ጠቁሟል።
🛑 የሚዲያ አፈና:
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚዲያዎች ላይ የሚደረገው ጫና መጨመሩን ያወሳው መግለጫው፤ አሻም ቲቪ ከስራ ውጪ መደረጉን እንዲሁም ጋዜጠኞች (ዮናስ አማረ፣ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ተስፋለም ወልደየስ) ለእስር መዳረጋቸውን በማሳያነት ጠቅሷል።
ጥሪ:
ባለስልጣኑ ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤን እና የዋዜማ ሬዲዮ የስራ ፈቃድ ተመልሶ ወደ ስራ እንዲገባ ማኅበሩ ጠይቋል።
ምንጭ፡
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#wazemaradio #pressfreedom #ethiopia #aejc #mediarights #journalism

9 months ago
"እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል አይደለም፤ አሳዝኖናል!" - ዋዜማ ሬዲዮ
* "ክሱን ለተደራሲዎች እና ለታዛቢዎች የህሊና ፍርድ እንተዋለን"
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዋዜማ ሬዲዮን የሥራ ፈቃድ መመለሱን ተከትሎ፤ ጣቢያው በሰጠው ምላሽ በውሳኔው ማዘኑን ገልጿል።
ዋዜማ በመግለጫው ምን አለ?
1️⃣ ስለ ውሳኔው፡
ባለሥልጣኑ ባዘዘን መሰረት ፈቃዱን ብንመልስም፤ "እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል ነው ብለን አናምንም፤ አሳዝኖናልም" ብሏል።
2️⃣ ስለ ክሱ፡
ሀገርን ጥቅም ጎድቷል፣ ስነ-ምግባር ጥሷል ተብሎ ለቀረበበት ክስ፤ "ለኢትዮጵያ ሚዲያ ተደራሲዎች እና ታዛቢዎች የህሊና ፍርድ እንተዋለን" በማለት ምላሽ ሰጥቷል።
3️⃣ ቀጣይ እርምጃ፡
ጉዳዩን መርምሮ አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጥ እና ሌሎች ህጋዊ አማራጮችንም እንደሚከተል ጠቁሟል።
የባለሥልጣኑ ምክንያት ምን ነበር?
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በበኩሉ፤ ሚዲያው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ፣ ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው እና ሁከት ቀስቃሽ ዘገባዎችን በመስራቱ እንዲሁም የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ባለመቀበሉ እርምጃውን መውሰዱን መግለጹ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#wazemaradio #mediaauthority #response #ethiopia #pressfreedom #newsupdate

Comments