5 months ago
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ትላንት ምሽት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ፓርኩ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ስድስት የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን እንዲሁም ሰባት የህፃናት መጫወቻዎችን ያካተተ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ሰፊ አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶች፣ ስድስት ካፌቴሪያዎች፣ ሦስት አንፊ ቲያትሮች፣ ልዩ ልዩ መናፈሻዎች እና በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እውን የሆነው ግዙፍ ፕሮጀክት በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፓርኩ መሳካት በጋራ በመሆን ድንቅ ስራ ላከናወኑት ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#addisababa #lemikura #greendevelopment #riversidepark #ethiopianbroadcastingcorporation

6 months ago
"ታፍነናል" በማለት 300 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው የጠየቁት ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | በከተማችን አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ (የካ አባዶ) የሚኖሩ የ15 እና የ16 ዓመት ሴት ታዳጊዎች፣ ለስደት መሄጃ ገንዘብ ፍለጋ ሲሉ የፈጠሩት "የታፈንን" ድራማ በፖሊስ ክትትል ከሸፈ።
የክስተቱ ዝርዝር፦
ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት የወጡት ታዳጊዎች ሳይመለሱ ቀርተው፣ "300 ሺህ ብር ካልተላከ ገዳዮቹ ጉዳት ሊያደርሱብን ነው" በማለት ቤተሰቦቻቸውን አስጨንቀዋል።
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታዳጊዎቹ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ ተገኝተዋል። አራቱም ታዳጊዎችና የመኝታ ክፍል ያከራያቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ታዳጊዎቹ ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው ገንዘብ ለማግኘት ድርጊቱን እንዳቀነባበሩት ለፖሊስ ቃል ሰጥተዋል።
ልጆቻችሁ የት እንደሚውሉ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉና ምን እያቀዱ እንደሆነ የመከታተል ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።
ሆቴሎችና የመኝታ ቤቶች ለታዳጊዎች አልኮል ከመሸጥና ክፍል ከማከራየት እንዲቆጠቡ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ልጆቻችንን እንከታተል፤ ከስደትና ከጥፋት እንታደጋቸው!
#getu #addisababapolice #lemikura #teenagecrime #safetyfirst #ethiopianfamily #awareness #socialissue #አዲስአበባፖሊስ #ለሚኩራ #የልጆችጥበቃ #ማስጠንቀቂያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments