(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሂውማን ራይትስ ዎች አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማእቀብ እንዳታነሳ ጠየቀ፡፡ የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር የሆኑት ላቲቲያ ባደር ‹‹ካለፈው ወር አንስቶ የአሜሪካ መንግስት ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ለመመለስ እያሰበ ስለመሆኑ እየተሰማ ነው›› በማለት ገልፀዋል፡፡
ይህ ከሆነ ደግሞ የኤርትራ መንግስትና ወታደራዊ ሀይል በጎረቤት አገር ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በፈፀመው ከባድ የመብት ጥሰት የተጣለበትን ማእቀብ ማንሳትን ሊያካትት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ዳይሬከተራ በመግለጫቸው ‹‹በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ለተፈፀሙ ከባድ የመብት ጥሰቶች ተጠያቂነት በሌለበት ይህንን ማእቀብ ማንሳት ወደፊት ለሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችም ቁጥጥር እንዳይኖር የሚያመቻች ነው›› ያሉ ሲሆን በቀይ ባህር ኮሪደር ላይ የምትገኘው ኤርትራ በወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ አሁን ላይ ጠቀሜታዋ እየጎላ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
እንዲህ አይነት እርምጃ ለመውሰድ ያሰበችው አሜሪካ ብቻም ሳትሆን የአውሮፓ ህብረትና ካናዳ ጭምር ከስደትና ከልማት ጋር በተገናኘ ግንኙነታቸውን ለማደስ እየገመገሙ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ ጨምረውም ‹‹ዲፕሎማሲ ለአስርት አመታት የዘለቀውን የሰብአዊ መብት ጥሰትን ችላ ካለ ተጨማሪ ጥሰቶችን ሊያስከትል ይችላል›› ብለዋል፡፡
ላቲቲያ ባደር በመግለጫቸው እ.ኤ.አ ከ1993 አንስቶ የኤርትራ ፕሬዝደንት የሆኑት ኢሳያስ አፈወርቂ በአለም ላይ ካሉ ጨቋኝ መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ጠቅሰው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ፖሊሲያቸውን እንደቀጠሉበት፣ የጉልበት ብዝበዛ እንደሚያከናውኑና ሸሽተው ከአገር የሚወጡ ዜጎችን ቤተሰቦች እንደሚቀጡ አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም በመንግስት ላይ ትችት የሚያቀርቡን፣ የሀይማኖት መሪዎችንና ጋዜጠኞችን ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት ለአመታት ያህል ማሰራቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ አስከትለውም ‹‹ከ2020 እስከ 2022 በኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች የጅምላ ግድያ፣ አፈና፣ አስገድዶ መድፈርና ዝርፊያ ፈፅመዋል፡፡ አሁንም ቢሆን የኤርትራ ወታደሮች በያዙት የትግራይ ክፍል ውስጥ ግፍ እየፈፀሙ ይገኛሉ›› በማለት አስታውቀዋል፡፡ በማጠቃለያቸውም ‹‹ኤርትራ ከዚህ ቀደም ለፈፀመችውና አሁንም እየፈፀመች ላለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂት እስካላሰፈነች ድረስ አሜሪካ የጣለችውን ማእቀብ ማንሳት የለባትም›› በማለት አሳስበዋል፡፡

1 month ago