85ኛው የዐርበኞች ድል በዓልና የዘመኑ ዐርበኝነት
******************
የኢትዮጵያ ዐርበኞች ተጋድሎን ልዩ የሚያደርገው፣ በወቅቱ የማዕከላዊ መንግሥት መዋቅር ፈርሶ መሪው በስደት ላይ ቢሆኑም፣ የነጻነት ትግሉ ግን ባልተማከለ መልኩ ሳይቋረጥ መቀጠሉ ነው።
"መሪ አልባ" ይመስል የነበረው ተጋድሎ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለነጻነቱ ያለውን ቀናዒነት በተግባር ያሳየበት ነው።
ይህም የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሕዝብ ልብ ውስጥ ጭምር እንጂ በቢሮክራሲያዊ መዋቅር ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዳልሆነ አሳይቷል።
ለኢትዮጵያውያን፣ "ነጻነት" የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ከባዕድ ኃይሎች የሚሰጥ ስጦታ ሳይሆን፣ ከፈጣሪ የተቸረ እና በታሪክ ሂደት ውስጥ የጸና የማይገሰስ መብት ተደርጎ ይወሰዳል።
ዐርበኞቻችን መተኪያ የሌላት ሕይወታቸውን የገበሩትና ዱር ቤቴ ብለው የተንከራተቱት የነጻነትን ጣፋጭ ስሜት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው።
የዛሬው ትውልድ ይህን የድል በዓል ሲያከብር፣ የቀድሞ አባቶቻችን በደማቸው ነጻ ኢትዮጵያን እንዳስረከቡን ሳይዘነጋ፣ የዘመኑን ዐርበኝነት በመላበስ መሆን አለበት።
የዘመኑ ዐርበኝነት ደግሞ ድህነትና ኋላቀርነትን አሸንፎ የተሟላ ሉዓላዊነት ያላት ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሆነ መገንዘብ ይገባል።
ድህነት የሰው እጅ ያሳያል፤ የሌሎች ባሪያ ያደርጋል፤ ሰብዓዊ ክብርን ዝቅ ያደርጋል፣ ያስንቃል፤ ስለ ራሳችን ጉዳይ በራሳችን እንዳንወስን ያደርገናል።
እናም ይህን ጠላት በጋራ ዘምተን ማጥፋት እና ነጻነታችንን የተሟላ ማድረግ የዘመናችን ታላቁ ዐርበኝነት ነው።
ሙሉ ጽሑፉን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #patriotism #freedom #sovereignty #development #ebc

1 month ago