21 days ago
ሆርሙዝን ለማለፍ ክፍያ ግዴታ‼️
ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ አዲስ የትራፊክ ስርዓት እየዘረጋች መሆኑን አስታወቀች።
👉'የአገልግሎት ክፍያ ይፈፀማል ብላለች።
'ከኢራን ጋር የሚተባበሩ የንግድ መርከቦች እና ወገኖች ብቻ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ - የኢራን የደህንነት ኃላፊ አዚዚ ገልፀዋል።
የነፃነት ፕሮጀክት (Freedom project) እያሉ ለሚጃጃሉ (ለአሜሪካ) ሆርሙዝ ዝግ ሆኖ ይቆያል ብላለች።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከአሁን በርካታ መርከቦች በሆርሙዝ እንደቆሙ ነው።
seledadotio

1 month ago
u12a8u12d0u122du1260u129du1290u1275 u1260u120bu12ed u121du1295 u12a0u1208? | u12a8u122bu1235 u12c8u12f3u12f5u1290u1275 u12e8u1290u133bu12cd u12e8u12a0u1263u1276u127bu127du1295 u1273u120bu1245 u1218u1235u12cbu12d5u1275u1290u1275 #ethiopia #patriotism #freedom #sacrifice #nationalidentity #miyazya27 #africanhistory #sovereignty #u12a2u1275u12eeu1335u12eb #u12a0u122du1260u129du1290u1275 ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ከዐርበኝነት በላይ ምን አለ? | ከራስ ወዳድነት የነጻው የአባቶቻችን ታላቅ መስዋዕትነት #ethiopia #patriotism #freedom #sacrifice #nationalidentity #miyazya27 #africanhistory #sovereignty #ኢትዮጵያ #አርበኝነት
1 month ago
85ኛው የዐርበኞች ድል በዓልና የዘመኑ ዐርበኝነት
******************
የኢትዮጵያ ዐርበኞች ተጋድሎን ልዩ የሚያደርገው፣ በወቅቱ የማዕከላዊ መንግሥት መዋቅር ፈርሶ መሪው በስደት ላይ ቢሆኑም፣ የነጻነት ትግሉ ግን ባልተማከለ መልኩ ሳይቋረጥ መቀጠሉ ነው።
"መሪ አልባ" ይመስል የነበረው ተጋድሎ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለነጻነቱ ያለውን ቀናዒነት በተግባር ያሳየበት ነው።
ይህም የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሕዝብ ልብ ውስጥ ጭምር እንጂ በቢሮክራሲያዊ መዋቅር ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዳልሆነ አሳይቷል።
ለኢትዮጵያውያን፣ "ነጻነት" የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ከባዕድ ኃይሎች የሚሰጥ ስጦታ ሳይሆን፣ ከፈጣሪ የተቸረ እና በታሪክ ሂደት ውስጥ የጸና የማይገሰስ መብት ተደርጎ ይወሰዳል።
ዐርበኞቻችን መተኪያ የሌላት ሕይወታቸውን የገበሩትና ዱር ቤቴ ብለው የተንከራተቱት የነጻነትን ጣፋጭ ስሜት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው።
የዛሬው ትውልድ ይህን የድል በዓል ሲያከብር፣ የቀድሞ አባቶቻችን በደማቸው ነጻ ኢትዮጵያን እንዳስረከቡን ሳይዘነጋ፣ የዘመኑን ዐርበኝነት በመላበስ መሆን አለበት።
የዘመኑ ዐርበኝነት ደግሞ ድህነትና ኋላቀርነትን አሸንፎ የተሟላ ሉዓላዊነት ያላት ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሆነ መገንዘብ ይገባል።
ድህነት የሰው እጅ ያሳያል፤ የሌሎች ባሪያ ያደርጋል፤ ሰብዓዊ ክብርን ዝቅ ያደርጋል፣ ያስንቃል፤ ስለ ራሳችን ጉዳይ በራሳችን እንዳንወስን ያደርገናል።
እናም ይህን ጠላት በጋራ ዘምተን ማጥፋት እና ነጻነታችንን የተሟላ ማድረግ የዘመናችን ታላቁ ዐርበኝነት ነው።
ሙሉ ጽሑፉን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #patriotism #freedom #sovereignty #development #ebc

“ኢራን ከምድር ገጽ ትጠፋለች!” — ዶናልድ ትራምፕ
#ethiopia | በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ እየተባባሰ የመጣውን ወታደራዊ ውጥረት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን እጅግ አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ከፎክስ ኒውስ ጋዜጠኛ ትሬይ ይንግስት ጋር ቆይታ ያደረጉት ትራምፕ፣ የንግድ መርከቦችን በማጀብ ላይ ባሉ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ሀገሪቱ “ከምድር ገጽ እንድትጠፋ” ይደረጋል ሲሉ በከባድ ቃላት ዝተዋል።
ይህ የአሜሪካ ጠንካራ አቋም የመጣው ዋሽንግተን በስትሬቱ በኩል የሚያልፉ የነዳጅ እና የንግድ መርከቦችን በጦር መርከቦች የማጀብ (Project Freedom) ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ ነው።
ትራምፕ በንግግራቸው አሜሪካ በአሁኑ ወቅት እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀች መሆኑን በመጥቀስ፣ ማንኛውንም ትንኮሳ ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በዛሬው ዕለት ብቻ የአሜሪካ ባህር ኃይል ስድስት የኢራን የፈጣን ጥቃት ጀልባዎችን ማውደሙ የተነገረ ሲሆን፣ ይህም አካባቢውን ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊያስገባው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ምንም እንኳን ትራምፕ የኃይል እርምጃ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም፣ ኢራን በድርድር ረገድ የተሻለ አቋም እንድታሳይ ግፊት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት የፔንታጎን እና የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ሲሆን፣ ተጨማሪ መግለጫዎች እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #መናኸሪያfm #trump #iran #straitofhormuz #breakingnews #ethiopia #amharicnewsm

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ አንድ የፈጣን ምግብ መሸጫ ውስጥ ባጋጠመ የጥይት ጥቃት፣ ሶስት ኢትዮጵያውያን እና ሁለት ናይጄሪያውያን መገደላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት አስታወቁ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት፣ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያደረገችበትን እና የነፃነት ቀኗን (Freedom Day) በምታከብርበት ሚያዝያ 27 ቀን ነው።
ኢትዮጵያውያኑ ግድያው የደረሰባቸው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ "ማክዶናልድ" የፈጣን ምግቦች መሸጫ ውስጥ ምግብ በመመገብ ላይ ሳሉ መሆኑ ተገልጿል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት ወቅት መጤ ጠል አራማጅ ደቡብ አፍሪካውያን በስደተኞች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ እያስተላለፉ ባሉበት ወቅት መሆኑ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
ይሁን እንጂ አንድ የአገሪቱ ፖሊስ መኮንን ለተለያዩ አካላት በሰጡት መረጃ፣ ግድያው በኢትዮጵያውያኑ መካከል በነበረ መጠቃቃት ወይም አለመግባባት የተነሳ የተፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል።
ፖሊስ ስለ ጥቃቱ መንስኤና ስለ አጥቂዎቹ ማንነት ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።
ዘገባው የ DW ነው
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ደቡብ_አፍሪካ #ጆሃንስበርግ #ኢትዮጵያ #ዜና #southafrica #johannesburg #ethiopians #breakingnews

3 months ago
ኪም ጆንግ ኡን እና ልጃቸው በአዲሱ የጦር ታንክ ልምምድ ላይ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ታዳጊ ሴት ልጃቸውን ጁ ኤን አስከትለው አዲስ የተመረተውን ዘመናዊ የጦር ታንክ ሲያስመርቁና ሲያስፈትኑ ታይተዋል። የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን (KCNA) ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ታዳጊዋ ጁ ኤ አባቷ በቅርብ ርቀት ሆኖ እየተከታተላት የጦር ታንኩን በብቃት ስታሽከረክር ታይታለች።
የአዲሱ ታንክ ልዩ ባህሪያት
ይህ አዲስ ታንክ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ምን ያህል እንደገፋ የሚያሳይ ነው ተብሏል። ዋና ዋናዎቹም፦
* የላቀ የመንቀሳቀስ ብቃት፦ በማንኛውም አስቸጋሪ መሬት ላይ በፍጥነት መጓዝ የሚችል፤
* ከፍተኛ የተኩስ ኃይል፦ ኢላማዎችን በከፍተኛ ጥራት መምታት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀ፤
* የመከላከያ ዘዴ፦ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን የመመከት ልዩ አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የጊዜው ስልታዊ መልዕክት
ይህ ወታደራዊ ትርኢት በአጋጣሚ የተከናወነ አይደለም። አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ "Freedom Shield" የተሰኘውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ ባጠናቀቁ ማግስት የተደረገ በመሆኑ፣ ፒዮንግያንግ ለጠላቶቿ የሰጠችው ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተንታኞች ይገልጻሉ።
የጁ ኤ መገኘት ምን ያሳያል?
ታዳጊዋ ጁ ኤ በጦር ሜዳ ልምምዶች እና በከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅቶች ላይ በብዛት መታየቷ፣ የሰሜን ኮሪያ ቀጣይ መሪ ለመሆን እየተዘጋጀች እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣል። መሪው ኪም ጆንግ ኡን ልጃቸው በታንክ አሽከርካሪነት መቀመጫ ላይ ሆና ልምምድ ስታደርግ በኩራት ሲመለከቱ የሚያሳዩት ምስሎች፣ የቤተሰቡን የሥልጣን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው ተብሎ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ሰሜንኮሪያ #ኪምጆንግኡን #ጁኤ #የጦርታንክ #ወታደራዊልምምድ #ጂኦፖለቲካ #northkorea #kimjongun

ዐድዋ፡- የአፍሪካና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ብሩሕ ፋና!!
#ethiopia | ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ፣ የነጻነት አርበኛና የዓለም ሰላም ኖቤል ተሸላሚው፣ ኔልሰን ሮሂላላ ማንዴላ- የዐድዋ ድልን ፋይዳና ትሩፋት በተመለከተ፣ በአንድ ወቅት አፍሪካውያን መሪዎች በተገኙበት አንድ ትልቅ የስብሰባ መድረክ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፤
"The Adowa Victory provided practical expression to Ethiopianism: self-worth, dignity, unity, confidence, self-reliance, race pride, spirituality, and freedom from colonialism."
ዐድዋ- በሺህ ዘመናት ታሪኳና ቅርስዋ፣ ገናና ሥልጣኔዋና አኩሪ ባህሏ ለምትታወቀው፣ በነጻነቷና በሉዓላዊነቷ ጸንታ የኖረችውን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ዳግመኛ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ነው።
ዐድዋ የአፍሪካውያን፣ የአፍሪካ አሜሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት አለኝታ፣ የወኔና ስንቅ የሆነ፤ ሰው የመሆን ከፈጣሪ ዘንድ የተቸረ መለኮታዊ ፍቅርንና ክብርን ያላቀ ነው፡፡
በርግጥም ኔልሰን ማንዴላ በንግግራቸው ለመጥቀስ እንደሞከሩት ዐድዋ- ለኢትዮጵያዊነት ዝርግፍ ጌጥ፣ የተደነቀ ውበት፣ ሰው የመሆን ክብርንና የመንፈስ ልእልናን ያጎናጸፈ፣ ከዘረኝነት እኩይ እሳቤን የናደ፤ የቅኝ ግዛት ቀምበር እንዲሰበር ያደረገ አንፀባራቂ ድል ነው፡፡
ታሪክ እንደሚነግረን ጥቁር ሕዝቦች ለአፍሪካዊ ማንነታቸው፣ ታሪካቸው፣ ቅርሳቸው፣ ነጻነታቸውና ሉዓላዊነታቸው መከበርና ዕውን መኾን የአኅጉሪቷ እልፍ ልጆቿ ደም እንደ ጅረት ፈሷል፣ አጥንታቸውም ተከስክሷል፡፡
አፍሪካውያንና መላው ጥቁር ሕዝብ በሰስትና በናፍቆት የሚያስቡትና የሚያዩት አረንጓዴው፣ ቢጫውና ቀዩ ሰንደቀ ዓላማችን፣ በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ክቡር ደም መሥዋዕትነትና አጥንታቸው መከስከስ ያሸበረቀና ያንጸባረቀ ነው፡፡
ተወዳጇ ከያኒ እጅጋየሁ ሽባባው/ጂጂ ‹‹ዓድዋ›› በሚለው ተወዳጅ ዜማዋ ዜማዋ እንዲህ ብላ እንዳጎራጎረችው፤
"… የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፡፡
ስንት ወገን ወደቀ፣ በነጻነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፣
እንዴት እንደቆምኩኝ በፊታችሁ ዛሬ …፤"
ይህ ዛሬ በነጻነት የቆምንባት ምድር በብዙዎች፣ በእልፎች ክቡር ደም መሥዋዕትነት የጸና መኾኑን ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋው አይገባም፡፡ በእነዛ ጥቁር መኾን እንደ ወንጀልና ክህደት በተቆጠረበት አስከፊ ዘመን፤ ለጥቁር ሕዝቦች ከእንሰሳ ያነሰ ክብር እንኳን በተነፈገበት የአፍሪካችን የጨለማና እንደ መርግ የከበደ የመከራ ዘመኗ- አፍሪካውያን የሰው ልጅ ሕሊና ሊሸከመው የማይችል ውርደትና መከራን አሳልፈዋል፡፡
ለዘመናት በእንዲህ ዓይነት ውርደትና መከራ ጀርባዋ ለጎበጠው አፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ- እማማ ኢትዮጵያ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ በናፍቆትና በሰቀቀን የሚያስቧት፣ በዘላለም ቃል ኪዳን በልባቸው ጽላት የተጻፈች፣ የታተመች ከሩቅ አሻግረው የሚያይዋት አፍሪካዊት የነጻነት ቀንዲል፣ የነጻነታቸውና የሉዓላዊነታቸው የተስፋቸው፣ ምድር ነበረች፡፡
አገራችን ኢትዮጵያን በብዙዎች አፍሪካውያንና በመላው የጥቁር ሕዝብ ዘንድ የነጻነታቸው ተስፋና ብርሃን ተምሳሌት ሆና ከፍ ብላ እንደትታይ ያደረጓት በርካታ ታሪካዊ ሐቆች አሉ፡፡
ኢትዮጵያችን በሺሕ ዘመናት የሚለካው ታሪኳ፣ ጥንታዊና ገናና የኾነ ሥልጣኔዋ፣ ነጻነታቸውን አፍቃሪ ለኾኑ የዓለም ሕዝቦች ተምሳሌት የኾነው የልጆቿ የአይበገሬነት ጽኑ የነጻነት መንፈስ የሚጠቀስ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚነሣው አንጸባራቂው የዓድዋው ድል በግንባር ቀደምትነትና በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ይህ መላው አፍሪካ በባርነት ቀንበር ስር ወድቆ በሚማቅቅበት ዘመን፣ ከምሥራቅ አፍሪካዊቷ፣ ጥንታዊት አገር የተሰማው የድል ብስራት፣ ለአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ሊሰሙትና ሊቀበሉት የተናነቃቸው ታላቅ መርዶ ነበር፡፡
በ1888 ዓ.ም. ከሮማ ገሥግሦ፣ ቀይ ባሕርን አቋርጦ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጣው ኃይል በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ብርቱ ክንድ ተመቶ በታላቅ እፍረት ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ ያ አንፀባራቂ የዓድዋ ድልም በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍን ከፈተ፡፡
የዚህ ድል ዜማም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ከፍ ብሎ ተሰማ፡፡ በአውሮፓ የሚታተሙ ጋዜጦችም ድሉን አስመልክተው በፊት ገጾቻቸው ዘገቡ፡፡ ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ጣይቱ! የሚሉ የድል ብስራቶችና ዜናዎች በመላው ዓለም ናኙ፡፡
በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በካረቢያንና በጃሜይካ በዓድዋው የድል ስሜትና፣ በኢትዮጵያዊነት የነጻነት ተጋድሎ ሰሜት የተረገዙ ንቅናቄዎችም ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ዓድዋ የአፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንዲል ኾኖ ደምቆ፣ ፈክቶ አበራ፡፡ በባርነትና በቅኝ ግዛት ስር ኾነው የሚማቅቁ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦችም ከዓድዋው ድል በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማሰማት ጀመሩ፡፡
ሁጊንስና ጃክሰን የተባሉ አውሮፓውያን ምሁራን፤ An Introduction to African Civilizations with Main Currents in Ethiopian History, በሚል ርእስ ባስነበቡት መጽሐፋቸው እንደገለጹትም፤
"ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ ሰራዊት በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ኃይሎች ላይ የተጎነጸፉት ድል፣ ጥንታውያኑን ኢትዮጵያውያንን ዘመናት ያስቆጠረ ነጻነታቸውንና ሉዓላዊነታቸውን ዳግም በተግባር ያረጋገጠ ድል ነው፤" በማለት ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፤
እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆርጅ በርኬሌይ ደግሞ፤ "የዓድዋ ድል ቅኝ ገዢ ተስፋፊ የኾኑ አውሮፓውያን ቆም ብለው እንዲያሰቡ ያደረጋቸው አንጸባራቂ ድል ነው፡፡" በማለት ነበር የገለጸው፡፡
ዐድዋ በቅኝ ግዛት ስር ወድቀው ሲማቅቁ ለነበሩ ለአፍሪካውያንና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተስፋ ጮራን የፈነጠቀ፣ ለነጻነት ታጋዮች ትልቅ ወኔንና መነቃቃት የፈጠረ ድል ነው፡፡
ዐድዋ ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ብቻ ሣይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ- ሰው የመሆን ከፈጣሪ ዘንድ የተቸረን መለኮታዊ ፍቅርና ክብርን ከፍ ከፍ ያደረገ የድል፣ የነጻት ታላቅ ዓርማ ነው፡፡ ይህ የነጻት ድል በአፍሪካና በመላው ዓለም ሲሰማ፣ ዳግመኛ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በዓለም መድረክ አብቦ፣ ፈክቶና ደምቆ፣ ከፍ ከፍ ብሎ ታየ፡፡
ለመውጫ ያህል፤
የኬንያው የነፃነት ታጋይና ዐርበኛ ጆሞ ኬንያታ ለትምህርት እንግሊዝ አገር በነበሩበት ወቅት የዐድዋን ታላቅ የነጻነት መንፈስ በልባቸው የናኘውን ገጠመኝ እናስታውስ።
ነገሩ እንዲህ ነው። ጆሞ ኬንያታ በዩኒቨርስቲያቸው ቤተ-መጻሕፍት መደርደሪያ ላይ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚተርከው መጽሐፍ ውስጥ ያገኙትን የዳግማዊ ዐጤ ምኒልክን ፎቶ ወደ ደረታቸው አስጠግተው በማቀፍ፣ ዓይኖቻቸው በደስታና በሲቃ እንባ ተሞልቶ እንዲህ አሉ፤
"ኦ! ምኒልክ የአፍሪካና ጥቁር ሕዝቦች ኩራት፣ ኦ! ኢትዮጵያ የአፍሪካ ድል ብስራት፣ የነጻነታችን ተስፋ መሬት፣ የልባችን ኩራት… የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት ታላቁ ንጉሥ ምኒልክ ሁሌም አከብርዎታለሁ!!"
ሰላም!!
ፍቅር እና ክብር የነጻነትን ክቡድ እና ክቡር መንፈስ ከዐድዋ ተራሮች እስከ አፍሪካና ዓለም ጫፍ ድረስ በክብር ለናኙት የዐድዋ ጀግኖች እናቶቻችንና አባቶቻችን ሁሉ!!
ፍቅር እና ክብር የነጻነትን ሕያውና ክቡድ መንፈስ በደማችን ላሰረፁብን፣ ኢትዮጵውያን ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ሁሉ!!
© Terefe Worku

Sponsored by
Surafel
4 months ago
የዶላር ዳግም ልደት ወይስ የኢኮኖሚ ቁማር? የኢትዮጵያ “ቢግ ባንግ” ሪፎርም እና የነፃ ገበያ መገፋፋት
1. የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ፣ ዝም ብሎ የቴክኒክ ሰነድ አይደለም፤ ይልቁንም ላለፉት 50 ዓመታት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ደም ስር አንቆ የያዘውን “የቁጥጥር ሰንሰለት” የሚበጣጥስ መጥረቢያ ነው። ይህ 19 ነጥቦችን የያዘው አዋጅ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ አድርጋው የማታውቀውን የኢኮኖሚ “ቢግ ባንግ” (Big Bang) ሽግግር መጀመሯን ያበስራል። በኢኮኖሚ ፈላስፎች መነጽር ሲታይ፣ ይህ እርምጃ አዳም ስሚዝ “የማይታየው እጅ” (Invisible Hand) ብሎ የጠራውን ገበያ መር ስርዓት በኢትዮጵያ ምድር ለመትከል የተደረገ ደፋር ሙከራ ነው።
2. የዚህ ሪፎርም ዋነኛው መነሻ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር የተደረሰው የ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ቢሆንም፣ ውስጣዊ ፍላጎቱ ግን የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ረሃብ በዘላቂነት መፍታት ነው። ቀደም ሲል በኦፊሴላዊው የምንዛሪ ዋጋ እና በጥቁር ገበያው መካከል የነበረው ልዩነት (Premium) ከ 100% በላይ ማደጉ፣ ምርት ወደ ውጭ የሚላክበትን ሳይሆን ዶላር የሚሸሸግበትን ኢኮኖሚ ፈጥሮ ነበር። አዲሱ መመሪያ ይህንን “የጥላ ኢኮኖሚ” አፍርሶ፣ ዶላርን ከጓዳ ወደ ባንክ አደባባይ ለማውጣት የታለመ ነው።
3. የአገልግሎት ላኪዎች 100% ገቢያቸውን እንዲይዙ መፈቀዱ (አንቀጽ 1)፣ ከቲዮሪ አንጻር “የባለቤትነት መብት” (Property Rights) ማረጋገጫ ነው። ጆን ሎክ እንደሚለው፣ አንድ ሰው በጥረቱ ያገኘውን ሀብት የመጠቀም ሙሉ መብት ሊኖረው ይገባል። መንግስት ቀደም ሲል ከላኪዎች ላይ ይነጥቅ የነበረውን 50% እና ከዚያ በላይ ድርሻ መተዉ፣ ላኪዎች ይበልጥ እንዲያመርቱ ትልቅ ማበረታቻ (Incentive) ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በረዥም ጊዜ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
4. ግለሰቦች ለቤተሰቦቻቸው እስከ 3,000 ዶላር እንዲልኩ መፈቀዱ (አንቀጽ 8)፣ የመንግስትን የቁጥጥር ስፋት (State Scope) በእጅጉ ይቀንሳል። ይህ እርምጃ ሚልተን ፍሪድማን “Capitalism and Freedom” በሚለው መጽሐፉ የጠቀሰውን የግል ኢኮኖሚ ነፃነት የሚያንፀባርቅ ነው። ዜጎች በገዛ ገንዘባቸው የልጆቻቸውን ትምህርትና ህክምና እንዲከፍሉ መፈቀዱ፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ለዘመናት ተሸርሽሮ የነበረውን ማህበራዊ ውል (Social Contract) መልሶ የማደስ አቅም አለው።
5. ዳታዎች እንደሚያሳዩት፣ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከዳያስፖራ የምታገኘው ሬሚታንስ (Remittance) ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በህገ-ወጥ መንገድ ይዘዋወር ነበር። አዲሱ መመሪያ ዶላርን ያለ ሰነድ መመንዘር መፍቀዱ (አንቀጽ 7)፣ ይህን በጥቁር ገበያ የሚመላለሰውን ቢሊዮን ዶላር ወደ ህጋዊው ስርዓት የሚመልስ “መግነጢሳዊ ኃይል” ነው። ይህ የገንዘብ ፍሰት ወደ ባንኮች ሲገባ፣ ባንኮች ለኢንዱስትሪው የሚሰጡት የብድር አቅም (Liquidity) በእጥፍ ሊያድግ ይችላል።
6. የውጭ ኢንቨስተሮች ትርፋቸውን ያለ ገደብ እንዲያወጡ መፈቀዱ (አንቀጽ 16) ግን የሁለት ስለት ቢላዋ ነው። ለዴቪድ ሪካርዶ የንግድ ቲዮሪ ተከታዮች፣ ይህ እርምጃ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን (FDI) የሚስብ ማር ነው። ሆኖም፣ እንደ ጆሴፍ ስቲግሊዝ ያሉ ሊቃውንት “የካፒታል ሽሽት” (Capital Flight) ስጋትን ያነሳሉ። በሀገር ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቢከሰት፣ ኢንቨስተሮች ያላቸውን ዶላር ይዘው በአንድ ጀምበር ቢወጡ፣ የኢትዮጵያ የውጭ መጠባበቂያ ክምችት (Foreign Reserve) ድንገት ሊሟጠጥ ይችላል።
7. የባንኮች ራስ-ገዝነት (Autonomy) መጨመር ሌላው የዚህ ሪፎርም ምሰሶ ነው። ባንኮች የፎርዋርድ ግብይት (Forward Transaction) እንዲያካሂዱ መፈቀዱ (አንቀጽ 9)፣ ነጋዴዎች ለወደፊት ግዢዎቻቸው የምንዛሪ ዋጋን ቀድመው እንዲቆልፉ (Hedging) ይረዳቸዋል። ይህ በንግድ ዓለም ውስጥ ያለውን እርግጠኛ አለመሆን (Uncertainty) በመቀነስ፣ የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት የሚረዳ ዘመናዊ የፋይናንስ መሳሪያ ነው።
8. ይሁን እንጂ፣ ባንኮች ከካፒታላቸው 10% ዋስትና እንዲሰጡ መፈቀዱ (አንቀጽ 14) ልብ አንጠልጣይ አደጋ አለው። የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ቀውስ የመመታት ልምድ የላቸውም። ባንኮች የገቡት ዋስትና ተቀባይነት አጥቶ ወይም ብድሩ ሳይከፈል ቢቀር፣ የሀገር ውስጥ ባንኮች መክሰር (Bank Failure) ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በዜጎች ቁጠባ ላይ ትልቅ አደጋ ስለሚደቅን፣ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ዓይን (Supervision) እጅግ ንቁ መሆን አለበት።
9. የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ጥሬ ገንዘብ የመያዝ አቅማቸው ወደ 25% ማደጉ (አንቀጽ 18)፣ የገበያውን የዶላር ዝውውር (Circulation) ያቀልጠዋል። ይህ እርምጃ የጥቁር ገበያ ደላሎችን ከስራ የሚያስወጣ ቢሆንም፣ አዲሶቹ የፍቃድ ባለቤቶች ራሳቸው ወደ “ህጋዊ ደላላነት” እንዳይቀየሩ ጥብቅ ኦዲት ይፈልጋል። የገንዘብ ማጠብ (Money Laundering) ወንጀሎችን ለመከላከል የዲጂታል ክትትል ስርዓት የግድ ይላል።
10. የቬትናምን ተሞክሮ ብንመለከት፣ ሀገሪቱ በ 1980 ዎቹ መጨረሻ መሰል እርምጃ ስትወስድ፣ በአምራች ዘርፉ ላይ ትልቅ ስራ ሰርታ ነበር። ኢትዮጵያ ግን አሁንም 80% የምትጠቀመውን ሸቀጥ ከውጭ ታስገባለች። ዶላር በነፃነት መዘዋወሩ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፤ የምርት አብዮት ካልታከለበት፣ ነፃ ገበያው የውጭ ሀገራት ምርቶች መጣያ (Dumping ground) የመሆን አደጋ አለው።
11. የዋጋ ግሽበት (Inflation) የዚህ ሪፎርም ትልቁ ጠላት ነው። የምንዛሪ ዋጋው ለገበያ ሲተው፣ የብር ዋጋ መውደቁ አይቀሬ ነው። ይህ ደግሞ የመድኃኒት፣ የነዳጅ እና የፋብሪካ ጥሬ እቃዎች ዋጋን ሊያስንረው ይችላል። ኬይንስ እንደሚለው፣ በመካከለኛ ጊዜ ኢኮኖሚው ቢረጋጋም፣ “በመጨረሻ ሁላችንም እንሞታለን”። ስለዚህ ዝቅተኛው ማህበረሰብ በዚህ የሽግግር ወቅት በኑሮ ውድነት እንዳይቀጠቀጥ መንግስት የማህበራዊ ድጋፍ መረቦችን ማጠናከር አለበት።
12. 100 ዶላር የነበረው የሂሳብ መክፈቻ መቅረት (አንቀጽ 5)፣ ለድሃው ዜጋ የተሰጠ የኢኮኖሚ “ዲሞክራሲ” ነው። ይህም የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን (Financial Inclusion) በመጨመር፣ ህዝቡ በዶላር እንዲቆጥብና የሀገር ውስጥ ካፒታል እንዲያድግ ያደርጋል። ይህ የባህሪ ለውጥ (Behavioral Change) በረዥም ጊዜ የሀገሪቱን የቁጠባ ባህል ይቀይረዋል።
13. ድርጅቶች ከሀገር ውጭ መዋእለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ መፈቀዱ (አንቀጽ 6) ግን እጅግ አነጋጋሪ ነው። ኢትዮጵያ ራሷ የካፒታል እጥረት ባለባት ሁኔታ፣ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ዶላር ይዘው ወደ ውጭ እንዲወጡ መፈቀዱ በምን ስሌት እንደመጣ ግልጽ አይደለም። ይህ ነጥብ ባለሀብቶች ሀብታቸውን ወደ አስተማማኝ ሀገራት እንዲያሸሹ (Flight to Safety) በር ሊከፍት ይችላል።

የሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ
ሥራዋ በኢትዮጵያ ቤተመንግሥት ሲኒማ ቤት እየታየ ነው
#ethiopia | መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉ ኢምባሲዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው 200 እንግዶች ዘጋቢ ፊልሙን በመመልከት ላይ ናቸው
***
ስለ ዳይሬክተሯ
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden and the Writer)
ሳራ ዶላታባዲ (Sara Dolatabadi)
የፊልም ዳይሬክተር፣ የምስል ጥበብ ባለሙያ (Visual Artist) እና ጸሐፊ
ሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ እና የመልቲሚዲያ ፊልም ሰሪ ናት። በልጅነቷ የኢራን እስላማዊ አብዮት እና የኢራን-ኢራቅ ጦርነት በህይወቷ ላይ ተፅእኖ አሳድሮባታል። እነዚህን ታሪካዊ ክስተቶች በልጅነት አይኖቿ ተመልክታለች። እነዚህ ትዝታዎች በምስል ጥበብ ባለሙያነቷ እና በፊልም ሰሪነቷ ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሲሆን፤ ስራዎቿ የግል ሕይወት (Microcosm) እና የፖለቲካው ዓለም (Macrocosm) የሚገናኙበት ነጥብ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።
ከቴህራን አዛድ የስነ-ጥበብ ዩኒቨርሲቲ (Azad Art University) ከተመረቀች በኋላ፣ ለአሥር አመታት በቶኪዮ፣ ፓሪስ እና ኒው ዮርክ በመስራት እና ስራዎቿን ለእይታ በማቅረብ አሳልፋለች። በኒው ዮርክ በሚገኘው ሃንተር ኮሌጅ (Hunter College) በስነ-ጥበብ የማስተርስ ዲግሪዋን (MFA) አግኝታለች። ለድህረ-ምረቃ መመረቂያ ጽሁፏ፣ ስለ ቤተሰቧ የሚያወሳ "Summer Light" (የበጋ ብርሃን) የተሰኘ አጭር ዶክመንተሪ ፊልም ዳይሬክት አድርጋ አዘጋጅታለች።
በመቀጠልም "An Owl, A Garden and the Writer" (ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ጸሐፊው) የተሰኘውን ዶክመንተሪ ፊልም የሰራች ሲሆን፤ ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ2023 በቪዥን ዱ ሪል (Vision du Réel) ፌስቲቫል ላይ ለእይታ በቅቷል። ይህ ፊልም በቡሳን የፊልም ፌስቲቫል (Busan Film Festival) እና በሴንተር ፖምፒዱ ኤክስትራ ፌስቲቫልን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች እና ፌስቲቫሎች ላይ ታይቷል።
በተጨማሪም ፊልሙ በዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doc Lisboa) "የመብት እና ነጻነት ሽልማት" (Rights and Freedom Award) እንዲሁም በ2024 በሞንትሪያል በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ ፊልም ፌስቲቫል ላይ "ምርጥ የቁም-ምስል ሽልማት" (Best Portrait Award) አሸንፏል።
በጋቦን ለሦስት ዓመታት በቆየችበት ጊዜ በሊብሬቪል (ሲሲባ) ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች ትምህርትን ለማስፋፋት የሚሠራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) ከመሰረቱት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ትኖራለች፣ ትሰራለችም።
***
ስለ ሀበሻ ቪው (habeshaview)
በ2015 (እ.ኤ.አ) የተመሰረተው ሀበሻ ቪው (habeshaview)፤ ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ቨርጂኒያ ያደረገ ሲሆን፣ በእንግሊዝ ለንደን እና በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉት። በተጨማሪም በኔዘርላንድ የዳታ ማዕከል (Data center) እና የቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አለው።
ሀበሻ ቪው ዘርፈ-ብዙ የሚዲያ፣ የመዝናኛ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የኦቲቲ (OTT) ፕላትፎርም እና አፕሊኬሽኖችን በማልማት ደረጃውን የጠበቀ የመመልከት ልምድን ያቀርባል።
የሚያቀርባቸው አገልግሎቶችም የቀጥታ የዜና ቻናሎችን፣ የመዝናኛ ጣቢያዎችን፣ እንደ ፍላጎት የሚታዘዙ ፊልሞችን (Video On Demand)፣ ጨዋታዎችን እና የኦዲዮ ቻናሎችን ያካትታሉ።
በተጨማሪም ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ የተለያዩ ስቱዲዮዎች የተገኙ ኦሪጂናል የሆኑ ፕሮግራሞችን በብዙ የቋንቋ አማራጮች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያለፉ ፕሮግራሞችን መልሶ የመመልከት (catch-up service) አማራጭ ጭምር ያቀርባል።
ሀበሻ ቪው ከዚህም በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፊልም አከፋፋይ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተሰሩ ጥራት ያላቸውን እና ኦሪጂናል ፊልሞችን በመምረጥ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎች እና የሲኒማ ቤቶች በማቅረብ ያስተዋውቃል።
በረጅም ጊዜ እቅዱም ከአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሌሎች ይዘቶችን በማሰራጨት በፓን-አፍሪካ የመዝናኛ እና የስትሪሚንግ ኢንዱስትሪ መሪ ለመሆን ራዕይ ሰንቋል።
***
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት
የሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ (habeshaview Technology and Multimedia) ተባባሪ መስራች እንደመሆኔ፣ ሞቅ ያለ ሰላምታዬን ሳቀርብላችሁ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።
የጉዞአችን ተካፋይ ስለሆናችሁ እጅግ ደስ ብሎኛል። ዛሬ አዲሱን የስራ ዘርፋችንን "ሀበሻ ቪው ሲኒማ" (habeshaview Cinema) በምናስጀምርበት በዚህ ወቅት፣ እንኳን ወደ ደማቁ የመዝናኛ፣ የባህል እና የፈጠራ ዓለማችን በሰላም መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ። ይህ በየወሩ የሚካሄድ የፊልም ክበብ፤ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ከተቀረው ዓለም የተውጣጡ ፊልሞችን ለእይታ የሚያቀርብ ነው።
ትዕግስት ከበደ
ተባባሪ መስራች፣
***
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden, & The Writer)
የፕሬስ ማስታወሻ እና ሽልማቶች
"እጅግ ዜማዊ እና ረቂቅ፣ ሆኖም ግን ጉልበት ያለው ስራ፤ እጅግ ታላቅ የሆነውን የፀሃፊውን ስብእና ሰብአዊ በሆነ መንገድ እያሳየን፣ ስላለፉት አስርት ዓመታት የኢራን ጨካኝ ስርዓት የሚያስተምረን ፊልም ነው።"
— ቢዝነስ ዶክ ዩሮፕ (BUSINESS DOC EUROPE)
ፌስቲቫሎች እና ሽልማቶች
ቪዥንስ ዱ ሪል 2023 (Visions du Réel): በርኒንግ ላይትስ ውድድር (የዓለም የመጀመሪያ እይታ)
ፖምፒዱ ሴንተር (Pompidou Centre): (የፈረንሳይ የመጀመሪያ እይታ)
ቡሳን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2023 (Busan IFF): (ዓለም አቀፍ የመጀመሪያ እይታ)
ዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doclisboa): የመብት እና ነጻነት ሽልማት አሸናፊ
ኦዛ (OZA) የዘመናዊ ዶክመንተሪ ፊልም ፌስቲቫል 2024: የዳኞች ልዩ ሽልማት
ፊፋ 2024 (FIFA): ምርጥ የቁም-ምስል (Portrait) ሽልማት
ካርሎቪ ቫሪ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2021: በሂደት ላይ ያሉ ስራዎች (Works in Progress) የድህረ-ምርት ልማት ሽልማት አሸናፊ
አይዲኤፍኤ ፎረም (IDFA Forum)
የአዘጋጆች መግለጫ [አሚር ናደሪ - ዋና አዘጋጅ (Executive Producer)]
ኢራናዊው ፊልም ሰሪ አሚር ናደሪ፤ "ቬጋስ፡ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ" (2008)፣ "ማንሃተን በቁጥሮች" (1993) እና "ዘ ረነር" (1985) በመሳሰሉ ፊልሞቹ ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2016 በቬኒስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለዘመናዊ ሲኒማ ፈጠራ እና እድገት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ለሚሰጠው "Jaeger-LeCoultre Glory to the Filmmaker" የተሰኘ ክቡር ሽልማት ባለቤት ሆኗል።
"[የፊልሙ ባለታሪክ] በዘመናችን ካሉ እጅግ ታዋቂ ኢራናውያን ደራሲያን አንዱ ነው። በስራዎቹ የሀገሩን ልብ እና ነፍስ መተረክ ችሏል። በፋርስ ቋንቋ ንጹህ እና ጠንካራ ድምጽ ያለው ይህ ደራሲ፤ በልብ ወለዶቹ እና በታሪኮቹ ውስጥ የህዝቡን ታሪክ መዝግቦ አስቀምጧል። ስለሆነም፣ በተለይም አሁን ካለው የዓለም እና የኢራን ሁኔታ አንጻር፣ የእሱን ህይወት እና ስራዎች መዝግቦ ማቅረብ (Document ማድረግ) ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።"
***
ሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ
በሀበሻ ቪው፤ ለኢትዮጵያ ስነ-ጥበብ፣ ባህል እና ተሰጥኦ ትልቅ ቦታ እና ክብር አለን። ተልዕኳችንም ይህንን የባህል ሀብት ከዘመናዊ እና ከላቀ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ ለክቡራን ደንበኞቻችን ልዩ እና ተመስጦን የሚፈጥር ልምድ ማቅረብ ነው።
በባህል እና በዘመናዊነት መካከል ድልድይ መሆን እንዳለብን እናምናለን፤ የፈጠራ ባለሙያዎቻችንን ድንቅ ተሰጥኦ ለዓለም ገበያ በማሳየት የኢትዮጵያን ስራዎች ለዓለም አቀፍ መድረክ ለማብቃት እንተጋለን።
እስካሁን ያደረግነው ጉዞ እጅግ አስደናቂ ነበር፤ ይህ ስኬትም ያለ እናንተ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሊታሰብ አይችልም ነበር። አሻራችንን እያሰፋን እና እያደግን ስንሄድ፣ ለዋና እሴቶቻችን ጸንተን እንቆማለን።
እነዚህም፦ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ እና ማልማት፣ የሀገር ውስጥ ተሰጥኦን ማሳደግ፣ እንዲሁም የቅርሶቻችንን እና የባህላችንን ተደራሽነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጎልበት ናቸው።

7 months ago
መልህቁን የሚደግፉ ሌሎች ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር ጥያቄን ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት አንፃር ከዚህ በፊት አጭር ሀሳብ ማቅረቤ ይታወሳል።ሀሳቡን ይበልጥ ለማዳበር እና በተለይም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ምንም ግንዛቤ ሌላቸው ሰዎች ይረዳ ዘንድ ሌሎች ንድፈ-ሐቦች ምን ይላሉ የሚለውን ለመመልከት የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ወረቀቶችን እና (Article Review) ለማድረግ ሞክሪያለሁ፤እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪዩን አለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንደ አጠና ሰው በተጨማሪም የተለያዩ ከፍተኛ ሥልጠናዎችን፤አለምአቀፍ ጉዳዬችን እንደ ሚከታተል ባለሙያ በድጋሚ ሌሎች መልህቁን ሊደጋፉ የሚችሉ ህልዩቶችን ተመልክቻለሁ ።
እንደ አንድ ዜጋ የሀገር እና የብሔራዊ ጥቅም (National Interest )ጉዳይ ሲነሳ በምንም ሁኔታ እና አስተሳሰብ ወደ ጎን የሚተው ነገር እንዳልሆነ አምናለሁ።ይህ አጀንዳ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አማካኝነት በመንግስት ደረጃ መነሳቱ በዘላቂነት አጥተነው(በሆነ ዘመን) የነበረውን እድል እና ባለቤትነት በትውልድ ቅብብሎሽ መሳካቱ እንደማይቀር በማመን(በኢትዮጵያ ልጆች፥ለታላቁ ህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ ገንብተን እንደጨረስነው ሁሉ)ይህም የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ የሚጠይቅ እንደመሆኑ ታሪክ ስንመረምር ደግሞ የጥንት ስልጣኔዎች ከአክሱም(አዱሊስ)ጀምሮ የኢትዮጵያ መርከቦች በቀይ ባህርና ወደብ ናኝተውበታል።እኛ የጥንት ህዝቦች እና የአባቶቻችን ልጆች ነን ለዚህም እንደ ሀገር ልጅነት በጋራ እና በትብብር በመቆም መስራት ይጠበቅብናል።
በዛሬው አጭር ሀሳቤ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በማቅረብ ይበልጥ መረዳትን ለማሳደግ እና በተለይ በአንዳንድ የመረጃ ምንጮች የሚተላለፉ ጥሬ መረጃዎች በእውቀት እና በግንዛቤ ላይ ያልተመሰረቱ እና የተሳሳቱ መሆኑን ባደረኩት ቅኝት ለመረዳት ችያለሁ።
ዛሬ የምንመለከተው የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ህልዮቶች መሰረት በማድረግ እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች መልካምድራዊ አቀማመጥ እና የኢኮኖሚ ጥቅሞች በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ሚና መሰረት በማድረግ እንፈትሻለን:-( ሌሎች በመስኩ የምርምር ስራ የሰራችሁ ሊቃውንት ሀሳባችሁን ወደ መድረክ በልዩ ልዩ አማራጮች በማቅረብ ለሀገር እና ለብሔራዊ ጥቅም የሚደረጉ ጥረቶችን በእውቀትና ሳይንስ ተኮር በሆኑ አስረጂዎች በማቅረብ ለሀገር እና ለህዝብ ያላችሁን አጋርነት አሳዩ)። (የተረዳነውን እናስረዳ)
🔴.የባህር ኃይል ፅንሰ-ሀሳብ (Sea Power Theory/ Mahanian Thought):-ይህ ንድፈ-ሀሳብ የሚያጠነጥነው የሀገር ልማትናብልጽግ እንዲሁም ኃይል የሚወሰነው በባህር ላይ ባለ ቁጥጥር እና አጠቃቀም ላይ ነው ብሎ ያምናል።የባህር መንገድን መቆጣጠር እና ነፃ የባህር ላይ ንግድ ማካሄድ ለብሔራዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል።ይህ ንድፈ ሀሳብ ለጥያቄው በተለያ መንገድ ድጋፍ ይሰጣል።ኢትዮጵያ ለንግድ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ቀይ ባህርን መድረስ፣መጋራት መፈለጓ፣የባህር በር እንደ "ህልውና ጉዳይ"(Existential Matter) መታየቱ፣ይህ ንድፈ-ሐሳብ እንደሚደግፈው፣አንድ ሀገር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ለመፍጠር ተሰሚነትን ለማሳደግ የባህር ላይ አቅም (Sea Power) ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።
🔴.የሪምላንድ ፅንሰ-ሀሳብ (Rimland Theory - Spykman):-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ በአህጉር ዳርቻ የባህር ጠረፎችን(ሪምላንድን) የሚቆጣጠር ሀይል የአለምን እጣ ፈንታ ይወስናል የሚል እምነት አለው።የባህር ዳርቻ አካባቢዎች በየብስ እና በባህር ኃይሎች መካከል ድልድይ በመሆናቸው ስልታዊ ጠቀሜታ አላቸው የሚል እይታ አለው።አስረጅ ሲያቀርብ ቀይ ባህር ከአፍሪካ ቀንድ፣ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእስያ ጋር የሚያገናኝ "ወሳኝ የንግድ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ መስመር"(Chokepoint)በመሆኑ፣በዚያ አካባቢ ተሳትፎና እንቅስቃሴ ማድረጉ የኢትዮጵያን አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሚና ለማሳደግ ስልታዊ ጠቀሜታ አለው።
🔴.ጂኦ-ኢኮኖሚክስ(Geo-economics):-የዚህ ንድፈ ሀሳብ መነሻ የሀገሮች ተሰሚነት፣ስልጣንና ግንኙነት በዋነኛነት የሚወሰነው በኢኮኖሚ አቅማቸው እና ንግድን በሚጠቀሙበት መንገድ ነው።የንግድ መስመሮችን እና የገበያ ተደራሽነትን መቆጣጠር ከወታደራዊ ኃይል የበለጠ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል ይላል።ለኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር አቅርቦት ጥያቄን ሲያስረዳ ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና (As the gateway to the Suez Canal and Bab el-Mandab)፣ለኢትዮጵያ ነፃ የባህር በር ማግኘቷ የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ወደ ውጭ መላክን ለማሳደግ እና በሌሎች ሀገሮች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
🔴.ዓለም አቀፍ የህግ እና ትብብር ንድፈ-ሐሳቦች:-እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ትብብር እና የህግ ማዕቀፎችን አስፈላጊነት ያመለክታሉ።የዓለም አቀፍ ሊብራሊዝም እና ተቋማዊነት (International Liberalism and Institutionalism)ሀገሮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመመርኮዝ በትብብር (Cooperation) እና በዓለም አቀፍ ተቋማት (እንደ የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ኮንቬንሽን-UNCLOS) አማካኝነት ግጭቶችን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን ይችላሉ የሚል እይታ አለው ።
🔴.የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት (UNCLOS) እና የባህር-በር የሌላቸው ሀገራት መብቶች:-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ (በህጉ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ) ይህ ኮንቬንሽን (A landlocked Country) የተዘጉ ወይም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባህር የመድረስ መብት (Right of Access to and from the Sea) እና በጎረቤት ሀገራት በኩል በነጻ የመጓጓዝ መብት (Freedom of Transit) እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል (አንቀጽ 125-127)። ይህ መርህ ታዲያ የኢትዮጵያን ወደብ የመጠቀም ፍላጎት "በዓለም አቀፍ ህግ የተደገፈ" መሆኑን ያረጋግጣል።
✍️እንደ መውጫ ⁉️:-
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ "የባህር ኃይል እና የጂኦ-ኢኮኖሚክስ" ንድፈ-ሐሳቦች በሚደግፉት መሠረት ለብሔራዊ ጥቅም እና ህልውና ወሳኝ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ፣ "የሊብራሊዝም እና ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች" (እንደ UNCLOS) ይህንን ጥያቄ በሰላማዊ እና በትብብር መንገድ ለመፍታት መነሻ መሆን እንደሚችሉ ያመለክታሉ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

9 months ago
አሜሪካና አጋሮቿ ወደ ኒኩሊየር ጦርነት እየወሰዱኝ ነዉ ! /ሰሜን ኮርያ /
ደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን 'ፍሪደም ኤጅ' የሚል ስያሜ የሰጡትን ለአምስት ቀናት የሚቆይ የሶስትዮሽ ባለ ብዙ ጎራ ልምምዳቸውን ሰኞ እለት መጀመራቸውን ተከትሎ ሰሜን ኮርያ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቋ ተናገረ ።
ዮንሃፕ ወታደሩን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከመስከረም 15-19 የሚዘልቅ የሶስትዮሽ ልምምዶች በደቡብ ኮሪያ ደቡባዊ ደሴት ጄጁ ማካሄድ መጀመራቸውን ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ በዩናይትድ ስቴትስ በኒውክሌር ኃይል የሚንቀሳቀሱ ሚሳኤሎችን ልምምዱ ወደሚደረግበት የፍሪደም ኤጅ ደሴት ለማሴወንጨፍ እንደምትገደድና ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ በማስጠንቀቅ በሶስቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የጋራ ልምምድ በመቃወም ተቃውሞዋን አሰምታለች።
ዮንሃፕ እንደዘገበው ሀገራቱ በልምምዱ "ጠንካራ እና የተረጋጋ" የሶስትዮሽ ትብብርን ለማስቀጠል የእርስ በርስ ትብብራቸውን ለማሳደግ አላማ እንደሚያደርጉ የገለፁ ሲሆን የዩኤስ ኢንዶ-ፓሲፊክ ኮማንድን በመጥቀስ ልምምዱ “የኤሲያ-ፓስፊክን ሰላም በጋራ ለማሳካት እና ለማስጠበቅ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያሳያል” ብሏል።
'Freedom Edge' የባለስቲክ ሚሳኤልን የመከላከል አቅም፣ የአየር መከላከያ ልምምዶች፣ የህክምና መልቀቂያ ስልጠና እና የባህር ውስጥ ጣልቃገብነት ስልጠናን ለማሰልጠን ያለመ ስልጠና ይሰጣል።ተብሏል ።
ከሶስትዮሽ ልምምዶች በተጨማሪ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያን ስጋት ለመከላከል መደበኛ እና የኒውክሌር አቅምን በማቀናጀት "አይሮን ማሴ" የተባለውን የጠረጴዛ ልምምዶች በሚቀጥለው ሳምንት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ደቡብ ኮሪያ በአሁኑ ወቅት ወደ 28,500 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮችን ታስተናግዳለች።
" እስከ አርብ ድረስ የሚካሄደው የፍሪደም ኤጅ ልምምዱ የሰሜን ኮሪያን ተለዋዋጭ የኒውክሌር እና የሚሳኤል ስጋት ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት አቅሙን ለማጠናከር ነው" ሲሉ የጄሲኤስ የጋራ አለቆች ቃል አቀባይ ያንግ ሴንግ-ኳን ለመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም እሁድ እለት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተፅእኖ ፈጣሪ እህት ኪም ዮ-ጆንግ እቅዱን አውግዘዋል እና "ግዴለሽነት ጡንቻን ማወዛወዝ" መጥፎ ውጤቶችን እንደሚያመጣ አስጠንቅቀዋል ሲል ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ፓክ ጆንግ ቾን በኮሪያ ቋንቋ መግለጫቸው ላይ ሀገራቱን አስጠንቅቀዋል:- “ጠላቶች በጡንቻ መተጣጠፍ ከቀጠሉ፣ ተቃርኖአችን ይበልጥ ግልጽ በሆነና በተጠናከረ መንገድ እንደሚገለፅ አፅንዖት ሰጥቻለሁ። በራሳቸው ላይ መጥፎ ውጤት እንደሚያመጣ መገንዘብ አለባቸዉ ብለዋል ።
"IRON MACE እና FREEDOM EDGE ልምምዶች ከታቀዱበት ጊዜ ጀምሮ፣ የመስክ የታክቲክ እና ስልታዊ የኒውክሌር ሃይሎችን እየጎበኙ የሚገኙት ሰሜን ኮሪያ በኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው የሀገራቱ ጠባ አጫሪነት በዚህ ከቀጠለ ሀገራቸው ኒኩሊየር ለማስወንጨፍ እንደምትገደድ አበክረው ገልፀዋል ። ሲሉ ያስነበቡት ኮርያ ታይምስና ዮንሃፕ የዜና ወኪሎች ናቸዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments