9 days ago
ባህር ዳር ምን ታሳይን ይሆን?
ጁን 9 2022 ከአራት ቀናት በፊት ማላዊ ድረስ ሄዶ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ የነበረው ብሔራዊ ቡድናችን በጉዳት ምክንያት እነ ሞሃመድ ሳላህን ከስብስብ ውጪ ካደረገችው ግብፅ ጋር ጨዋታውን አደረገ። ልክ እንደ ዛሬው የሴኔጋል ጨዋታ ሁሉ—ባለፈው በሱዳን እንደተሸነፈችው—በወቅቱም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አብዛኛው ዓለም "ኢትዮጵያ የለመደችውን ሽንፈት ትቀምሳለች፤ ግብፅ ግብፅ ናት" ብለው ነበር የጠበቁት። ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ግብፅ ከኢትዮጵያ ሲገናኙ ማንም ያልጠበቃት ሀገራችን የመጀመሪያ ግቧን በአንበሳው ዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት ገና ጨዋታው እንደጀመረ በ20ኛው ደቂቃ ላይ አገኘች።
ደቂቃዎች ነጎዱ ዓለም ገና ከአሁኑ "ኢትዮጵያ ካገባች መስራውያን ውጤቱን ለመቀልበስ ይሰራሉ አለ። እነ ኡመር ማርሙሽ፣ ዚዞ እና ሞሃመድ ሙስጠፋን የመሳሰሉ ግብፃውያንን ስም እያነሱ "ኢትዮጵያ ተስፋ ቁረጪ፣ አንድ ጎል አያስተማምንም" እያሉ የሚሳለቁ አልጠፉም ነበር። ነገሩ ግን ፍጹም ሌላ ሆነ! ዓለም "ግብፅ ከመቼ ጀምሮ ቢጫ እና አረንጓዴ መለያ ማድረግ ጀመረች?" እያሉ እስኪገረሙ ድረስ ዋልያዎቹ ግብፅን በሜዳ ላይ መጫን ቀጠሉ።
ዓለም የቱ ግብፅ የቱስ ኢትዮጵያ እንደሆነ ግራ ተጋብቶ እያየ 30 ደቂቃዎችን ተሻገርን፤ አምበሉ ሽመልስ በቀለ ኢትዮጵያን በሁለት ግብ ልዩነት እንድትመራ አደረጋት። አሁንም የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪ በነገሩ ተገርሟል በዕለቱ ዕድለኛ ያልነበረው ብሔራዊ ቡድናችን ጨዋታውን በሁለት ጎሎች ብቻ አጠናቀቀ አቡበከር ናስር ያለቀላቸውን ኳሶች ባያመክን እንዲሁም ሌላ ግብ በኦፍሳይድ ምክንያት ባይሻር ኖሮ ሀገራችን ግብፅን ታሪካዊ ውርደት አከናንባት ነበር።
ታዲያ ያ ታሪክ ዛሬስ ይደገም ይሆን? ዛሬ ማክሰኞ በባህር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ምን እናይ ይሆን?
ዋልያዎቹ የ2022ቱን ተአምር ደግመው አፍሪካን የሚያስደምሙበት ምሽት እንዲሆን ምኞታችን ነው።
ግብፅን በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ስንገጥም ኮከባቸው ሳላህ አልነበረም!
ሴኔጋልን ዛሬ በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ስናገኛት ኮከቦቻቸው ማኔና ሳር የሉም!👀
@Bisrat_sport_433et

13 days ago
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች
የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ
ጆርጂያ 0-1 ሰሜን አየርላንድ
አርሜንያ 2-0 ላቲቪያ
ጣልያን 0-2 ቤልጂየም
ቱርክ 0-1 ፈረንሳይ
ሃንጋሪ 0-1 ዩክሬን
ፖላንድ 0-0 ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና
ሲዊደን 2-1 ሮማኒያ
ሞንቴኔግሮ 2-1 ሳይፕረስ
🌍 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ
ሞዛምቢክ 1-1 ሴኔጋል
ታንዛኒያ 0-2 ጊኒ ቢሳው
ኒጀር 2-1 ሌሶቶ
ጋምቢያ 2-1 ሶማሊያ
ማላዊ 2-1 ደቡብ ሱዳን
ናይጄሪያ 2-1 ማዳጋስካር
ሩዋንዳ 3-1 ላይቤሪያ
ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
ቶጎ 1-0 ቡሩንዲ
አልጄሪያ 3-1 ዛምቢያ
ቡርኪና ፋሶ 1-1 ቤኒን
ግብፅ 0-0 አንጎላ
ማሊ 3-1 ኬፕ ቨርዴ
ሞሮኮ 2-0 ጋቦን
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ጆርጂያ 0-1 ሰሜን አየርላንድ
አርሜንያ 2-0 ላቲቪያ
ጣልያን 0-2 ቤልጂየም
ቱርክ 0-1 ፈረንሳይ
ሃንጋሪ 0-1 ዩክሬን
ፖላንድ 0-0 ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና
ሲዊደን 2-1 ሮማኒያ
ሞንቴኔግሮ 2-1 ሳይፕረስ
🌍 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ
ሞዛምቢክ 1-1 ሴኔጋል
ታንዛኒያ 0-2 ጊኒ ቢሳው
ኒጀር 2-1 ሌሶቶ
ጋምቢያ 2-1 ሶማሊያ
ማላዊ 2-1 ደቡብ ሱዳን
ናይጄሪያ 2-1 ማዳጋስካር
ሩዋንዳ 3-1 ላይቤሪያ
ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
ቶጎ 1-0 ቡሩንዲ
አልጄሪያ 3-1 ዛምቢያ
ቡርኪና ፋሶ 1-1 ቤኒን
ግብፅ 0-0 አንጎላ
ማሊ 3-1 ኬፕ ቨርዴ
ሞሮኮ 2-0 ጋቦን
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
14 days ago
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ
01:00 | ጆርጂያ ከ ሰሜን አየርላንድ
01:00 | አርሜንያ ከ ላቲቪያ
03:45 | ጣልያን ከ ቤልጂየም
03:45 | ቱርክ ከ ፈረንሳይ
03:45 | ሃንጋሪ ከ ዩክሬን
03:45 | ፖላንድ ከ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና
03:45 | ሲዊደን ከ ሮማኒያ
03:45 | ሞንቴኔግሮ ከ ሳይፕረስ
🌍 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ
10:00 | ሞዛምቢክ ከ ሴኔጋል
10:00 | ታንዛኒያ ከ ጊኒ ቢሳው
12:00 | ኒጀር ከ ሌሶቶ
01:00 | ጋምቢያ ከ ሶማሊያ
01:00 | ማላዊ ከ ደቡብ ሱዳን
01:00 | ናይጄሪያ ከ ማዳጋስካር
01:00 | ሩዋንዳ ከ ላይቤሪያ
01:00 | ሱዳን ከ ኢትዮጵያ
01:00 | ቶጎ ከ ቡሩንዲ
04:00 | አልጄሪያ ከ ዛምቢያ
04:00 | ቡርኪና ፋሶ ከ ቤኒን
04:00 | ግብፅ ከ አንጎላ
04:00 | ማሊ ከ ኬፕ ቨርዴ
04:00 | ሞሮኮ ከ ጋቦን
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
01:00 | ጆርጂያ ከ ሰሜን አየርላንድ
01:00 | አርሜንያ ከ ላቲቪያ
03:45 | ጣልያን ከ ቤልጂየም
03:45 | ቱርክ ከ ፈረንሳይ
03:45 | ሃንጋሪ ከ ዩክሬን
03:45 | ፖላንድ ከ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና
03:45 | ሲዊደን ከ ሮማኒያ
03:45 | ሞንቴኔግሮ ከ ሳይፕረስ
🌍 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ
10:00 | ሞዛምቢክ ከ ሴኔጋል
10:00 | ታንዛኒያ ከ ጊኒ ቢሳው
12:00 | ኒጀር ከ ሌሶቶ
01:00 | ጋምቢያ ከ ሶማሊያ
01:00 | ማላዊ ከ ደቡብ ሱዳን
01:00 | ናይጄሪያ ከ ማዳጋስካር
01:00 | ሩዋንዳ ከ ላይቤሪያ
01:00 | ሱዳን ከ ኢትዮጵያ
01:00 | ቶጎ ከ ቡሩንዲ
04:00 | አልጄሪያ ከ ዛምቢያ
04:00 | ቡርኪና ፋሶ ከ ቤኒን
04:00 | ግብፅ ከ አንጎላ
04:00 | ማሊ ከ ኬፕ ቨርዴ
04:00 | ሞሮኮ ከ ጋቦን
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
1 month ago
በኢትዮጵያ ለበርካታ ዐሥርት ዓመታት በዋነኛ ማነቆነት የቆየውን የረጅም ጊዜ የቤት መግዣ ፋይናንስ እጥረት በዘላቂነት የሚቀርፍ እና ባንኮች ብድር በስፋት እንዲያቀርቡ የሚያስችል አዲስ "የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ" (Mortgage Refinance Company) ወደ ሥራ ሊገባ ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አደራጀው ሹመቴ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳብራሩት፣ ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት በሀገራችን የቤት ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ከፍተኛ ክፍተት ተፈጥሮ ቆይቷል።
ለዚህም የመሬት፣ የቴክኖሎጂ እና የግንባታ ግብዓት እጥረት በምክንያትነት ቢጠቀሱም፣ ዋነኛው ተግዳሮት ግን በቂ፣ ተመጣጣኝ እና ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር ነው።
የኢትዮጵያ ባንኮች ከደንበኞቻቸው የሚሰበስቡት ቁጠባ በአማካይ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ብቻ የሚቆይ በመሆኑ፣ ይህን የአጭር ጊዜ ተቀማጭ ይዘው ከ25 እስከ 30 ዓመት ለሚፈጅ የቤት ግዢ ብድር ሲያውሉት የጥሬ ገንዘብ እጥረት እና የጊዜ መጣረስ ያጋጥማቸዋል።
በዚህም የተነሣ ባንኮቹ የቤት ብድር ከመስጠት ሲታቀቡ፣ ቢሰጡም እንኳ በአማካይ 17.8 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ወለድ ስለሚያስከፍሉ፣ ሥርዓቱ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ያገለለ ነበር።
በዚህም ኢትዮጵያ ከማላዊ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ የቤት ወለድ ከሚያስከፍሉ ሀገራት ተርታ ተሰልፋ መቆየቷን ዶ/ር አደራጀው አስረድተዋል።
ይህን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ስምምነት የተቋቋመው አዲሱ ኩባንያ በቀጥታ ለግለሰቦች ብድር አይሰጥም።
ይልቁንም ለቤት ግዢ ብድር ለሚያቀርቡ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት፣ ያበደሩትን ብድር በመያዣነት በመውሰድ በጅምላ መልሶ ብድር የሚሰጥ "የአበዳሪዎች አበዳሪ" መሆኑን አማካሪው አብራርተዋል።
በመንግሥት እና በግል አጋርነት የሚቋቋመው ይህ ግዙፍ ተቋም፣ የባንኮችን የማበደር አቅም በማሳደግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ያደረጉትን የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ለማሳካት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
አዲሱ ሥርዓት ቋሚ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ተመጣጣኝ የቤት ብድር ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር፣ መንግሥት አስፈላጊውን የወለድ እና የቅድመ ክፍያ ድጋፍ እንዲሁም የብድር ዋስትና እንዲያቀርብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
ከዚህም በተጨማሪ ተቋሙ የሀብት ምዝገባን፣ የንብረት ግመታን እና የዋስትና አፈጻጸምን በማዘመን በዘርፉ ሰፊ መነቃቃትን የሚፈጥር ሲሆን፣ ከካፒታል ገበያው ጋር ተያይዞ ትልቅ የኢንቨስትመንት መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል በቃለ-ምልልሱ ተጠቁሟል።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #housing #mortgagefinance #ifcethiopia #development #economicgrowth #ebc

2 months ago
የዲኤንኤ ምርመራ ካደረጉ አባቶች አብዛኞቹ የልጆቻቸው ባዮሎጂካዊ አባት አለይደሉም
#ethiopia | በማላዊ በትዳር አጋሮቻቸው ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸው የዲኤንኤ ምርመራ ያደረጉ ወንዶችን አስመልክቶ የወጣው መረጃ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
በሀገሪቱ የዘር ፍሬ ምርመራ ካደረጉት ጥርጣሬ ያደረባቸው ወንዶች መካከል 80 በመቶ ያህሉ የልጆቹ እውነተኛ አባቶች አለመሆናቸው ተገልጿል።
ይህ ይፋ የሆነው አኃዝ በብዙ ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትንና ክርክርን ጭሯል።
ነገር ግን ይህ ስታቲስቲክስ የሚያመለክተው ቀድሞውኑ ጥርጣሬ አድሮባቸው ወደ ምርመራ ተቋማት የሄዱትን ወንዶች ብቻ ነው።
በመሆኑም መረጃው በጠቅላላው በማላዊ የሚገኙ አባቶችን ሁኔታ የሚያንጸባርቅ እንዳልሆነና የሁሉም አባቶች እውነታ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት ባለሙያዎች ያብራራሉ።
#malawi #dna #dnatest #africa #africanews #family #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የካሜሩን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ ዋንጫ በመክበብ አዲስ ታሪክ አስመዘገበ
#ethiopia | በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ውድድር ካሜሩን አዲስ አቅጣጫ ይዛ የቀረበችውን የማላዊ ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ በታሪኳ የመጀመሪያውን የዋንጫ ድል አግኝታለች።
በጨዋታው ወቅት ማሪ ንጋህ ማንጋ በግንባር በገጨቻቸው ሁለት ግቦች ቡድኗን መሪ ማድረግ የቻለች ሲሆን፣ ናኦሚ ኢቶ ደግሞ ሶስተኛዋን ግብ ከመረብ በማሳረፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች።
ናኦሚ ግብ ከማስቆጠሯም ባሻገር ለሌላኛው ግብ መገኘት ተገቢውን ድጋፍ አድርጋለች።
በዚህ ጨዋታ ላይ ድንቅ የእግር ኳስ ማSkill ያሳየችው ማሪ ንጋህ ማንጋ ያስቆጠረቻቸውን ሁለት ግቦች ጨምሮ በውድድሩ ላይ ያላትን አጠቃላይ የግብ ብዛት ወደ 5 ከፍ ማድረግ ችላለች።
ካሜሩን ከዚህ ቀደም ሶስት ጊዜያት ያህል ለፍጻሜ ውድድር ደርሳ በናይጄሪያ ተሸንፋ የነበረ ቢሆንም፣ በዘንድሮው አራተኛ ሙከራዋ የተመኘችውን ታሪካዊ ድል ለመቀናጀት በቅታለች።
በጨዋታው የማላዊዎቹ ተጫዋቾች ታቢታ ቻዊንጋ እና ተምዋ ቻዊንጋ የካሜሩንን የተከላካይ መስመር በተደጋጋሚ ለማስጨነቅ ቢሞክሩም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።
ይህን ታሪካዊ የፍጻሜ ጨዋታ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኢቶ በስታዲየም ተገኝተው ተከታትለውታል።
#cameroon #malawi #caf #football #womensfootball #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹ከደቡብ አፍሪካ የተባረሩትን ጋናዊያን በተመለከተ የምንጠየቀው ገንዘብ የለም›› ሲል የጋና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፀ፡፡ የጋና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ በቅርቡ መጤ ጠል በሆነ ጥቃት ከደቡብ አፍሪካ የተመለሱትን ዜጎቹን በተመለከተ ማንም ገንዘብ መጠየቅ እንደማይችል አስታወቀ፡፡ ከቀናት በፊት የደቡብ አፍሪካ መንግስት ከአገሩ ያባረራቸውን የውጭ አገር ዜጎች በተመለከተ ያወጣውን የመቆያና የትራንስፖርት ወጪ ከአገራቸው እንደሚቀበል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ወጪም ወደ18 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የገለፀ ሲሆን ይህንን ገንዘብ እንዲከፍሉት ለኢትዮጵያ፣ ለማላዊና ለናይጄሪያ ጥያቄ ማቅረቡን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ በዚህ ጥያቄ ላይ ስሟ ያልተካተተው ጋና በመግለጫዋ ‹‹የአገራችንን ዜጎች ለማስወጣት ከደቡብ አፍሪካ የገንዘብ ወይንም የቁሳቁስ ድጋፍ አንፈልግም›› ካለች በኋላ ደቡብ አፍሪካ ለሌሎች አገራት ያቀረበችውን ጥያቄ እንደማታቀርብላት ገልፃለች፡፡
የጋና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመግለጫው ጋናዊያንን ወደአገራቸው ለመመለስ የተደረገው እንቅስቃሴ በሙሉ በጋና መንግስትና በአጋሮቿ የተደገፈ መሆኑን አስታውቆ ደቡብ አፍሪካ ምንም የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አለማድረጓን አስታውቋል፡፡ ጋናዊያንን ከደቡብ አፍሪካ ለማስወጣት በሚል ያወጣውን ገንዘብ በዝርዝርም አቅርቧል፡፡

የካሜሩኗ ግብ ጠባቂ ሚካኤሊ ኪሪያ ቢሂና በ2026 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ደምቀው ከወጡ ታላላቅ ኮከቦች አንዷ ሆናለች
#ethiopia | የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው የወቅቱን አሸናፊ የናይጄሪያን ብሔራዊ ቡድን1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፎ ከውድድር ውጪ ሲያደርግ ሚካኤሊ ቢሂና ድንቅ ብቃቷን አሳይታለች።
በግማሽ ፍጻሜው ከአስተናጋጇ ሞሮኮ ጋር በተደረገው ጨዋታ ሌላ አስደናቂ ብቃት ማሳየት ችላለች።
ጨዋታው በመደበኛውና በተጨማሪው ደቂቃ ያለ ምንም ግብ በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት ካሜሩን፣ ሞሮኮን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ቢሂና በጭማሪው ደቂቃ ላይ ሞሮኮ ያገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት ከማዳኗም በላይ አሸናፊውን ለመለየት ከተሰጡት የፍጹም ቅጣት ምቶች ሦስቱን በማዳን ብቃቷን አሳይታለች።
የግብ ጠባቂዋ አስደናቂ ተጋድሎ ካሜሩንን ወደ 2026ቱ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እንድትደርስ ያስቻላት ሲሆን፤ በፍፃሜውም ካሜሮን ከማላዊ አቻዋ ጋር ይገናኛሉ።
የበ22 ዓመቷ ቢሂና በውድድሩ ባሳየችው ብቃት የግርኳስ ቤተሰቡን ቀልብ መሳብ ችላለች።
በሂና በዚህ ብቃቷ ከቀጠለች ሞሮኮ እያስተናገደች ያለችው የ2026 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ግብ ጠባቂ የመሆን እድሏንም ከፍተኛ ነው ተብሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

ደቡብ አፍሪካ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመመለስ ያወጣችውን ወጪ ኢትዮጵያ እንድትከፍል ጠየቀች‼️
ደቡብ አፍሪካ በተያዘው ዓመት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ካወጣችው ከ18 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተወሰነውን ወጪ እንዲሸፍኑ ለኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ማላዊ ጥያቄ አቀረበች።
የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄው መቅረቡን ይፋ ያደረገው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፓርላማው የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ወቅት ነው።
የቋሚ ኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር ቶሚ ማኮዴ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ለዚህ ተግባር ቀደም ሲል የመደበው በጀት 60 ሚሊዮን ራንድ ብቻ ቢሆንም፣ እስካሁን 292 ሚሊዮን ራንድ ስደተኞችን ለመመለስ ወጪ አድርጓል።
ማኮዴ ስደተኞችን የመመለስ መርሃ-ግብር «በጀት ያልተያዘለት ኃላፊነት» መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ ያህል ሰፊ እንቅስቃሴ በጀት እንዳልመደቡ ተናግረዋል።
አክለውም የትራንስፖርት ክፍያው ወጪው ከፍተኛ እንዲሆን ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
Seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የደቡብ አፍሪካ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደአገራቸው ላባረራቸው ዜጎች ያወጣው ወጪ እንዲከፈለው ጠየቀ፡፡ የደቡብ አፍሪካ ድንበር አስተዳደር ባለስልጣን እንደገለፀው በዚህ አመት ወደ90,000 ያህል ሰዎች ወደአገራቸው እንዲባረሩ ከተወሰነባቸው በኋላ የአገሪቱን ድንበር አልፈው ሄደዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 83,000 ያህሉ በምእራባዊ ጆሀንስበርግ በሚገኘው ሊንዳላ የተመላሾች ማእከል በኩል ህጋዊ ሰነድ እንደሌላቸው ተረጋግጦ እንዲመለሱ የተደረጉ መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡ ይሁንና በዚህ ሂደት ውስጥ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደአገራቸው ለመመለስ ከያዘው በጀት ውስጥ በአምስት እጥፍ የበለጠ ለማውጣት መገደዱን አስታውቋል፡፡ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቶሚ ማክሆዴ ዛሬ ለደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ባቀረቡት ማብራሪያ ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደአገራቸው ለመመለስ ወደ300 ሚሊየን ራንድ ወጪ ማድረጋቸውን ገልፀው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተመላሾች የማላዊ ዜጎች እንደሆኑና በተከታይነት የዚምባቡዌና የሞዛምቢክ ዜጎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡
ባለፈው አመት ወደአገራቸው የተባረሩት ሰዎች ቁጥር 44,607 መሆኑን አውስተውም ዘንድሮ ቁጥሩ በእጥፍ እንደጨመረ ገልፀዋል፡፡ ለመስሪያ ቤታቸው ስደተኞችን ወደአገራቸው ለመመለስ በሚል የተያዘለት በጀት 60 ሚሊዮን ራንድ እንደሆነ የጠቀሱት ሚኒስትሩ ነገር ግን በዚህ አመት 292 ሚሊዮን ወጪ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ ወጪው በአብዛኛው የተመላሾችን የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን እንደዋለና የተወሰነው ደግሞ ከኢሽዋኒና ኬፕታውን ከተሞች ስደተኞቹን በአውቶቡስ ለማጓጓዝ እንደዋለም ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በሙሲሀ ለተገነባውና 20,000 ሰዎችን መያዝ ለሚችለው አዲስ የተመላሾች ማእከል 48 ሚሊዮን ራንድ ማውጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ በማጠቃለያቸውም ‹‹የማላዊ፣ የኢትዮጵያና የናይጄሪያ መንግስታት ዜጎቻቸውን ለመመለስ ያወጣነውን ወጪ ሊከፍሉን ይገባል›› ያሉት ሚኒስትሩ ይህ ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙት የእነዚህ አገራት ኤምባሲዎች መቅረቡን አስረድተዋል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኦገስት 1 ቀን 2026 ጀምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ 25 የአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች የሚሰጠውን መደበኛ የቪዛ ማስተናገጃ አገልግሎት ማቋረጡን አስታውቋል። የትራምፕ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ በቅርብ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ የቪዛ አገልግሎቶች ትልቁ የማሻሻያ መርሃ ግብር ሲል ገልጾታል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት የቪዛ አመልካቾች ከዚህ በኋላ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቀጠሮ መያዝም ሆነ የቪዛ ሂደታቸውን ማጠናቀቅ አይችሉም። ከዚህ ይልቅ በአህጉሪቱ ወደተመደቡ 20 ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት እንዲያቀኑ ይደረጋል።
የቪዛ አገልግሎታቸው የተቋረጠባቸው 25ቱ ሚሲዮኖች አቡጃ (ናይጄሪያ)፣ አንታናናሪቮ (ማዳጋስካር)፣ አስመራ (ኤርትራ)፣ ባማኮ (ማሊ)፣ ባንጁል (ጋምቢያ)፣ ብራዛቪል (የኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ቡጁምቡራ (ብሩንዲ)፣ ኮናክሪ (ጊኒ)፣ ኮቶኑ (ቤኒን)፣ ደርባን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ፍሪታውን (ሴራሊዮን)፣ ጋቦሮኔ (ቦትስዋና)፣ ሃራሬ (ዚምባብዌ)፣ ጁባ (ደቡብ ሱዳን)፣ ሊብረቪል (ጋቦን)፣ ሊሎንግዌ (ማላዊ)፣ ሉሳካ (ዛምቢያ)፣ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)፣ ማሴሩ (ሌሴቶ)፣ ምባባኔ (ኤስዋቲኒ)፣ ንጃሜና (ቻድ)፣ ኒያሜይ (ኒጀር)፣ ኑዋክሾት (ሞሪታኒያ)፣ ዋጋዱጉ (ቡርኪና ፋሶ) እና ዊንድሆክ (ናሚቢያ) ናቸው። በደቡብ አፍሪካ ደርባን የሚገኘው የቪዛ ማዕከል ቢዘጋም፣ በኬፕታውን የሚሰጠው ተመሳሳይ አገልግሎት ግን ሳይቋረጥ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
20ዎቹ አዳዲስ ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት በአቢጃን፣ አክራ፣ አዲስ አበባ፣ ኬፕታውን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ዳካር፣ ዳሬሰላም፣ ጅቡቲ፣ ጆሃንስበርግ፣ ካምፓላ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሌጎስ፣ ሎሜ፣ ሉዋንዳ፣ ማላቦ፣ ሞንሮቪያ፣ ናይሮቢ፣ ፖርት ሉዊስ፣ ፕራያ እና ያውንዴ የሚገኙ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ማዕከል በርካታ ጎረቤት ሀገራትን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ለምሳሌ ከማሊ የሚመጡ አመልካቾች በዳካር (ሴኔጋል)፣ እንዲሁም ከቤኒን እና ኒጀር የሚመጡት ደግሞ በሎሜ (ቶጎ) የቪዛ ሂደታቸውን እንዲያከናውኑ ይመራሉ።
ሚኒስቴሩ ውሳኔውን የትራምፕ አስተዳደር ብሔራዊ ደህንነትን ለማጠናከር፣ የማጣራት ሂደቶችን ወጥ ለማድረግ፣ የመንግስት ወጪን ለመቀነስ እና የአሰራር ቅልጥፍናን ለማሻሻል ከሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን አብራርቷል። ተመሳሳይ የውህደት ስራዎች በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና በአውሮፓ ክፍሎች ቀደም ሲል መከናወናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ብሔራዊ ደህንነትን በማጠናከር እና የመንግስትን ብክነት በመቀነስ አሜሪካን እና አሜሪካውያንን እያስቀደሙ ነው ብሏል።
ይህ ማሻሻያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የቪዛ ማመልከቻዎችን የሚያስተናግዱ የአሜሪካ ሚሲዮኖችን ቁጥር ከ50 ገደማ ወደ 20 ዝቅ ያደርገዋል። ይህ በአመልካቾች ላይ ጉልህ የሆነ ተግባራዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን፣ የአገር ውስጥ የቪዛ አገልግሎት በተቋረጠባቸው ሀገራት የሚገኙ ዜጎች በአካል ለሚደረግ ቃለ ምልልስ እና የጣት አሻራ (ባዮሜትሪክ) ምዝገባ አለም አቀፍ ድንበሮችን አቋርጠው ለመጓዝ ስለሚገደዱ ለተጨማሪ የትራንስፖርት እና የማረፊያ ወጪዎች ይዳረጋሉ።

20,000 ዶላር ዋስትና‼️
አሜሪካ የቪዛ ዋስትና ክፍያን ቋሚ አደረገች፣ ተጓዦች እስከ 20 ሺህ ዶላር ይጠየቃሉ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች 30 የአፍሪካ ሀገራት ጨምሮ የ50 ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ለንግድና ለጉብኝት (B1/B2) ቪዛ ሲያመልክቱ እስከ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የቪዛ ዋስትና (Visa Bond) ማስያዝ የሚያስገድደውን መመሪያ በቋሚነት ማጽደቁን አስታወቀ።
እንደ አዲሱ መመሪያ አሰራር፣ ተጓዦች የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ሳያሳልፉ እና የሀገሪቱን ህግ አክብረው ከተመለሱ ያስያዙት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። ነገር ግን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የሚቆዩ ወይም የቪዛ ደንብ የሚጥሱ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ተገልጻል።
ይህ አሰራር ቀደም ሲል ለሙከራ ትግበራ ተዘርግቶ የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረገው ግምገማ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ችግርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ በቋሚነት ስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል። የቆንስላ ክፍሎች እንደ አመልካቾቹ ሁኔታ ከ10 ሺህ፣ 15 ሺህ እስከ 20 ሺህ ዶላር የሚደርስ ገንዘብ በዋስትና መልክ እንዲያዝ የመወሰን ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ቤኒን፣ ቦትስዋና፣ ቡሩንዲ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮትዲቯር፣ ጅቡቲ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሌሶቶ፣ ማላዊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞሪሸስ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ሴኔጋል፣ ሲሼልስ፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው።

አሜሪካ የቪዛ ዋስትና ክፍያን ቋሚ አደረገች፣ ተጓዦች እስከ 20 ሺህ ዶላር ይጠየቃሉ!
#fastmereja I የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች 30 የአፍሪካ ሀገራት ጨምሮ የ50 ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ለንግድና ለጉብኝት (B1/B2) ቪዛ ሲያመልክቱ እስከ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የቪዛ ዋስትና (Visa Bond) ማስያዝ የሚያስገድደውን መመሪያ በቋሚነት ማጽደቁን አስታወቀ።
ቀን፦ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. (August 1, 2026)

የአሜሪካ ባለስልጣናት እርምጃው የህገ-ወጥ ስደተኞችን ቁጥር እና የቪዛ ጊዜ ማለፍን ለመግታት ያለመ ነው ሲሉ ቢገልጹም፣ የስደት ህግ አዋቂዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ግን አሰራሩ ህጋዊ ተጓዦችን እንደሚያሰናክልና ከፍተኛ የፋይናንስ ጫና እንደሚፈጥር በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በአደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት ወንጀል የተጠረጠረውን አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ በቁጥጥር ሥር በማዋል ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷል።
ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በተለይም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች በርካታ ወጣቶችን ሕይወታቸውን እንደሚያሻሽል በመሐላና በአጉል ተስፋ በማታለል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር መቆየቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል።
ተጓዦችን ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ያስከፍል የነበረ ሲሆን፣ በቅድመ ክፍያ በኢትዮጵያ እስከ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ በባንክ ይቀበል እንደነበር የምርመራ መዝገቡ ያመላክታል።
ተጓዦቹን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ካሻገረ በኋላ በጋንቦ ጫካ ውስጥ በድብቅ በማስቀመጥ በየ24 ሰዓቱ ትንሽ ሩዝ ከቁራጭ ዳቦ ጋር ብቻ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና የውሃ ጥም የዳረጋቸው ሲሆን፣ በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል።
ናይሮቢ ካደረሳቸው በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ በማጎር ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ በማስገደድ፣ ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ በመደብደብና በኤሌክትሪክ ንዝረት በማሰቃየት ተጨማሪ ገንዘብ በኢትዮጵያ ባሉ ግብረ አበሮቹ በኩል እንዲከፈለው አድርጓል።
በተጨማሪም ተጓዦቹን ከናይሮቢ ወደ ሞምባሳና ታንዛኒያ በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች፣ በተሳቢና በሸራ በተሸፈኑ መኪኖች ውስጥ አጉሮ በመጫን ታንዛኒያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ጥሏቸው የተሰወረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ወጣቶች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በተለያዩ ሀገራት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እስከ ሦስት ዓመት እስራት ከተቀጡ በኋላ እስከ 170 ሺህ ብር ከፍለው ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል።
ፌደራል ፖሊስ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪውን በማላዊ ፖሊስ አስይዞ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ተረክቦ ወደ ሀገር ያመጣው ሲሆን፣ ህብረተሰቡ በEFPApp፣ በ991 እና በSPS ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

3 months ago
ደቡብ አፍሪካ ከ53 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎችን ማባረሯን ገለጸች
የደቡብ አፍሪካ መንግስት ከሳምንታት በፊት የጀመረውን ‹‹የስደት አስተዳደር›› ዘመቻ ተከትሎ ከ53 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ወይም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስታውቋል።
ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ ተባራሪዎች ከማላዊ፣ ከዚምባብዌ እና ከሞዛምቢክ የመጡ ሲሆን ፥ የሀገሪቱ የመልሶ ማቋቋም እና የማባረር ሂደት አሁንም እየቀጠለ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካ ባለፉት ሳምንታት ሁከት፣ ማስፈራራት እና ዝርፊያ የታየባቸውን ፀረ-ስደተኛ ተቃውሞዎች ተከትሎ በህገ-ወጥ ስደተኞች ላይ በቅርብ አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ እርምጃ እየወሰደች ትገኛለች።
ተቃዋሚዎቹ ስደተኞች ለከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር፣ ለወንጀል መጠን መጨመር እና ለህዝብ አገልግሎቶች መበላሸት ምክንያት ናቸው በማለት በመወንጀል፥ ጥብቅ የድንበር ቁጥጥር እንዲደረግና ሰፊ የማባረር እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኞችን ለደቡብ አፍሪካ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ማስተባበያ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
የፀረ-ስደተኛ አንቀሳቃሾች ፍላጎታቸው እስኪሟላ ድረስ መንግስትን ለመጫን በየሳምንቱ ተቃውሞ እንደሚያደርጉ ያስፈራሩ ሲሆን ፥ይህም ተቃውሞ ወደ ሁከት ሊቀየር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
አስተያየት ሰጪዎች ህገ-ወጥ ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የጊዜ ገደብ ያስቀመጡ ሲሆን፥ይህም በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ከጥቃት እና ከማስፈራራት ለማምለጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል።
ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ኡጋንዳ እና ኬንያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ዜጎቻቸውን ወደ ሀገራቸው መልሰዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ህዝቡ ስለ ስደት ያለውን ስጋት ቢገነዘቡም በስደተኞች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ኮንነዉ፤ ዜጎች ህግን በእጃቸው ከመውሰድ እንዲቆጠቡ አስገንዝበዋል።
ደቡብ አፍሪካ የአህጉሪቱ ባለጸጋ ሀገር ስትሆን የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድል ለሚፈልጉ ስደተኞች ለረጅም ጊዜ መዳረሻ ሆና ቆይታለች፡፡
ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ወደ ሀገሪቱ በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚገቡ ይታወቃል።
ሀና ሰይፉ ደቡብ አፍሪካ ከ53 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎችን ማባረሯን ገለጸች

ሀና ሰይፉ

ቀነ ገደቡ መጠናቀቅ የወለደው ውጥረት በደቡብ አፍሪካ
#ethiopia | የደቡብ አፍሪካ ፀረ-ስደተኛ ቡድኖች ህገ-ወጥ የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጡት የሰኔ 30 /ሰኔ 23 የጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።
የተቃውሞ ሰልፉ ወደ ከፋ ሁከትና ብጥብጥ ያመራል የሚለው ስጋት በሰፊው በማንዣበቡ ፣ በሀገሪቱ ያሉ ሰራተኞች ወደ ስራ ከመሄድ ተቆጥበዋል ፣ የንግድ ሱቆች ተዘግተዋል ፣ እንዲሁም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።
በደርባን እና በጆሃንስበርግ መሃል የሚገኙ አብዛኞቹ ሱቆች እና የንግድ ተቋማት የዝርፊያ ስጋት ስላለባቸው ተዘግተዋል።
ሰራተኞችና ጉዳይ ያለባቸው ተጓዦችም በቤታቸው ለመቆየት መርጠዋል።
በደርባን ከተማ የዙሉ ባህላዊ አልባሳትን የለበሱ፣ ዱላ እና ጋሻ የያዙ አነስተኛ የሰልፈኞች ቡድኖች በአንድ ፓርክ ውስጥ ተሰብስበው „አባሀምቤ“ (ይሂዱ/ልቀቁ) የሚሉ መፈክሮችን እያዜሙ ይገኛሉ።
የደቡብ አፍሪካ የፀጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹን በቅርብ እየተከታተሉ ነው።
ይህ የጊዜ ገደብ ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በፈጠረው ፍርሃት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ቆንስላዎችን እንዲሁም ጊዜያዊ መጠለያዎችን እያጨናነቁ ይገኛሉ።
ባለፉት ሳምንታት በተቀሰቀሰ የፀረ-ስደተኛ ጥቃት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ስጋቱን ይበልጥ አባብሶታል።
የደቡብ አፍሪካ መንግስት ሊፈጠር የሚችል ሁከትን ለመከላከል ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ያሰማራ ሲሆን ወታደራዊ ኃይሉንም በተጠንቀቅ አቁሟል።
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ህግ የሚጥሱ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።
በደቡብ አፍሪካ እየተባባሰ የመጣውን የፀረ-ስደተኞች ጥላቻ እና እንቅስቃሴ ተከትሎ ጆን አለን የተባለ ማላዊያዊ ስደተኛ ጥቂት ልብሶቹን በቦርሳው ጠቅልሎ፣ ደቡብ አፍሪካዊት ፍቅረኛውን እና የአንድ ዓመት ልጁን በሀዘን ተሰናብቶ ከሀገሪቱ ለመውጣት አውቶቡስ ለመያዝ ተገዷል።
ጆን አሁን ላይ በደርባን ከተማ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ይገኛል።
ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች በሙሉ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ፀረ-ስደተኛ ቡድኖች ያስቀመጡት መደበኛ ያልሆነ የጊዜ ገደብ (እስከ ዛሬ ጁን 30 ድረስ) ከመጠናቀቁ በፊት ሀገሪቱን ለቀው ለመውጣት ተስፋ በማድረግ ላይ ከሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ስደተኞች ጋር ለአራት ቀናት ያህል አውቶቡስ ሲጠብቅ ቆይቷል።
ምንም እንኳን የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህንን የጊዜ ገደብ ባይቀበለውም እና በስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ቢያወግዝም፣ ድርጊቱን በቁርጠኝነት ማስቆም ባለመቻሉ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና የሲቪክ ማህበራት ጠንካራ ትችት እየቀረበበት ይገኛል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#southafrica #emigrants #nigeria #ethiopia #ghana #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሙኒኬሽንስ #getutemesgenmediacommunications

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ስደተኞች ሀገሪቱን ጥለው እየሸሹ ነው!
እንደ አልጀዚራ (Al Jazeera) የዜና ዘገባ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ከፍተኛ የውጭ ዜጎች ጥላቻ (Xenophobia) እና ጥቃት ምክንያት፣ እንዲሁም June 30 ሊደረግ ከታቀደው መጠነ-ሰፊ ፀረ-ስደተኞች ሰልፍ አስቀድሞ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ሀገሪቱን በከፍተኛ ስጋት እየለቀቁ ይገኛሉ።
እንደ ማላዊ፣ ዚምባብዌ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ሞዛምቢክ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ዜጎቻቸውን በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ (Repatriation) የአውቶቡስ እና የሎጂስቲክስ ዝግጅቶችን እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ስደተኞችም ጥበቃ ፍለጋ በየሀገራቱ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ደጅ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።
ይህ የጊዜ ገደብ መጀመሪያ ላይ የደቡብ አፍሪካን መንግስት አርማ ተጠቅሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት በተሰራጨ የሀሰት (AI-generated) ፖስተር የተነሳ የመጣ ቢሆንም፣ "ማርች ኤንድ ማርች" (March and March) የተባሉ የፀረ-ስደተኛ አደረጃጀቶች እና ቡድኖች ግን ህገ-ወጥ ስደተኞች በሙሉ እስከ June 30 ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በማስገደድ የራሳቸውን መጠነ-ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል።
ምንም እንኳን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ህጋዊ ባይሆንም፣ በተለያዩ ከተሞች (ለምሳሌ በሞሰል ቤይ) በስደተኞች መኖሪያ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረቶች ተዘርፈዋል እንዲሁም የሰው ህይወት ጠፍቷል።
ጋና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን በልዩ የአየር በረራ የመለሰች ሲሆን፣ ማላዊ ከ5,000 በላይ ሰዎችን በባስ ለማጓጓዝ እየሰራች ነው።
ናይጄሪያ እና ሞዛምቢክም በተመሳሳይ ሁኔታ ዜጎቻቸውን የማስወጣት ስራ ላይ ናቸው።
ጉርሻ

4 months ago
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው።
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በቅርቡ በነበረው የኢራን ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የኤኮኖሚ ቀውስ ለመታደግ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተወሰኑ የአፍሪቃ ሃገራት የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሊያሳድግ ነው። ድርጅቱ ድጋፉን ከማሳደግ በተጨማሪ ገንዘቡን በፍጥነት ለማቅረብ ማቀዱም ተሰምቷል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ እንዳሉት በመርኃ ግብሩ ኢትዮጵያ ፣ጋምቢያ እና ቡርኪና ፋሶ ተጠቃሚ ሲሆኑ በተጨማሪ ማላዊ አዲስ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ከተቋሙ ጋር የተፋጠነ ውይይት እያደረገች መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔም የ25 ሚሊዮን ዶላር የትብብር መርሃግብር አካል የሆነውን 6.1 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ከስምምነት መድረሳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የአይ ኤም ኤፍ (IMF) የአፍሪካ ዳይሬክተር ዘይን ዘይዳን በዋሽንግተን በሰጡት መግለጫ፥ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የአፍሪካ ቀጠና "ከባድ ፈተና" ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሁን የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም በጦርነቱ ምክንያት የተስተጓጎለው የባህረ ሰላጤው ሀገራት የኃይል እና የነዳጅ ምርት ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ ከ6 እስከ 7 ወራት ሊፈጅ እንደሚችል ጠቁመዋል።
የነዳጅ ምርት አቅርቦቱ መቋረጥ በአፍሪካ ሀገራት ላይ ከፍተኛ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ንረትን ያስከተለ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው አይ ኤም ኤፍ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአደጋ ጊዜ ፕሮግራሞቹን እያሰፋ መሆኑን ገልጿል።
እንደ ድርጅቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ያደረጓቸው የኤኮኖሚ ማሻሻያዎች አሁን ለተከሰተው የኃይል አቅርቦት መናወጥ የተሻለ የመቋቋም አቅም እንዲኖራቸው ረድቷቸዋል ። ይሁን እንጂ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ሊጠይቁ እንደሚችሉ ግን አልሸሸገም።
DW Amharic

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የደቡብ አፍሪካ መንግስት ጁን 30 መቃረቡን ተከትሎ የፀጥታ ሀይሉን ማጠናከሩን አስታወቀ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ መጤ ጠል ቡድኖች ማንኛውም በአገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ህገ ወጥ ስደተኛ እስከ ጁን 30 ለቆ እንዲወጣ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡ ከተቀመጠው ቀነ ገደብ በኋላ በአገሪቱ ውስጥ ከተገኘ ግን ንብረቱን እንደሚዘርፉና ህይወቱን እንደሚያጠፉ ጭምር ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፀጥታ ሀይሉን ለማጠናከር መወሰኑን አስታውቋል፡፡
የአገሪቱ ተጠባባቂ የፖሊስ ሚኒስትር ፊሮዝ ካቻሊያ ሲናገሩ ‹‹በሁሉም የአገራችን ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ፣ መሰረተ ልማቶችንና ቁልፍ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለመጠበቅ አስፈላጊውን የተቀናጀ ሀይል የማስፈር እቅድ አለን›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ሰዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የማሰማት መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሽፋን ወንጀል መፈፀም፣ አመፅ ማስነሳትና ንብረትን ማውደም አይችሉም፡፡ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን አንታገስም›› በማለት አስታውቀዋል፡፡ የ
ደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር በበኩላቸው ከጁን 30 አንስቶ እንደአውሮፕላን ማረፊያ የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ ወታደሮችን እንደሚያሰማሩ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል የአገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር ማሞሎኮ ኩባይ እስካሁን ድረስ አምስት ሺህ ህገ ወጥ የማላዊ ዜጎች ወደአገራቸው መሄዳቸውን ጠቅሰው በህገ ወጥ ስደተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስልጣን ያለው መንግስት ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ክልል መምህራን ማኅበር፣ በክልሉ የመምህራን ደመወዝ ለበርካታ ወራት ባለመክፈሉ መምህራን ከነቤተሰቦቻቸው በርሃብ ምክንያት እየታመሙ፣ እየተሠቃዩ እና አልፎ አልፎም ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ ሲል ዛሬ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።
ማኅበሩ፣ በፖለቲከኞች መካከል በተፈጠረ የሃሳብ ልዩነት ምክንያት የመምህራን ደመወዝ መከልከል ''የግፍ ግፍ" እና "በታሪክ የሚያስወቅስ" ተግባር ነው በማለት ኮንኗል።
የክልሉ መምህራን ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው ከዚህ ቀደም በደብዳቤና በሠማላዊ ሠልፍ ጭምር በተደጋጋሚ መጠየቁን የጠቀሠው ማኅበሩ፣ ኾኖም ለችግሩ ምላሽ የሚሠጥ አካል አልተገኘም ብሏል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ከፌዴራሉ መንግሥትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሩ መፍትሔ እንዲያፈላልግም ማኅበሩ ጠይቋል።

''አሁን የብርድ ወራት በመሆኑ ልጄ እየታመመች ነበር''
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ ውስጥ ለሳምንታት ሰፍረው የነበሩ ከ1,000 በላይ የማላዊ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችል የሰነድ ማጣራት ሂደት መጠናቀቁ ተገለጠ።
የማላዊ ኤምባሲ ዜጎቹን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለማጓጓዝ የሚያስችሉ አውቶቡሶችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ እስካሁንም በደርባን ሸርዉድ አካባቢ የትራንስፖርት እገዛ ሲጠባበቁ ከነበሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ማላውያን መካከል የ1,140 ሰዎችን ማንነት ማረጋገጥ ተችሏል። በጥቅሉ ለጉዞው ቅድሚያ የተሰጣቸው ለሕፃናትና ለሴቶች መሆኑ ታውቋል።
የኳዙሉ-ናታል ግዛት ሃላፊ ታሚ ንቱሊ እንደገለጹት፣ የመመለስ ሂደቱ ሰብአዊ መብትን፣ ክብርንና አክብሮትን በጠበቀ መልኩ እየተመራ ይገኛል። ሃላፊው አክለውም፦
“ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሕግ ሳይጥሱ እንዲመለሱ ከተለያዩ ሀገራት ጋር እጅና ጓንት ሆነን በመስራታችን ደስተኛ ነኝ። ወደፊት መመለስ ቢፈልጉ እንኳ ፈቃድ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል” ብለዋል።
አያይዘውም “ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው በርካታ የውጭ ዜጎች ከእኛ ጋር ይኖራሉ። ደቡብ አፍሪካውያንም በሌሎች ሀገራት እንደሚኖሩ ስለምንረዳ ይህ ለእኛ ችግር አይደለም፤ ደቡብ አፍሪካ የሁሉም ሀገር ነች ብለን እናምናለን። ዜጎች ነገር ግን በማንኛውም ሌላ ሀገር ውስጥ ሲኖሩ ሕጋዊ ሰነድ መያዝ ግድ ይላል” ሲሉ አስገንዝበዋል።
ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ለመሸኘት የመጡ አንድ የማላዊ ዜጋ “ጉዟችን በመጀመሩ በጣም ደስተኞች ነን፤ ሴቶችና ሕፃናት ደግሞ ቅድሚያ ማግኘታቸው ተገቢ ነው” ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል። ባለቤታቸው በበኩሏ ወደ ሀገሯ ለመመለስ በጉጉት ላይ መሆኗን ጠቅሳ “ለሁለት ሳምንታት ያህል ከባድ መከራ አሳልፌአለሁ፤ ዛሬ ግን ወደ ሀገሬ በመመለሴና ቤተሰቦቼን ለማየት በመታደሌ በጣም ደስተኛ ነኝ። አሁን የብርድ ወራት በመሆኑ ልጄ እየታመመች ነበር። እዚህ እኛ ባዕድ በመሆናችን ወደ ሆስፒታል መሄድ አትችሉም ተብለን ነበር፤ አሁን ግን ወደ ሀገሬ ተመልሼ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ስለምችል ነፃነት ይሰማኛል” ስትል ተናግራለች።
በሌላ በኩል፣ በክሩገርስዶርፕ ከሚገኘው የሊንዴላ መመለሻ ማዕከል ወደ 980 የሚጠጉ ማላውያን የሰነድ ማጣራታቸውን ጨርሰው፣ ሐሙስ ምሽት በ14 አውቶቡሶች አማካኝነት ወደ ሀገራቸው መሸኘታቸው ታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ናይጄሪያ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ እያስወጣች ነው
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ፀረ-ስደተኛ ስሜቶች እያደጉ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ ናይጄሪያ የተወሰኑ ዜጎቿን ወደ ሀገራቸው እየመለሰች ያለች አራተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።
ሐሙስ ጠዋት ከጆሀንስበርግ የተነሳችና 268 ናይጄሪያውያንን የጫነች አውሮፕላን ሌጎስ ገብታለች። እነዚህ ተጓዦች በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የናይጄሪያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከተመዘገቡት ወደ 1,000 ገደማ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ናቸው።
አንዳንድ የቅስቀሳ ዘመቻ አድራጊዎች ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካስቀመጡት የሰኔ 30 የጊዜ ገደብ ቀደም ብለው ጋና፣ ዚምባብዌ እና ማላዊ ዜጎቻቸውን የማስወጣት ሥራ አከናውነዋል።
በጆሀንስበርግ ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ፣ ከናይጄሪያውያን ተጓዦች አንዱ የሆነው ጀስቲን ከ1998 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ እንደኖረ ለቢቢሲ አፍሪካ ተናግሯል።
"እየወጣሁ ያለሁት እዚህ በሰጡን ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ነው። እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወይም ከዚያ በፊት መውጣት እንዳለብን እየነገሩን ነው። በተጨማሪም ሰዎችን፣ ወንድሞቻችንን እየተገደሉ ነው እና እኔ እዚህ ደኅንነት አይሰማኝም" ሲል ጀስቲን ተናግሯል።
ጀስቲን እርሱ ራሱ ቀደም ሲል የጥቃቱ ኢላማ ሆኖ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጿል።
"በቅርቡ በአንድ ታክሲ ውስጥ ጥቃት ሰነዘሩብኝ። እኔም ዕቃዎቼን ጥዬ ሮጥኩ፤ ስልኬንና ሁሉንም ነገሬን ትቼ ነው ያመለጥኩት።"
"የተለያዩ ስሞችን እየሰጡ ይሰድቡናል፣ 'ይህችን ሀገር ለቃችሁ መውጣት አለባችሁ' ይሉናል። ልንለምናቸው ስንሞክር ደግሞ ማዋረድና መሳደብ ጀመሩ።"ብሏል፡፡
እሑድ ዕለት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለተቃውሞ ሰልፎቹ ምላሽ ለመስጠት በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ ሕገ-ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር የሚረዱ አዳዲስ ጠንካራ እርምጃዎችን ይፋ አድርገዋል።
እነዚህም እርምጃዎች ሰነድ የሌላቸውን ሠራተኞች የሚቀጥሩ አሰሪዎችን ማሰር፣ የስደት (የማባረር) ሂደቱን ለማፋጠን ልዩ ፍርድ ቤቶችን ማቋቋም እና የማንነት ስርቆትን ለመከላከል በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ሰዎች ባዮሜትሪክ (የአካል መገለጫ) መረጃ ቋት ማደራጀትን ያካትታሉ።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ደቡብ አፍሪካውያን በሀገሪቱ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ይኖራሉ ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች ኢላማ በማድረግ ሕግን በገዛ እጃቸው እንዳይተረጉሙ አስጠንቅቀዋል ሲል የኢትዮ ኤፍ ኤም ዘገባ አስታውሷል።

የኢትዮጵያና የማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀቁ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ግጥሚያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ ለዋልያዎቹ ብቸኛዋን ግብ ቢኒያም በላይ ከመረብ ማገናኘት የቻለ ሲሆን የማላዊን የአቻነት ግብ ደግሞ አዴፖጁ ባባቱንዴ አስቆጥሯል።
በዋና አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባሳለፍነው ቅዳሜ በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታዲየም ከማላዊ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
#walyas #football #diredawa #ethiopianfootball #malawi #friendlymatch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር ያደረገውን ሁለተኛ ዙር የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 1 አቻ አጠናቅቋል።
በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ግብ ቢንያም በላይ ሲያስቆጥር የማላዊን ግብ አዴፖጁ ባባቱንዴ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ዋልያዎቹ በተመሳሳይ ስታዲየም ከቀናት በፊት ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማላዊ ላይ የ1 ለ 0 አሸነፈ
#ethiopia | ለሁለቱ አገራት የዝግጅት ምዕራፍ ተብሎ በተዘጋጀው የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ግጥሚያ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የማላዊ አቻውን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ባለድል ያደረገችውንና በጨዋታው የታየችውን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ተጫዋች ፍጹም ጥላሁን ነው።
እነዚህ ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ከሁለት ቀናት በኋላ ማለትም በመጪው ማክሰኞ በድሬዳዋ ስታዲየም ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን በድጋሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
#የኢትዮጵያብሔራዊቡድን #ኳስ #ስፖርት #ድሬዳዋ #ጌጡተመስገን #ጌጡ #ጌጡ #getutemesgen #getu #addisababa

ዋሊያዎቹ የማላዊ አቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ የማላዊ ብሄራዊ ቡድንን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የዋሊያዎቹን የአሸናፊነት ግብ ፍጹም ጥላሁን አስቆጥሯል፡፡
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታቸውን በመጪው ማክሰኞ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋሉ፡፡

5 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በደርባን ከተማ ዶክመንት በሌላቸው ስደተኞች ላይ የአፈሳ ዘመቻ ተጀመረ፡፡ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ሲቢዲ አካባቢ የመንግስት ሀይሎች ህጋዊ ዶክመንት በሌላቸው ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን አስታወቁ፡፡ በዚህ ዘመቻ የኢቲኪዊኒ ማዘጋጃ ቤት ከተለያዩ መንግስታዊ ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዛሬው እለት ብቻ 23 ዶክመንት የሌላቸው ስደተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ከተያዙት ውስጥ ኢትዮጵያዊያን፣ ዚምባቡያዊያን፣ የማላዊ ዜጎችና ቻይናዊያን እንደሚገኙበት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገልጿል፡፡ በተጨማሪም በተደረገው ዘመቻ 5 ያህል በህገ ወጥ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የተገኙ ሱቆች ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ ከታሸጉት ውስጥም በኢትዮጵያዊያን የሚተዳደሩ ሱቆች ይገኙበታል፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ በመግለጫው ‹‹እነዚህ ሱቆች የህገወጥ ስደተኞች መደበቂያ፣ ህጋዊ ያልሆነ አደንዛዥ እፅ መሸጫና የሴተኛ አዳሪነት ስራዎች ሲፈፀሙባቸው የነበሩ ናቸው›› ብሏል፡፡
የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህንን እርምጃ መውሰድ የጀመረው በአገሪቱ ውስጥ ስደተኛ ጠል ተቃውሞው እየተቀጣጠለ መምጣቱን ተከትሎ ነው፡፡ የአገሪቱ የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቶች ትላንት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ተቃውሞውን ለማብረድ በህገ ወጥ ስደተኞች ላይ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ የሚል ውሳኔ ላይ የደረሱ ሲሆን ዛሬ በደርባን የተጀመረው አይነት እርምጃ በሌሎች ከተሞችም እንደሚቀጥል ከስፍራው የተሰራጩ መረጃዎች ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ ከፍተኛ የአርሰናል ደጋፊ ያላቸው 10 ቀዳሚ አገራት ደረጃ ይፋ ሆኑ!
መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የዘንድሮውን የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ክለቡ በአፍሪካ አህጉር ያለው ግዙፍ ተፅዕኖ ዳግም ትኩረት ስቧል።
በቢቢሲ (BBC) የምርምር መረጃዎችና በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መስተጋብሮች መነሻነት የወጣው የአፍሪካ ቀዳሚ የአርሰናል ደጋፊዎች ደረጃ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስገራሚ ውጤቶችን አሳይቷል።
በዚሁ መረጃ መሠረት፣ አርሰናልን በከፍተኛ ስሜትና በብዛት በመደገፍ በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆኑት 10 አገራት የሚከተሉት ናቸው ተብሏል:-
1.
ናይጄሪያ (Nigeria)
2.
ኬንያ (Kenya)
3.
ኡጋንዳ (Uganda)
4.
ኢትዮጵያ (Ethiopia)
5.
ታንዛኒያ (Tanzania)
6.
አልጄሪያ (Algeria)
7.
ጋና (Ghana)
8.
ሞሮኮ (Morocco)
9.
ቱኒዚያ (Tunisia)
10.
ማላዊ (Malawi)
seledadotio
seledadotio
መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የዘንድሮውን የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ክለቡ በአፍሪካ አህጉር ያለው ግዙፍ ተፅዕኖ ዳግም ትኩረት ስቧል።
በቢቢሲ (BBC) የምርምር መረጃዎችና በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መስተጋብሮች መነሻነት የወጣው የአፍሪካ ቀዳሚ የአርሰናል ደጋፊዎች ደረጃ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስገራሚ ውጤቶችን አሳይቷል።
በዚሁ መረጃ መሠረት፣ አርሰናልን በከፍተኛ ስሜትና በብዛት በመደገፍ በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆኑት 10 አገራት የሚከተሉት ናቸው ተብሏል:-
1.
2.
3.
4.
5.
6.
7.
8.
9.
10.
seledadotio
seledadotio
5 months ago
ክቡር ቴዎድሮስ ጌታቸው በኮሜሳ ፍርድ ቤት በዳኝነት ተሾሙ
#ethiopia | በኬንያ ናይሮቢ ስቴት ሃውስ በተከናወነ ደማቅ ስነ ስርአት ክቡር ቴዎድሮስ ጌታቸው በኮሜሳ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
ላለፉት ሁለት አመታት በአለም አቀፍ የህግ መድረኮች የህግ የበላይነትን ለማስከበርና አድሎአዊ አሰራሮችን ለመቃወም ሲደረግ የነበረው ከፍተኛ ጥረት በዚህ ሹመት በድል ተጠናቋል።
ይህ ሂደት በውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙሀንና ተቋማት ዘንድ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የቆየ ቢሆንም በሀገር ውስጥ ግን በስፋት ሳይነገር ቆይቷል። በታህሳስ ወር በተካሄደው የኮሜሳ ሀገራት ምርጫ ኢትዮጵያዊው ባለሙያ ጥብቅ መስፈርቶችን አልፈው በከፍተኛ ድምጽ መመረጣቸው ይታወሳል።
በዚሁ የሹመት መርሃ ግብር ላይ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የዛምቢያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ብሩንዲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ኡጋንዳ፣ ዚምቧብዌ እና ግብፅ ተወካዮች የዳኝነት ስልጣን ተረክበዋል።
ከዚህም ባለፈ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ የቀድሞ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ውብሸት ሽፈራው የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በመሆን መሾማቸው ለሀገራችን ድርብ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
#comesa #justice #ethiopianexcellence #law #africa #nairobi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
"በሞዴስ" ውስጥ የተደበቀው ኮኬይን፦ ኡጋንዳዊቷ ተጠርጣሪ በቦሌ ተያዘች
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 500 ግራም ኮኬይን በረቀቀ መንገድ ደብቃ ለማለፍ የሞከረች ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት በቁጥጥር ስር መዋሏን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልፇል።
ተጠርጣሪዋ እጹን በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ውስጥ ደብቃ ከማላዊ ወደ ፊሊፒንስ በመጓዝ ላይ ሳለች፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጥብቅ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል።
ተጠርጣሪዋ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፋ መሰጠቷን አገልግሎቱ ገልፇል።

Comments