ናይጄሪያ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ እያስወጣች ነው
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ፀረ-ስደተኛ ስሜቶች እያደጉ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ ናይጄሪያ የተወሰኑ ዜጎቿን ወደ ሀገራቸው እየመለሰች ያለች አራተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።
ሐሙስ ጠዋት ከጆሀንስበርግ የተነሳችና 268 ናይጄሪያውያንን የጫነች አውሮፕላን ሌጎስ ገብታለች። እነዚህ ተጓዦች በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የናይጄሪያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከተመዘገቡት ወደ 1,000 ገደማ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ናቸው።
አንዳንድ የቅስቀሳ ዘመቻ አድራጊዎች ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካስቀመጡት የሰኔ 30 የጊዜ ገደብ ቀደም ብለው ጋና፣ ዚምባብዌ እና ማላዊ ዜጎቻቸውን የማስወጣት ሥራ አከናውነዋል።
በጆሀንስበርግ ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ፣ ከናይጄሪያውያን ተጓዦች አንዱ የሆነው ጀስቲን ከ1998 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ እንደኖረ ለቢቢሲ አፍሪካ ተናግሯል።
"እየወጣሁ ያለሁት እዚህ በሰጡን ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ነው። እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወይም ከዚያ በፊት መውጣት እንዳለብን እየነገሩን ነው። በተጨማሪም ሰዎችን፣ ወንድሞቻችንን እየተገደሉ ነው እና እኔ እዚህ ደኅንነት አይሰማኝም" ሲል ጀስቲን ተናግሯል።
ጀስቲን እርሱ ራሱ ቀደም ሲል የጥቃቱ ኢላማ ሆኖ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጿል።
"በቅርቡ በአንድ ታክሲ ውስጥ ጥቃት ሰነዘሩብኝ። እኔም ዕቃዎቼን ጥዬ ሮጥኩ፤ ስልኬንና ሁሉንም ነገሬን ትቼ ነው ያመለጥኩት።"
"የተለያዩ ስሞችን እየሰጡ ይሰድቡናል፣ 'ይህችን ሀገር ለቃችሁ መውጣት አለባችሁ' ይሉናል። ልንለምናቸው ስንሞክር ደግሞ ማዋረድና መሳደብ ጀመሩ።"ብሏል፡፡
እሑድ ዕለት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለተቃውሞ ሰልፎቹ ምላሽ ለመስጠት በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ ሕገ-ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር የሚረዱ አዳዲስ ጠንካራ እርምጃዎችን ይፋ አድርገዋል።
እነዚህም እርምጃዎች ሰነድ የሌላቸውን ሠራተኞች የሚቀጥሩ አሰሪዎችን ማሰር፣ የስደት (የማባረር) ሂደቱን ለማፋጠን ልዩ ፍርድ ቤቶችን ማቋቋም እና የማንነት ስርቆትን ለመከላከል በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ሰዎች ባዮሜትሪክ (የአካል መገለጫ) መረጃ ቋት ማደራጀትን ያካትታሉ።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ደቡብ አፍሪካውያን በሀገሪቱ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ይኖራሉ ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች ኢላማ በማድረግ ሕግን በገዛ እጃቸው እንዳይተረጉሙ አስጠንቅቀዋል ሲል የኢትዮ ኤፍ ኤም ዘገባ አስታውሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 days ago