4 months ago
"አቅማችን ተሟጧል!"
— ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበች
#ethiopia | ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የመንግስት አቅም እየተሟጠጠ መሆኑን በይፋ አስታወቀች።
በተለይ በትምህርትና በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች በስደተኞች ቁጥር መጨመር ምክንያት ከፍተኛ ጫና ወድቆባቸዋል።
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋዓብ ክበበው በተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የሀገሪቱን ስጋት በዝርዝር አቅርበዋል።
ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ ተጠይቋል።
ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ፣ ለስደቱ መሠረት የሆኑ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደሩ አሳስበዋል።
#ethiopia #refugees #humanitarianaid #unhcr #geneva #addisadmas #breakingnews #globalcall #ኢትዮጵያ #ስደተኞች

8 months ago
በርካታ የአፍሪካ አገራት በአዲሱ
የአሜሪካ የጉዞ ገደብ ተካትተዋል
ጋና፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳና ሩዋንዳ አይመለከታቸውም
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአፍሪካ የሚገኙ በርካታ ሀገራትን ጨምሮ በተለያዩ የአለም ሀገራት ላይ ሰፊ የጉዞ ገደቦች መጣላቸውን አስታወቁ።
ከፊል ገደቦች (ጎብኚ፣ ተማሪ እና የልውውጥ ቪዛ);
ከሚከተሉት የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ዜጎች ጥብቅ የመግቢያ ቅድመ ሁኔታ ይጠብቃቸዋል።
ናይጄሪያ
ታንዛኒያ
ብሩንዲ
ጋምቢያ 🇬🇲
ማላዊ 🇲🇼
ሴኔጋል 🇸🇳
ጋቦን 🇬🇦
ዛምቢያ 🇿🇲
ዚምባብዌ 🇿🇼
የመግቢያ ሙሉ እገዳ
ከሚከተሉት አገሮች የመጡ ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡-
ቡርኪናፋሶ 🇧🇫
ኒጀር 🇳🇪
ማሊ 🇲🇱
ሴራሊዮን 🇸🇱
ደቡብ ሱዳን 🇸🇩
ኤርትራ 🇪🇷
ሱዳን 🇸🇩
የኮንጎ ሪፐብሊክ 🇨🇬
ሶማሊያ 🇸🇴
*የጋና፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳና ሩዋንዳ ዜጎች እገዳው የማይመለከታቸው ሲሆን፤ በነባር የአሜሪካ ቪዛ ህጎች ለመጓዝ ብቁ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡
#addisadmas

12 months ago
የአባቴን ቤት እሸጣለሁ እንጅ አልቆምም!!
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ መስራችና ባለቤት አሰፋ ጎሳዬ
#ethiopia | ሽቅርቅሪት ቅዳሜ ላይ ቆመን ዕለቷን ያስናፍቋት ስለነበሩት አንዷ "አዲስ አድማስ" ጋዜጣ ትንሽ ብናወራስ!?
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ህልው ሆኖ ወደ አንባቢ የመጣው በወርሃ ጥር 1991 አ.ም የዛሬ 26 አመት ግድም ነበር።
አዲስ አድማስ የንባብ ዐውዱን ከመቀላቀሏ በፊት ይዘትና ቅርጿን በተመለከተ ብዙ ዝግጅት፣ ብዙ ጥንቃቄ፣ ብዙ ምክክር፣ ብዙ ሙያዊ ርብርብ ተደርጎባታል። ይህንን ጥንቃቄና ዝግጅት አሳምረው የሚያውቁት ባለቤቷ አሰፋ ጎሳዬና ጓደኞቹ ጋዜጣዋን "እንከን የለሽ" በሚል እርግጠኝነት የንባብ ዐውዱን ቢቀላቀሉም፤ እንደታሰበውና እንደተለፋበት ያህል ግን ወዲያው ምላሽ አላገኘም። ይልቁንም በሸክም የወጣው ጋዜጣ በሸክም እየተመለሰ፤ በጋዜጣው ዝግጅት ላይ የአቅም አቅማችንን እንተጋ የነበርነውን ሁሉ ልብ የሚያርድ ሁኔታ ተፈጠረ።
እንዴት? ለምን? በሚል ግራ መጋባት ራሳችንን እስከመጠራጠር አደረሰን!
ከዚህ የተነሳም 'ቢሆን፣ ቢደረግ፣ የምንለውን ሃሳብ እያነሳን እየጣልን ተነጋገርን። ብዙዎቻችን ከአንባቢው አለመብሰልና ፈጣን መረጃ ፈላጊነት እንጅ በይዘቱ አንዳች እንከን እንደሌለው እንገምታለን።
ከይዘት ባሻገር አውጥተን አውርደን ቶሎ ተቀባይነት እንዳያገኝ እንቅፋት የሆነበት ሌላው ምክንያት 'ቅርፁ ሊሆን ይችላል' በሚል ግምት ባልተለመደው ብርቱካናማው የስያሜው ቀለም መደብና የጽሑፉ ቅርፅ ላይ አተኮርን። እናም አሰፋን "በቃ ችግሩ ይሄ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ስያሜና ጽሑፍ ሊሆን ስለሚችል እንቀይረው" አልነው። አሰፋም ያቺን ሽራፊ ፈገግታውን እያሳዪን "በመቃብሬ ላይ" በፈረንጅ አፍ On my dead body ወዶ ሳይሆን ተገዶ ይለምዳታል አለን።
"ኪሳራውስ?" ብንለው "የአባቴን ቤት እስኪያስሸጠኝ ሊቀጥል ይችላል እንጅ አላደርገውም" አለን!
አሰፋ "ስኬትህን በመዳፍህ መጨበጥ ካሻህ በያዝከው ነገር ፀንተህ ግፋ፤ እንዳትዝልም ፀንተህ ወጥር Push and Persist" የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ ቀድሞ የገባው ነበር። እናም እንዳለው ሆነ "አዲስ አድማስ" በይዘቱም ይሁን በዝግጅቱ በየሳምንቱ በጉጉት የሚጠበቅና የሚነበብ ተወዳጅ ጋዜጣ ለመሆን በቃ!!
ዛሬ ይህንን ከ26 አመታት በፊት የሆነ ትውስታ ያስመዘዘኝ ትላንት ያነበብኩት የ ናፍቆት ዮሴፍ የቁጭትና መብሰክሰክ ጽሑፍ ነው።
እናም ከእሷ ቁጭትና መብሰክሰክ ተነስቼ "እውን አሰፋ በህይወት ቢኖር አዲስ አድማስ ከህትመት ትወጣ ነበር?" ብዬ እንዳስብ አድርጋኝ ነው!
ሞት ቀደመው እንጅ አሴ ቢኖርማ እንኳን ጋዜጣው ሊቆም ይቅርና ዛሬ በሀገራችን ቁጥር አንድ የሚባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስም "አዲስ አድማስ ቲቪ" የሚባል በሆነ ነበር!!
ቸር ቀዳሚት ትሁንላችሁ! #addisadmas

Comments