Logo
FIDEL POST NEWS
​"በሞዴስ" ውስጥ የተደበቀው ኮኬይን፦ ኡጋንዳዊቷ ተጠርጣሪ በቦሌ ተያዘች

​በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 500 ግራም ኮኬይን በረቀቀ መንገድ ደብቃ ለማለፍ የሞከረች ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት በቁጥጥር ስር መዋሏን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልፇል።

ተጠርጣሪዋ እጹን በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ውስጥ ደብቃ ከማላዊ ወደ ፊሊፒንስ በመጓዝ ላይ ሳለች፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጥብቅ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል።

ተጠርጣሪዋ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፋ መሰጠቷን አገልግሎቱ ገልፇል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.