4 days ago
🔴 GUNNERS MEDIA × YOD ABYSSINIA
የአርሰናል ፍቅር ከእድል ጋር ሲገናኝ!
ዛሬ ገነርስ ሚዲያ እና ዮድ አቢሲኒያ የመድፈኞችን ቤተሰብ በአንድነት ለማሰባሰብ፣ በጋራ ለመስራት እና ለአርሰናል ደጋፊዎች የተሻለ የደጋፊነት ልምድ ለመፍጠር የትብብር ስምምነት ፈጽመናል።
ይህ ከንግድ በላይ ነው። የመድፈኞችን ቤተሰብ ለማቀራረብ፣ እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና እድሎችን በጋራ ለመፍጠር የተጀመረ አዲስ ምዕራፍ ነው።
🎁 ለGunners Media አባላት ልዩ ጥቅም
በዮድ አቢሲኒያ የምግብና የመጠጥ ግዢ ላይ 20% ልዩ ቅናሽ ያገኛሉ።
ይህ ግን መጀመሪያው ነው! 🔥
Gunners Media አባላቱን ከተለያዩ የንግድና የአገልግሎት አጋሮች ጋር በማገናኘት እስከ 20% የሚደርስ ጥቅም የሚያስገኝ የአባልነት መረብ እየገነባ ነው።
🛒 አስቤዛ | 👕 Garment & Fashion | 🎟️ ቲኬትና ጉዞ | 🏨 ሆቴል | 🏥 ጤና | 🛍️ ሌሎች አጋር ተቋማት
የGunners Media ራዕይ የአርሰናል ዜናን ብቻ ማቅረብ አይደለም።
Arsenal Fans Supporting Arsenal Fans — እርስ በርስ የምንደጋገፍ፣ እድል የምንፈጥር እና አንድ ጠንካራ የገነርስ ቤተሰብ የምንገነባ ማህበረሰብ።
አርሰናልን እንወዳለን።
እርስ በርስ እንደጋገፋለን።
እድልን በጋራ እንፈጥራለን።
አንድ ቤተሰብ ነን!
GUNNERS MEDIA × YOD ABYSSINIA
አንድ ፍቅር። አንድ ቤተሰብ። ብዙ እድሎች።
Once a Gunner, Always a Gunner.

12 days ago
የብሪክስ+ የፋሽን ጉባዔ እና የሞስኮ የፋሽን ሳምንት የዓለምን ትኩረት ስቧል
******************
የዓለም አቀፍ የፋሽን ማዕከል ትኩረት ወደ ሞስኮ የዞረበት የብሪክስ+ የፋሽን ጉባኤ እና የሞስኮ የፋሽን ሳምንት ትናንት በይፋ የጀመረ ሲሆን፣ በታሪካዊው ክሬምሊን አቅራቢያ የሚገኘውን ማኔዥ የኤግዚቢሽን አዳራሽን በደማቅ የፋሽን ድባብ አድምቆታል።
ከ70 በላይ ማራኪ የመድረክ ትርዒቶች እና የቀይ ምንጣፍ ሥነ-ሥርዓቶችን ያካተተው ይህ መርሐ ግብር፣ ትናንት በከፍተኛ የፋሽን ዲዛይኖች፣ በዘመናዊ የጎዳና አልባሳት እና በባህላዊ እሴቶች ቅንብር የተከፈተ ሲሆን፣ ዛሬም በበርካታ ደማቅ ዝግጅቶች ቀጥሎ ይገኛል።
በትናንቱ የመክፈቻ ዝግጅት ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ የፈጠራ ባለቤቶች ያቀረቧቸው ስብስቦች ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል።
ትርዒቱ ታዋቂ ዓለም አቀፍ እና የሩስያ ብራንዶች ባህላዊ የእጅ ጥበብን ከዘመናዊ ፋሽን ጋር በማቀናጀት ያቀረቡበት ነበር።
ዲዛይነሮቹ ባህላዊ ጥልፎችን፣ ማራኪ ቅርጾችን እና ባህላዊ የሸማ ጥበቦችን በመጠቀም ጥንታዊ የባህል እሴቶችን ለዝነጣ ተስማሚ ወደሆኑ ዘመናዊ አልባሳት ቀይረው አቅርበዋል።
በመክፈቻው ከበርካታ ሀገራት የተውጣጡ ታዋቂ የፋሽን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመገኘት ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል።
ከመድረክ ትርዒቶቹ ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ ፋሽን መሪዎች እና ልዑካን በወደፊቱ የፋሽን ኢንዱስትሪ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዲዛይን፣ ለአካባቢ ተስማሚ በሆኑ ጨርቃጨርቅ እና በአዲስ አህጉር አቋራጭ የፋሽን ትስስሮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ያደርጋሉ።
ዲዛይነሮች አዳዲስ ሥራዎቻቸውን ቀኑን ሙሉ በሚያቀርቡበት በዚህ ዝግጅት፣ ፋሽን የዓለም ሕዝቦችን የሚያገናኝ ማራኪ የፈጠራ ጥበብ መሆኑን በድጋሚ አስመስክሯል።
ኢቢሲ ከቦታው የሚካሄዱትን ዝግጅቶች እየተከታተለ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
#russia #moscow #brics +FashionSummit #moscowfashionweek #fashion #ebc

16 days ago
🌻 AMAZON FASHION 🌻
🌻 አዲስ አመት አዲስ ዕቃ🌻🌻
👉 1ኛ ደረጃ orginal quality ጨርቅ ሱሪ ከ2500 እስከ 4ሺ፤
👉 ሙሉ ልብስ ከ15ሺ እስከ 23ሺ የተለያዩ ሱፎች ።
👉ባለ ሁለት ቁልፍ ሁሉም ሊኖረዉ ሚገባ (solid black,midium grey,blue black,charcol) ከለሮች ብዙ አማራጭ አሁንም አሉን።
👉 ለድርጅት አስተያየት አለዉ።
ሳይመረጥበት እና ሳያልቅቦት ይምጡ።
ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ፎቶዋቸው ተለቀዋል። follow ያድርጉ ከፎቶቹ ላይ ይምረጡ።
በ2ሺ 500ም ኳሊቲ ሸሚዞች አለን፤ አሪፍ ኮቶችንም አስመጥተናል፤ በርካታ አማራጭ ስላለን ለብዛት ፈላጊዎች በብዙ አማራጭ አለን።
አድራሻ :-ፒያሳ downtown ህንፃ ምድር ላይ
☎️ 0911072936 / 0919339250/ 0948547080
https://t.me/joinchat/AAAA...

26 days ago
የኢትዮጵያን ባህል ከዘመናዊ የፋሽን ጥበብ ጋር ያጣመረችው ዲዛይነር ተሻለች እጋ በአሜሪካው ላ ሮዝ መጽሔት ከፍተኛ እውቅና ተቸራት
#ethiopia | በአሜሪካ በሚታተመው ላ ሮዝ (LA ROSE) መጽሔት የሽልማት ልዩ ዕትም ላይ የ አዶት ዲዛይን (Adot Design) መሥራችና ዋና የፈጠራ ዳይሬክተር ተሻለች እጋ በፋሽን ዘርፍ ጉልህ ተፅዕኖ ከፈጠሩ መሪዎች አንዷ በመሆን ተመርጣለች።
መጽሔቱ በባህል ላይ የተመሠረተ ለወደፊት የተነደፈ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ዘገባ እንደገለጸው ተሻለች ሀገር በቀል እሴቶችን ከዘመናዊ ዲዛይን ጋር በማዋሃድ የአፍሪካን የፈጠራ ጥበብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብቃት በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች።
ለዚህ ታላቅ ስኬቷ መሠረት የሆነው ከቤተሰቧ የወረሰችው ጥበብና መነሳሳት ነው። እናቷ እንሰት ሲያመርቱና ቃጫ ሲያወጡ በጥንቃቄ ትከታተል የነበረችው ተሻለች የእፅዋቱን እያንዳንዱ ክፍል ለአገልግሎት ማዋላቸውን በማየቷ ዛሬ ለምትከተለው ከቆሻሻ ነፃ የሆነ ዘላቂ የፋሽን መርህ መሠረት ጥሏል።
በተጨማሪም ጫማ ጠጋኝ ከነበሩት አባቷ የቁሳቁስ ጥራትን፣ የጥንካሬና የስራ ትክክለኛነት መርሆዎችን በመውረስ ለስራዎቿ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ እንድታወጣ ረድቷታል።
በኢትዮጵያ የራብ ታደግ ዛፍ ተብሎ የሚታወቀውን እንሰት ጠንካራ ቃጫ ዘመናዊና ውድ ለሆኑ አልባሳት ማዘጋጃነት በማዋል ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የፋሽን ጥበብ አስተዋውቃለች።
የእጅ ሽመናን፣ ባህላዊ ጥለቶችን እና የእንሰት ቃጫን በማጣመር የሀገሯን ባህላዊ ማንነት በዓለም አቀፍ የፋሽን መድረኮች ላይ በኩራት አቅርባለች።
በመጽሔቱ መሪ ተብላ መመረጧ የግል ስኬቷ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ባህላዊ እውቀት፣ የሴቶች አመራር እና የአፍሪካ የፈጠራ አቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረትና ክብር እያገኘ መምጣቱን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው። አዶት ዲዛይን ባህልን በመጠበቅና እሴትን በማስቀደም ዓለምን ማስደነቅ እንደሚቻል በተግባር ያሳየበት መንገድ ነው።
#adotdesign #fashion #ethiopianfashion #culture #design #enset #fashiondesigner #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

28 days ago
ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና የሀስትካላ አካዳሚ
(National Crafts Museum & Hastkala Academy)
የጉዞ ማስታወሻ ( ክፍል - 2 )
#ethiopia |በኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የዕደ-ጥበብ ሙዚየምና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ዘለቅን። የብሪክስ ባዛር (BRICS Bazaar - ከመስከረም 10–15, 2026) እየተካሄደ ነው።
የብሪክስ ባዛር፦ ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት (BRICS Bazaar: Crafting Cultures, Connecting People) መሪ ቃል ይዟል። የንግድ ትርኢቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጨርቃጨርቅ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ አማርኛ፣ ህንዲ፣ አረብኛ፣ እስፓንኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ቻይንኛ ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክቶችን ያካተተ ነው።
Ms. Shakshi Gupta - አስጎብኚያችን ስለሙዚየሙ መተንተን፤ ማስረዳት ጀመረች።
የቤንጋል መንደር ገጽታ (ምዕራብ ቤንጋል)
በ'ኩምሃር' (የሸክላ ሰሪ) ባለሙያዎች ማህበረሰብ ከተሰሩ የክሪሽናናጋር (ናዲያ ዞን) የሸክላ ምስሎች፣ ከሳርና የቀርከሃ ጎጆዎች እንዲሁም ከጌጣጌጥ ስራዎች ጋር የገጠር ሕይወትን ያሳያል።
የኪንሃል አሻንጉሊቶች (ካርናታካ)
ከኪንሃል የመጡ በእጅ በእንጨት የተቀረጹ አሻንጉሊቶች ሲሆኑ፣ በኮምጣጤ ፍሬ የተወለወሉና በደማቅ የከለር ቀለም የተሸለሙ ናቸው፤ በታሪክ ለሙሽሮች በስጦታ መልክ ይሰጡ ነበር።
የፓታቺትራ ስዕል (ኦዲሻ)፦ ከፑሪ፣ ራጉራጅፑር እና ቡባኔስዋር የመነጨ ባህላዊ የጨርቅ ላይ ስዕል (ፓታ + ቺትራ) ሲሆን፣ ከራማያና፣ ማሃባራታ እና ባጋቫታ ታሪኮችን ያቀርባል።
የናጋ ጥበብ (ናጋላንድ / ሰሜን-ምስራቅ ህንድ)፦ የጎሳ ባህል ያላቸው የእንጨት የቀደመ አባቶች ምስሎች፣ የተሸመኑ የሸንበቆና ቀርከሃ ቅርጫቶች፣ እንዲሁም በዐጥንት፣ ቀንድ እና ፀጉር ያጌጡ የትንባሆ ማጫሻዎች፣ ጦሮች እና ባርኔጣዎች ናቸው።
የፓቡጂ ፋድ (Phad of Pabuji - ራጃስታን)
በታጠበ የጥጥ ጨርቅ ላይ የሚሳሉ የመጠቅለያ (ስክሮል) ስዕሎች ሲሆኑ፣ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በምዕራብ ራጃስታን ኮሉ (ማርዋር) ይኖር የነበረውን የፓቡጂ የተባለ የህዝብ ጀግና ህይወትና ተረቶች ያሳያሉ።
ታሪኩ ሙሉ ሌሊት በሚከናወኑ ስነ-ስርዓቶች ላይ 'ቦፓስ' (ከናያክ ማህበረሰብ የተወጣጡ ዘማሪዎች) በትልልቅ የሸክላ ማማዎች እየታጀቡ 'ፓቡጂ ራ ፓንዋራ' የተሰኙ የጀግንነት ዜማዎችን ሲዘምሩ ይተረካል።
ስዕሎቹ በቢልዋራ (ሜዋር) ሻህፑራ በሚገኙ የ'ጆሺ' ቤተሰብ ባለሙያዎች ብቻ የሚሳሉ ሲሆን፣ ጨርቁን አዘጋጅተው መልካም ቀን በመጠበቅ በባህላዊ ተፈጥሯዊ ቀለሞች ይስሏቸዋል።
አስጎብኚያችን Ms. Shakshi Gupta - ፈትፍታ የማጉረስ ትህትና ያላት ናት።
ጥያቄ አለ? - አለች።
የዶክራ ብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ (Dhokra Metal Craft - ቻቲስጋርህ እና ማዕከላዊ/ምስራቅ ህንድ) ጥበብ ማውጋት ቀጠለች።
በሸክላ ቅርጾች ላይ በሚቀልጥ ሰም (cire perdue) የሚሰራ የ5,000 ዓመታት ዕድሜ ያለው የብረት ማቅለጥና ማፍሰስ ጥበብ ሲሆን፣ የተጠላለፈ ወይም የተጠቀለለ የላይኛው ገጽታ ቅርፅ በመያዙ ይታወቃል።
በቻቲስጋርህ (ባስታር)፣ ኦዲሻ፣ ጃርካንድ፣ ምዕራብ ቤንጋል እና አንድራ ፕራዴሽ ባሉ ከፊል-ዘላን የጎሳ ብረት ሰሪዎች የተሰራ ሲሆን፣ የእህል መለኪያ ማሰሮዎችን፣ የከብት ቃጭሎችን እና የነሐስ የጎሳ ምስሎችን (እንደ ከአደን የሚመለሱ አደንኞችን ምስል) ያመርታሉ።
የኮንድሃ / ኮንድ ነሐስ ስራዎች
(Kondha Bronzes - ኦዲሻ)
በኦዲሻ የራያጋዳ እና ጋጃፓቲ ዞኖች በሚኖሩ የኮንድሃ (ዶንጋሪያ ኮንድሃ) የጎሳ ቡድኖች በብረት ሰሪዎች ለዘመናት የተከናወነ የነሐስ ማፍሰስ ጥበብ ነው።
ሙሉ በሙሉ በማፍሰስና ሰም በማቅለጥ ቴክኒኮች ለ'ዳራኒ ፔኑ' (የምድር አምላክ) የመስዋዕት ስጦታዎች፣ የክብረ-በዓል ምልክቶች፣ የተለያዩ ቅርሶች እና በስጦታ (ሚዜ) የሚሰጡ አሻንጉሊቶችን ለመስራት ያገለግላል።
የካርናታካ የቡታ እምነት ቅርጻ ቅርጾች
(Bhuta Cult Sculptures - ካርናታካ)
በባህር ዳርቻይቱ ካርናታካ ኡዱፒ ዞን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጡ በእንጨት የተቀረጹ ምስሎችና የነሐስ ጭንብሎች ሲሆኑ፣ ከ'ቡታራዳኔ' (የመንፈስ አምልኮ ስነ-ስርዓት) ጋር የተያያዙ ናቸው።
በ'ጉዲጋር' የእደ-ጥበብ ማህበረሰብ ከጽኑ የጃክፍሩት እንጨት የሚቀረጹ ሲሆን፣ እንደ 'ፓንጁርሊ' (የዱር አሳማ መንፈስ)፣ 'ፒሊቻንዲ' (የነብር መንፈስ)፣ 'ጁማዲ' እና እንደ 'ኮቲ እና ቼናያ' ያሉ የአባቶች ጀግኖችን ይወክላሉ።
በወፍ በረር ማጠቃለያ ላይ ደረሰች
የማዱባኒ ስዕል (Madhubani Painting - ቢሃር)
በሰሜን ቢሃር የሚቲላ አካባቢ የሚገኝ ጥንታዊና መስመራዊ የህዝብ ስዕል ዘይቤ ሲሆን፣ በባህላዊ መልኩ በመንደር ሴቶች በግድግዳዎችና ወለሎች ላይ ይሳላል።
'ኮህባርቺትራ' (ለአዲስ ተጋቢዎች የመኝታ ክፍል ግድግዳ ስዕል) እና 'አሪፓና' (ለስለትና ባህላዊ ስነ-ስርዓቶች የሚሰራ የወለል ጌጣጌጥ) የሚያካትት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በወረቀትና በሸራ ላይ ይሰራል።
ጠቅላላ የብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ
(General Metal Crafts)
ከዕለት ተዕለት ቁሳቁሶች፣ የማስቀመጫ ሳጥኖችና የአልጋ እግሮች እስከ ባህላዊ ምስሎችና የወፍ እና የእንስሳት ቅርጽ ያላቸው የሱፓሪ መቁረጫዎች (sarota) ድረስ ያሉትን ባህላዊ የህንድ የነሐስና የብረት ጥበቦችን ያጎላል።
***
ከሙዚየም ወደ ባዛር ዘለቅን
ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በBRICS Bazaar 2026 ላይ ተሳትፈዋል
በሕንድ ኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ከመስከረም 10 እስከ 15 ቀን 2026 እየተካሄደ ባለው BRICS Bazaar 2026 ላይ ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ሀገራቸውን ወክለው ተሳትፈዋል።
ዝግጅቱ “Crafting Cultures, Connecting People” — “ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ የተለያዩ የBRICS አገራትን ባህላዊ የእደ ጥበብ፣ ፋሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ሸክላ ስራ እና ሌሎች ባህላዊ የእጅ ሥራዎችን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ያስተዋውቃል።
እጂጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ
ከኢትዮጵያ በHandweaving – የእጅ ጨርቃ ጨርቅ ሥራ የተሳተፈችው እጅጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ የፋሽን ዲዛይነርና ሥራ ፈጣሪ ስትሆን፣ Ejig Tibeb መስራች እና Ethiopian Fashion Designers Association ተባባሪ መስራች ናት።
የኢትዮጵያን ቡና ለታዳሚዎቹ በክብር አጠጥታለች።
መዓዛ አሰግድ አሰፋ
በሌላ በኩል መአዛ አሰግድ አሰፋ (Meaza Asegid Assefa) በHand Modelling / Pottery – የእጅ ሸክላ ሥራ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላለች።
“Meaza Pottery – መአዛ ሸክላ ሥራ” በሚል የንግድ ስም ትሠራለች። በእጅ የተሰሩ ባህላዊ የሸክላ እቃዎችንና መያዣዎችን በማምረት የባህላዊ የሸክላ ጥበብን ለመጠበቅና ለማስቀጠል እየሰራች መሆኑ ተናግራለች።
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ውበት በዓለም መድረክ
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በዚህ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረክ መሳተፋቸው፣ የአገሪቱን ባህላዊ የእጅ ሥራዎች፣ ፋሽንና የፈጠራ ሥራዎችን ለዓለም ማስተዋወቅ ከመቻሉ ባሻገር ለእደ ጥበብ ምርቶች አዳዲስ የገበያና የትብብር ዕድሎችን የሚከፍት አጋጣሚ ነው።
የጉዞ ማስታወሻ
ከፍል ( 3 ) ይቀጥላል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
Special thanks :
#india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics2026 #bricsbazaar2026 #ethiopia #india #newdelhi #crafts #handicraft #handweaving #pottery #ethiopianfashion #getutemesgen

4 months ago
የኢትዮጵያ የፋሽን ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ሊያስተዋውቁ ነው
#ethiopia | ታዋቂዋ የካሜሩን አርቲስት ሽሪ አቹ የአፍሪካን አህጉራዊ ትስስር በስነ-ጥበብና በፋሽን ለማጠናከር ያለመውን ፓን አፍሪካን ኢኒሼቲቭ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የጨርቅ ዲዛይን ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች።
ይህንን ተከትሎም የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉበት ትልቅ የፋሽን ውድድር በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክ እና መገለጫዎች በልዩ ሁኔታ በሚያንጸባርቅ ጨርቅ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ይህ ውድድር፣ ከኢትዮጵያ የተሳተፉትን ባለሙያዎች ለመለየት ነገ በሚካሄድ የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ትዕይንት እና በዳኞች ምዘና አማካኝነት ማጠቃለያውን ያገኛል።
የፕሮጀክቱ አዘጋጅ ሽሪ አቹ ቀደም ሲል በአውስትራሊያ ባቀረበቻቸው የስዕል ስራዎቿ አማካኝነት በርካታ ተመልካቾች አፍሪካን ለመጎብኘት መነሳሳታቸውንና ይህም ትልቅ እርካታ እንደሰጣት ገልጻለች።
ይህንኑ መነሻ በማድረግ ሰዎችን በባህል ማስተሳሰር የሚችለውን የፓን አፍሪካን ጨርቅ ሀሳብ ያመጣች ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ዓመት በካሜሩን ኤምባሲ ውስጥ ይፋ ተደርጓል።
ጨርቁ የሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካን የሚወክሉ የዘጠኝ አገራትን ታሪክና ምልክቶች የያዘ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም አገራቱ ጨርቁን በመጠቀም አስደናቂ ዲዛይኖችን እንዲፈጥሩ እና የአፍሪካን አንድነት እንዲያሳዩ ማስቻል ነው።
የዘንድሮው የመጀመሪያው ውድድር በካሜሩን እና በኢትዮጵያ ብቻ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ ሽሪ አቹ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ላይ የቀረበውን የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ እንቅስቃሴና የኮሌጁን ዲሬክተር ቃለ-መጠይቅ ከተመለከተች በኋላ ከተቋሙ ጋር አብራ ለመስራት መወሰኗን አስታውቃለች።
በዚሁ መሠረት ለዋናው የብቃት ውድድር ያለፉት የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች ናታንሊ አስፋው፣ ያሲሚን ኢብራሂም እና ሜቴ ሀይለማሪያም መሆናቸው ታውቋል።
እነዚህ ሶስት ወጣት ዲዛይነሮች ያዘጋጇቸው አልባሳት ነገ በሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ሾው ላይ በሞዴሎች አማካኝነት ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣ አሸናፊውን ለመለየት ከኢትዮጵያ የሚሰበሰበው የሕዝብ ድምፅ 25 ፐርሰንት ድርሻ ይኖረዋል።
ጠቅላላው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እና የዳኞች ግምገማ ተደምሮ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ውጤቱ በይፋ የሚገለጽ ሲሆን፣ ከአገሪቱ አሸናፊ የሚሆነው ዲዛይነር በመጪው መስከረም 26 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ታዋቂው የስሚዝሶኒያን ብሔራዊ የአፍሪካ ስነ-ጥበብ ሙዚየም ላይ በሚዘጋጀው ታላቅ የፋሽን ሾው ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የመቅረብ እና ስራዎቹን ለዓለም የማሳየት ሰፊ ዕድል ያገኛል።
#fashion #art #panafrican #design #ethiopiandesigners #nextfashioncollege #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
ቴክኖ ኢትዮጵያ ለመላው የስነ ጥበብ ባለሙያዎች አሪፍ ነገር ይዞ መጥቷል፡፡ ቴክኖ ኦትዮጵያ በካሞን የስልክ ሞዴሉ ባላፉት አመት ከBoard CellPhone Ethiopia ጋር በመሆን እና ኢትዮጵያን በመዞር እና በመቃኘት በቴክኖ ካሞን ስልክ የተነሱ ፎቶዎችን በኤግዚቢሽን መልክ ለናንተ ሲያደርስ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ በካሞን 50 ሲሪየስ ስልኩ ለሚያዘጋጀው ለየት እና ከፍ ያለ የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ከስነ ጥበብ ባላሙያዎች ጋር አብሮ መስራትን አስቧል፡፡
ከቴክኖ ሞባይል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን ይህን ዕድል ማንኛውም Installation Artists፤ Muralists፤ Sculptors፤ Set Designers ፤Fashion / Textile Artists፤ Digital Artists፤ Motion Graphic Artists ፤Traditional Craft Artists ፤Multidisciplinary Creatives ሙያዎች ላይ ያለ ግለሰብ ወይንም ቡድን ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንዲሁም መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡ መልካም ዕድል ቴክኖ ኦትዮጵያ
https://docs.google.com/fo...

Sponsored by
Surafel
5 months ago
ቴክኖ ኦትዮጵያ ለመላው የስነ ጥበብ ባለሙያዎች አሪፍ ነገር ይዞ መጥቷል፡፡ ቴክኖ ኦትዮጵያ በካሞን የስልክ ሞዴሉ ባላፉት አመት ከBoard CellPhone Ethiopia ጋር በመሆን እና ኢትዮጵያን በመዞር እና በመቃኘት በቴክኖ ካሞን ስልክ የተነሱ ፎቶዎችን በኤግዚቢሽን መልክ ለናንተ ሲያደርስ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ በካሞን 50 ሲሪየስ ስልኩ ለሚያዘጋጀው ለየት እና ከፍ ያለ የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ከስነ ጥበብ ባላሙያዎች ጋር አብሮ መስራትን አስቧል፡፡
ከቴክኖ ሞባይል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን ይህን ዕድል ማንኛውም Installation Artists፤ Muralists፤ Sculptors፤ Set Designers ፤Fashion / Textile Artists፤ Digital Artists፤ Motion Graphic Artists ፤Traditional Craft Artists ፤Multidisciplinary Creatives ሙያዎች ላይ ያለ ግለሰብ ወይንም ቡድን ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንዲሁም መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡ መልካም ዕድል ቴክኖ ኦትዮጵያ
https://docs.google.com/fo...
ከቴክኖ ሞባይል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን ይህን ዕድል ማንኛውም Installation Artists፤ Muralists፤ Sculptors፤ Set Designers ፤Fashion / Textile Artists፤ Digital Artists፤ Motion Graphic Artists ፤Traditional Craft Artists ፤Multidisciplinary Creatives ሙያዎች ላይ ያለ ግለሰብ ወይንም ቡድን ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንዲሁም መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡ መልካም ዕድል ቴክኖ ኦትዮጵያ
https://docs.google.com/fo...
7 months ago
የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች የዓለምን የፋሽን መድረክ እንዲቀላቀሉ የሚያስችል አዲስ ዕድል ይፋ ሆነ!
#fastmerjea :የፋሽን ኢንዱስትሪውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረጽና የፈጠራ ዘርፉን ዓለም አቀፋዊ .የተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያለመ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተጀመረ።
"የፋሽን ረዚደንሲ" (Fashion Residency) የተሰኘውና በብሪቲሽ ካውንስል፣ በፖል ስሚዝ ፋውንዴሽን፣ በስቱዲዮ ስሚዝፊልድ እና በአይስ አዲስ (iceaddis) ትብብር የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፤ በኢትዮጵያ፣ በዚምባብዌ እና በዩናይትድ ኪንግደም ዲዛይነሮች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የብሪቲሽ ካውንስል ተወካይ ረሺዳ እንደገለፁት፤ ስድስት ተማሪ ዲዛይነሮች በለንደን በሚገኘው ስቱዲዮ ስሚዝፊልድ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ ጥልቅ ስልጠና እንደሚያገኙ የገለፁ ሲሆን ስልጠናው ዲዛይነሮቹ ከዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች ጋር እንዲገናኙና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ነዉ የተገለፀዉ።
በዕለቱ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር ሰሎሜ አስፋው፤ በፋሽን ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እና የቴክኒክ ስልጠና ውስንነት የገለጸች ሲሆን፤ እንዲህ አይነት መድረኮች ግን አዳዲስ አመለካከቶችን ለማግኘትና የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ መሆናቸውን አስረድታለች።
መርሃ ግብሩ በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባራዊ ልምምድ የተመጣጠነ ሲሆን፣ የባህል ልውውጥ፣የስራ ጉብኝት እንዲሁም የንግድ ስልጠና እንደሚያካትት ሰምተናል።
መርሃ ግብሩ የባህል ልውውጥን፣ የስራ ጉብኝቶችን እና በብራንድ ግንባታ ላይ ያተኮሩ የንግድ ስልጠናዎችን ያካተተ ሲሆን፤ በሀገራቱ መካከል ያለውን የፈጠራ ኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

9 months ago
🎁 የበዓል ስጦታ ለ608 ህጻናት! 👗👕
"ግዮን ፋሽን፡ በ95% ሴቶች የሚመራው ሀገር በቀል ተቋም በጎ ተግባር!"
#ethiopia | ለጥምቀት በዓል ስጦታ ይሆን ዘንድ፤ በልጆች አልባሳት ምርት ላይ የተሰማራው ሀገር በቀል ድርጅት ግዮን ፋሽን (Ghion Fashion)፤ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የ608 ህጻናት አዳዲስ አልባሳትን በድጋፍ አበርክቷል።
ስለ ድጋፉ እና ተቋሙ:
ዛሬ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገው የድጋፍ መርሐግብር ላይ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል ሲሳይ እንደገለጹት፤ እነዚህ አልባሳት በተለይ ለሙዳይ ልጆች ታስበው በፋብሪካው የተመረቱ ናቸው።
ግዮን ፋሽን ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 95 ከመቶው ሴቶች መሆናቸው ተቋሙን ልዩ ያደርገዋል!
ወ/ሮ ሙዳይ ምን አሉ?
የማህበሩ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፤ "ግዮን ፋሽኖች እዚሁ ተገኝተው፣ ልጆቻችንን ጎብኝተውና በልዩ ሁኔታ ልብስ አምርተው ስላመጡልን እናመሰግናለን" ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
እንዲህ ያሉ ሀገር በቀል እና ለወገን የሚደርሱ ተቋማት ይብዙልን!
መልካም በዓል!
🌼
#ghionfashion #mudaycharity #donation #timket #madeinethiopia #womenempowerment #charity #muday #charity #ethiopia

የቬንዙዌላው ሰው ቱታ ''ቀን ወጣለት''
የደራው መጽሔት
#yederaw | በቅርቡ በአሜሪካ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት የቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ፣ በወቅቱ ለብሰውት የነበረው የናይኪ (Nike) ብራንድ ቱታ ባልተጠበቀ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነትን እያገኘ መሆኑ ተዘግቧል።
📈 ገበያው የደራለት ናይኪ
ማዱሮ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳዩ ምስሎች በዓለም መገናኛ ብዙኃን ከተሰራጩ በኋላ፣ እርሳቸው ለብሰውት የነበረው ተመሳሳይ ቱታ በአሜሪካ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ የናይኪ መደብሮች ውስጥ ሙሉ በሙሉ እስከመሸጥ ደርሷል። ኩባንያው ከዚህ ክስተት በኋላ የቱታው ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረለት ታውቋል።
⚽ የማዮርካ ተጫዋቾች
ይህ ቱታ ወደ ስፖርቱ ዓለምም ዘልቋል። በትናንትናው ዕለት የስፔኑ ክለብ ማዮርካ ተጫዋቾች ለጨዋታ ወደ ስታዲየም ሲያመሩ፣ ሁሉም ተመሳሳይ የሆነውን የማዱሮ የናይኪ ቱታ ለብሰው መታየታቸው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ይህም ክስተት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
🔍 ለምን ትኩረት ሳበ?
አብዛኛውን ጊዜ የዓለም መሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚለብሷቸው አልባሳት ለታሪክ ማስታወሻነት ወይም ለተቃውሞ ምልክትነት ይውላሉ። አሁን ግን ይህ የናይኪ ቱታ ከፖለቲካዊ ትርጉሙ ይልቅ እንደ ዘመናዊ የፋሽን ምርጫ (Fashion Statement) እየታየ ይገኛል።
የደራው መጽሔት
''ፀሐይ አትጠልቅም''
#yederaw #maduro #niketracksuit #mallorca #fashiontrend #breakingnews #nike #sportsfashion #venezuela #currentevents

10 months ago
ፍቅረኛህን ነካ ነካ አድርጋትና ከውጪ ዘፋኞች የማን የማን ሙዚቃ ይመችሻል? በላት!
Tayla, Shenseea ፣ Spice, Ayra Starr, Burna Boy, Rema, Wizkid, Davido, Tiwa Savage ወዘተ ካለችህ:: ይቺ Generation Alpha የዚህ ዘመን ፈረካ ቸከስ ናት:: Stereotype & Extrovert ናት:: ሪትም ባለበት ነገር በሙሉ ምቾቷ አለ:: አስተሳሰቤም ሆነ ንግግሬ ግልፅ እና ግልብ ነው ትልሃለች ግን ከሎጂክ በእልፍ አዕላፍ ማይል የራቀ ግልፅነት ነው ያላት:: ኢ-ሎጂካል ምስኪን የዋህ ናት:: ውስብስብ እና Global Trend በሆኑ አጀንዳ ዙሪያ የሚያግባባ የንግግር ጠረጴዛ አይኖርህም ከዚህች ጋር:: የተመተረ ውስጥ ዓለም ነው ያላት:: ሰውነቷን የማያንቀሳቅስ ሙዚቃ በሙሉ ቴስቷ አይደለም:: በማህበራዊ ህይወቷም ይሄንኑ ነው የምታንፀባርቀው:: አብራችሁ ለቅሶ ብትሄዱ 'ምንድነው ጭር አለ ዲጄው አይመጣም እንዴ?" ማለቷ አይቀርም:: የወደፊት መፃኢ ዕድሌም ሆነ ያለፈው ህይወቴ ቴራፒ የሚያገኙት ክለብ እና ፓርቲ ላይ ነው ብላ ታስባለች:: ይቺን ጠዋት እና ማታ በልዩ ክትትል ያዛት!
__
Young Thug, 21 Savage, Gucci Mane, Young Jeezy, Future, Lil Uzi Vert,ካለችህ ደግሞ Rich or Die Flexing የሚል ሜንታሊቲ ነው ያላት:: ገንዘብ ከሌለህ አፍንጫህን ላስ ብላ ትሄዳለች:: በአስኮም አለች በፍራንችስኮ አምልኮ እና ስግደቷ ለገንዘብ ብቻ ነው:: በገዛ ህይወቷ መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ የምትፈቅደው ገንዘብንን እና ላግዠሪ Flex ሰዎችን ነው:: ነፃነት አፍቃሪ ናት ደንብ ፣ ገደብ ፣ ወደብ የመሳሰለ ኮተት አይመቻትም:: እንደ እሷ አይነት Luxury Flex የሆነ ጀማ ነው የሚመቻት ፎከታም Hustler ትፀየፋለች። የነፍሷም የስጋዋም ኢንጂን ገንዘብ እና ምቾት ነው:: በዛ ላይ ድብቅ እና ወላዋይ ናት:: በአጭሩ ወንድሜ ለፍቅርም ለትዳርም አትሆንም እሷ Toxic Romance Enthusiast እና Fashion Killa ጎልድ ዲገር ናት:: አጠገብህ ባለው ሁለት ሊትር ጎልድ ውሃ አናቷን ብለህ ወደ እነ ላካትና አንተ አርፈህ ስራህን ወጥር ብሮ::
_
Pop Smoke, Lil Durk, Chief Keef ምናምን ይመቹኛል ካለችህ ደግሞ ይቺ ፍፁም ከራሷ የራቀች ናት:: አለመብሰሏን ፣ ድክመቷን ፣ እንጭጭነቷን በPost Traumatic Stress Disorder (PTSD) ለመሸፈን ነው የምትጥረው። ቤተሰቦቼ ፣ ዘመዶቼ በዙሪያዬ ያሉ በሙሉ አይወዱኝም ትልሃለች:: ጠጋ ብለህ አቅፈህ ልታስረዳት ስትሞክር አመናጭቃህ የሆነ ጥግ ስር ትሄድና ከጥቁር ሆዲዋው ኪስ ውስጥ ግድንግድ ስቲክ አውጥታ መሸብለል ትጀምራለች:: ይቺን ወስደህ ሌዘር ጫኬት በአንበሳ ቆዳ ጫማ ለሚለብሰው እና ወያኔ DX ለሚነዳው ኮስታራው አጎቷ አስረክባት:: እዛው የሚያደርጉትን ያድርጓት:: ምንም አባቷ አልሆነችም የሰፈሯ ፍሪክ ነው ዊድ አስጀምሯት እንዲህ ጨለፍ ጨለፍ የምትጫወትብህ ተዋት:: ኑሮህ ላይ ፎከስ አድርግ ብሮ!
_
Dr. Dre, Ice Cube, Eazy-E, DJ Yella, Snoop Dogg, 50 Cent, The Game, Eminem, Lil Wayne ወዘተ አይነት Gangsta Rappers ይመቹኛል ካለችህ ይቺ ማንንም አታምን ተጠራጣሪ ናት። ከሙገሳ ቀድማ ስራዋ ላይ ነው ፎከስ የምታደርገው:: የውሸት ፍቅር አይመቻትም:: አታስመስል:: ስታስመስል ካገኘችህ በዚዳን ቴስታ ነው ኮማ ውስጥ የምትከትህ:: እውነተኛ ፍቅር ዋጋ ትሰጣለች:: በራሷ ጥራ ያመጣችውን ስኬት ታከብራለች:: ነገሮች ከሆኑ በኋላ ወደ ኋላ ለመመለስ ምንም አይነት የኋላ የስሜታት ማርሽ አልተገነባላትም: ነገሮችን በቀጥታ ታስተናግዳለች:: አግብተሃት ልጅ ብትወልድ እንኳ አራስ ጥየቃ የመጡትን የመንደር አዛውንቶች F- Word እየተጠቀመች ልታስተናግድ ስለምትችል አትቀየማት ነፍሷ እንደ ፍየል ማህፀን ግልብ ነው ይልቅ በንስሃ አቧቷ አስመክራት:: እንዳትለያት!
____
Don Williams, Kenny Rogers, Keith Urban, Dolly Parton, B.B. King, Etta James, Tracy Chapman ወዘተ አይነት የCountry, Blues እና Folk ዘውግ ዘፋኞች ይመቹኛል ካለችህ ይቺ በችግር እና በፅናት የተሞረደ ማንነት ነው ያላት:: በብዙ መከራ ውስጥ መሽቶ በመንጋት አልፋለች። ስብዕናዋ በመከራ እና በችግር ወይም በግርግር ህይወት ተሞርዷል:: ጫጫታ ቱማታ ከሞላበት ቦታ ይልቅ ትናንሽ አርምሞን የካደሙ ቦታ ምቾት ይሰጣታል:: ለቤተሰቧ ለመንደራ ለማህበረሰቧ ታስባለች የአደባባይም የቤት ውስጥም ጭምት ናት:: ግን ደግሞ ከዚህ ጀርባ የትም Grand Mall ውስጥ ያልተሸጠ ግላዊ ነፃነት እና ግልብነት አላት:: በሯን ዘግታ እርቃኗንን ምናምኗን እየነካካች እያጨሰች ዋይኗን ትጠጣለች:: ትፅፋለች:: ትሰርዛለች:: ትደልዛለች:: ወዘተ! ይቺ የያ ትውልድ የአይን እማኝ ናትና ምርጫው የአንተ ነው
_
Tupac, Nas, B.I.G, Wu-Tang Clan ወዘተ ካለችህ ይቺ ደግሞ ጦር ሳትሰብቅ ጋሻ ሳትወድር በመፈጠሯ ውስጥ ብቻ ከአምላኳ የተሰጣትን ነፃነት መቀዳጀት የቻለች ስማርት ነፍስ ናት:: ስለማህበራዊ እና ፖለቲካ ነገሮች ግንዛቤ አላት:: ስለ ጥቁሮች መብት ፣ መልዕክት በንቃት ታዳምጣለች:: ፊልም መርጣ ትሾፋለች::
ሮክስ ቲምበርላንድ ፣ ቪንቴጅ ቲሸርት ፣ ክላሲክ ስኒከር ትለብሳለች ምናምን ነገር ይቺ ፀዴ ናት ከቻልክ አግባት ካልቻልክ ስልኬን ስጣት እኔ አገባታለሁ!
____
የፍቅረኛችሁን የሙዚቃ ቴስት ንገሩኝና ባህሪዋን እነግራችኋላሁ 🙌
ተጻፈ በYoakin Bekele Pachi

11 months ago
De-Next-Ev ዲፕሎማቲክ ባዛር
በሦስት ሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች የተዘጋጀ ልዩ ዲፕሎማቲክ ባዛር በዲሊኦፖል ሆቴል ሊካሄድ ነው
📌መግቢያ በነፃ
#ethiopia | የElvezet International Events መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሩት ሀይሉ፣ ከዲሊኦፖል ሆቴል እና ከNext Fashion Design ጋር በመተባበር በዓይነቱ ልዩ የሆነውን "De-Next-Ev ዲፕሎማቲክ ባዛር" በጋራ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ይህ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ታላቅ ዝግጅት ከኅዳር 19/2018 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21/2018 ዓ.ም ድረስ በዲሊኦፖል ሆቴል ይካሄዳል። ዝግጅቱ ልዩ የሚያደርገው በሦስት ሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች ትብብር መፈጠሩ ነው።
ባዛሩ ዲፕሎማቶችን፣ የኤምባሲ ተወካዮችን፣ የንግድ ተቋማት መሪዎችን እና ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ እንግዶችን የሚያገናኝ
ሲሆን ዋናው ዓላማ ጠንካራ የሆኑ ጀግና ሴቶችን ማበረታታትና፣ ሴቶች በጋራ ሲሰሩ ምን ማከናወን እንደሚችሉ ማሳያ መሆን ነው ተብሏል።
* ኅዳር 19/2018 ዓ.ም (ዓርብ)፡ ዝግጅቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይኖረዋል። ቀኑን ሙሉ የተለያየ አማራጮችን የያዙ ተፈላጊ ቬንደሮች የሚገኙ ሲሆን፣ ምሽት ላይ ደግሞ የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት እና ልዩ የምግብ መስተንግዶ ይኖራል።
* ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)፡ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ በNext Fashion Design የተዘጋጀው ዓመታዊው AFFA Award መርሃ ግብር ይካሄዳል።
* ኅዳር 21/2018 ዓ.ም (እሁድ)፡ የመጨረሻው ቀን በዲሊኦፖል ሆቴል የተዘጋጀ ልዩ ብራንች(ቁርስ እና ምሳ) ፣ እንዲሁም በመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ማራኪ የባህል ውዝዋዜዎች ይቀርባሉ ባዛሩም አመሻሽ ላይ በደማቅ ሁኔታ ይደመደማል ተብሏል።
ሩት ሀይሉ እንዳሉት፣ ''ዝግጅቱ ከማዝናናት ባለፈ በርካታ የኔትዎርኪንግ (Networking) እድሎችን ያካተተ ነው። የዝግጅቱ አዘጋጆች ይህን ባዛር በአመት ሦስት ጊዜ ማለትም በአዲስ ዓመት፣ በገና እና በፋሲካ ሰሞን ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

📢 ለድምፅ ማሰባሰቢያ (Vote Campaign)
(African Fashion & Arts Award - AFAA) 2025 በይፋ ታጭታለች! 🏆
✨ ታላቋን ኢትዮዽያዊት ዲዛይነር ዬርዲ ዲዛይን (ጁዲ) ተባብረን Vote እናድርጋት ✨
ነገ November 15 /2025
በሚጠናቀቀዉ African Fashion & Arts Award - AFAA 2025 የሁላችንም ድምፅ ያስፈልጋታል ።
ድምፅዎ ለፋሽን ኢትዮጵያ ወሳኝ ነው!
ታላቅና አስደሳች ዜና!
የኛዋ የፈጠራ ዲዛይነር ዬርዲ ዲዛይን (ጁዲ) ለታላቁ አፍሪካ ፋሽን እና ጥበብ ሽልማት (African Fashion & Arts Award - AFAA) 2025 በይፋ ታጭታለች! 🏆
የዬርዲ ዲዛይን ሥራ ቀላል ፋሽን አይደለም፤ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ባህላዊ ውበት ከዘመናዊነት ጋር በማዋሃድ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ልዩ አሻራ እያሳረፈች ነው። ድሏ የሷ ብቻ ሳይሆን፣ የእኛ የኢትዬዽያዊያን የፈጠራ ኃይል ማሳያ ነው።
🗳️ አሁን ድምፅዎ ያስፈልጋታል!
ይህንን ክቡር እውቅና እንድታገኝ ሁላችንም ለዬርዲ ዶዛይን (ጁዲ) ድምጻችንን እንስጣት። ጊዜው አሁን ነው!
ድምፅ ለመስጠት: በኢንሰተግራም ላይ AFAA -Africa Fashion and Art Award ሊንኩን በመጫን Emerging Fashion Designer Award በሚለው ስር Yordi Design የሚለው ስም ላይ vote ያድርጉ
ድምፅ ስለሰጡ እናመሰግናለን!
ይህን መልዕክት ለሁሉም ፋሽን ወዳጆች በማጋራት (Share በማድረግ) የድርሻችሁን ተወጡ !!!
https://afaawards.org/cont...

📌የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተጀመረ
የአፍሪካን የቆዳ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የአልባሳትና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን የሚመራው 11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት (AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK) ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ይካሄዳል።
የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ከጨርቃጨርቅ፣ ከአልባሳት፣ ከቆዳ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከቤት ማስጌጫ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን ያሳትፋል።
ከ30 በላይ አገሮችን የሚወክሉ ከ200 በላይ አምራቾች በሚሳተፉበት በዚህ ዝግጅት ላይ፣ ምርቶችና ፈጠራዎች ከ7ሺ ለሚበልጡ የንግድ ባለሙያዎችና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ተመልካች ፊት ቀርበው የሚታዩበት መድረክ ነው።
የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ላለፉት ዓመታት ከ50ሺ በላይ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለወጣቶች መፍጠር መቻሉን ተገልጿል።
በዚህ በ11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ላይ በዘርፉ ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን ማለትም የኢኮኖሚ፣ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች (INTELLECTUAL PROPERTY RIGHTS) እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚና ላይ ትኩረት ያደርጋል።

1 year ago
ዮፍቲ ጊፍት እና ሰርፕራይዝ
#ethiopia | እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ እያለ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ፓኬጆችን አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ነው 📱0941510996#reels #reelsinstagram #instagram #viral #trending #explore #explorepage #instagood #fyp #love #reelitfeelit #tiktok #trendingreels #reelsvideo #foryou #fashion #photography #like #instadaily #india #follow #reel #viralreels #followforfollowback #memes #viralvideos #instagramreels #music #instareels #reelkarofeelkaro

ዳ ማሪዮስ ፋሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ከአለም አቀፍ ትምህርት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ !!
Damarios Fashion & Technology Institute በቦሌ ብራስ ኬኬር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ አለም አቀፍ ይዘትን በጠበቀ መልኩ በቅርቡ የተከፈተ የስልጠና ተቋም ሲሆን የአገራችንን የትምህርት ጥራት ደረጃን ለማሻሻል በማለምና ሙያዊ ትምህርቶችን በመስጠት የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በማተኮር ወጣቶችን በማስተማርና ወደስራ ለማሰማራት አቅዶ በፋሽን ዲዛይን ፥በስነዉበት ትምህርት ( Makeup ) ፥ በ ቢዝነስና ኮምፕዩተር ስልጠናዎች ፥ Security Officers (መሳሪያ ኣልባ ጥበቃ አገልግሎቶች ) እና በ ሞደሊንግ ስልጠና የትምህርት ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ሙሉ እውቅና እና ፈቃድ ያገኘ ተቋም ነው ።
Rome business school በጣሊያን ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመርያው ሲሆን በካምፓስ ሆነ በ(online ) ማስተር እና MBA ፕሮግራሞችን በመስጠት ተቋሙ ከ150 አገራት የመጡ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ የሚገኝ እውቅ ተቋም ነው ።
በሁለት የትምህርት ተቋማት መካከል የተደረገው የጋራ ስምምነት ሰነድ የትምህርትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የተሻሻሉ የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ፤ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን የትምህርት አቅርቦቶች እና አዳዲስ የትምህርት እድሎችን በመስጠት፣ ሙያዊ እድገትን በማስተዋወቅ እና አጠቃላይ የትምህርት ልምድን በማሳደግ ተማሪዎችን፣ መምህራንና አጠቃላይ የተቋሙን ማህበረሰብ ዓለም አቀፍ ትምህርትን ለማዳበር የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉም እንዲሁም መምህራን ከአለም አቀፍ ባልደረቦች እንዲማሩና የልምድ ልዉዉጥ እንዲቀስሙ ዕድል የሚያገኙበት እና ለተማሪዎቻችን ደግሞ ከአገር ዉጭ በመዉጣት ተጨማሪ የበለፀገ የትምህርትና የተግባር እውቀት የሚቀስሙበት አልፎም በአለም አቀፉ ገበያ ተዎዳዳሪ የሚሆኑበት እድልን የሚፈጥር ስምምነት ነው ። በተቋማችን የትምህርት ጥራት በመተማመንና የኢትዮጲያን የትምህርት ደረጃን አብሮ ለማሳደግ ይህንን መሰል ዕድል ስላመቻቸልን Rome business school እያመሰገንን ያሉን ቦታዎች ውስን እነደመሆናቸው እርሶም የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በመረጡት የሞያ ዘርፍ ተመዝግበው ይሰለጥኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ።

ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር በፋሽን ኢንደስትሪው አሸናፊ ሆነች
በፋሽን ኢንደስትሪው ውስጥ የአፍሪካን ተሰጥኦ ለማጉላት ያለመውና በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ “African Fashion Up 2025” ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር ሐዊ ሲሳይ ሚደቅሳ አሸናፊ ሆናለች።
ሐዊ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ከተውጣጡ ምርጥ ዲዛይነሮች ጋር በተወዳደረችበት በዚህ ውድድር፣ የፈጠራ ብቃቷን፣ ልዩ የአልባሳት ቅንጅቷን እና ከአፍሪካዊ ማንነት ጋር የተዋሃደውን ዘመናዊ አቀራረቧን በማሳየት የዳኞችን ቀልብ ለመሳብ ችላለች።
የኢትዮጵያዊቷ ሐዊ ሲሳይ ድል የአፍሪካ ፋሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን እውቅና ከፍ የሚያደርግ ነው። ዲዛይኖቿ የአፍሪካን ወግና ታሪክ ከዘመናዊነት ጋር በማጣመር ልዩ የሆነ ውበትን ይፈጥራሉ። ይህ ደግሞ በዓለም አቀፍ የፋሽን ገበያ ላይ የአፍሪካ ዲዛይነሮች ተወዳዳሪነታቸውን ከፍ ያደርጋል - ተብሏል።
የ“African Fashion Up 2025” ውድድር የአፍሪካን ፋሽን ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ ሲሆን፣ እንደ ሐዊ ሲሳይ ላሉ ብሩህ ተስፋ ላላቸው ዲዛይነሮች ትልቅ መድረክ ሆኖ ያገለግላል።
ሐዊ ያገኘችው ይህ ድል ወደፊት ለሌሎች ወጣትና ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች መነሳሳትን የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፣ የኢትዮጵያን ፋሽን ኢንዱስትሪ ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።
እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያ
እንኳን ደስ አለሽ ሐዊ

#ethiopia | በፋሽን ኢንደስትሪው ውስጥ የአፍሪካን ተሰጥኦ ለማጉላት ያለመውና በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ “African Fashion Up 2025” ውድድር ላይ
ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር ሐዊ ሲሳይ ሚደቅሳ አሸናፊ ሆናለች።

Comments