ፍቅረኛህን ነካ ነካ አድርጋትና ከውጪ ዘፋኞች የማን የማን ሙዚቃ ይመችሻል? በላት!
Tayla, Shenseea ፣ Spice, Ayra Starr, Burna Boy, Rema, Wizkid, Davido, Tiwa Savage ወዘተ ካለችህ:: ይቺ Generation Alpha የዚህ ዘመን ፈረካ ቸከስ ናት:: Stereotype & Extrovert ናት:: ሪትም ባለበት ነገር በሙሉ ምቾቷ አለ:: አስተሳሰቤም ሆነ ንግግሬ ግልፅ እና ግልብ ነው ትልሃለች ግን ከሎጂክ በእልፍ አዕላፍ ማይል የራቀ ግልፅነት ነው ያላት:: ኢ-ሎጂካል ምስኪን የዋህ ናት:: ውስብስብ እና Global Trend በሆኑ አጀንዳ ዙሪያ የሚያግባባ የንግግር ጠረጴዛ አይኖርህም ከዚህች ጋር:: የተመተረ ውስጥ ዓለም ነው ያላት:: ሰውነቷን የማያንቀሳቅስ ሙዚቃ በሙሉ ቴስቷ አይደለም:: በማህበራዊ ህይወቷም ይሄንኑ ነው የምታንፀባርቀው:: አብራችሁ ለቅሶ ብትሄዱ 'ምንድነው ጭር አለ ዲጄው አይመጣም እንዴ?" ማለቷ አይቀርም:: የወደፊት መፃኢ ዕድሌም ሆነ ያለፈው ህይወቴ ቴራፒ የሚያገኙት ክለብ እና ፓርቲ ላይ ነው ብላ ታስባለች:: ይቺን ጠዋት እና ማታ በልዩ ክትትል ያዛት!
__
Young Thug, 21 Savage, Gucci Mane, Young Jeezy, Future, Lil Uzi Vert,ካለችህ ደግሞ Rich or Die Flexing የሚል ሜንታሊቲ ነው ያላት:: ገንዘብ ከሌለህ አፍንጫህን ላስ ብላ ትሄዳለች:: በአስኮም አለች በፍራንችስኮ አምልኮ እና ስግደቷ ለገንዘብ ብቻ ነው:: በገዛ ህይወቷ መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ የምትፈቅደው ገንዘብንን እና ላግዠሪ Flex ሰዎችን ነው:: ነፃነት አፍቃሪ ናት ደንብ ፣ ገደብ ፣ ወደብ የመሳሰለ ኮተት አይመቻትም:: እንደ እሷ አይነት Luxury Flex የሆነ ጀማ ነው የሚመቻት ፎከታም Hustler ትፀየፋለች። የነፍሷም የስጋዋም ኢንጂን ገንዘብ እና ምቾት ነው:: በዛ ላይ ድብቅ እና ወላዋይ ናት:: በአጭሩ ወንድሜ ለፍቅርም ለትዳርም አትሆንም እሷ Toxic Romance Enthusiast እና Fashion Killa ጎልድ ዲገር ናት:: አጠገብህ ባለው ሁለት ሊትር ጎልድ ውሃ አናቷን ብለህ ወደ እነ ላካትና አንተ አርፈህ ስራህን ወጥር ብሮ::
_
Pop Smoke, Lil Durk, Chief Keef ምናምን ይመቹኛል ካለችህ ደግሞ ይቺ ፍፁም ከራሷ የራቀች ናት:: አለመብሰሏን ፣ ድክመቷን ፣ እንጭጭነቷን በPost Traumatic Stress Disorder (PTSD) ለመሸፈን ነው የምትጥረው። ቤተሰቦቼ ፣ ዘመዶቼ በዙሪያዬ ያሉ በሙሉ አይወዱኝም ትልሃለች:: ጠጋ ብለህ አቅፈህ ልታስረዳት ስትሞክር አመናጭቃህ የሆነ ጥግ ስር ትሄድና ከጥቁር ሆዲዋው ኪስ ውስጥ ግድንግድ ስቲክ አውጥታ መሸብለል ትጀምራለች:: ይቺን ወስደህ ሌዘር ጫኬት በአንበሳ ቆዳ ጫማ ለሚለብሰው እና ወያኔ DX ለሚነዳው ኮስታራው አጎቷ አስረክባት:: እዛው የሚያደርጉትን ያድርጓት:: ምንም አባቷ አልሆነችም የሰፈሯ ፍሪክ ነው ዊድ አስጀምሯት እንዲህ ጨለፍ ጨለፍ የምትጫወትብህ ተዋት:: ኑሮህ ላይ ፎከስ አድርግ ብሮ!
_
Dr. Dre, Ice Cube, Eazy-E, DJ Yella, Snoop Dogg, 50 Cent, The Game, Eminem, Lil Wayne ወዘተ አይነት Gangsta Rappers ይመቹኛል ካለችህ ይቺ ማንንም አታምን ተጠራጣሪ ናት። ከሙገሳ ቀድማ ስራዋ ላይ ነው ፎከስ የምታደርገው:: የውሸት ፍቅር አይመቻትም:: አታስመስል:: ስታስመስል ካገኘችህ በዚዳን ቴስታ ነው ኮማ ውስጥ የምትከትህ:: እውነተኛ ፍቅር ዋጋ ትሰጣለች:: በራሷ ጥራ ያመጣችውን ስኬት ታከብራለች:: ነገሮች ከሆኑ በኋላ ወደ ኋላ ለመመለስ ምንም አይነት የኋላ የስሜታት ማርሽ አልተገነባላትም: ነገሮችን በቀጥታ ታስተናግዳለች:: አግብተሃት ልጅ ብትወልድ እንኳ አራስ ጥየቃ የመጡትን የመንደር አዛውንቶች F- Word እየተጠቀመች ልታስተናግድ ስለምትችል አትቀየማት ነፍሷ እንደ ፍየል ማህፀን ግልብ ነው ይልቅ በንስሃ አቧቷ አስመክራት:: እንዳትለያት!
____
Don Williams, Kenny Rogers, Keith Urban, Dolly Parton, B.B. King, Etta James, Tracy Chapman ወዘተ አይነት የCountry, Blues እና Folk ዘውግ ዘፋኞች ይመቹኛል ካለችህ ይቺ በችግር እና በፅናት የተሞረደ ማንነት ነው ያላት:: በብዙ መከራ ውስጥ መሽቶ በመንጋት አልፋለች። ስብዕናዋ በመከራ እና በችግር ወይም በግርግር ህይወት ተሞርዷል:: ጫጫታ ቱማታ ከሞላበት ቦታ ይልቅ ትናንሽ አርምሞን የካደሙ ቦታ ምቾት ይሰጣታል:: ለቤተሰቧ ለመንደራ ለማህበረሰቧ ታስባለች የአደባባይም የቤት ውስጥም ጭምት ናት:: ግን ደግሞ ከዚህ ጀርባ የትም Grand Mall ውስጥ ያልተሸጠ ግላዊ ነፃነት እና ግልብነት አላት:: በሯን ዘግታ እርቃኗንን ምናምኗን እየነካካች እያጨሰች ዋይኗን ትጠጣለች:: ትፅፋለች:: ትሰርዛለች:: ትደልዛለች:: ወዘተ! ይቺ የያ ትውልድ የአይን እማኝ ናትና ምርጫው የአንተ ነው
_
Tupac, Nas, B.I.G, Wu-Tang Clan ወዘተ ካለችህ ይቺ ደግሞ ጦር ሳትሰብቅ ጋሻ ሳትወድር በመፈጠሯ ውስጥ ብቻ ከአምላኳ የተሰጣትን ነፃነት መቀዳጀት የቻለች ስማርት ነፍስ ናት:: ስለማህበራዊ እና ፖለቲካ ነገሮች ግንዛቤ አላት:: ስለ ጥቁሮች መብት ፣ መልዕክት በንቃት ታዳምጣለች:: ፊልም መርጣ ትሾፋለች::
ሮክስ ቲምበርላንድ ፣ ቪንቴጅ ቲሸርት ፣ ክላሲክ ስኒከር ትለብሳለች ምናምን ነገር ይቺ ፀዴ ናት ከቻልክ አግባት ካልቻልክ ስልኬን ስጣት እኔ አገባታለሁ!
____
የፍቅረኛችሁን የሙዚቃ ቴስት ንገሩኝና ባህሪዋን እነግራችኋላሁ 🙌
ተጻፈ በYoakin Bekele Pachi

5 months ago