Logo
Getu Temesgen
De-Next-Ev ዲፕሎማቲክ ባዛር

በሦስት ሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች የተዘጋጀ ልዩ ዲፕሎማቲክ ባዛር በዲሊኦፖል ሆቴል ሊካሄድ ነው

📌መግቢያ በነፃ
#ethiopia | የElvezet International Events መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሩት ሀይሉ፣ ከዲሊኦፖል ሆቴል እና ከNext Fashion Design ጋር በመተባበር በዓይነቱ ልዩ የሆነውን "De-Next-Ev ዲፕሎማቲክ ባዛር" በጋራ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ታላቅ ዝግጅት ከኅዳር 19/2018 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21/2018 ዓ.ም ድረስ በዲሊኦፖል ሆቴል ይካሄዳል። ዝግጅቱ ልዩ የሚያደርገው በሦስት ሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች ትብብር መፈጠሩ ነው።

ባዛሩ ዲፕሎማቶችን፣ የኤምባሲ ተወካዮችን፣ የንግድ ተቋማት መሪዎችን እና ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ እንግዶችን የሚያገናኝ
ሲሆን ዋናው ዓላማ ጠንካራ የሆኑ ጀግና ሴቶችን ማበረታታትና፣ ሴቶች በጋራ ሲሰሩ ምን ማከናወን እንደሚችሉ ማሳያ መሆን ነው ተብሏል።

* ኅዳር 19/2018 ዓ.ም (ዓርብ)፡ ዝግጅቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይኖረዋል። ቀኑን ሙሉ የተለያየ አማራጮችን የያዙ ተፈላጊ ቬንደሮች የሚገኙ ሲሆን፣ ምሽት ላይ ደግሞ የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት እና ልዩ የምግብ መስተንግዶ ይኖራል።

* ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)፡ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ በNext Fashion Design የተዘጋጀው ዓመታዊው AFFA Award መርሃ ግብር ይካሄዳል።

* ኅዳር 21/2018 ዓ.ም (እሁድ)፡ የመጨረሻው ቀን በዲሊኦፖል ሆቴል የተዘጋጀ ልዩ ብራንች(ቁርስ እና ምሳ) ፣ እንዲሁም በመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ማራኪ የባህል ውዝዋዜዎች ይቀርባሉ ባዛሩም አመሻሽ ላይ በደማቅ ሁኔታ ይደመደማል ተብሏል።

ሩት ሀይሉ እንዳሉት፣ ''ዝግጅቱ ከማዝናናት ባለፈ በርካታ የኔትዎርኪንግ (Networking) እድሎችን ያካተተ ነው። የዝግጅቱ አዘጋጆች ይህን ባዛር በአመት ሦስት ጊዜ ማለትም በአዲስ ዓመት፣ በገና እና በፋሲካ ሰሞን ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.