Logo
FIDEL POST NEWS
📌የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተጀመረ

የአፍሪካን የቆዳ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የአልባሳትና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን የሚመራው 11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት (AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK) ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ይካሄዳል።

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ከጨርቃጨርቅ፣ ከአልባሳት፣ ከቆዳ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከቤት ማስጌጫ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን ያሳትፋል።

ከ30 በላይ አገሮችን የሚወክሉ ከ200 በላይ አምራቾች በሚሳተፉበት በዚህ ዝግጅት ላይ፣ ምርቶችና ፈጠራዎች ከ7ሺ ለሚበልጡ የንግድ ባለሙያዎችና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ተመልካች ፊት ቀርበው የሚታዩበት መድረክ ነው።

የአፍሪካ  ፋሽን ሳምንት ላለፉት ዓመታት ከ50ሺ በላይ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለወጣቶች መፍጠር መቻሉን  ተገልጿል።

በዚህ በ11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ላይ በዘርፉ ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን ማለትም የኢኮኖሚ፣ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች (INTELLECTUAL PROPERTY RIGHTS) እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚና ላይ ትኩረት ያደርጋል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.