Logo
FastMereja
ዳ ማሪዮስ ፋሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ከአለም አቀፍ ትምህርት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ !!

Damarios Fashion & Technology Institute በቦሌ ብራስ ኬኬር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ አለም አቀፍ ይዘትን በጠበቀ መልኩ በቅርቡ የተከፈተ የስልጠና ተቋም ሲሆን የአገራችንን የትምህርት ጥራት ደረጃን ለማሻሻል በማለምና ሙያዊ ትምህርቶችን በመስጠት የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በማተኮር ወጣቶችን በማስተማርና ወደስራ ለማሰማራት አቅዶ በፋሽን ዲዛይን ፥በስነዉበት ትምህርት ( Makeup ) ፥ በ ቢዝነስና ኮምፕዩተር ስልጠናዎች ፥ Security Officers (መሳሪያ ኣልባ ጥበቃ አገልግሎቶች ) እና በ ሞደሊንግ ስልጠና የትምህርት ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ሙሉ እውቅና እና ፈቃድ ያገኘ ተቋም ነው ።

Rome business school በጣሊያን ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመርያው ሲሆን በካምፓስ ሆነ በ(online ) ማስተር እና MBA ፕሮግራሞችን በመስጠት ተቋሙ ከ150 አገራት የመጡ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ የሚገኝ እውቅ ተቋም ነው ።

በሁለት የትምህርት ተቋማት መካከል የተደረገው የጋራ ስምምነት ሰነድ የትምህርትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የተሻሻሉ የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ፤ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን የትምህርት አቅርቦቶች እና አዳዲስ የትምህርት እድሎችን በመስጠት፣ ሙያዊ እድገትን በማስተዋወቅ እና አጠቃላይ የትምህርት ልምድን በማሳደግ ተማሪዎችን፣ መምህራንና አጠቃላይ የተቋሙን ማህበረሰብ ዓለም አቀፍ ትምህርትን ለማዳበር የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉም እንዲሁም መምህራን ከአለም አቀፍ ባልደረቦች እንዲማሩና የልምድ ልዉዉጥ እንዲቀስሙ ዕድል የሚያገኙበት እና ለተማሪዎቻችን ደግሞ ከአገር ዉጭ በመዉጣት ተጨማሪ የበለፀገ የትምህርትና የተግባር እውቀት የሚቀስሙበት አልፎም በአለም አቀፉ ገበያ ተዎዳዳሪ የሚሆኑበት እድልን የሚፈጥር ስምምነት ነው ። በተቋማችን የትምህርት ጥራት በመተማመንና የኢትዮጲያን የትምህርት ደረጃን አብሮ ለማሳደግ ይህንን መሰል ዕድል ስላመቻቸልን Rome business school እያመሰገንን ያሉን ቦታዎች ውስን እነደመሆናቸው እርሶም የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በመረጡት የሞያ ዘርፍ ተመዝግበው ይሰለጥኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.