3 months ago
የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች የዓለምን የፋሽን መድረክ እንዲቀላቀሉ የሚያስችል አዲስ ዕድል ይፋ ሆነ!
#fastmerjea :የፋሽን ኢንዱስትሪውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረጽና የፈጠራ ዘርፉን ዓለም አቀፋዊ .የተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያለመ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተጀመረ።
"የፋሽን ረዚደንሲ" (Fashion Residency) የተሰኘውና በብሪቲሽ ካውንስል፣ በፖል ስሚዝ ፋውንዴሽን፣ በስቱዲዮ ስሚዝፊልድ እና በአይስ አዲስ (iceaddis) ትብብር የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፤ በኢትዮጵያ፣ በዚምባብዌ እና በዩናይትድ ኪንግደም ዲዛይነሮች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የብሪቲሽ ካውንስል ተወካይ ረሺዳ እንደገለፁት፤ ስድስት ተማሪ ዲዛይነሮች በለንደን በሚገኘው ስቱዲዮ ስሚዝፊልድ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ ጥልቅ ስልጠና እንደሚያገኙ የገለፁ ሲሆን ስልጠናው ዲዛይነሮቹ ከዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች ጋር እንዲገናኙና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ነዉ የተገለፀዉ።
በዕለቱ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር ሰሎሜ አስፋው፤ በፋሽን ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እና የቴክኒክ ስልጠና ውስንነት የገለጸች ሲሆን፤ እንዲህ አይነት መድረኮች ግን አዳዲስ አመለካከቶችን ለማግኘትና የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ መሆናቸውን አስረድታለች።
መርሃ ግብሩ በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባራዊ ልምምድ የተመጣጠነ ሲሆን፣ የባህል ልውውጥ፣የስራ ጉብኝት እንዲሁም የንግድ ስልጠና እንደሚያካትት ሰምተናል።
መርሃ ግብሩ የባህል ልውውጥን፣ የስራ ጉብኝቶችን እና በብራንድ ግንባታ ላይ ያተኮሩ የንግድ ስልጠናዎችን ያካተተ ሲሆን፤ በሀገራቱ መካከል ያለውን የፈጠራ ኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።