4 days ago
ለፊፋ ፕሬዝዳንትነት ማን ሊወዳደር ነው ?
የ አለም እግርኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ፊፋ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በቀጣዩ አመት 2027 ይካሄዳል።
በምርጫው የቀድሞ የስዊዘርላንድ እና ቶተንሀም ተከላካይ ራሞን ቬጋ እንደሚወዳደሩ ይፋ አድርገዋል።
የ 55ዓመቱ ራሞን ቬጋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን በምርጫው ለመፎካከር ያቀዱ የመጀመሪያው ሰው ሆነዋል።
በተለያዩ ክለቦች ተጫውተው ያሳለፉት ቬጋ ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ ፋይናንስ ላይ ሲሰሩ እንደነበር ተገልጿል።
“ በእግርኳስ ወዳድ ማህበረሰብ ውስጥ እምነት ተጓድሏል "ያሉት ቬጋ “ እንደገና መገንባት ፤ የፊፋን ተአማኒነት መመለስ አለብኝ " ብለዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

10 days ago
ፊፋ በአሜሪካ ሌላ ውድድር ሊያዘጋጅ ነው !
የ አለም እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ፊፋ በአሜሪካ ሌላ ትልቅ ውድድር ለማዘጋጀት አስቧል።
ፊፋ በ 2028 የሴቶች ክለቦች አለም ዋንጫ በአሜሪካ ለማዘጋጀት ማቀዱን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን ፊፋ ሶስተኛውን ትልቅ ውድድር በአሜሪካ የሚያካሂድ ይሆናል።
ከዚህ በፊት የአለም ዋንጫ እና ክለቦች አለም ዋንጫ በአሜሪካ መካሄዱ አይዘነጋም።

የእስራኤል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በኔዘርላንድስ እንዳይገኙ ታገዱ
የውሳኔው መነሻ የጋዛው ጦርነት መሆኑም ተገልጿል
የእስራኤል ክለብ የሆነው ሃፖኤል ቤር-ሼቫ ጥቅምት 15 በኔዘርላንድስ አልክማር ከተማ ከኤዜድ ጋር በሚያደርገው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ላይ ደጋፊዎቹ በስታዲየም እንዳይገኙ ተከልክለዋል። የአካባቢው ባለስልጣናት ይህን የወሰኑት ከጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎች አንፃር ጨዋታው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ስላለው መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው እ.ኤ.አ. በ2024 በአምስተርዳም ከተማ በአያክስ እና ማካቢ ቴል አቪቭ ጨዋታ ወቅት የተነሳውን ሁከት እና ግጭት መነሻ በማድረግ ነው። ከዚህ ቀደም የእንግሊዙ አስቶን ቪላ ከማካቢ ቴል አቪቭ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ተመሳሳይ የደጋፊዎች እገዳ ተጥሎ የነበረ ሲሆን፤ በወቅቱ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ውሳኔውን አውግዘውት ነበር።
የእስራኤል ክለቦች እና ብሔራዊ ቡድን በአለም አቀፍ ውድድሮች መሳተፋቸው በጋዛው ጦርነት ምክኒያት በተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ እያስነሳባቸው ይገኛል። ጦርነቱ የተቀሰቀሰው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2023 ሀማስ 1ሺ 200 ሰዎችን ገድሎ 250 ሰዎችን ካገተ በኋላ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ የጋዛ ጤና ጥበቃ እንዳስታወቀው በእስራኤል የአጸፋ ጥቃት እስካሁን 73ሺ ሰዎች ተገድለዋል። አንድ የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ቡድንም እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ሲል የደመደመ ሲሆን፣ የእስራኤል መንግስት ግን ክሱን አጥብቆ አስተባብሏል።
ባለፈው ሳምንት የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከእስራኤል ጋር ያደረገው ጨዋታም በህዝቡ ዘንድ ጠንካራ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ እስራኤል በፊፋ እና በዩኤፋ የሚመሩ ማንኛውንም ጨዋታዎች በገዛ ሜዳዋ እንዳታስተናግድ መታገዷ ይታወቃል።
ምንጭ፡-The Athletic
@Yenetube Fikerassefa

14 days ago
የዓለም አቀፍ እረፍት መርዘም ለሀገር ክብር ወይንስ የሊጉን ማራኪነት መሸርሸር?
በዘንድሮው የውድድር ዓመት የእግር ኳስ አፍቃሪያን ከምንጊዜውም በላይ ረጅም የሆነ የብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍትን እያስተናገዱ ይገኛሉ። ያለ መደበኛ የሊግ ጨዋታዎች ሙሉ ሦስት ሳምንታትን ማሳለፍ፣ ውድድሩ በነበረው ከፍተኛ ፍጥነትና የፉክክር ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የቸለሰ ክስተት ሆኗል። ይህ ዓይነቱ ረጅም መቋረጥ በሜዳ ላይ ከሚታየው ስፖርታዊ ውበት ይልቅ፣ የአደራጁን አካል አሠራር በጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት አጀንዳ ሆኖ ብቅ ብሏል።
የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል (ፊፋ) ይህንን አዲስ አሠራር ይዞ የመጣው በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ አጫጭር መቆራረጦችን ለመቀነስ እና የተጫዋቾችን የጉዞ ድካም ለማቅለል በማሰብ እንደሆነ ይገልጻል። ይሁን እንጂ ውሳኔው በተግባር መሬት ላይ ሲወርድ ያሳየው ውጤት ግን ተቃራኒ ይመስላል። የጊዜ ርቀቱ በዚህ ልክ ሲለጠጥ ጨዋታዎችን በናፍቆት ከመጠበቅ ይልቅ፣ በደጋፊው ዘንድ ከፍተኛ መሰላቸትንና የስሜት መውረድን እየፈጠረ ይገኛል። የሊግ ጨዋታዎች በጥሩ ፉክክር ላይ እያሉ በዚህ መልኩ መቋረጣቸው የውድድሩን ማራኪነት በእጅጉ ይቀንሰዋል።
ይህ አዲስ ስትራቴጂ የብሔራዊ ቡድኖችን ዕድገት ለመደገፍና ለሀገር ክብር ተገቢውን ዋጋ ለመስጠት መልካም ጎን እንዳለው መካድ አይቻልም። ይሁን እንጂ የዓለም አቀፍ ውድድሮች መነቃቃት የደጋፊዎችን የየሳምንቱ ፍላጎት ፍጹም በሆነ መልኩ የሚሸረሽር መሆን የለበትም። እግር ኳስ በደጋፊዎች ስሜት ላይ የሚቆም ስፖርት እንደመሆኑ መጠን፣ የእረፍት ቀናቱ መርዘም የደጋፊውን የስታዲየም ናፍቆት ወደ ቸልተኝነት የመቀየር ዕድሉ የሰፋ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ረጅም እረፍት የክለቦችን የታክቲክ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው። ተጫዋቾች በተለያየ የኳስ ፍልስፍና እና አካላዊ ጫና ውስጥ ቆይተው ወደ ክለባቸው ሲመለሱ፣ የቡድኖችን ወጥ እንቅስቃሴ እና የነበራቸውን የመሸናነፍ ሥነ ልቦና መልሶ ማግኘት እጅግ ፈታኝ ይሆናል። ይህ ደግሞ ታክቲካዊ ወጥነታቸውን ጠብቀው መጓዝ ለሚፈልጉ የክለብ አሰልጣኞች እጅግ ከባድ የሆነ ተጨማሪ የሥራ ጫና የሚፈጥርባቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
ስለሆነም ፊፋ የወደፊት የውድድር ዓመታትን ካላንደር ሲያቅድ የደጋፊዎችን ፍላጎትና የክለቦችን መዋቅራዊ ጤንነት ታሳቢ ያደረገ ይበልጥ ሚዛናዊ የሆነ መፍትሔ ሊፈልግ ይገባል። የብሔራዊ ቡድኖች ዕድገት የሚደገፈው የክለቦች ውድድር ማራኪነት ሳይቀነስ ሲቀር ብቻ በመሆኑ፣ የሊግ ጨዋታዎች በጋለ ፉክክር ላይ እያሉ በዚህ ልክ መርዘም የለባቸውም። ፍትሃዊ እና ሁለቱንም ወገን የሚጠቅም አሠራር መዘርጋት የዘመናዊ እግር ኳስ ዋነኛ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል።
Alillovess ✍
@Bisrat_Sport_433et

Sponsored by
Surafel
18 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ጨዋታ የለም› ሲሉ የብራዚሉ አሰልጣኝ አንቸሎቲ ተናገሩ፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም የፊታችን ኦክቶበር 3 በህንድ ኮልካታ ከተማ ብራዚልና ህንድ የወዳጅነት ግጥሚያቸውን ያደርጋሉ፡፡ የአምስት ጊዜ የአለም ሻምፒዮኖቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለዚህ ግጥሚያ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጡት ገልፀው ‹‹ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ጨዋታ የለም›› ብለዋል፡፡
እንደቪኒሺየስ ጁኒየርን የመሳሰሉ ኮከብ ተጨዋቾችን ያካተተችው ብራዚል በአለም የእግር ኳስ ሰንጠረዥ በ5 ደረጃ ላይ የምትገኝ ናት፡፡ በአብዛኛው የክሪኬትስ ወዳጅ የሆነችው ህንድ ደግሞ ለእግር ኳስ ያን ያህል ብትሆንም በርካታ ህዝቧ ለአለም አቀፍ ተጨዋቾች አድናቆት አለው፡፡ ህንድ እንዲህ አይነት አለም አቀፍ የወዳጅነት እግር ኳስ ውድድር ስታስተናግድም የመጀመሪያዋ በመሆኑ ጉዳዩ ትልቅ ትኩረትን ስቧል፡፡ አንቸሎቲ በንግግራቸው ‹‹ብራዚል በአለም ዙሪያ ሁሉ ደጋፊዎች አሏት፡፡ በህንድ መጫወት ለእኛ ትልቅ ደስታ ነው፡፡ የምንጫወተው ደግሞ በብራዚል ለሚገኙ ብቻም ሳይሆን በህንድ ላሉም ደጋፊዎቻችን ጭምር ነው›› ብለዋል፡፡
ጨዋታው ምንም እንኳ የወዳጅነት ቢሆንም አንጋፋው ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ግን በሙሉ አቅማቸው እንደሚጋጠሙ ገልፀዋል፡፡ የ67 አመቱ አሰልጣኝ ጨምረውም ‹‹ይህ የወዳጅነት ጨዋታ ቢሆንም ዝግጅት የምናደርግበትም ነው፡፡ ስለዚህም ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ቀለል አድርገን የምንመለከተው ጨዋታ የለም›› ማለታቸውን ዘታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል፡፡ ህንድ በፊፋ የእግር ኳስ ሰንጠረዥ በ138ተኛ ደረጃ ብትቀመጥም በአለም ዋንጫ ተሳትፋ ግን አታውቅም፡፡

20 days ago
የመጀመሪያው የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያዎች ስልጠና ተጠናቀቀ
#ethiopia | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የተሰጥኦ ልየታ (Talent ID) ባለሙያዎች ስልጠና ተጠናቀቀ።
በአምስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው ስልጠና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ 31 ሰልጣኞች ተሳትፈዋል። ሰልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተሰጥኦ ልየታን በተመለከተ ስልጠና ያገኙ ሲሆን፣ ስልጠናውን የፊፋ ከፍተኛ ብቃት ስፔሻሊስት ላይሰን ዙሉ፣ የፊፋ የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያ ሚካኤል ሬንስችለር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰጥኦ አሰልጣኝ ሲፕሪያን አሹ መርተዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ሰልጣኞቹ ያገኙትን እውቀት በየአካባቢያቸው በተግባር እንዲያውሉ አሳስበዋል።
አቶ ባሕሩ የሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድኖች የወደፊት ጥንካሬ ዛሬ በሚለዩ ወጣት ተጫዋቾች ጥራት ላይ የሚመሠረት መሆኑን ጠቅሰው፣ የተሰጥኦ ልየታና ምልመላ ሂደቱ ከስሜትና ከአድልዎ በፀዳ መልኩ መከናወን እንዳለበት ገልጸዋል። ሰልጣኞቹ በሚሰማሩበት አካባቢ ሁሉ የፌዴሬሽኑን የተሰጥኦ ልየታ ስርዓት በአግባቡ እንዲያስፈጽሙም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን TDS ክፍል ኃላፊ አቶ ሸዋንግዛው አበበ በበኩላቸው፣ በተሰጥኦ ልየታ አሠራርና ሂደት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በፌዴሬሽኑ ወጥ የሆነ የምልመላና የተሰጥኦ መለያ መስፈርት መዘጋጀቱን ገልጸው፣ የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያዎቹ የመረጃ አሰባሰብና ልውውጥ ሥርዓትን በተዘጋጀው ማንዋል መሠረት እንደሚያከናውኑ ጠቁመዋል።
“ለእያንዳንዱ ታላንት ዕድል መስጠት” በሚል መሪ ቃል በፊፋ TDS ሥር ከሚሰጡት ሦስት ስልጠናዎች መካከል ይህ የመጀመሪያው ነው።
በቀጣይ ስልጠናዎቹ ያልተዳረሱ አካባቢዎችን በማካተት እንዲሁም የሴት ሰልጣኞችን ተሳትፎ በማሳደግ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። የመጀመሪያውን ስልጠና ያጠናቀቁት ባለሙያዎችም ያገኙትን እውቀት በተግባር ለማዋል ከፌዴሬሽኑ TDS ክፍል ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ተጠቁሟል።

23 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማክሰኞ ዕለት ማንቸስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ በይፋ ደብዳቤ ያስገባው የጄጄ ገብርኤል ውሳኔ፣ በእግር ኳሱ ዓለም ያልታሰበ ማዕበል ፈጥሯል። ገና በ15 ዓመቱ በአውሮፓ ከሚገኙ እጅግ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች አንዱ ተብሎ የሚታሰበው ይህ ድንቅ አጥቂ፣ ከዘጠኝ ዓመቱ ጀምሮ ያሳለፈበትን ክለብ ለመሰናበት ቋምጧል፤ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችም እሱን ለመጥለፍ አሰፍስፈዋል።
ሪያል ማድሪድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ በጥሩ ቁመና ላይ ሲገኝ፣ ባርሴሎና፣ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን እና ባየር ሙኒክም ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። ዩናይትዶች ልጁን ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ነገሮች ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ይመስላሉ። ገብርኤል ባለፈው ሀሙስ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ከ19 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር በዩኤፋ የወጣቶች ሊግ ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ወደ ስፍራው ድርሽ አላለም፤ አሁን ባለው ሁኔታም ይመለሳል ተብሎ አይጠበቅም። በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ዩናይትድ ወደፊት 100 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያወጣ የሚችልን አልማዝ በገዛ እጁ እያጣ መሆኑን ይገምታሉ።
ይህ ውሳኔ ድንገት የመጣ አይደለም። የችግሩ ጭላንጭል የታየው ባለፈው ሀሙስ ነበር። ገብርኤል በኦልድ ትራፎርድ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሚጫወተው ዋናው ቡድን ጋር ከመሰለፍ ይልቅ፣ ከአዘርባጃኑ ሳባህ ጋር ለሚጫወተው የ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲሰለፍ ተደረገ። በጨዋታው ሶስት ግቦችን ቢያስቆጥርም፣ እሱና ቤተሰቡ ግን የሻምፒዮንስ ሊግ ድባብን በዋናው ቡድን ውስጥ ሆኖ እንዲቀምስ ፈልገው ነበር። ይህ ክስተት ትልቅ ስብራት ፈጠረ፤ ውሳኔውም ወዲያውኑ ለክለቡ ተነገረ። ቅዳሜ ዕለት ከዋናው ቡድን አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ጋር ልምምድ ማድረግ ሲገባው፣ ከካሪንግተን በመቅረት ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል አቃጨለ። ወዲያውም ከኢንስታግራም ገጹ ላይ ስለ ዩናይትድ የሚገልጹ መረጃዎችን በሙሉ አጠፋ። ሰኞ ዕለት ደግሞ ምዝገባው እንዲሰረዝለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለክለቡ አስገባ። የማንቸስተር ዩናይትድ ኃላፊዎች፣ በተለይም ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ እና አብሮ ባለቤቱ ሰር ጂም ራትክሊፍ በጉዳዩ ክፉኛ ተደናግጠዋል።
ሪያል ማድሪድ ይህንን ታዳጊ ለማስፈረም በስውር ሲሰራ ወራት አልፈውታል። ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ፣ የፊፋን ጥብቅ ህጎች ላለመጣስ ሲባል ክለቡ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። የማድሪድ እቅድ ልጁን መጀመሪያ ለካስቲላ (የማድሪድ ሁለተኛ ቡድን) እና ከ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲጫወት አድርጎ፣ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ነው። ይህ ከዚህ ቀደም በአያክሱ የ17 ዓመት ታዳጊ አብደላ ኦዋዛኔ ላይ ሊሞክሩት ያሰቡት ዓይነት ስልት ነው። የማድሪድ ሰዎች የገብርኤልን የሀሙስ ዕለት ሀትሪክ በቅርበት ሲከታተሉና ሲያከብሩ ነበር።
በህግ አግባብ ዩናይትድ የልጁን ውል የመቀደድ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ገብርኤል የአውሮፓ ህብረት ፓስፖርት ካገኘ፣ ልክ ጥቅምት 6 ቀን 16 ዓመት ሲሞላው ወደ ሌላ የአውሮፓ ክለብ መዘዋወር ይችላል። አባቱ ጆ ኦኬሩይል የተወለደው ለንደን ቢሆንም ለአየርላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል፤ እናቱም የሳይፕረስ ትውልድ አላት። ይህ ደግሞ ፓስፖርቱን በቀላሉ እንዲያገኝ በር ይከፍትለታል። ከዚህም ባሻገር፣ ገብርኤል መደበኛ የትምህርት ቤት ትምህርቱን በቤት ውስጥ የሚከታተል በመሆኑ፣ በዩናይትድ ሙሉ ጊዜ አካዳሚ ስር አይወድቅም፤ ይህም ክለቡ በልጁ ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያላላዋል። ገብርኤል ዩናይትድን የሚለቅ ከሆነ፣ ፊፋ ባስቀመጠው የካሳ ስሌት መሰረት ዩናይትድ ከ100,000 ፓውንድ በላይ የማሳደጊያ ካሳ ሊያገኝ ይችላል።
ገብርኤል ገና በዘጠኝ ዓመቱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ ሲወጣ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ይነጻጸር ነበር። ነገር ግን የእሱ ተወዳጅ ተጫዋች ኔይማር ሲሆን፣ ኳስን አጣብቆ የመያዝ፣ ፈጣን እንቅስቃሴ የማድረግ እና በሁለቱም እግሮቹ ግሩም አጨራረስ ያለው በመሆኑ የጨዋታ ስታይሉ ከብራዚላዊው ኮከብ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። በዩናይትድ የዋናው ቡድን ልምምዶች ላይ በተደጋጋሚ በመሳተፍ፣ አንጋፋ ተጫዋቾችን ሳይቀር በቴክኒክ ብቃቱ አስገርሟል። በአካላዊ ጥንካሬ ከእሱ በሚበልጡ ተጫዋቾች ቢገፋም፣ በተፈጥሮ ያገኘው ክህሎት ወደፊት ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታ እንደሚያሰልፈው ብዙዎች ይስማሙበታል። ባለፈው ታህሳስ በኤፍኤ የወጣቶች ዋንጫ ለዩናይትድ በመሰለፍ እና ግብ በማስቆጠር ታሪካዊ ሪከርድ ሰብሯል፤ በወጣቶች ሊግ ባደረጋቸው 34 ጨዋታዎችም 31 ግቦችን እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዩናይትድ ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ታላቅ ታሪክ አለው። "በቂ ብቃት ካለህ፣ በቂ ዕድሜ አለህ" የሚለው የሰር ማት ባስቢ ብሂል ክለቡን ለዘመናት መርቶታል። ገብርኤልም የዚህ ታሪክ ቀጣይ አካል ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን በቅርብ ጊዜ የተፈጠሩ ክስተቶች ጥርጣሬን አጭረዋል። በክረምቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ በቂ የመጫወት ዕድል አላገኘም፤ በአትሌቲኮ ማድሪዱ ጨዋታ ከተፈጥሮ ቦታው ውጪ እንዲጫወት ሲደረግ፣ አዲሱ ፈራሚ የ18 ዓመቱ ታይናን ቶምሰን ግን በገብርኤል ተወዳጅ ቦታ በግራ ክንፍ ላይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቷል። በሻምፒዮንስ ሊግ የ'ኤ' ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም ሌላው ቅር ያሰኘው ጉዳይ ነው። አርሰናል የ15 ዓመቱን ማክስ ዶውማንን በዝርዝሩ ውስጥ አካቶ ክብረ ወሰን ሲሰብር፣ የገብርኤል ስም ግን አልነበረም። አላማው በቋሚነት መሰለፍ ሳይሆን፣ ክለቡ በእሱ ላይ ያለውን እምነት በተጨባጭ ማየት ነበር።
ባለፈው ክረምት ማንቸስተር ሲቲ ገብርኤልን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ የዩናይትድ የስፖርት ዳይሬክተር ጄሰን ዊልኮክስ እና የድርድር ዳይሬክተሩ ማት ሀርግሪቭስ ጣልቃ ገብተው አክሽፈውት ነበር። ወደ ሌላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ማምራቱ በህግ አግባብ እጅግ ፈታኝ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዩናይትድ ልጁን ለማሳመን ከቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና ከታላቁ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ጭምር አገናኝቶታል። ማይክል ካሪክ በቅርበት ያሰለጠነው ሲሆን፣ የዋናው ቡድን ማሊያ ቁጥር 77ም ተሰጥቶታል።
አሁን ላይ ዩናይትዶች በቀጣዩ ወር 16ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲያከብር የማበረታቻ የትምህርት ኮንትራት እና በ17 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ውል ለማቅረብ እየተዘጋጁ ነበር። በፋይናንስ አቅርቦት ማንም ክለብ እንደማይበልጣቸው ያምናሉ። ነገር ግን የገብርኤል ውሳኔ የተቆረጠ ይመስላል፤ ስለዚህ ዩናይትድ ውጤቱን በትዕግስት ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። አርብ ዕለትም ክለቡ ለቀረበው የምዝገባ ስረዛ ደብዳቤ ይፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

26 days ago
በፊፋ እና ካፍ ህግ መሰረት ብቸኛው እጩ አቶ ኢሳያስ ጅራ 50 ከመቶ ድምፅ ካላገኙ ምርጫው ይሰረዛል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ድምፅ መስጠት በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ይገኛል።
ለቦታው ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከጠቅላላው ድምፅ 50 ከመቶ ካላገኙ ምርጫው ተሰርዞ በድጋሚ እንደሚደረግ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሀይሉ ሞላ ገልጸዋል።
ምርጫው አንድ እጩ ብቻ የቀረበበት መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታና ስጋት የደቀነ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የምርጫ መመሪያ (Standard Electoral Code) ግን ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ ደንግጓል።
በነዚህ አለም አቀፍ ህጎች መሰረት አንድ ተወዳዳሪ ያለተፎካካሪ ብቸኛ እጩ ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ እንኳን ድምፅ መስጠት ሳያስፈልግ ወይም በቀጥታ አሸናፊ ተደርጎ አይሾምም።
በህጉ መሰረት ብቸኛው እጩ የጠቅላላ ጉባኤተኞቹን አብላጫ ድምፅ (50% + 1) የማያገኝ ከሆነ፣ ሂደቱ ውድቅ ተደርጎ አዲስ እጩዎች የሚካተቱበት ድጋሚ ምርጫ እንዲደረግ ይገደዳል።
ይህም አሰራር ድምፅ ሰጪዎች እጩውን የመቃወም እና ምርጫውን ወደ አዲስ ውድድር የመመለስ ሙሉ መብት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው።
በአሁኑ ሰዓት የፌደሬሽኑ አባላት ድምፃቸውን እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን፣ አቶ ኢሳያስ ጅራ አስፈላጊውን ድምፅ ማግኘት አለማግኘታቸው የታገደውን የምርጫ ሂደት ወደ አዲስ ውድድር የሚመልሰው ወይም የሚያጸናው ይሆናል።

1 month ago
የቀድሞ ኮከብ የባንክ ምስጢር ወጣ
#ethiopia | የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኢቶ በከባድ የሙስና እና የገንዘብ ምዝበራ ክስ ተመሠረተበት።
የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኢቶ ከሩሲያ ወደ ግል የባንክ ሂሳባቸው የተላከ ከ500,000 ዩሮ በላይ ገንዘብን በተሳሳተ መንገድ ተጠቅሟል በሚል መከሰሱን የፊፋ ሕጋዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ።
ኢቶ ለመልካም አስተዳደር ብልሹነት እና ለገንዘብ ምዝበራ ውንጀላ መጋለጡን የፊፋ የፍርድ ቤት መዝገቦች እና ሕጋዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ።
በክሱ ወደ ኳታር ብሔራዊ ባንክ የግል የባንክ ሂሳባቸው ሁለት የተያዩ ክፍያዎች ቀጥታ እንዲገቡ የተደረጉበት ደረሰኞች በክስ ሰነዱ ላይ መቅረባቸው ተገልጻል።
ይህ ገንዘብ ለምን ዓላማ እንደዋለ እና ወደ ግል ሂሳብ እንዲገባ የተደረገበት ሕጋዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ግልጽ አለመሆኑ ክሱን ጠንካራ ያደርገዋል።
የፊፋ ፕሬዚዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ቅርብ ወዳጅ የሆነው ኢቶ ስሙ የተነሳው ፊፋ ሊተገብረው አቅዶት በነበረውና በኋላ ላይ በተሰረዘው የዓለም ዋንጫ ሽያጭ ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀረበ የፍርድ ቤት መዝገብ ላይ ነው።
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ሳሙኤል ኢቶ ከተፈጸሙት የገንዘብ ዝውውሮች ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ የሕግ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና ምርመራዎች ከፊቱ ተደቅነውበታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #samueletoo #fecafoot #fifa #caf #footballnews #breakingnews #cameroonfootball #sportsnews

ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙት የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ዓለም አቀፉን የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ለመምራት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ ዳግም እንደሚወዳደሩ የተቋሙ ቃል አቀባይ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ በጎርጎሮሳዊው 2027 በሚካሔደው ምርጫ በድጋሚ እንደሚወዳደሩ በሚያዝያ ወር ማስታወቃቸውን ያስታወሱት የፊፋ ቃል አቀባይ “ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ኢንፋኒቲኖ በድጋሚ ለመመረጥ ይቀርባሉ” ብለዋል።
ፊፋ የ56 ዓመቱ ስዊትዘርላንዳዊ በድጋሚ ለፕሬዝደንትነት እንደሚወዳደሩ ያረጋገጠው ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰ ዕቅድ ካቀረቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ኢንፋንቲኖ በፊፋ መርሐ-ግብሮች የግል ኢንቨስትመንት ለማካተት “ፊፋ ፎርዋርድ ኢንተርፕራይዝ” የተባለ ተቋም ለማቋቋም የጀመሩት ውጥን ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው ነበር። ተሳክቶላቸው በድጋሚ ከተመረጡ እስከ ጎርጎሮሳዊው 2031 ፊፋን በፕሬዝደንትነት ይመራሉ።
DW Amharic

“በፌዴሬሽን ቲኬት ከሀገር ወጥቼ አላውቅም” — ኢሳያስ ጅራ
ከሰሞኑ ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ለፕሬዝዳትነት ቀርበው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፌዴሬሽኑ አመራርነት በነበሩበት ጊዜ ለውጭ ጉዞዎቻቸው የተጓጓዥ ቲኬት ወጪ በፌዴሬሽኑ ተሸፍኖላቸው እንደማያውቅ ገለጹ።
ኢሳያስ ጅራ ይህን የተናገሩት ከኢቲቪ “ስለ ስፖርት” ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ሲሆን፣ በፊፋ እና በካፍ በሚያከናውኗቸው ኃላፊነቶች ምክንያት የውጭ ጉዞዎቻቸው ወጪዎች በእነዚህ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተቋማት እንደሚሸፈኑ አስረድተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው የኢትዮጵያን እግር ኳስ መምራት ፈታኝ እንደሆነም ገልጸዋል። በተለይም ብሔራዊ ቡድኑ የሚጠበቀውን ውጤት ሳያስመዘግብ ሲቀር ማየት እንደሚከብዳቸው አስረድተዋል። ኃላፊነቱ የሀገር ጥሪ ቢሆንም፣ በሕዝቡ የሚጠበቀው ውጤትና በሜዳ የሚመዘገበው ውጤት መራራቁ የፌዴሬሽኑን አመራር ከባድ እንዳደረገው ኢሳያስ ጅራ ገልጸዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ለ8 አመታት በፕሬዝዳንት እግር ኳስ ፌደሬሽኑን የመሩት አቶ ኢሳያስ አዲስ ለውጥ በሚፈልጉ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ተቀባይነታቸው ዝቀተኛ መሆኑን በፕሬዝዳንትነት የምርጫ ወቅት ጊዜ ተቀናቃኞቻቸው ሲያነሱ ቢቆዩም ለእጩነት የቀረበ ሌላ ተወዳዳሪ ባለመገኘቱ ለተጨማሪ 4 አመታት በአመራርነት እንዲቆዩ ተመርጠዋል።

2 months ago
ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ የሰጡት አራት የአፍሪካ ሀገራት ብቻ ናቸው!
#ethiopia | ለፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እስካሁን ድረስ ድጋፋቸውን የሰጡት አራት የአፍሪካ ሀገራት ብቻ መሆናቸው ተገለፀ።
ሞሮኮ፣ ግብፅ፣ ሱዳን እና ሞሪታኒያ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
አራቱ የአፍሪካ ሀገራት በፌደሬሽናቸው በኩል በኢንፋንቲኖ አመራር እና አስቸዳደራቸው እምነት እንዳላቸው በመግልጽ ለፕሬዝዳንቱ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ከአራቱም ማዕዘናት በፕሬዝዳንቱ እየተሰነዘረ የሚገኘው ትችት እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት አራቱ ሀገራት ብቻ ሙሉ ድጋፋቸውን ችረዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ኢንፋንቲኖ ሥልጣን እንዲለቁ የሚቃወሙ አካላት በሚቀጥለው ምርጫ ከፕሬዝዳንቱ ጋር እንዲወዳደሩ እራሳቸውን ያዘጋጁ ሲሉ ተናግረው ነበር።
ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ንግግር ተከትሎ ከአፍሪካ አንስቶ እስከ አውሮፓ ድረስ ያሉ የእግር ኳስ ማህበራት በፓትሪስ ሞትሴፔ ላይ ወቀሳ አድርሰዋል።
አንዳንዶቹ ከወቀሳ አልፈው የኢንፋንቲኖ ተላላኪ በማለት ወርፈዋቸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #africa #fifa #football #morocco #egypt #sudan #mauritania

"ይህ ለእኔ የዓለም ዋንጫዬ ነበር" - ሶማሊያዊው ዳኛ ኦመር አርታን
****************
በፈረንጆቹ 2025 የአፍሪካ ኮከብ ዳኛ ክብርን የተቀናጀው ሶማሊያዊው ዳኛ ኦመር አርታን፣ ለስፖርት ህይወቱ ትልቅ ምዕራፍ የሚሆነውን የ2026 የዓለም ዋንጫ የዳኝነት ጥሪ ከፊፋ አግኝቶ ነበር።
ነገር ግን ለቅድመ ውድድር ስልጠና ወደ አሜሪካ ባደረገው ጉዞ ወቅት በትራምፕ አስተዳደር ጥብቅ የቪዛ ማጣራትና የጉዞ እገዳ መመሪያ ምክንያት ከአውሮፕላን ማረፊያ እንግልት በኋላ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ተደረገ።
በብዙ ልፋት ያመጣው የዓለም ዋንጫ ህልሙ በዚህ መልክ በድንገት ቢደናቀፍም፣ ያጋጠመው ፈተና ግን ለሌላ ታላቅ ስኬት መንገድ ከፍቶለታል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ጋር በመተባበር በፒኤስጂ እና በአስቶንቪላ መካከል የተካሄደውን የ2026 የሱፐር ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንዲመራ ለአርታን ኃላፊነቱን ሰጠው።
ይህ አጋጣሚ ኦመር አርታንን በዓለም እግር ኳስ ታሪክ የአውሮፓን የሱፐር ካፕ ፍልሚያ በመሃል ዳኝነት የመራ የመጀመሪያው አውሮፓዊ ያልሆነ ዳኛ የሚያደርገውን ታሪካዊ ስም አጎናጽፎታል።
ፒኤስጂ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፎ ዋንጫውን ባነሳበት በዚህ ታሪካዊ ፍልሚያ፣ አርታን ጨዋታውን በከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና በጥራት መርቶ አጠናቋል።
ኦመር አርታን ከጨዋታው ማብቃት በኋላም በጨዋታዋ ኳስ ላይ፤ "ይህ ለእኔ የዓለም ዋንጫዬ ነበር፤ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አመሰግናለሁ፣ ህይወቴን ይበልጥ ያማረ አድርጋችሁታል" ሲል አስፍሯል፡፡

ግብፅ ለአሰልጣኟ ሀውልት አቆመች
#ethiopia | በዓለም ዋንጫው ጉዟቸው የተደነቁት የግብፅ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ሀውልት ተቆመላቸው።
በዓለም ዋንጫው የ16ቱ ግጥሚያ ግብፅ ከአርጀንቲና ጋር ባደረገችው ውጥረት የበዛበት ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እጆቻቸውን በማንሳት የ 'x' ምልክት አሳይተው ነበር።
ግብጽ ለቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እውቅና የሚሰጥ የመታሰቢያ ሀውልት በግብፅ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ላይ አቁናለች።
ይህ ምልክት በፊፋ ደንብ መሰረት በጨዋታ ላይ የሚፈጸም ዘረኝነትን ወይም ማንኛውንም የልዩነት ጥቃት ለማመልከት የሚያገለግል ምልክት ነው።
ሆሳም ሀሰን በወቅቱ በሰጡት ማብራሪያ ምልክቱን ያሳዩት በዳኞች ውሳኔ ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ እንጂ ዘረኝነትን ለማመልከት እንዳልሆነ አብራርተዋል።
ይህ የቆመላቸው የመታሰቢያ ሀውልት አሰልጣኙ ላሳዩት የላቀ አመራር እና በግብፅ ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #egypt #worldcup #statue #manager #hosamhassen

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማርክ ዋልተር በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ማኅበር (NBA) ከሚገኙት ታላላቅ ክለቦች አንዱ የሆነውን የሎስ አንጀለስ ሌከርስን አብላጫ ድርሻ ከገዙ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ክለቡ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር (9.3 ቢሊዮን ፓውንድ) ሊሸጥ መሆኑ ተዘግቧል።
ይህንን በዓለም ላይ በታላቅነቱ የሚታወቀውን የስፖርት ክለብ አብላጫ ድርሻ እየገዙ ያሉት፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች የሆኑት የጃሬድ ኩሽነር ወንድም ጆሽ ኩሽነር እና የቀድሞው የDisney ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቦብ አይገር ናቸው። ማርክ ዋልተር የክለቡን ድርሻ በጥቅምት 2025 በ10 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ከባስ ቤተሰብ የገዙ ሲሆን፣ ይህ ሽያጭ በወቅቱ በኤንቢኤ የቦርድ አባላት በሙሉ ድምፅ ጸድቆ የነበረ የሪከርድ ዋጋ ነበር።
ጆሽ ኩሽነር እና ቦብ አይገር በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የዕድሜ ልክ የኤንቢኤ ደጋፊዎች እንደመሆናቸው በዓለም ላይ ካሉት ታዋቂ የስፖርት ክለቦች አንዱ የሆነውን የሎስ አንጀለስ ሌከርስን የማስተዳደር ዕድል በማግኘታቸው ትልቅ ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸዋል። ለጄሪ እና ጂኒ ባስ አመራር እና ራዕይ ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው የገለጹት ገዢዎቹ፣ የረዥም ጊዜ ግባቸው ይህንን መሠረት በማጠናከር፣ በከፍተኛ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እና ለዚህ ድንቅ ቡድን፣ ለደጋፊዎቹ እንዲሁም ለሎስ አንጀለስ ከተማ ማገልገል መሆኑን አብራርተዋል።
ጄሪ ባስ ሌከርስን በ1979 በ67.5 ሚሊዮን ዶላር የገዙት ሲሆን፣ በወቅቱ ግዢው የሎስ አንጀለስ ኪንግስ የሆኪ ቡድንን እና ኪያ ፎረም የተባለውን ስታዲየም ያካተተ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2013 ካረፉ በኋላ የክለቡ ባለቤትነት ለስድስት ልጆቻቸው በትረስት ተላለፈ ሲሆን፣ በመቀጠልም ከቶድ ቦህሊ ጋር የኤልኤ ዳጀርስ (LA Dodgers) ባለድርሻ ለሆኑት ለማርክ ዋልተር ተሽጦ ነበር። በድርድሩ ዙሪያ ማርክ ዋልተር በበኩላቸው፣ የሎስ አንጀለስ ሌከርስ ባለቤት መሆን በሕይወታቸው ካገኟቸው ታላላቅ ክብሮች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል። ድንቅ ኢንቨስትመንት እንደነበር በማስታወስም፣ ከእርሳቸው ጋር ሁልጊዜ የሚኖረው ይህንን ቡድን እንደ ቤተሰብ የሚንከባከበው ማኅበረሰብ፣ ደጋፊው እና ከተማዋ መሆኑን ገልጸው፣ ሌከርስ የሎስ አንጀለስ በመሆኑ ቡድኑ ወደፊትም ብሩህ ጊዜ እንዳለው ሙሉ እምነት እንዳላቸው አክለዋል።
በታሪኩ ሌከርስ 17 የኤንቢኤ ዋንጫዎችን ያነሳ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር ቦስተን ሴልቲክስ ከያዘው የ18 ዋንጫዎች ሪከርድ በአንድ ብቻ የሚያንስ ነው። በሌላ በኩል በዚህ የሽያጭ ሂደት የተሳተፉት ጆሽ ኩሽነር በቅርቡ ከፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በተያያዘ በተነሳው አወዛጋቢ ጉዳይ ውስጥ ስማቸው መነሳቱ ይታወሳል። የፊፋን ውድድሮች ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ታቅዶ በከሸፈው የ'Fifa Forward Enterprise (FFE)' ውጥን ላይ፣ በኩሽነር የተመሰረተው 'Thrive Eternal' የተሰኘው የአሜሪካ የኢንቨስትመንት ኩባንያ የባለሀብቶቹን ቡድን ይመራል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የሚደረገው ሙከራ "ትልቅ ስህተት" መሆኑን በመግለጽ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢንፋንቲኖ ፊፋን እጅግ ትርፋማ እና ስኬታማ እንዳደረጉት በመጥቀስ፣ ተቋሙ ያለ እርሳቸው ዳግም ስኬታማ ሊሆን እንደማይችል አስጠንቅቀዋል።
በኢንፋንቲኖ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው፣ የዓለም ዋንጫን የንግድ እና ኦፕሬሽን ስራዎች የሚያስተዳድር ኩባንያ በማቋቋም 20 በመቶውን ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ባቀረቡት (እና አሁን ላይ በከሸፈው) እቅድ ምክንያት ነው። ይህንን ተከትሎ የአውሮፓ ፣ የሰሜን አሜሪካ እና የእስያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽኖች በጋራ ባወጡት ግልጽ ደብዳቤ፣ የፕሬዝዳንቱ ድርጊት አሳሳች እና የተቋሙን እምነት መሰረታዊ በሆነ መንገድ የጣሰ መሆኑን በማውገዝ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርበዋል። የአሜሪካ እግር ኳስ ማህበርም የፊፋ አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት ሊኖረው ይገባል ሲል ድጋፉን ገልጿል።
ኢንፋንቲኖ ባቀረቡት እቅድ ዙሪያ ይቅርታ ቢጠይቁም፣ ኮንፌዴሬሽኖቹ በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። በተለይም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) አባል ሀገራት የዓለም ዋንጫን ጨምሮ በፊፋ ውድድሮች ላይ ቦይኮት እስከማድረግ (ውድድሮችን እስከማቋረጥ) ሊደርሱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ከ2016 ጀምሮ ፊፋን እየመሩ የሚገኙት ኢንፋንቲኖ፣ የአሁኑ የስልጣን ዘመናቸው በ2027 የሚያበቃ ሲሆን፣ ስልጣናቸውን እስከ 2031 ለማራዘም በድጋሚ ለመወዳደር ማቀዳቸው ይታወቃል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለፊፋ ፕሬዝደንት ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ለፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በሙሉ ድምፅ ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን ገለፀ፡፡ በኢንፋንቲኖ አመራር ላይ በመላው አለም ተቃውሞ እየተነሳ ባለበት በዚህ ወቅት ካፍ ተቃራኒ አቋም በማንፀባረቅ ፕሬዝደንቱን ደግፏል፡፡ ካፍ ይህንን አቋሙን ዛሬ ይፋ ያደረገው የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ኢንፋንቲኖ በስልጣን ላይ የሚቆዩ ከሆነ በፊፋ ውድድሮች ራሱን እንደሚያገል ማስታወቁን ተከትሎ ነው፡፡ ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ያደነቀው ካፍ የፊፋ ፕሬዝደንትና ዋና ፀሀፊው ያቀረቡለትን ወቅታዊ ገለፃ እንደተቀበለው አስረድቷል፡፡
በዚህም በፊፋ ውስጥ ግልፅነት ያለው መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡ የካፍ ፕሬዝደንት ፓትሪስ ሞትሴፕ ሲናገሩ ‹‹ለእኛ ለአፍሪካዊያን በአስተዳደርና በፍትህ ሂደት ውስጥ ግልፅነት ለድርድር የማይቀርብ ነው፡፡
ስለዚህም ከመንግስቶቻችን፣ ከንግድ ድርጅቶችና ከሌሎችም ተቋማት ይህንን እንጠብቃለን፡፡›› ያሉ ሲሆን ካፍ እነዚህን መርሆዎች በማክበር ከፊፋ፣ ከአባል ማህበራትና ሌሎችም አህጉራዊ ኮንፌዴሬሽኖችና የእግር ኳስ ባለድርሻ አካላት ጋር መስራቱን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውይይት አድርጎ በሙሉ ድምፅ ለኢንፋንቲኖ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ እንደደረሰም አስታውቀዋል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የፊፋ ፕሬዝደንት በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሀም የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ የመጀመሪያው የአገር መሪ ሆነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊፋ የአለም ዋንጫን የተወሰነ ድርሻ ለመሸጥ ያወጣውን እቅድ ‹‹አፀያፊ ሀሳብ›› በማለት ገልፀውታል፡፡
ስልጣን ከያዙ ገና ሁለት ሳምንት የሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በርንሀም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ‹‹የእኔ አቋም ጠንካራ ነው፡፡ ይህ በጣም አፀያፊ ሀሳብ በመሆኑ ለጥያቄ እንኳ መቅረብ አልነበረበትም፡፡ ሀሳቡ መቅረቡ የፊፋው ፕሬዝደንት ድርጅቱን መምራት እንደማይችሉ የሚያሳይ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ቀንደኛ የኤቨርተን ክለብ ደጋፊ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ‹‹በግልፅ ለመናገር እግር ኳስ የባለሀብቶች አይደለም፡፡ ኳስ በየሳምንቱ በዝናብም ሆነ በፀሀይ ስቴዲየም የሚቆሙ ሰዎች ነው፡፡ አለም ዋንጫም ምርት አይደለም፡፡ በአለም ላይ እጅግ ትልቅ የሆነው ይህ ውድድር ሊሸጥ አይገባውም›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡

"18 ሰው ቀርቶብናል፥ እናትና ልጅም ይገኙበታል፥ ለአዘጋጆቹ ወዲያው አሳውቀናል" - የፕሮጀክቱ መስራች
ለጎቲያ ካፕ ወደ ስዊዲን ከሄዱ የኢትዮጵያ ቡድኖች መካከል ደብል ፓስ የእግር ኳስ ፕሮጀክት አንዱ ነው፤ ከቀሩት ተጫዋቾች አብዛኞቹ ከዚህ ስብስብስ የተገኙ በመሆናቸው ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጠን የፕሮጀክቱ መስራች ታዲዮስ ተክሉ ጋር ደውለን ተከታዩን ቆይታ አድርገናል፥ እነሆ፦
ታዲዮስ ስለ ትብብርህ በቅድሚያ እናመሰግናለን፤ ስለራስህና ስለ ፕሮጀክታችሁ በማስተዋወቅ እንጀምር እስኪ?
"ጉዳዩን ለማጥራት ስለደወልክልኝ ታምሩ እኔም አመሰግናለሁ፤ ታዲዮስ ተክሉ እባለሁ፤ የቀድሞ ተጫዋች የአሁን አሰልጣኝ ነኝ፤ ከጫካ ሜዳ ፕሮጀክት ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክና ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድኖችን አሰልጥኛለሁ፤ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኜም በሴካፋ ተሳትፌያለሁ፤ አሁን ደግሞ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሴቶች ቡድንን አሰለጥናለሁ፤ በተጨማሪ የደብል ፓስ ፕሮጀክት መስራችና ዋና አሰልጣኝ ነኝ፤ ይህ ፕሮጀክት ከተቋቋመ ዘጠኝ አመት ሆኖታል፤ በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር ተመዝግበን በከተማው ከ20 አመት በታች ውድድር ላይ እንሳተፋለን"
የስዊዲን ጎቲያ ካፕ እድልን እንዴት አገኛችሁ?
"በራሳችን ጥረት ተፃፅፈን ነው እድሉን ያገኘነው፤ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ነው የተሳተፍነው፤ ከዚህ ቀደም ዴንማርክ ላይም ውድድር አድርገናል"
እስኪ ስለ ስዊዲን ጉዟችሁ አጫውተን
"18 ተጫዋቾችንና 4 የአሰልጣኝ አባላትን በጥቅሉ 22 ልዑካንን ይዘን ነው የሄድነው፤ በውድድሩም ጥሩ ተሳትፎ ነበረን"
22 ሆናችሁ ሄዳችሁ ስንት ሆናችሁ ተመለሳችሁ?
"1 ተጫዋች( የዘማሪ አሸናፊ ገብረ ማርያም ልጅ ፣ ሚካኤል አሸናፊ ) ና 3 የአሰልጣኝ አባላት በአጠቃላይ 4 ሰዎች ብቻ ነው ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው፤ 18ቱ አልመጡም"
ይህ እንዴት ሊፈጠር ቻለ?
"የሁላችንም መመለሻ ቀን ውድድሩ ከተጠናቀቀ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር፤ ሆኖም የአንዱ ታዳጊ ተጫዋች የቅርብ ቤተሰብ ሰርግ ሀምሌ 12 ስለነበር ወላጆቹ ቶሎ ቢመጣልን አሉን፤ በእድሜው ምክንያት ብቻውን መላክ ስለማንችል እኔና ሁለት የአሰልጣኝ አባላት እንዲሁም ተጫዋቹን ጨምሮ አራት ሆነን ትኬታችንን አስተካክለን በፍፃሜው ቀን ቅዳሜ ሀምሌ 11/2018(ጁላይ 18/2026) ወደ አዲስ አበባ ተመለስን፤ ቀሪዎቹ 18ቱ ሰኞ ሀምሌ 13 ነበር የመመለሻ ቀናቸው፤ እኛ አዲስ አበባ ሳንደርስ ለትራንዚት በቆየንበት ኳታር ሆነን ግን ተጫዋቾቹ ቡድናችን ካረፈበት ትምህርት ቤት ሳያሳውቁ እንደወጡ ተነገረን"
ከዛ ምን አደረጋችሁ?
"ወዲያው ለአዘጋጆቹ አሳወቅናቸው፤ እነሱም ለመረጃው አመስግነውን ለሚመለከተው የፀጥታ አካል እንሳውቃለን አሉን፤ አዲስ አበባ ከደረስን በኋላ ድጋሚ አንዷ የቡድን መሪ ጋር ስደውል እንደማይመለሱ፥ ተጫዋቾቹንም ስዊዲን የሚኖሩ ቤተሰብና ዘመዶቻቸው እንደወሰዷቸው ነገረችን፤ ኢትዮጵያ ያሉ ወላጆችንም ጠየቅን፤ ልጆቹ ያሉበትን ቦታ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም፤ ይህንንም ለአዘጋጆቹ በድጋሚ አሳውቀናል፤ ከ10 ቀን በኋላ ዜናውን አወጡት"
ይህ እንዳይከሰት ቅድሚያ ዝግጅት አላደረጋችሁም?
"በደንብ አድርገናል፤ ውል አዘጋጅተን የሁሉንም ተጫዋቾች ወላጆች አስፈርመናል፤ ስዊዲን ከደረስን በኋላም የሁሉም ተጫዋቾች ፓስፖርት እኔ ጋር ነበር፤ ሆኖም እኔ ቀድሜ መመለስ ስለነበረብኝ ፓስፖርቱን ለቡድን መሪ ሰጠሁ፤ ተያይዘው ቀሩ፤ ውስጥ ውስጡን በደንብ ተዘጋጅተውበት ነበር"
ለመሆኑ ወጪያችሁን የሸፈነው ማነው?
"የተጫዋቾቹን የጉዞ ወጪ የቻሉት ወላጆቻቸው ናቸው"
ምን ያህል ከፈሉ?
" ለስልጠና፣ ለጉዞና ለተለያዩ አቅርቦቶች እያንዳንዳቸው 300ሺህ ብር ከፍለዋል፤ የተሻለ አቅም ያላቸው ደግሞ 400ሺህ ብር ከፍለው አግዘውናል"
ለምን 400ሺህ ብር?
"የመክፈል አቅም የሌላቸውን ሶስት ያህል ተጫዋቾችን ይዘን ሄደናል፤ የእነሱን ወጪ ደግሞ እኛና አቅም ያላቸው ወላጆች ሸፍነናል፤ ወላጆቹ ከ300ሺህ ብር በተጨማሪ 100ሺህ ብር እየጨመሩ 400ሺህ ብር እየከፈሉ አቅም የሌላቸው ተጫዋቾች እንዲሄዱ አግዘውናል"
ከተጫዋቾች በተጨማሪ ወላጆችስ ሄደዋል?
"አዎ ሁለት ተጫዋቾች ከእናቶቻቸው ጋር አብረው ወደ ስዊዲን ሄደዋል"
እና ተመለሱ?
"ሁለቱም ተጫዋቾችም ሆኑ እናቶቻቸው አልተመለሱም"
ተጓዥ ተጫዋቾች ከእግርኳስ ጋር ያላቸው ግንኙነትና ችሎታ ደካማ የሆኑ፥ የባለሀብትና የባለስልጣን ልጆች ናቸው ይባላል እውነት ነው?
"ፕሮጀክታችን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና በፊፋ ኮኔክት የተመዘገበ ነው፤ ሆኖም እድሜያቸው ከ16 አመት በታች ስለሆኑ ችሎታ ላይ ብቻ የተመሰረተ ምልመላ አናደርግም፤ ይህን መሰል አለም አቀፍ ውድድር ላይ ስንሳተፍ ደግሞ ቪዛ ለማግኘት አንዱ መስፈርት የወላጆቹ ኢኮኖሚያዊ አቅም ይታያል፤ ስለዚህ የባለሀብትም የባለስልጣንም ልጆች ይኖሩናል፤ ከቀሩት ውስጥ ግን የባለስልጣን ልጅ የለም"
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተጫዋቾቹ መጥፋት አዝኛለሁ ሆኖም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላት አይደሉም ብሎ መግለጫ አውጥቷል፤ ምን ትላለህ?
"እንዳልኩህ በራሳችን ጥረት ነው ተሳትፎውን ያገኘነው፤ ከብሄራዊ ቡድን ጋርም አይገናኝም፤ በተፈጠረው ነገር ዋነኛ ተጎጂዎችም እኛ ነን፤ ስማችን ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፤ በጣም አዝነናል"
በድጋሚ ለትብብርህ ላመስግንህና የመጨረሻ ጥያቄ ላንሳ፥ የቡድኑ ፎቶ ላይ አንድ ህፃን ልጅ ይታያል፤ ተጫዋች ነው?
"ኸረ አይደለም፤ የእኔ ልጅ ነው፤ ገና ስድስት አመቱ ነው፤ አብረን ሄደን አብረን ተመልሰናል"
★ ማስታወሻ፦ ከደብል ፓስ ፕሮጀክት በተጨማሪ በአሰልጣኝ እድሉ ደረጄ የሚመራው ኢዲዋይ እና ዳን አቢሲኒያ የተባሉ ቡድኖች በስዊዲን ጎቲያ ካፕ ተሳትፈዋል፤ እነሱም ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀን ምላሻቸውን እየጠበቅን ነው
(ታምሩ ዓለሙ)

''አምታታው በከተማ''
ግብፅ ፌዴሬሽን
#ethiopia | የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የግብፅ የሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾቹ በማልያቸው ላይ ያሳረፉት የሰባት ከዋክብት ነገር የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ቡድኑ በታሪኩ አህጉራዊውን ዋንጫ አንስቶ የማያውቅ በመሆኑ የከዋክብቱ መኖር በርካታ ሰዎችን "ሴቶቹ የተደበቀ የዋንጫ ታሪክ ይኖራቸው ይሆን?" በሚል ጥያቄና ግራ መጋባት ውስጥ ጥሏቸው ነበር።
ሆኖም የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዚህ ምስጢር መልስ የሚያያዘው ከግብፅ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ጋር ነው የሚል አስቂኝ ምላሽ ሰጥቷል።
ፌዴሬሽኑ በእውኑ ሴቶች ወንዶች ናቸውን የሚለው ጥያቄ ግን ወደ ጎን የተወው ይመስላል።
ማልያው ላይ ያረፉት ሰባት ከዋክብት የሴቶቹ ቡድን ያሸነፋቸውን ዋንጫዎች ሳይሆን ከግብፅ የወንዶች ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ጋር የሚያያዝ ነው።
የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እነዚህን ከዋክብት የጠቅላላ ሀገሪቷ የእግር ኳስ ስኬት መግለጫ አድርጎ በመውሰዱ በሁሉም ብሔራዊ ቡድኖቹ ማልያ ላይ የሰባቱን ከዋክብት ምልክት እንዲያርፍ ወስኗል ነው የተባለው።
የግብፅ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን እስካሁን በመድረኩ የመጨረሻዎቹ የዋንጫ ደረጃዎች ላይ ደርሶ የማያውቅ ቢሆንም ሴቶቹ ተጫዋቾች ደረት ላይ ከዋክብቱ እንዲሰቅሉ ግድ ሆኖባቸዋል።
በዚህ ወር ፍጻሜውን ባገኘው 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ በሞሃመድ ሳላህ የሚመራው የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድንም ተመሳሳይ ከዋክብት በደረታቸው ላይ አድርገው የነበረ ሲሆን ፊፋ ይሄን ኮከብ ቀዳችሁ ጣሉት ሲል ቀጭን ትዕዛዝ እንደሰጣቸው ይታወሳል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፊፋው ፕሬዝደንት ተቺዎቻቸውን ‹‹ፀልዩ›› አሉ፡፡ የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ዛሬ ባሰራጩት ዘለግ ያለ ‹‹ግልፅ ደብዳቤ›› ተቺዎቻቸውን ‹‹ጊዜ ወስዳችሁ አሰላስሉ፣ ፀልዩ›› ሲሉ ገለፁ፡፡ ከስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ መናር አንስቶ እስከ ቪዛ ጥያቄ ድረስ በርካታ ውዝግቦችን ያስተናገደው አለም ዋንጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በበተኑት በዚህ ደብዳቤ ‹‹በጥላቻና በትችት ለተዋጣችሁ በጣም አዝናለሁ›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹ከስክሪብቶና ከወረቀት ጀርባ ሆነው፣ ከስክሪኖች ፊት ለፊት ተቀምጠው ጥላቻናው የሀሰት ወሬዎችን ለሚያሰራጩ እኛ እንደፊፋ ከፊት ሆነን በአለም ላይ ምርጥ የሆነውን ውድድር ጠንክረን በመስራት ማጠናቀቃችንን ለመግለፅ እፈልጋለሁ፡፡ በውድድሩ ላይ ምንም አይነት ጥቃት ወይንም ክስተት ሳይፈጠር 100 ፐርሰንት ደህንነቱንና ፀጥታው የተጠበቀ ሆኖ አልፏል፡፡
ያጋጠመን ደስታና ሀሴት ብቻ ነበር›› በማለት ገልፀዋል፡፡ ኢንፋኒኖ አስከትለውም ‹‹እናንተ ጥላቻን ስታሰራጩ እኛ ሁለት በጦርነት ውስጥ ያሉ አገራት አንድ እንዲሆኑ ያለመታከት ሰርተናል፡፡ ኢራን ያለምንም አደጋ ወይንም ግጭት አሜሪካ ለመግባት ችላ ነበር፡፡ የኢራን ቡድን የተቀበለው መግባት የሚያስችል ቪዛ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እግር ኳስ ፖለቲካ ሳይሆን ሰላም ነው›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

3 months ago
በአለም ዋንጫው 289 ተጫዋቾች ላልተወለዱባቸው አገራት ተሰልፈው ተጫውተዋል
#ethiopia | በ2026 የአለም ዋንጫ ከተሳተፉ 48 ቡድኖች መካከል ስምንቱ ብቻ ናቸው ከግዛታቸው ውጪ የተወለዱ ተጫዋቾች ያላሰተፉት ተብሏል።
ይህም በውድድሩ ከሚሳተፉ ተጫዋቾች መካከል አንድ አራተኛውን ይሸፍናል
በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ኪዩራሳው ለውድድሩ ከመረጠቻቸው 26 ተጫዋቾች መካከል አንዱ ብቻ ነው በደሴቲቱ ውስጥ የተወለደው።
ኪዩራሳው የአውሮፓዊቷ ኔዘርላንድስ ንጉሣዊ መንግሥት አካል ስትሆን አብዛኛው የቡድኗ አባላት ኔዘርላንድስ ውስጥ የተወለዱ ናቸው።
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓለም ዋንጫ ቡድኖች ውስጥ የውጭ አገር ተወላጅ የሆኑ ተጫዋቾች ቁጥር ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍ እና ዝቅ ሲል ተስተውሏል።
በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ አገራት ቁጥር ከ32 ወደ 48 ከፍ ያለ ሲሆን አገራቱ ያሰለፏቸው ተጫዋቾችም ቁጥር 1,248 ነው።
ከዚህ ውስጥም ከሚጫወቱበት አገር ውጪ የተወለዱ የተጫዋቾች ቁጥር 289 ደርሷል።
አጠቃላይ መጠኑም ከ23 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል።
ፊፋ በአውሮፓውያኑ 1904 የተቋቋመው ቢሆንም በ1960ዎቹ ውስጥ ነበር መደበኛ የተጫዋቾች የዜግነት ደንቦችን ያወጣው።
እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን ተጫዋቾች ለመረጡት የትኛውም አገር ተሰልፈው ለመጫወት ዜግነት አያስፈልጋቸውም ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fifaworldcup2026 #nationalityplayers

ፊፋ በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ የግጥሚያ ማስተካከል አልተፈጸመም ሲል አስታወቀ
#ethiopia | የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት የግጥሚያ ማስተካከል (Match-fixing) ተፈጽሟል የሚሉ ወሬዎችን በድጋሚ በማስተባበል፣ በውድድሩ ሙሉ ጊዜ ከውርርድ ወይም ከግጥሚያ ማጭበርበር ጋር የተያያዘ ማንኛውም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ አልተገኘም ብሏል።
ፊፋ እንደገለጸው፣ በውድድሩ 104 ጨዋታዎች በሙሉ የስፖርት ታማኝነትን የሚከታተል ልዩ ቡድን ከዓለም አቀፍ የውርርድ ቁጥጥር ተቋማት ጋር በመተባበር ቁጥጥር ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉም የግጥሚያ ውጤት መቀየር ወይም ሕገ-ወጥ የውርርድ እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ አልተገኘም ብሏል።
ይህ መግለጫ የወጣው በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ በተፈጠሩ የዳኝነት ውሳኔዎችና የVAR አጠቃቀም ዙሪያ የተነሱ ክርክሮች ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተስፋፉ የ“ውድድሩ ተስተካክሏል” የሚሉ ውንጀላዎችን ተከትሎ ነው።
ቀደም ሲልም የፊፋ የዳኝነት ኃላፊ ፒየርሉጂ ኮሊና የዳኞችን ታማኝነት የሚጠራጠሩ ያልተደገፉ ክሶች በስፖርቱ ውስጥ ቦታ የላቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር።

የእግር ኳስ ኢንዱስትሪውን እያወደሙት ነው፦ ጃቪየር ታባስ
#ethiopia | የላ ሊጋ ፕሬዝዳንት ጃቪየር ተባስ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቀረቡ።
ተባስ ኢንፋንቲኖ የእግር ኳስ ኢንዱስትሪውን እያወደሙ ነው ሲሉ ከሰዋል።
ለጣሊያኑ ላ ጋዜታ ዴሎ ስፖርት በሰጡት ቃለ ምልልስ የላ ሊጋው ኃላፊ በፊፋ አመራር ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ገልጸዋል።
በተለይም በዓለም ዋንጫው ወቅት የተደረጉ የውሃ መጠጫ እረፍቶች፣ የፍጻሜ ጨዋታ የዕረፍት ሰዓት ርዝማኔ፣ እና የወደፊት የ64 ቡድኖች የዓለም ዋንጫ ሃሳብ ስፖርቱን የሚጎዳ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተባስ አክለውም በእኔ እይታ የእሳቸው ጊዜ አብቅቷል ካሉ በኋላ የፊፋ የምርጫ ስርአት በመበላሸቱ እና ተፎካካሪ ባለመኖሩ ኢንፋንቲኖ በስልጣን ላይ ለመቆየት አስበዋል ያ ትክክል አይደለም ብለዋል።
ብዙዎች በእርሳቸው ደስተኛ አይደሉም ነገር ግን ዝምታን መርጠዋል ይህም ዝምታ ከእርሳቸው ተግባር በምን ያህል እንደሚለይ አላውቅም በማለት አቋማቸውን በግልጽ አስቀምጠዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #laligapresidentjaviertebas #fifapresidentgianniinfantino

የአለም ዋንጫ ያለ እሷ አይታሰብም፦
የፊፋ ፕሬዝዳንት
*ፊፋ ሻኪራ የውድድሩ ቅመም ብሏታል።
#ethiopia | የዓለም ዋንጫዋ ድምቀት ሻኪራ እና የሙዚቃው ስሜት በአረንጓዴው ሜዳ ትላንት ምሽትም ደምቆ ታይቷል።
በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ከስፖርታዊ ብቃት ባሻገር በሙዚቃዊ ስሜት ሲታወስ የኖረው የዓለም ዋንጫ ዘንድሮም የኮሎምቢያዊቷን ኮከብ ሻኪራን ብቃት ተደምሟል።
ሻኪራ ከእግር ኳስ ዓለም ጋር ያላት ቁርኝት እጅግ የጠበቀ ነው።
በተለይም በ2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ላይ የዘፈነችው Waka Waka (This Time for Africa) ዘፈን እስካሁን ድረስ ከዓለም ዋንጫ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ምርጥ የሙዚቃ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
የእሷ ሙዚቃ በዓለም ዙሪያ ያሉ የተለያዩ ባህሎችን የሚያቀናጅ በመሆኑ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን በማቀራረብ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።
የፊፋው ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ሻኪራ መድረክ ላይ መገኘት ለጨዋታዎቹ ተጨማሪ ድምቀት በመስጠት የስታዲየሙን ድባብ ከፍ ታደርጋለች ብለዋል።
እሷ የአለም ዋንጫው ቅመም ናት ሲሉም አሞካሽተዋታል።
ሻኪራ የሙዚቃ ንግሥት ብቻ ሳትሆን የእግር ኳስ ዓለም የቅርብ ወዳጅ መሆኗን እንደገና ያረጋገጠችበት ሆኗልም ሲሉ አክለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fifaworldcup2026 #colombiansinger #shakiradaidaiwakawaka

ስታዲየም ተገኝቶ ጨዋታውን የተከታተለው ህዝብ ከኬፕ ቬርዴ ሕዝብ ብዛት በ12 እጥፍ ይበልጣል
#ethiopia | እንደ ፊፋ መረጃ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር በመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ውድድር ላይ ከፍተኛ የተመልካቾችን ቁጥር አስመዝግቧል።
4.6 ሚሊዮን ሰዎች በ72 ጨዋታዎች ላይ መገኘት ችለዋል።
ይህም በአውሮፓውያኑ 1994ቱ በአሜሪካ አስተናጋጅነት በተካሄደው ውድድር የተመዘገበውን ቁጥር የሚበልጥ ነው።
በ16ቱ ዙር መጨረሻ ላይ የተመልካቾች ቁጥር ወደ 6.25 ሚሊዮን ከፍ ብሏል።
ይህም ከኬፕ ቬርዴ ሕዝብ ብዛት በ12 እጥፍ ይበልጣል።
በዚህ መሰረት ፊፋ ከተመልካች ገቢ አረብጣ ቢሊዮን ዶላሮች ወደ ካዝናው አስገብቷል።
አንዳንድ መረጃዎች እንደገለፁት ከሆነ ፊፋ በዚህ አለም ዋንጫ እስከ 10ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldcup2026 #fifarevenuefromsupporter

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኳታር መንግሥት ለአሜሪካ መሪዎች የሥራ ጉዞ በስጦታ ያበረከተውና በአሁኑ ወቅት እንደ ዋናው ፕሬዝደንታዊ አውሮፕላን እያገለገለ ያለው ጃምቦ ጄት፣ የደኅንነት ገፅታዎቹን በተመለከተ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ በቅርቡ ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት እንደሚላክ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ዓመት በስጦታነት የተቀበሉትን ይህንን ቦይንግ 747-8 አውሮፕላን ለፕሬዝደንታዊ አገልግሎት እንዲውል በፍጥነት የማደስ ሥራ ከተከናወነ በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ጁላይ 1፣ 2026 (እ.ኤ.አ.) በሜሪላንድ ከሚገኘው ጆይንት ቤዝ አንድሪውስ ወደ ሰሜን ዳኮታ ለቴዎዶር ሩዝቬልት ፕሬዝደንታዊ ላይብረሪ ምረቃ ስነ-ስርዓት ለመጓዝ ተጠቅመውበታል።
ይሁን እንጂ ጁላይ 8 ቀን ከአሜሪካ ጋር በነበረው ከፍተኛ የኢራን ውጥረት መባባስ ምክንያት፣ ትራምፕ ከቱርክ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) በሚያደርጉት በረራ ላይ ይህንን አዲስ አውሮፕላን ባልተጠበቀ ሁኔታ ትተውት ነበር። በወቅቱ ወደ ለንደን የተጓዙት በአሮጌው ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ሲሆን፣ ድርጊቱንም “ለቀድሞው ትዝታ ሲባል” ያደረጉት እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን በኋላ ላይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ በአዲሱ አውሮፕላን ተሳፍረዋል።
ትራምፕ በኒው ጀርሲ ከተካሄደው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ አዲስ የታደሰው አውሮፕላን የሚሳይል መከላከያ ሥርዓት ይጎድለዋል ወይ ተብለው በጋዜጠኞች ተጠይቀው ነበር።
ትራምፕ ስለ አውሮፕላኑ ሲናገሩ “ከፍተኛ የሆነ የመከላከልና የአገልግሎት አቅም አለው” ካሉ በኋላ፣ “ነገር ግን እኔ እንደተረዳሁት፣ በሚቀጥለው አንድ ወር ገደማ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሙሉዕ እንዲሆን እና ከፍተኛ ማሻሻያ እንዲደረግበት ይልኩታል። ይህም አንድ ወር ገደማ ይወስዳል” ብለዋል።
የአሜሪካ አየር ኃይል በዚህ ጉዳይ ላይ በይፋ አስተያየት ለመስጠት የቀረበለትን ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

* "አርጀንቲና በጨዋታዋም ሆነ በባህሪዋ ፍጹም አሳፋሪ ነበረች" - ካፒቴን አላን ሺረር #bbc
* "ሜሲ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል?"
#ethiopia | በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስፔን አርጀንቲናን 1ለ0 ካሸነፈች በኋላ የተፈጠረው ግጭት በዓለም የስፖርት ሚዲያዎች በስፋት ተወግዟል።
የጨዋታው ፍጻሜ ጩኸት እንደተሰማ የስፔን ተጫዋቾች ድላቸውን ለማክበር ሲሮጡ፣ የአርጀንቲና ተጫዋቾች ከእነሱ ጋር በመጋጨት የተወሰኑ አካላዊ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል።
በተለይ ሊያንድሮ ፓሬዴስ የስፔኑን ተከላካይ ኤሪክ ጋርሲያ በአንገቱ በመያዝ እና ጋቪን ወደ መሬት በመጣል ቀይ ካርድ ተመልክቶ ከዋንጫ ስነ-ሥርዓቱ ተሰናብቷል። በሌላ በኩል ናሁኤል ሞሊና አንድ የስፔን ተጫዋችን በሆዱ መትቶታል የሚል ክስም ቀርቦበታል።
ጨዋታው በራሱም ጠንካራ ፉክክር የታጀበ ሲሆን፣ የአርጀንቲናው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በመደበኛው ሰዓት መጨረሻ በፓው ኩባርሲ ላይ በፈጸመው ከባድ ጥፋት ቀይ ካርድ ተመልክቶ ነበር።
የስፖርት ተንታኞች ያሰሙት ከባድ ትችት
የቀድሞው የእንግሊዝ ካፒቴን አላን ሺረር በBBC ላይ ሲናገር፦
"ይህ በጣም አስከፊ ነው። ሽንፈት ያማል፤ ግን ሽንፈትን የሚቀበሉበት መንገድ አለ። ከአርጀንቲና ይህን አይነት ባህሪ ብዙ ጊዜ አይተናል።"
የቀድሞው የስኮትላንድ ተጫዋች ክሬግ በርሌይ ደግሞ በESPN ላይ በእጅጉ አጥብቆ ተችቷል።
"አርጀንቲና ዛሬ በጨዋታዋም ሆነ በባህሪዋ ፍጹም አሳፋሪ ነበረች። ከኳስ ውጭ የሚደረጉ ነገሮችን ጠብቀን ነበር፤ ግን በኳስ ውስጥ የተሻለ ነገር እንጠብቅ ነበር። ያሳዩት አፀያፊና አሳፋሪ ነበር።"
ለሜሲ የማይገባ መጨረሻ
የቀድሞው የጋና ኮከብ ኬቨን-ፕሪንስ ቦአቴንግ ደግሞ ይህ ድርጊት ለሊዮኔል ሜሲ የማይገባ እንደነበር ገልጿል።
"ከጨዋታው በኋላ የታዩት ትዕይንቶች የመጥፎ ተሸናፊነት ምልክት ናቸው። ሊዮ ሜሲ ይህን አይገባውም።"
39 ዓመቱ የደረሰው ሊዮኔል ሜሲ ከጨዋታው በኋላ በእንባ ሲያለቅስ የታየ ሲሆን፣ ይህ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫው ሊሆን እንደሚችል በርካታ ተንታኞች ይገምታሉ።
የስፔን ተጫዋቾች የሚገባቸውን የድል ክብር ሲያከብሩ፣ ከጨዋታው በኋላ የተፈጠረው ውዝግብ ግን በዓለም የስፖርት ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስከትሏል።
"ሜሲ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል?"
– በ2026 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የተነሳው ክርክር
በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስፔን አርጀንቲናን 1-0 ካሸነፈች በኋላ፣ በሜዳ ውስጥ የተፈጠረው አንድ ክስተት በዓለም አቀፍ ሚዲያና በማኅበራዊ ሚዲያ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
ጨዋታው ወደ ፍጻሜው በተቃረበበት ወቅት፣ የስፔኑ ተከላካይ ማርክ ኩኩሬያ አፉን በእጁ ሸፍኖ ሲናገር የታየ ሲሆን፣ የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ለዳኛው ስሎቬንያዊው ስላቭኮ ቪንቺች ይህ በአዲሱ የፊፋ ደንብ መሠረት ቀይ ካርድ ሊያስከትል ይገባል በማለት ቅሬታ አቅርቧል። ሆኖም ዳኛውም ሆነ VAR ምንም ዓይነት እርምጃ አልወሰዱም።
ይህ ድርጊት በርካታ የስፖርት ተንታኞችን ለትችት አነሳስቷል።
የእንግሊዝ ታዋቂው ዋይን ሩኒ፣ "ይህ የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው፤ ከሜሲ የሚጠበቅ የስፖርታዊነት ባህሪ አይደለም" ሲል ተችቷል። የቀድሞው ግብ ጠባቂ ጆ ሃርትም "ከሜሲ እንዲህ ያለ ነገር ማየት አላስደሰተኝም" ብሏል። ሊ ዲክሰን ደግሞ ሜሲን "እንዲህ በማድረግ ተጫዋች ለማስወጣት መሞከር ተገቢ አይደለም" ሲል ተችቷል።
ከዚህ በኋላም የተነሱ ውይይቶች ሜሲ የዳኛውን ውሳኔ ለመቀየር ሞክሯል ወይስ የደንቡን ተፈጻሚነት ብቻ ጠይቋል በሚል ተከፍለዋል። ነገር ግን በይፋ የተረጋገጠ ማስረጃ ኩኩሬያ ዘረኛ ወይም አድሎአዊ ስድብ ተናግሯል የሚል አልቀረበም፣ ስለዚህም ዳኛው ቀይ ካርድ አላሳየም።
በማጠቃለያ፣ ሜሲ ለዳኛው ቅሬታ ማቅረቡ እውነት ቢሆንም፣ ድርጊቱ "አሳፋሪ" ነው ወይስ የውድድር ስልት አካል ነው የሚለው የአስተያየት ጉዳይ ነው። ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ግን ብዙዎቹ የሜሲን ድርጊት "ተስፋ የቆረጠ" እና "ስፖርታዊነትን የማይመጥን" በሚል መልኩ እንደተቹት ዘግበዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ማጠቃለያ ላይ ስፔን አርጀንቲናን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፋ ዋንጫዋን በተረከበችበት የሽልማት ስነ-ስርዓት ወቅት፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፊፋው ፕሬዝደንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ወደ ሜዳ ሲገቡ በስታዲየሙ በነበሩ ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ የቅሬታ ጩኸትና ተቃውሞ አስተናግደዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ከጨዋታው መጀመር 45 ደቂቃ ያህል ቀደም ብሎ “ማሪን ዋን” በተሰኘችው የፕሬዝደንቱ ሄሊኮፕተር ስታዲየሙን ከበው በመብረር ነበር የደረሱት። በጨዋታው ወቅትም ከፊፋው ፕሬዝደንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን በመስተዋት በተከለለ የክብር እንግዶች ወንበር ላይ ተቀምጠው ጨዋታውን ተከታትለዋል። በአቅራቢያቸውም የስፔኑ ንጉሥ ፊሊፔ ስድስተኛ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ እና የሜክሲኮዋ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሼይንባውምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች ተገኝተው ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ከተዘመረ በኋላ የፕሬዝደንት ትራምፕ ምስል በስታዲየሙ ትላልቅ የቪዲዮ ስክሪኖች ላይ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ከታዳሚዎች ዘንድ መጠነኛ የተቃውሞ ድምፅ ቢሰማም፣ በፕሬዝደንትነት ዘመናቸው በሌሎች የስፖርት መድረኮች ላይ እንደገጠማቸው ዓይነት የከረረ ጠላትነት የተሞላበት አቀባበል አልነበረም።
ነገር ግን ስፔን ድሏን ካረጋገጠች በኋላ፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት እና ኢንፋንቲኖ ለሽልማት ስነ-ስርዓቱ ወደ ሜዳ ሲዘልቁ በስታዲየሙ ዙሪያ ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት አስተጋብቷል። የዋይት ሃውስ (የነጭ ማሊያ) የጋዜጠኞች ቡድን ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ሁለቱ ግለሰቦች ወደ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት በስታዲየሙ የነበረው የተለመደው የሕዝብ ድምፅ ጩኸት 78 ዴሲበል ገደማ የነበረ ሲሆን፣ ትራምፕ ሜዳውን ሲረግጡ ግን ደጋፊው ባሰማው ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት ምክንያት ድምፁ ወደ 84 ዴሲበል ከፍ ሊል ችሏል።
ከዚህም በላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ የሜዳውን መድረክ ተቀላቅለው ዋንጫው በሚነሳበት ወቅት በምስል ዕይታ ውስጥ በመግባት፣ የስፔንን ብሔራዊ ቡድን ታሪካዊ የድል አከባበር ድግስ (Victory party) በጋራ ለመጋራት እና ለመቀላቀል ጥረት ማድረጋቸው በሰፊው ተስተውሏል።

ስፔን ~ "የአዲሱ ትውልድ ንጉሥ"
Ethiopia | በኒው ጀርሲ የሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በማስተናገድ የእግር ኳስ ታሪክ አዲስ ገጽ ጻፈ።
ስፔን አርጀንቲናን 1ለ0 ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ በማሸነፍ ሁለተኛዋን የዓለም ዋንጫ አነሳች። የድሉን ግብ ፌራን ቶሬስ በ106ኛው ደቂቃ አስቆጠረ።
ይህ ፍጻሜ የተገለጸው "የታክቲክ፣ የፍጥነት እና የጥራት ውጊያ" በሚል ነበር። ስፔን በኳስ ቁጥጥር፣ በአማካይ ክፍል ብልጫ እና በፈጣን የጎን ጥቃት ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች፤ አርጀንቲና ደግሞ በጠንካራ መከላከል እና በኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ድንቅ ብቃት ረጅም ጊዜ ጨዋታውን አቆየች።
የስፔን የበላይነት
ስፔን በኳስ ቁጥጥር፣ በትክክለኛ ቅብብሎች እና በማያቋርጥ ግፊት ጨዋታውን አስተዳደረች። የሮድሪ የመሀል ሜዳ ብቃት፣ የላሚን ያማል ፈጣን እንቅስቃሴ፣ የፓው ኩባርሲ መከላከል እና የኡናይ ሲሞን የግብ ጥበቃ ስፔንን ወደ ክብሩ አድርሰዋል።
በአንጻሩ አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ እና ባልደረቦቹ ጥረት ብትታገልም የስፔንን ግፊት መቋቋም አልቻለችም። የኤንዞ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ደግሞ የቡድኑን ተስፋ አዳከመ።
የ2026 የዓለም ዋንጫ የውድድሩ ኮከቦች
የፊፋ የውድድሩ ሽልማቶች እንዲህ ተሰጥተዋል፦
🏆 የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች (Golden Ball): ሮድሪ (ስፔን)
🧤 የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ (Golden Glove): ኡናይ ሲሞን (ስፔን)
⭐ የውድድሩ ምርጥ ወጣት ተጫዋች: ፓው ኩባርሲ (ስፔን)
⚽ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አግቢ (Golden Boot): ኪሊያን ምባፔ (ፈረንሳይ)
የዓለም ሚዲያዎች ምን አሉ?
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስፔንን እንደ "የአዲሱ ትውልድ ንጉሥ" ገልጸዋታል። በተለይ የመሀል ሜዳ ቁጥጥር፣ የቡድን ቅንጅት እና የወጣት ተጫዋቾቿ ጥራት የድሉ ቁልፍ መሆናቸው ተወድሷል። አርጀንቲና በመከላከል ብትታገልም የስፔንን ግፊት መቋቋም አልቻለችም ብለዋል።
የ2026 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ እግር ኳስ የታክቲክ፣ የቴክኒክ እና የአዲስ ትውልድ ብልጫ የተንጸባረቀበት ታሪካዊ ምሽት ሆኖ በዓለም የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ይታወሳል።
አለባቸው ደሳለኝ ( ከኢትዮጵያ )

Comments