16 days ago
የእግር ኳስ ኢንዱስትሪውን እያወደሙት ነው፦ ጃቪየር ታባስ
#ethiopia | የላ ሊጋ ፕሬዝዳንት ጃቪየር ተባስ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቀረቡ።
ተባስ ኢንፋንቲኖ የእግር ኳስ ኢንዱስትሪውን እያወደሙ ነው ሲሉ ከሰዋል።
ለጣሊያኑ ላ ጋዜታ ዴሎ ስፖርት በሰጡት ቃለ ምልልስ የላ ሊጋው ኃላፊ በፊፋ አመራር ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ገልጸዋል።
በተለይም በዓለም ዋንጫው ወቅት የተደረጉ የውሃ መጠጫ እረፍቶች፣ የፍጻሜ ጨዋታ የዕረፍት ሰዓት ርዝማኔ፣ እና የወደፊት የ64 ቡድኖች የዓለም ዋንጫ ሃሳብ ስፖርቱን የሚጎዳ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተባስ አክለውም በእኔ እይታ የእሳቸው ጊዜ አብቅቷል ካሉ በኋላ የፊፋ የምርጫ ስርአት በመበላሸቱ እና ተፎካካሪ ባለመኖሩ ኢንፋንቲኖ በስልጣን ላይ ለመቆየት አስበዋል ያ ትክክል አይደለም ብለዋል።
ብዙዎች በእርሳቸው ደስተኛ አይደሉም ነገር ግን ዝምታን መርጠዋል ይህም ዝምታ ከእርሳቸው ተግባር በምን ያህል እንደሚለይ አላውቅም በማለት አቋማቸውን በግልጽ አስቀምጠዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #laligapresidentjaviertebas #fifapresidentgianniinfantino

Comments