Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) እንግሊዝና አርጀንቲና ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፊፋ 2026 አለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ሮብ እለት በአትላንታ ይገናኛሉ፡፡ ይህ ጨዋታ ወደፍፃሜ ለማለፍ የሚደረግ መሆኑ በራሱ ከባድ ቢሆንም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ተቀናቃኝነት ደግሞ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡ የእንግሊዝና አርጀንቲና ተቀናቃኝነት መነሻው እግር ኳስ ሳይሆን ደቡባዊ አትላንቲክ ነው፡፡ በኤፕሪል ወር 1982 አርጀንቲና ‹‹ኢስላስ ማልቪናስ›› ብላ የምትጠራውንና እንግሊዝ ደግሞ ፋክላንድ ደሴት ብላ ስያሜ የሰጠችውን ቦታ የእንግሊዝ ጦር ሀይል ወረረ፡፡

ይህ ደግሞ በሁለቱ አገራት መካከል 2 ወር ከ1 ሳምንትና ከ5 ቀናት የፈጀ ጦርነትን ሊያስከትል ችሏል፡፡ በውጤቱም ከአርጀንቲና በኩል 649 ወታደሮች ሲገደሉ ከእንግሊዝ በኩል ደግሞ የ255 ወታደሮችን ህይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ 3 የደሴቱ ነዋሪዎችም ህይወታቸው አልፏል፡፡ ጦርነቱ የተጠናቀቀው ደግሞ ደሴቱን የእንግሊዝ ወታደሮች እንዲይዙት አርጀንቲና ፈቅዳ ነበር፡፡ አሁንም ድረስ ፋክላንድ ደሴት በእንግሊዝ አስተዳደር ስር የምትገኝ ቢሆንም ራስ ገዝ መንግስት ያላት ናት፡፡ በእንግሊዝና በአርጀንቲና መካከል ቀደም ሲልም በእግር ኳስ ተፎካካሪነት ያለ ቢሆንም ይህ ጉዳይ ግን የተቀናቃኝነቱን ደረጃ ከፍ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም በሁለቱ አገራት መካከል ጨዋታ ሲኖር ደጋፊዎችና ሚዲያዎች ልዩ ትኩረት ይሰጡታል፡፡

ያለፉትን አራት አስርት አመታት በአለማችን ላይ ከሚከናወኑ አለም አቀፍ ጨዋታዎች ሁሉ ይህኛው እጅግ ትልቅ ፉክክር የሚታይበት ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ከፋክላንድ ደሴት ጦርነት ከአራት አመታት በኋላ ሁለቱ አገራት በ1986 የሜክሲኮ አለም ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ ተገናኝተው ነበር፡፡ ከጠቀስነው የሜዳና ከሜዳ ውጭ ካለው ፉክክር ባሻገር ይህ ጨዋታ በአለማችን የአለም ዋንጫ ታሪክ በብዙዎች የታየና በከፍተኛ ሁኔታ መነጋገሪያ ለመሆን የቻለበት አጋጣሚ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ ይህንን አጋጣሚ የፈጠረው ደግሞ አንጋፋው የኳስ ኮከብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ነው፡፡ ያንን ጨዋታ አርጀንቲና ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ብትችልም ማራዶና በእጁ ያስቆጠራት ጎል ግን የማትረሳ ነበረች፡፡ ይህ ከሆነ ከ12 አመታት በኋላ በ1998 የፈረንሳይ አለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ድጋሚ ተገናኝተው ነበር፡፡

ይህኛውም ጨዋታ ከባድ ፉክክር የታየበት ሆኖ ሁለት እኩል ለመለያየት የቻሉ ቢሆንም በፍፁም ቅጣት ምት አርጀንቲና ለማሸነፍ በቅታለች፡፡ በመቀጠል በጃፓንና ደቡብ ኮሪያ በተካሄደው አለም ዋንጫ በምድብ ግጥሚያ ተገናኝተው እንግሊዝ አንድ ለባዶ አሸንፋ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሁለቱ አገራት በአለም አቀፍ ውድድር ሜዳ ላይ ተገናኝተው አያውቁም፡፡ ነገር ግን ባለፈው አመት በጄኔቫ የወዳጅነት ግጥሚያ አድርገው እንግሊዝ 3 ለ 2 ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ በነገው እለት ሁለቱ አገራት ከ24 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ዋንጫ ተገናኝተው የሚያደርጉት ግጥሚያ ከጨዋታም በላይ ልዩ ትኩረት ያገኘው ለዚህ ነው፡፡

23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.