13 days ago
በአለም ዋንጫው 289 ተጫዋቾች ላልተወለዱባቸው አገራት ተሰልፈው ተጫውተዋል
#ethiopia | በ2026 የአለም ዋንጫ ከተሳተፉ 48 ቡድኖች መካከል ስምንቱ ብቻ ናቸው ከግዛታቸው ውጪ የተወለዱ ተጫዋቾች ያላሰተፉት ተብሏል።
ይህም በውድድሩ ከሚሳተፉ ተጫዋቾች መካከል አንድ አራተኛውን ይሸፍናል
በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ኪዩራሳው ለውድድሩ ከመረጠቻቸው 26 ተጫዋቾች መካከል አንዱ ብቻ ነው በደሴቲቱ ውስጥ የተወለደው።
ኪዩራሳው የአውሮፓዊቷ ኔዘርላንድስ ንጉሣዊ መንግሥት አካል ስትሆን አብዛኛው የቡድኗ አባላት ኔዘርላንድስ ውስጥ የተወለዱ ናቸው።
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓለም ዋንጫ ቡድኖች ውስጥ የውጭ አገር ተወላጅ የሆኑ ተጫዋቾች ቁጥር ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍ እና ዝቅ ሲል ተስተውሏል።
በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ አገራት ቁጥር ከ32 ወደ 48 ከፍ ያለ ሲሆን አገራቱ ያሰለፏቸው ተጫዋቾችም ቁጥር 1,248 ነው።
ከዚህ ውስጥም ከሚጫወቱበት አገር ውጪ የተወለዱ የተጫዋቾች ቁጥር 289 ደርሷል።
አጠቃላይ መጠኑም ከ23 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል።
ፊፋ በአውሮፓውያኑ 1904 የተቋቋመው ቢሆንም በ1960ዎቹ ውስጥ ነበር መደበኛ የተጫዋቾች የዜግነት ደንቦችን ያወጣው።
እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን ተጫዋቾች ለመረጡት የትኛውም አገር ተሰልፈው ለመጫወት ዜግነት አያስፈልጋቸውም ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fifaworldcup2026 #nationalityplayers

Comments