Logo
Getu Temesgen
ፕሬዝዳንቱ እየተለመኑ ነው
#ethiopia | እንደ ቶክ ስፖርት (talkSPORT) ዘገባ ከሆነ የፓሪስ ሴንት ዠርሜን (PSG) ፕሬዝዳንት የሆኑት ናስር አል ካሊፋ የፊፋን ፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) አባል የሆኑ በርካታ ሀገራት ግፊት እያደረጉባቸው ነው።

በፊፋ እና በ UEFA መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ የአውሮፓ ሀገራት በፊፋ ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ላይ አማራጭ እጩ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገለጸ።

ኢንፋንቲኖ በኤፕሪል ወር ላይ ለሶስተኛ ጊዜ የፊፋ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ማሰባቸውን አረጋግጠዋል።

የፊፋ የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ህዳር 18 በሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ናስር አል-ኬላፊ እስካሁን ለዚህ ቦታ የመወዳደር ፍላጎት እንደሌላቸው እና እንዲወዳደሩ ለማሳመን የአውሮፓ ሀገራቴ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተዘግቧል።

የ UEFA ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ቢታሰብም በ UEFA ፕሬዝዳንትነት መቀጠል እንደሚፈልጉ ይነገራል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fifapresidentenfantino #casablanca #uefa
#parissaintgermain #presidentnasseralkhelaifi

20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.