Logo
Getu Temesgen
የአለም ዋንጫ ያለ እሷ አይታሰብም፦
የፊፋ ፕሬዝዳንት

*ፊፋ ሻኪራ የውድድሩ ቅመም ብሏታል።
#ethiopia | የዓለም ዋንጫዋ ድምቀት ሻኪራ እና የሙዚቃው ስሜት በአረንጓዴው ሜዳ ትላንት ምሽትም ደምቆ ታይቷል።

በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ከስፖርታዊ ብቃት ባሻገር በሙዚቃዊ ስሜት ሲታወስ የኖረው የዓለም ዋንጫ ዘንድሮም የኮሎምቢያዊቷን ኮከብ ሻኪራን ብቃት ተደምሟል።

ሻኪራ ከእግር ኳስ ዓለም ጋር ያላት ቁርኝት እጅግ የጠበቀ ነው።

በተለይም በ2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ላይ የዘፈነችው Waka Waka (This Time for Africa) ዘፈን እስካሁን ድረስ ከዓለም ዋንጫ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ምርጥ የሙዚቃ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

የእሷ ሙዚቃ በዓለም ዙሪያ ያሉ የተለያዩ ባህሎችን የሚያቀናጅ በመሆኑ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን በማቀራረብ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።

የፊፋው ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ሻኪራ መድረክ ላይ መገኘት ለጨዋታዎቹ ተጨማሪ ድምቀት በመስጠት የስታዲየሙን ድባብ ከፍ ታደርጋለች ብለዋል።

እሷ የአለም ዋንጫው ቅመም ናት ሲሉም አሞካሽተዋታል።

ሻኪራ የሙዚቃ ንግሥት ብቻ ሳትሆን የእግር ኳስ ዓለም የቅርብ ወዳጅ መሆኗን እንደገና ያረጋገጠችበት ሆኗልም ሲሉ አክለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fifaworldcup2026 #colombiansinger #shakiradaidaiwakawaka

15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.