የስፔን ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በአካል ይከታተላሉ
#ethiopia | የስፔን ብሔራዊ ቡድን እሁድ በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ከአርጀንቲና ጋር በኒውዮርክ ኒውጀርሲ ስታዲየም በሚያደርገው ጨዋታ፣ የስፔን ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ በአካል እንደሚገኙ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።
በሪፖርቶቹ መሠረት፣ ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ ብቻቸውን ሳይሆን ንግሥት ሌቲዚያ፣ ልዕልት ሌዮኖር እና ልዕልት ሶፊያ ጋር በመሆን የስፔንን ብሔራዊ ቡድን ከመድረኩ ላይ ያበረታታሉ።
ስፔን በግማሽ ፍጻሜ ፈረንሳይን 2ለ0 አሸንፋ ወደ ፍጻሜ ካለፈች በኋላ፣ የንጉሣዊው ቤተሰብ የስፔንን ማልያ ለብሶ ጨዋታውን ሲከታተል የታየ ሲሆን፣ የስፔን ብሔራዊ ቡድንን በማመስገን የድጋፍ መልዕክትም አስተላልፏል።
ንጉሡ ከድሉ በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ በስልክ ደውለው እንኳን ደስ አለዎት ማለታቸውም ተነግሯል።
በእሁዱ ፍጻሜ ላይ የስፔን ንጉሥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በስፔን ወገን ከፍተኛ የመንግሥት ውክልናን እንደሚያደርጉ ሲገለጽ፣ በአርጀንቲና በኩል ፕሬዚዳንት ሃቪዬር ሚሌይ በእምነታዊ ልማዳቸው (superstition) ምክንያት ጨዋታውን በአካል እንደማይከታተሉ ተገልጿል።

19 days ago